Translate

Monday, September 17, 2012

የኢትዮጵያ ተስፋ ወጣቶች ድርጅት የተለያዩ ወረቀቶችን በአዲስ አበባ መበተኑን አስታወቀ


ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ የተለያዩ ቀስቃሽ ጽሁፎችን እና መግለጫዎችን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች መበተኑ ታውቋል።
ድርጅቱ  ” የአንባገነኑ ስርአት በየቤተ እምነቱ ውስጥ ጣልቃ እየገባ የአማኞቹን ሰላም እየነሳ እንደሚገኝ፣  ዘረኛው ስርአት ሀገሪቷን በዘር ከፋፍሎ አንዱን ብሄር ከሌላኛው ጋር በማጋጨት የህዝቡን የመኖር ህልውና አስጊ ደረጃ ላይ ማድረሱን ፣ በአገዛዙ ቅጥረኞች የአማራውን ህዝብ ከደቡብ ክልል ማባረሩን፣የኦሮሞን፣የአፋርን፣ የጋንቤላን፣ የሱማሌን እንዲሁም ሌላውንም ኢትዮጵያዊ በልማት ስም ከቦታው እያፈናቀለ እንደሚገኝ ፤ለም መሬታችንን ለባእዳን አሳልፎ እንደሚሰጥ፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎችን እና አባሎቻቸውን ማስፈራራት፣ማሰቃየት፣ማዋከብ፣ ማሰር እንዲሁም በነጻ ጋዜጠኞች ላይ እስር፣እንግልት፣ማሰደድ፣በማስፋራራት ከስራቸው እንዲርቁ ማድረጉን ” መቀጠሉን የሚያትት ጽሁፍ  በትነዋል።
በተበተነው የድርጅቱ መግለጫ ላይ “የመንግስትን እኩይ ተግባር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የምትፈጽሙም ሆነ የምታስፈጽሙ ድርጅቶች፣ግለሰቦች፣የአገዛዙ የፖሊስ፣የደህንነት፣የመከላከያ ሰራዊት፣የቀበሌና ወረዳ ባለስልጣን ሌሎቹም ጭምር ይህን እኩይ ተግባራችሁን ባስቸኳይ በማቆም ወደ ህዝብ ትግል በማንኛውም መንገድ በመቀላቀል ከህዝብ ጎን በመቆም የበደላችሁትን ህዝብና አገር ግዜው ሳያልፍ በመካስ ከታሪክ ተወቃሽነትና ከህዝብ ቁጣ እራሳችሁን ታድኑ ዘንድ እና ለማይቀረው ለውጥ አስተዋጽኦ ታደርጉ ዘንድ እንጠይቃለን” የሚል ይዘት መኖሩንም ለማወቅ ተችሎአል።
ድርጅቱ በአዲስ አበባ ተመሳሳይ የቅስቀሳ ወረቀቶችን ሲበትን አሁን ለአራተኛ ጊዜው ነው።

No comments:

Post a Comment