Translate

Saturday, February 28, 2015

ኢህአዴግ 98ቢሊዮን ብር ነጠፈበት!!

“ታላቅ ሥራ ተሰርቷል! እናመሰግናለን!” ኦባንግ

anuak-woman-abobo
 
ኢህአዴግ በዓለም ባንክ በኩል ከእንግሊዝ የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤት ሊለግስለት ታቅዶ የነበረው 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) የገንዘብ ድጋፍ ነጠፈበት፡፡ አቶ ሬድዋን አልነጠፈብንም ይላሉ፡፡ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው “የታላቅ ሥራ ውጤት ነው፤ እናመሰግናለን” ብለዋል፡፡

ሰበር ዜና፣ የወያኔ ሰላይ ከሆላንድ ተባረረ!

ሂሩት መለሰ – ከሮተርዳም
ሮተርዳም፣ ጥቅምት 28 ቀን 2015 – በስደት ስሙ አለማየሁ ስንታየው በመባል የሚታወቀው የህወሃት ሰላይ ከኔዘርላንድስ ተባረረ። አለማየሁ ስንታየሁ ቋሚ ነዋሪ ከነበረበት ከኔዘርላንድስ እንዲባረር የተደረገው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በከፈቱበት የስለላ ክስ መሆኑም ታውቋል።
TPLF spy in Netherlands
ከሆላንድ የተባረረው የወያኔ ሰላይ አለማየሁ ስንታየሁ (ሀለቀ ፎላ)
የሮተርዳም ከተማ ፍርድ ቤት በአለማየሁ ላይ የተመሰረተውን የስለላ ክስና ማስራጃ ለረጅም ጊዜ ሲመረምር ከቆየ በኋላ የግለሰቡ የመኖርያ ፈቃድ እና ቤት እንዲነጠቅ፣ የሆላንድን ምድርም በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ውሳኔ አስተላልፏል። ከሆላንድ የምመራ ቡድን እንደተረዳነው ከሆነ – የግለሰቡ ቤት ሲፈተሽ ወያኔ የሰጠው እውነተኛ መታወቂያ እና በርካታ የስለላ ሰነዶች ተገኝተውበታል። በእርዳታ ስም የተቋቋመለት ድርጅትም ተፈትሾ ማስረጃዎች እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል።

ቻው! ቻው! በኢትዮጵያ የካሩቱሪ ቅኝ ግዛት (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

መልካም የጉዞ ፍታት ለካራቱሪ: በኢትዮጵያ የካሩቱሪ አሟሟ አስከሬን ምርመራ
በምዕራብ ኢትዮጵያ በምትገኘው በጋምቤላ ክልል ካሩቱሪ እየተባለ ከሚጠራው ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል የውጭ የግብርና ልማት ድርጅት ጋር የወያኔ ወሮበላ የዘራፊA post-mortem on Karuturistan, Ethiopia ቡድን ስብስብ ባደረገው ስምምነት መሰረት ሲተገበር የቆየው የመሬት ቅርምት የመድረክ ላይ ተውኔት ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅም እና በእውነትም ለዕድገት የእራሱን ድርሻ ሊያበረክት የሚችል ቢሆን ኖሮ እጅግ በጣም ጥሩ ነገር ነበር፡፡ ሆኖም ግን በተግባር እየሆነ ያለው ነገር በሸፍጥ እና በመሬት ዘረፋ ላይ ያተኮረ ዕኩይ ምግባር በመሆኑ ለኢትዮጵያ ህዝብ እጅግ በጣም አስከፊ እና ጎጅ በመሆን አስጠያፊ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ አልፏል፡፡
ባለፈው ወር “የኢትዮጵያ ሳራማ የረግረግ ቦታ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት/Ethiopian Meadows Plc“፣ “በኢትዮጵያ የጋምቤላ አረንጓዴ ሸለቆ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት/Gambella Green Valley Plc“ እና “በኢትዮጵያ የካሩቱሪ የግብርና ምርት ውጤቶች አምራች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት/Karuturi Agro Products Plc (Ethiopia)“ እየተባሉ የሚጠሩትን የግል የርሻ ንግድ ድርጅቶች አካትቶ በመያዝ ጋምቤላ እየተባለ የሚጠራውን የኢትዮጵያ የግዛት ክልል ለም መሬት በመዝረፍ ሲንቀሳቀስ የቆየው ካሩቱሪ ዓለም አቀፍ የህንድ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት/Karuturi Global, Ltd ምንም ዓይነት የመድረክ ላይ ትወና ሳይደረግና የፕሮፓጋንዳ ጥሩንባ ሳይነፋ በድብቅ እና በሚስጥር የሞቱ መርዶ ይፋ ተደርጓል፡፡

Thursday, February 26, 2015

ምርጫ ለኢትዮጵያ ወታደርና ፓሊስ: – ለህወሓት ባርነት ወይስ ለኢትዮጵያ ነፃነት

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውትድርና ከፍተኛ ክብር አለው። ውትድርና ከሙያና ሥራ በላይ የነፃነትና የክብር መገለጫ፤ ሀገርን ከባዕድ ወረራ መከላከያ ጋሻ ነው ብሎ ያምናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ህግና ሥርዓት አክባሪ በመሆኑ ለፓሊስም ከፍተኛ አክብሮት አለው። የፓሊስ ሥራ ወንጀልን መከላከልና ወንጀለኞችን ወደ ፍርድ ማቅረብ መሆኑ በኢትዮጵያ ባህል የተከበረ ቦታና እውቅና አለው።
በህወሓት የአገዛዝ ዘመን ግን ይህ እየተቀየረ ነው። የህወሓት አዛዦች እየመሩት ያለው የኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ሀገርን ከባዕድ ጠላት ከመከላከል ጋር ምንም ዝምድና በሌላቸው ሁለት አበይት ተግባራት ላይ ተጠምዷል። በህወሓት አዛዦች የሚመራው ሠራዊት ዋነኛ ተግባር ለሰብዓዊ መብቶቻቸው መከበር እና ለፍትህ መስፈን የሚታገሉ ዜጎችን ማጥቃት ሆኗል። የጦሩ ሁለተኛው አቢይ ተግባር ደግሞ ለአዛዦች የግል ጥቅም ማካበቻ ገቢዎችን በሚያስገኙ ሥራ ላይ መሠማራት ነው።
የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያዊያንን ማጥቂያ ሠራዊት መሆኑ ሲቪሉን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የሠራዊቱንም አባላትን ጭምር ለህሊና ወቀሳ የዳረገ ጉዳይ ነው። ሆኖም ግን ይህ በህሊና ወቀሳ ብቻ ሊታለፍ የማይችል ወንጀል ነው። ሠራዊቱ በህወሓት እየታዘዘ የሚዘምተው በገዛ ራሱ ልጆች፣ እህቶች፣ ወንድሞችና ወላጆች፤ በገዛ ራሱ ጥቅሞች እና በገዛ ራሱ ላይ መሆኑ መገንዘብ ይኖርበታል። በገዛ ራሱ ጥቅሞች ላይ የሚዘምት አንድም ህሊና የሌለው አሊያም ነፃነት የተነፈገው ሰው ብቻ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ሠራዊቱ እየተራበና እየታረዘ አለቆቹ የታላላቅ ህንፃዎች ባለቤቶች፣ ባለፋብሪካዎች፣ የባንክና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ባለአክሲኖች የሚሆኑበት ሥርዓት ከዳር ሆኖ የሚመለከት መሆኑ የሚገርም ነው። ሠራዊቱ ቤተሰቦቹን መመገብ አቅቶት እያለ የአዛዦቹ ልጆች ለሽርሽር ዓለምን ይዞራሉ። እንዴት ነው ሠራዊቱ እየደኸየና እየሞተ አዛዦቹ እየከበሩ የሚሄዱት? ይህ አዋራጅ ሁኔታ እንዲያበቃ መታገል የሠራዊቱ ግንባር ቀደም ኃላፊነት ነው። ሠራዊቱ ወይ ባርነትን አሜን ብሎ መቀበል አለበት አለበዚያም እሱም እንደነሱ ሰው መሆኑን ማሳየት መቻል አለበት። በኢትዮጵያ ውስጥ የህወሓት አገዛዝ ወድቆ የሕዝብ ይሁንታ ያገኘ መንግሥት መመሥረቱ በከፍተኛ ሁኔታ ከሚጠቅማቸው የኅብረተብ ክፍሎች ግንባር ቀደሙ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ናቸው። በዚህም ምክንያት የሠራዊቱ አባላት ለሥርዓቱ መውደቅ በግልጽም በስውርም መታገል የዜግነት ብቻ ሳይሆን አዕምሮ ያለው ሰው ሆነው በመፈጠራቸው የተቀበሉት ግዴታ ነው።

ልታሰር ነው 3

ልታሰር ነው 3
(አሌክስ አብርሃም)
ሰው እንኳን መታሰር ይሞት ይለ እንዴ ? ብየ ራሴን አበረታታተሁ …ሰዎች ስንባል መቸም ንፅፅር ስንወድ …በቃ አንድ ችግር አፍጥጦ ሲመጣብን ያንን ችግር እንቢ ብለን ማምለጥ ሲያቅተን የባሰ ነገር እየመዘዝን ችግራችንን ‹‹ምናላት ይች›› ብለን ማቃለል እንወዳለን ! ጉንፋን ሲየዘን ‹‹ሰው ቲቢ ይያዝ የለ እንኳን ጉንፋን ተመስገን ነው ›› አንድ ጣታችን ሲቆረጥ …‹‹ሰው እግርና እጁ በፈንጅ ይቆረጥ የለ እንኳን ጣት ›› እግርና እጃችን ቢቆረጥ ‹‹ሰው አንገቱ ይቆረጥ የለ …›› ሚስታችን ጥላን ብትሄድ ‹‹ትሂዳ ደሞ ለዛች ጣሙጋ ስንት ልእልት የመሳሰሉ ቆንጆዎች በሞሉበት አገር ›› …..አንድ ቀን እንኳን ከማወዳደር መለስ ብለን ለምን ይሄ ይሆናል ብለን መጋፈጥ እንዴት ያቅተናል ….!! ይሄው እኔም ልታሰር ተጠራሁ….. ግን ምን ይደረግ ሰው እንኳን መታሰር ይገደል የለ (ሃሃሃ)
ሜላን ልነግራት ወሰንኩና በእኩለ ሌሊት ስልክ ደወልኩላት
‹‹አብርሽየ በሰላም ነው ?›› አለችኝ
‹‹ሰላም ነው ሜላየ ይቅርታ ረበሽኩሽ በሌሊቱ ››
‹‹ፊልም እያየሁ ነበር ችግር የለውም ….ምነው? ››
‹‹ እ…..ላግኝሽ …? ›› አልኳት ያው ባሏ እንደሌለ አውቃለሁ መቸስ ! ሜላ እንቅልፋም ነበረች እስካሁን በመቆየቷ እግዜር ተሰነባበቱ ሲለን ነው ብ አሰብኩ !
‹‹እንዴ በደንብ ነዋ ! እኔ ልምጣ ወይስ ትመጣለህ ?…››
‹‹ኧረ እመጣለሁ ….›› ብየ ተነሳሁ በሯ ሲከፈት ተሰማኝ ….

Wednesday, February 25, 2015

“መረጃ አውጡ፣ የደበቃችሁትን ሁሉ ተናገሩ”

“መረጃ አውጡ፣ የደበቃችሁትን ሁሉ ተናገሩ”

የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች በጨለማ ቤት መታሰራቸውን አስታወቁ
dark


በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ የሚገኙት የሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀጠና/ዞን አመራሮች ለ16 ተከታታይ ቀናት በጨለማ ክፍል መታሰራቸውን ለፍርድ ቤት አስታወቁ፡፡

Tuesday, February 24, 2015

ልታሰር ነው !!


 (አሌክስ አብርሃም)
አዳሜ ቀልጅ ….እኔ እንደሆንኩ ልታሰር ነው ! በቃ ግልግል … ምን ታመጫለሽ…. ሁለት ቀን ከግማሽ ‹‹አሌክስ ይፈታ ›› ትያለሽ ከዛ በሶስተኛው ቀን …‹‹ባፍ ይጠፉ በለፈለፉ …ተው እያልነው ሲቀባጥር ….›› እያልሽ እኔኑ ትወርጅብኛለሽ ! አለቀ !! ከዛ አለም ይረሳህና ሚስኪን ቤተሰብ የተቋጠረ ሰሃን ሲያመላልስ ይኖራል !!ቢመርም እውነቱ ይሄ ነው ! ቢበዛ የሆነ አገር አምባሳደር ይመጡና እስረኞቹን ጎብኝተው አገራቸው ላይ መግለጫ ሊሰጡ ነው ይባላል ‹በቃ አሳሪዎች ጉዳቸው ፈላ› ተብሎ መግለጫው በጉጉት ሲጠበቅ ‹‹ሚስተር አምባሳደር ›› እንዲህ ይላሉ
‹‹ ኢትዮጲያ ውስጥ በነበረኝ ቆይታ አገሪቱ በመልካም የእድገት ጎዳና ላይ መሆኗን ታዝቢያለሁ … ይሁንና አንድ ቅር ያለኝ ነገር ታሪካዊ ቅርሶቿን ለመጎብኘት ለሚሄዱ የውጭ አገር ዜጎች በቂ ሆቴሎች የሏትም ….አገራችንም በዚህ ዘርፍ ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሃብቶች ስልጠናና ድጋፍ እንደምታደርግ ገልፀንላቸዋል ›› በቃ!
‹‹እንዴ ስለእስረኞቹስ ክቡር አምባሳደር ?›› … ይባል የለ...?ሚስተር አምባሳደር ኮስተር ባለ አነጋገር ‹‹የገደለው ባልሽ የሞተው ወንድምሽ.. ሃዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ !›› ብለው በእንግሊዝኛ ቅኔ ይዘርፉብናል ሃሃ ! ፍርድ ቤት ስቀርብ መጀመሪያ አስር ሰው ፍርድ ቤቱ በር ላይ ቁሞ አያለሁ …‹‹ውይ ይሄ ሁሉ ሰው ለኔ ነው የመጣው …ህዝቤ አገሬ እንኳን መታሰር ቢሞትላትስ ምናምን›› ስል …አንዱ እስረኛ ወደጆሮየ ጠጋ ብሎ …
‹‹ባክህ ላንተ የመጡ አይደሉም ! አንድ ሰውየ ከአራት ሴቶች የወለዳቸው ልጆች ናቸው… ሰውየው በቅርቡ ስለሞተ ያለችውን ላዳታክሲ ውርስ ሊያሳውጁ መጥተው ነው ›› ብሎ ኩም ያደርገኛል !! ወይ ነዶ ! ለዚች አገር እንኳን ለአመታት መታሰር ይቅርና ለደይቃ ዜብራ ላይ መቆም እንኳን አያስፈልግም !! እያልኩ ወደችሎት እገባለሁ …..‹‹ በእነ እከሌ የክስ መዝገብ ….አስራአራት ቀን የጊዜ ቀጠሮ !›› ይላሉ ዳኛው ! በቃ!! በነገራችን ላይ ‹‹ በእነእከሌ የክስ መዝገብ የተከሰሱት አስር ተከሳሾች ›› ሲባል ይሄ አስሩ ሰዎች የተከሰሱበት መዝገብ በስሙ የተሰየመው ሰው ‹አምበል› ይመስለኛል !

ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር – ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም


የጎረቤት ኬንያ ዳኛ ለኬንያ መንግሥት አስፈጻሚው ክፍል ልኩን ነገረው፤ ሕገ መንግሥቱን በመርፌ አስተኝተህ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር ሕግ ለማውጣት አትችልም፤ ስለዚህም የሰነዘርኸውን የጉልበት ሕግ አንሣ፤ አለው፤ ዳኛ አይጥፋ! ሌላ ቢቀር ከጎረቤት ዳኝነትን እንስማ፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር ስንት ጋዜጠኛ፣ ስንት የሃይማኖትና ስንት የፖሊቲካ መሪዎች ከየወህኒ ቤቱ ይወጡ ነበር! ሁላችንም እንደልባችን ሳንፈራ፣ ሳንፈራራ በሙሉ ነጻነት ችግሮቻችንን የወያኔን ጭቆና ጨምሮ ለመወያየትና መፍትሔዎችን ለመለዋወጥ የምንችልበት መድረክ፣ ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ ራድዮና ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ውስጥ ይኖረን ነበር፤ ስንት ሰው ሥራ ያገኝ ነበር፡፡
ከሁሉም በላይ በየመንገዱ ጠመንጃ የያዘ ሊያስፈራራን የሚሞክር ሆድአደር እያየን፣ እንደዚሁም በየጫካው ያሉትን እያሰብን ሰላማችንን ከምናጣ አበባውን ትተን፣ ሩዙን ትተን፣ የተወደደልንን ጤፋችንን እያመረትን አዲስ ኑሮ ብንጀምር የተሻለ ነበር፡፡
ግን አንድ እንቅፋት አለብን፤ እነዚህ ከየኪዮስኩ እውቀት ገዝተን አዋቂዎች ሆነናል የሚሉት እንትኖች እንመጀመሪያ ችግሩ እንዲገባቸው፣ ሁለተኛ መፍትሔው እንዲገባቸው፣ ሦስተኛ ጉልበትና እውቀት አንድ አለመሆናቸውን ብቻ ሳይሆን በጉልበት እውቀት የማይገኝ መሆኑን ማሳመን በረዶ እየወረደ የስሜን ተራራን መውጣት ነው፤ በረዶ ሳይኖር ወጥቼዋለሁ!
እነዚህን የጉልበት አዋቂዎች — ስለሽማጌሌዎችና አሮጊቶች ሳያስቡ፣ ስለመብራት ኃይል ሳያስቡ፣ ስለውሀ ሳያስቡ ሁሉም በጉልበት ፎቅ ይውጣ የሚሉ! ይባስ ብለው ለእስረኛውም ፎቅ እየሠሩለት ውጣ! ሊሉት ነው!
እነዚህ የጉልበት አዋቂዎች የአበሻ ኑሮ፣ ቡናው፣ ሙቀጫው፣ ምጣዱ፣ በርበሬው፣ ቁሌቱ፣ ቄጤማው፣ ዶሮና በግ ማረዱ፣ ኧረ ስንቱ! ሳይገባቸው ቻይና በነገራቸው የሚያውቁትን የሚረሱ ማን ያስተምራቸው! እናውቃለን ስለሚሉ እንዴትስ ይማራለ? በእውነት ለመማር ቢፈልጉስ ስንት ዓመት ሊያስፈልጋቸው ነው! እግዚአብሔር እንሱንም እኛንም በምሕረቱ ይጎብኘን! የሚያስተምር ጎረቤት አያሳጣን!

የዚህ ሁሉ እልቂት “ኩሹፍ” ሲገለጥ( አርአያ ተስፋማሪያም)

ጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም፣ ባለቤታቸውና ሌሎች አንገታቸው ላይ ስላጠለቁት በተመለከተ አንድ የቀድሞ አንጋፋ የድርጅቱ ታጋይ በግል ያደረሱኝ መልእክት እንዲህ ሲል ይጀምራል « በታጋዮች ዘንድ “ኩሹፍ” ተብሎ ይጠራል። ታጋዩ ከሞተ በኋላ የሚገነዝበት ጨርቅ ነው። ድርጅቱ አላማ ያለው የመሰለው አብዛኛው ታጋይ ያን ጨርቅ አንገቱ ላይ በማጥለቅ ለመሰዋት (ለመሞት) ቁርጠኝነቱን የሚያሳይበት ነበር። 98 በመቶ የሚሆነው ተዋጊ ያልተማረ ስለነበረ የድርጅቱ አላማና አካሄድ ሊያውቅበት የሚችል አንድም መንገድ አልነበረም። በእሱ ደምና አጥንት ተረማምደው ሲያበቁ የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ አስፈፀሙ። 36 ሺህ የህወሀት ታጋዮችን ገና በጠዋቱ አባረው ለአስከፊ የጐዳና ህይወት ዳረጓቸው። ኢትዮጵያውያን ወንድማማቾችን በብሄር ፖለቲካ እርስ በርስ እንዲናቆሩ እነመለስ የጥፋት ወጥመድ ዘረጉ።

Monday, February 23, 2015

የኢትዮጵያ ጉዳይ የካቲት 2007 ዓ.ም አንደኛ ዓመት ቁጥር ፪

የኢትዮጵያ ጉዳይ

የካቲት 2007 ዓ.ም አንደኛ ዓመት ቁጥር ፪
tplf and control


ግልፅ ደብዳቤ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች
ሀገር ማለት
ባሕርዳር ዛሬም ስለልጆቿ አነባች
የአምባገነኖች አከርካሪ በተባበረ የሕዝብ ክንድ
ይሰበራል
በሴቶች ላይ የሚፈጸም በደልና ጾታዊ ጥቃት ይቁምtplf and control
ኢትዮጵያዊነት በዘር ማንነት አይደበዝዝም
ለነፃነትና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚደረገው ትግል በቀላሉ አይቀለበስም
ፖሊስና ሰብዓዊ መብት በኢትዮጵያ
መጽሔቷ በእነዚህና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ታተማለች፡፡ ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

ሐዋሳ በእሣት ተመታች – እሣት አደጋ ነበር?

ሐዋሳ በእሣት ተመታች – እሣት አደጋ ነበር?

ህይወት ጠፍቷል፤ ንብረት ወድሟል!
hawassa fire


በሐዋሳ ለጊዜው የጉዳቱ መጠን ያልታወቀ የእሣት ቃጠሎ መድረሱን በአደጋው ያዘኑ ገለጹ፡፡ ከስፍራው እንደተሰማው ለሰኞአጥቢያ የተነሳው ቃጠሎ ምናልባትም በከተማዋ ታሪክ ከፍተኛው ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ አደጋው ሲደርስ የእሣት አደጋ “አገልግሎት” በነዋሪዎች ላይ ቅሬታ አስነስቷል፡፡

Wednesday, February 18, 2015

የ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› ትግል የሁላችንም ነውና በጋራ እንነሳ! ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

ትብብራችን ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የሠላማዊ ትግል ፕሮግራም ካደረገው እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የተከሰቱትን ወቅታዊ ሁኔታዎች በመገምገም ሁለተኛ ዙር ፕሮግራሙን ነድፎ ለምርጫ ዕጩዎችን የማስመዝገብ ተግባር ጎን ለጎን ለተግባራዊነቱ በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡ የዚህ የሁለተኛ ዙር ፕሮግራም ማጠቃለያም የካቲት 15 /2007 በተመረጡ 15 የአገራችን ከተሞች በተመሳሳይ ጊዜ የሚደረጉ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በመነሳት የዛሬው መግለጫ ለየካቲት 15 የታቀደውን በ15 ከተሞች የሚደረግ ሰላማዊ ሰልፍ ፕሮግራም በአንድ ሳምንት ተራዝሞ ወደ የካቲት 22/07 መተላለፉን ለማሳወቅና ትብብራችን እስከ ዛሬ ያደረገውን ሰላማዊ ትግል አስፈላጊነት፣ወቅታዊነትና ትክክለኝነት በተጨባጭ በማረጋገጥ፣የተያያዝነውን ሰላማዊና ህዝባዊ ትግል እንዴት ማስቀጠልና ውጤታማ ማድረግ ስለሚቻልበት የገዢዎቻችንን ከግምት ያለፈ የፍርኃትና ስጋት ደረጃን ያገናዘበ ስልት መቀየሳችንን ፣ የቆምንበትን ህገመንግስታዊነትና ህጋዊነት እንዲሁም የትግሉን ትኩረት የሚመለከቱ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ የደረስንበትን ጭብጥ ለህዝባችን በዝርዝርና በስፋት በማቅረብ ለቀጣዩ ትግል ጥሪያችንን ለማቅረብ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት የተደረሰባቸው ጭብጦች፡-

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የትግል ጥሪ አስተላለፈ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የሁለተኛ ዙር የሠላማዊ ትግል ጥሪውን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተላለፈ፡፡ ትብብሩ የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት በ15 ከተሞች ሊያደርገው አቅዶት የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ በሳምንት አራዝሞ ለየካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም ማስተላለፉንም አስታውቋል፡፡Ethiopian opposition coalition statement
ትብብሩ ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ገዢው ፓርቲ የቱንም ያህል አሰቃቂና አረመኔያዊ የአፈና እርምጃዎች ቢወስድም የህዝብ ጥያቄዎች እስካልተመለሱ ድረስ ህዝባዊ ትግሉን ማዳፈን እንጂ ማስቆም እንደማይችል ይልቁንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከተለያዩ የህዝብ እንቅስቃሴዎች መገንዘቡን ገልጹዋል፡፡ ትብብሩ ምርጫን በተመለከተ እንዳስታወቀው ኢህአዴግ ስለመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ከቃላት ያለፈ እምነትም ሆነ ቁርጠኝነት የሌለው መሆኑን በዚህ የምርጫ ወቅት በተፎካካሪ ፓርቲዎች ላይ እየወሰደ ያለው ህገ-ወጥ እርምጃ ማሳያ ነው ብሏል፡፡

Monday, February 16, 2015

አምባገነን ብሔር የለውም !! - አሌክስ አብርሃም

ሰሞኑን የህወሃት 40ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በመላው ኢትዮጲያ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ በቅድሚያ እንኳን ለአርባኛው አመት የምስረታ በዓል አደረሳችሁ እላለሁ ፡፡ በትጥቅ ትግሉም ወቅት ሆነ ከትጥቅ ትግሉ በኋላ ይህን ቀን ለማየት ሳይታደሉ ያለፉ ብዙዎች ናቸውና ምንም ይሁን ምን ለዚህ ቀን መብቃት ትልቅ ነገር እንደሆነ ይሰማኛል ፡፡ ይህን ፅሁፍ የምፅፈው በተወለድኩባት ባደኩባትና አሁንም እየኖርኩባት ባለችው ኢትዮጲያ ከተመሰረተ ድፍን 40 ዓመት ያስቆጠረ ጎልማሳ የፖለቲካ ድርጅት ላይ እንደአንድ ዜጋ ያለኝን ቅሬታ ለማሳወቅ ነው ፡፡

ቀና በል ይሉኛል– ወዴት ልበል ቀና

10989028_861493467244057_5753878234862957005_nቀና በል ይሉኛል– ወዴት ልበል ቀና
ከላይ ተደፍቶብኝ- አገር እንደቁና
ጣራው ባጡ ቀርቦኝ
በር አልባ ግድግዳ- እንደ ዝናር ከቦኝ
በጫጩት ጉልበቴ- እየተወራጨሁ
እንባየን ዘግኘ- ሽቅብ እየረጨሁ
ወደ አማልክት ብጮህ-ጠሎቴን አይሰሙት
በየት በኩል ኖሬ በየት በኩል ልሙት::
በምን ይገለጻል- የትውልዴ አበሣ
ከመንበርከክ ብዛት- መራመድ የረሣ
ያልፋል ተለጉሞ ያልፋል ተከርችሞ
የጉልበቱን ኮቴ- ምድር ላይ አትሞ::
ወፈፌ ቀን አልፎ- እብድ ቀን ሲመጣ
ማልቀስ አመጽ ሲሆን- በሸንጎ ሚያስቀጣ
እንባዬን የት ላርገው ወዴት ልሸሽገው?
ዞትር የሚስቁት፣
ወዴት ገቡ አበቦች
የሚፍለቀለቁት የታሉ ኮከቦች
ምን አጋይቶት ይሆን፤ ሰማይ የከሠለ
ምን ነካው ደመናው፤ ኩበት የመሠለ
አስፋልቱስ የት ሄደ
የተለጠለጠው
ወንዙስ ተሰደደ?
ድልድዩስ ምን ዋጠው
የት ተነነ ጫካው
የት መነነ ዋርካው
በለምለም ጣቶቹ፤
ሰማይ የሚነካው
ዳበስኩኝ ፈተሸኩኝ
መረመርሁኝ ካርታ
አገሬን አጣሁዋት፤
ባስቀመጥሁዋት ቦታ፡፡
ኢትዮጵያ እመ-መከራ
የግዜር መመራመሪያው የስቃይ ቤተ-ሙከራ
መውደቅማ ነበር ያባት
እንደ ያሬድ እስከ ሰባት
እንደ በላ ብላቴና ፣ የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ
የትውልዴ እጣ ፋንታ፣ መውድቅ መውድቅ መውድቅ ብቻ…

የኢሳያስ ቃለመጠየቅና የብሔርተኞች ጫጫታ

G. Tekola
ESAT journalists interview with Eritrean president
ኢሳት ወደ ኤርትራ ተጉዞ የኤርትራውን ፕሬዝዳንት ማናገሩ ከተሰማ ወዲህና በተለይም የቃለመጠይቁ ቅንጣቢ ከቀረበ ቦኋላ እየበገኑ ያሉት ወያኔዎች ብቻ ሳይሆኑ በወያኔ የብሄር ፖለቲካ እናተርፋለን ብለው ሲዳክሩ አመታት ያስቆጠሩ ብሄርተኞች ጭምር መሆናቸውን ጭፍሮቻቸው በሶሻል ሚዲያ ላይ ለማስተጋባት ከሚሞክሩ አስተያየቶች ለማየት እየቻልን ነው::

Sunday, February 15, 2015

ሰበር ዜና – ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲን ከምርጫ ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ታወቀ፣ ‹‹ሰማያዊ ሳይጠብቁት በመላ አገሪቱ ዕጩ በማቅረቡ ደንግጠዋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

• ‹‹ሰማያዊ ሳይጠብቁት በመላ አገሪቱ ዕጩ በማቅረቡ ደንግጠዋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
Image result for semayawi party
(ነገረ-ኢትዮጵያ) ምርጫ ቦርድ በየወረዳው ለሚገኙ የምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች ‹‹ከቦርድ የሚጠበቅ ውሳኔ ስላለ፣ ሰኞ ተሰብስበን እስክንወስን ድረስ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎቹን ወደ ቅጽ 4 እንዳታዘዋውሩ›› የሚል መልዕክት ማስተላለፉን እና ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረባቸውን ዕጩዎች ከመቀነስ ጀምሮ ፓርቲውን ከምርጫው ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ከምርጫ አስፈጻሚዎች መረጃዎች ደርሰውናል ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

‹‹ሰላማዊ ትግሉ ሲጠናከር ስርዓቱ ወደ አውሬነት ይቀየራል›› • ‹‹ቃል ኪዳናችንን ማጥበቅ አለብን!››

Image result for semayawi party
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
(በዛሬው ዕለት ለቀድሞው የአንድነት አመራሮችና አባላት የተዘጋጀው የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ላይ ከተናገሩት)
ፓርቲ ጣኦት አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ቅንጅትንም አፍርሶታል፡፡ አንድነትንም አልፈረሰም ብለው እንዳይከሱኝ እንጅ አፍርሰውታል ማለት እችላለሁ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሰማያዊ ላይም አንድ ነገር ማምጣታቸው የማይቀር ነው፡፡ ያ ማለት ግን ሰላማዊ ትግሉ ምን ያህል እንዳስፈራቸው ነው የሚያሳየው፡፡ አገዛዙ በፓርቲዎች ላይ የሚወስደው እርምጃ የሚያሳየው ሰላማዊ ትግሉ መጠናከሩን እንጅ ወደኋላ መመለሱን አይደለም፡፡ አንዳንዶቹ እንዲህ አይነት ችግር ሲከሰት ሰላማዊ ትግሉ አበቃለት ይላሉ፡፡ ሆኖም አገዛዙ ሰላማዊ ትግል አስፈርቶት አውሬ ሲሆን የሚያረጋግጥልን ሰላማዊ ትግሉ መጠናከሩን ነው፡፡
በመሳሪያ ትግል ውስጥ አንድ ጀኔራል ሲሞት አሊያም አንድ የጦሩ አካል ችግር ሲደርስበት ‹‹የትጥቅ ትግል አበቃለት›› እንደማይባለው ሁሉ ሰላማዊ ትግል ላይ አንድ ጫና ወይንም የስርዓቱ ደባ ሲከሰት ትግሉ አይሰራም ማለት አይደለም፡፡
ሰላማዊ ትግል መስዋዕትነት አያስከፍልም ማለት አይደለም፡፡ እንዲያውም ሰላማዊ ትግል ውጤት ማምጣት ሲጀምር፣ ዙሩም ሲካረር፣ የሚከፈለው ዋጋም ይበልጥ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ የስርዓቱ አውሬነት በተገለጠ ቁጥር፣ እኛም በተሻለ አመራር ትግሉን ስንመራው መስዋዕትነቱ ይበልጡን እየበዛ እንደሚመጣ እንረዳለን፡፡

Saturday, February 14, 2015

የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የአቋም መግለጫ

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላማዊ፣ ተዓማኒና ፍትሀዊ በሆነ ምርጫ የማይፈልጋቸውን መሪዎች መሻር፤ የሚፈልጋቸውን ደግሞ መሾም የሚያስችሉትን መሠረቶች ለመጣል የሚታገል ንቅናቄ ነው። እንደሚታወቀው የሕዝብ እውነተኛ ፍላጎት የሚገለጽበት እውነተኛ ምርጫ እንዲኖር ገለልተኛና ቀልጣፋ የፍትህ ሥርዓት፣ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ሊኖሩ ይገባል። ነፃ የሚዲያ ተቋማትና በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የሲቪክ ማኅበራት መኖርም መታለፍ የሌለባቸው አቢይ ጉዳዮች ናቸው። አማራጭ ፓሊሲዎችን ማቅረብ የሚችሉ በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከሌሉም አማራጮች የሉምና ምርጫ ትርጉም የለውም። ይህ ሁሉ ቢሟላ እንኳን ምርጫውን የሚያስፈጽመው አካል ገለልተኛ፣ ሀቀኛና ተዓማኒ ካልሆነ የሚደረገው ምርጫ የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ሊሆን አይችልም።

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

የምርጫ ሂደቱ በኢህአዴግና በምርጫ ቦርድ ከፍተኛ ችግር እየደረሰበት ነው!
ሰማያዊ ፓርቲ በ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ የመንግስትን ስልጣን ለመያዝ የሚያበቃውን ውጤት ለማስመዝገብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ነፃና ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጋራ በመሆን ነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ የሚል መርሀ ግብር በማዘጋጀት ምርጫ ቦርድን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ነፃና ገለልተኛ እንዲሆኑ በተለያዩ መንገዶች ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡

Friday, February 13, 2015

ለጨካኝ ስርአት የጨከነ ትግል

የኢትዮጵያ ህዝብ በህውሃት ስራአት የደረሰበትን መዘርዘር ብዙ ቢሆንም ለህልውናችን ፀር የሆነው የወያኔ ስራአት ፍጹም በሚሰቀጥጥ ሁኔታ ህዝባችንን ያለማቋረጥ እያሰቃየ ይገኛል::Protest in front of TPLF embassy in Washington DC
በ 23 አመት የግፍ አገዛዙ የመጨረሻው ምእራፍ ላይ የደረሰው ወያኔ እንደ ከዚህ ቀደሙ በግፍ መቀጠል የማይችልበት፣ የኢትዮጵያ ህዝብም የሚገዛበት የባርነት መሸከሚያ ትከሻው እየተሰባበረ ያለበት፤ ወያኔን ወልደው ያሳደጉት እና ያሰማሩት ባእዳን ሃገሮችም የመቀጠል ሀይሉን ለክተውት፣የኢትዮጵያ ህዝብንም የአልገዛም ባይነት መንፈሱን ተረድተውት ወያኔን እያጣጣሉት ይገኛሉ፡፡ ወያኔም የመጨረሻ የጣር በትሩን አንስቶ ገና በእናቱ ሆድ ያለን ፅንስ በግፍ ዱላ እያፈርሰ፣ ታዳጊ ህጻናትን ከራሱ አልፎ በባእዳን እያስገደለ ይገኛል።
የኢትዮጵያ መጥፋት ለወያኔ ትንሳኤ ሲሆን፤ የወያኔ ስርአት መወገድ ደግሞ ለኢትዮጵያዊያን ትንሳኤ ነው። በመሆኑም ህውሃት አርባኛ አመቱን ለማክበር በሚሊዮኖች ብር መድቦ በመከራ ላይ ባለው ወገናችን የካቲት 11 ከበሮ ሲደልቅ እኛም በውጭ የምንገኝ ህውሃት የተፈጠረበትን እለት በክፉ ቀን ማስታወሻነት በከረረ ተቃውሞ በወያኔ ኢንባሲ ፊት ለፊት እናሳልፋለን:: እርሶም በስፍራው ጥቁር ልብስ በመልበስ ይህ መርገምት የሆነው ወያኔ የተፈጠረበትን ቀን በአንድላይ ሆነን በተቃውሞ እንድናሳልፍ እንጠይቃለን።
ቦታ፦ Embassy Of Ethiopia 3506 International Dr NW Washington,DC.20008
ቀን፦ እሮብ Feb 18, 2015
ሰአት፦ 9:00 AM
ለበለጠ መረጃ፦ dcjointtaskforce@gmail.com ወይም 571 403 2474

Thursday, February 12, 2015

“ክቡር” አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳ የሃሰት ዲግሪዎችን ሸምተው መጠቀማቸው ተረጋገጠ

(አዲስ ቮይስ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የሆኑት አባዱላ ገመዳ በኢንተርኔት ያለምንም ትምህርት ዲግሪ በመሸጥ ከሚታወቅ አንድ የዲፕሎማ ወፍጮ ቤት (diploma mill) የሃሰት ዲግሪዎችን ገዝተው መጠቀማቸውን አዲስ ቮይስ አረጋገጠ።
Speaker Abadula Gemeda has fake degrees
አፈጉባኤው የባችለርስ ዲግሪ እ.ኤ.ኤ በ2001 እንዲሁም የማስተርስ ዲግሪ በ2004 አሜሪካን አገር በሚኖረውና አሊ ሚርዛኢ በሚባል ኢራናዊ ከሚንቀሳቀሰው “አሜሪካን ሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ” (ሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ) ያለምንም ትምህርት መግዛታቸው በመረጃ ተረጋግጧል። አባዱላ ሁለቱንም ዲግሪዎች የህዝብ አስተዳደር ትምህርት ተምረው አንዳገኟቸው ሲገልጹ የቆዩ ሲሆን ይህንንም በፓርላማ ድረገጽ፣በፌስቡክ፣ ዊኪፔድያ፣ በመንግስትና በግል የመገናኛ ተቋማት በይፋ ታትሞ እንዲሰራጭ አድርገዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከቻይና መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በወታደራዊ አመራር የባችለርስ ዲግሪ እንዳገኙ በህይወት ታሪካቸው ላይ በይፋ ያሰፈሩት አባዱላ እንዲህ አይነት ዲግሪም ይሁን ትምህርት ከቻይና የትምህርት ተቋም አለማግኘታቸው ታውቋል።

የኢትዮጵያ “የድብቅ ዕዳ” በድብቁ የዓለም ባንክ (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የወያኔ ወሮበላ ስብስብ ቡድን በቀፈቀፈው ድብቅ ዕዳ ምክንያት እንደ በረዶ ክምር የተቆለለባትን ዕዳ መክፈል የማትችለው ሉዓላዊቷ ኢትዮጵያ፣ ባለፈው ሳምንትEthiopia’s “Odious Debt” to the Odious World Bankየዓለም ባንክ እና የኢትዮጵያ “የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የቁማር ጨዋታ” በሚል ርዕስ ባቀረብኩት ትችት የሚከተለውን ድብቅ ዕኩይ ድርጊት ለማጋለጥ ሞክሪያለሁ፣ “…በኢትዮጵያ ህዝብ ስም የዓለም ባንክ በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ለሚገኘው እና እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ ለሚጠራው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ 600 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሰጥቷል፡፡ የኢትዮጵያ የወደፊት ትውልዶች ምንም ዓይነት ተጠቃሚ ባልሆኑበት ሁኔታ ይህንን የተቆለለ እና የሚኮመዝዝ ዕዳ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ፡፡ ይህንን ፍትሀዊ ያልሆነ የወያኔ የሸፍጥ ዕዳ ለመክፈል በህግ ሊገደዱ ይችላሉን!?! እም!“ የወያኔ የወሮበላ ስብስብ ቡድን እንክት አድርጎ የበላውን እና የተቀራመተውን የብድር ገንዘብ የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም ዓይነት ተጠቃሚነት ያልሆነበትን የተቆለለ የዓለም ባንክ የድብቅ ዕዳ የመክፈል ኃላፊነት ሊኖርበት ይችላልን?

Thursday, February 5, 2015

“ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ አንድነትንና ሰማያዊን አዋህደዋቸዋል” ኢ/ር ይልቃል ጌትነት


Engineer Yilkal Getnet Semyawi party chairman
(ሰማያዊ ፓርቲ) የአንድነት መዋቅር በጣም ብዙ ነው፡፡ በየ ክፍለሀገሩ (በጎንደር፣ በወሎ፣ በጎጃም፣ በደቡብ ኢትዮጵያና በሌሎቹም) ለምዝገባ በተንቀሳቀስንበት ወቅት አብዛኛዎቹ በብዙ መንገድ ተባባረውናል፣ በግልጽም ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር እየሰሩ ነው፡፡ ብዙዎቹም እኛ በሌለን ቦታ ላይ የሰማያዊ ፓርቲን ፎርም ሞልተው ቀድመው ተመዝግበዋል፡፡ ይህን ስል ደግሞ ሰማያዊ በህግ ይህን የማድረግም መብት ስላለን ነው፡፡

ሰበር ዜና – የአንድነት አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ

ሰበር ዜና – የአንድነት አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ

UDJ party members joins Semayawi party
(ሰማያዊ ፓርቲ) ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡

Monday, February 2, 2015

ኤርምያስ ለገሰና የመለስ ዳቪንቺ ኮድ አሰባበ – እንግዳ ታደሰ

ኤርምያስ ለገሰና የመለስ-ዳቪንቺ ኮድ አሰባበሩ ! ርዕስ ከሰጠሁት ዝርዝር ጉዳይ በጥልቀት ከመግባቴ በፊት ፣ ብዙ ጊዜ ወያኔያዊው አገዛዝ ከጥንቷ ኮሚንስት ሶቭየት ህብረት ጋር መንግሥታዊ መዋቅሩም ሆነ የአገዛዝ ስልቱ ስለሚመሳሰልብኝ ፣ ዘና አርገው ወደ ሚያዝናኑኝ የሶቭየቶች ቀልድ ቤት ዘው ማለቴ አልቀረም ፡፡ ከገባሁ አልቀረም በየአምስት አመቱ ፣ በአገራችን እና በህዝቧ ላይ የሚሰራውን ቀልዳዊ ምርጫ አስመልክቶ የሚደሰኮርልን የአምስት ዓመት ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከጥንቷ የሶቭየት ህብረት የቅድ ፕላን ጋር ፍጹም ስለተመሳሰለብኝ በዚህ ምጸታዊ ቀልድ አሃዱ ልበል ፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቦርድ የፓርቲዎች ሚዲያ አጠቃቀም ድልድል ፍትሃዊ አለመሆኑን አስታወቀ

ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቦርድ ያወጣው ረቂቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ውድድር የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሰዓት አጠቃቀም ድልድል ፍትሃዊና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አለመሆኑን አስታወቀ፡፡Ethiopia's Semayawi (Blue) party logo
ዛሬ ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሀገር አቀፍ ፓርቲዎችን በረቂቅ የሰዓት ድልድሉ ላይ ጊዮን ሆቴል ጋብዞ ውይይት አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) ኃላፊዎች ረቂቁን ለውይይት ያቀረቡ ሲሆን፣ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ እና ሌሎች ኃላፊዎችም በውይይቱ ተገኝተዋል፡፡
የኢብኮ ኃላፊዎች ባቀረቡት የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚዲያ አጠቃቀም ረቂቅ ድልድል መሰረት 55 ፐርሰንት በፓርላማ መቀመጫ ወንበር ላላቸው ፓርቲዎች፣ 20 ፐርሰንት ፓርቲዎቹ በሚያቀርቧቸው ዕጩዎች ብዛት እንዲሁም ቀሪ 25 ፐርሰንቱ ለሁሉም ፓርቲዎች በዕኩል የሚከፋፈል እንደሆነ ተገልጹዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲን በመወከል በውይይቱ ላይ የተገኙት የፓርቲው የህግ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ከበደ ለነገረ ኢትዮጵያ እንደገለጹት፣ ረቂቅ የሚዲያ አጠቃቀሙ ድልድል ሲወጣ እንደ መስፈርት የተጠቀሙባቸው ነጥቦች ችግር ያሉባቸው ናቸው፡፡

Sunday, February 1, 2015

አንድነትን “እናኝከዋለን፤ እንገድለዋለን” – ምርጫ ቦርድ

ትዕግስቱ አወሉ እንደ አየለ ጫሚሶ

tplfs election board


የዛሬ አስር ዓመት “የሕዝብ ሱናሚ” እያለ ሲምል ሲገዘት የነበረው ህወሃት ሱናሚው ወደ እርሱ እየጎረፈ ሲመጣ በረገገ፡፡ መፍትሔ በጠብመንጃ አፈሙዝና በብረት ብቻ እንደሆነ የሚያምነው ህወሃት በረሃ የለመደውን በትሩን አነሳ፤ ንጹሃንን ጨፈጨፈ፤ ደም አፈሰሰ፤ ኢትዮጵያን ወደ እስርቤትነት ቀየራት፡፡ ትዕዛዙን በቀጥታ የሰጡት “ባለራዕዩ” ለፍርድ ሳይቀርቡ “እንደጀመርን እንጨርሰዋለን” ያሉትን ሰፊውን ሕዝብ ሳይጨርሱት እንደ ክዳን ቆርኪ ተስፈነጠሩት፤ ላይመለሱ ሄዱ፡፡

አንዳርጋቸው ጽጌ በእኔ እይታ

በየትናዬት (Awash_43)
አንዳርጋቸው ለኔ እንደ ሙሴ ነው። እንዴት ብትሉ እንዲህ እላችኋለሁ። ሙሴ ምቾት ከበዛበት ከፈርኦን ቤት ይልቅ የወገኖቹን ስቃይና መከራ እቀበላለሁ ብሎ በእምነት ለቆ ወጣ። ሙሉ ታሪኩን በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ታገኙታላችሁ።Andargachew Tsige, Ginbot 7 secretary
አንዳርጋቸው ከወያኔ ቤት ይልቅ የወገኖቹን ግፍና መከራን እጋራለሁ ብሎ በእምነት በገዛ ፈቃዱ ስልጣኑን ለቀቀ። እንዳውም ለማስታወስ ያህል “ነፃነትን የማያውቅ ነፃ አውጭ” ብሎ በፃፈው መፅሀፍ ቂም ተቋጥሮበት ቂምን አርግዞ መገላገል ያቃተው ወያኔ አሰረውም፣ ደበደበውም። ከዛም አገር ለቆ ከወጣ በኋላ እጁን አጣጥፎ በቃኝ ብሎ እንደሌሎቹ አልቀመጠም። የአገሩ ጉዳይ እረፍት ስለሚነሳው ቅንጅት ከተፈጠረ በኋላ በዛው ውስጥ ሆኖ ተሳትፎውን አበርክቶ በዝዋይ ማረሚያ ታሰረ።
እምቢ ለሀገሬ ብሎ ገና ለጋ ወጣት እያለ ልጓዝ በድል ጎዳና የዘመረውን ዝማሬውም በድል ስላልተወጣው እንደገና ሊያድሰው ብሎም ለመታገል ግንቦት ሰባት (7) ተብሎ የሚጠራውን ንቅናቄ ከመሰረቱት አንዱ ሆኖ በዛም ብቻ ሳይወሰን የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ሲመሰረት በግንባር ቀደምነት በኤርትራ በርሃ ዱር ቤቴ ብሎ ገባ።

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

UDJ/Andinet party logoየገዢውን ፓርቲና መንግስትን ሽፍትነት ያጋለጠው አንድነትን የማፍረስ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ በኢትዮጵያዊን ዘንድ ተቀባይነት አይኖረውም!!!
ጥር 21/2007 ዓ.ም በኢትዮጵያ ታሪክ የምርጫ ቦርድ የሚባል ተቋም ያለበትን ደረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ በዚህ ደረጃ እንዲዋራድ ከጀርባ ሆኖ አመራር የሚሰጠው ገዢ ፓርቲም ሆነ መንግሰት በዚያው ልክ የሚገባቸውን የተዋረደ ደረጃ የያዙበት ዕለት ነው ብለን እናምናለን፡፡ አንድነት ፓርቲ አንድም የህግ ጥሰት ሳይፈፅም የሚያደርጋቸውን ሁሉ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብና በሀገሪቱ ህግ እየፈፀመ ባለበት ሁኔታ በህግ ሽፋን የገዢው ፓርቲ ልሳን የሆነው ፋና ሬዲዮ፣ የመንግሰት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር የከፈቱት ዘመቻ የመጨረሻ የሆነውን አንድም ህጋዊ መሰረት የሌለውን ህገወጥ ውሳኔ በአንድነት ፓርቲ እና አባላት ላይ አሰተላልፈዋል፡፡

ካልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ - በእዉቀቱ ስዩም

(ክፍል ሦስት)
እንደምነሽ ሸገር
እንደምነሽ ሸገር
ማሽተት የተሣነው፤ የጋሽ ጣሰው ኣገር፡፡
ልክ እንደነ ፓሪስ፤ እንደሎንደን ሁላ
ፏፏቴም ባይኖርሽ፤ ሽቅብ የሚፈላ
ወንዝሽ ከማን ያንሳል
ከፈነዳ ቱቦ፤ የወጣ ሰገራ፤ ሰንጥቆሽ ይፈስሳል
ሲያቀብጠኝ ያን ሜሪላንድን የመሰለ ኣገር ትቸ ወደ ሸገር ተመለስሁ ፡፡ የተመለስኩበት ምክንያት ግልጥ ነው፡፡ ኣሜሪካን ኣገር ጥገኝነት ለመጠየቅ ውስጥ ውስጡን በምዘጋጅበት ሰኣት ዲሲ የሚኖሩ ጓደኞቼ የስንብት ፓርቲ ኣዘጋጅተው ጠሩኝ፡፡“የወጣው ሰው ሁሉ ወጥቶ በሚቀርበት በዚህ ቀውጢ ሰኣት ወደ ኣገርህ ለመመለስ ያሳየከው ቁርጠኝነት በጣም የሚያኮራ ነው” እያሉ ትከሻየን ተምተም ተምተም ኣረጉት፡፡ ሼም ይዞኝ ወደ ሸገር ተመለስሁ፡፡ ጸጸት የለበለበኝ ገና ኣውሮፕላኑ ሲነሣ ነው፡፡ እንድያውም ዱባይ ላይ ትራንዚት ስናደርግ ወደ ሳኡዲ ኣረብያ ልሸበልል ኣስቤ ነበር፡፡ የኣረብ ፖሊሶች በኮሌታየ ጠርዘው ኣስገቡኝ፡፡ “ኧረ ጎበዝ የንጉሥ ኣብደላ ቀብር ላይ ለመገኘት ነው” ብል ማን ሊሰማኝ፡፡ ሩቢላው ወደ ሸገር ሲወርድ ቁልቁል ኣገሬን ሾፍኳት፡፡ ልምላሜ የሚባል ነገር ኣልጣፈባትም ፡፡በርግጥ እንጦጦ ላይ የጥልያኑን ተጫዋች የባላቶሊን ቁንጮ የምታክል ጫካ ቀርታለች፡፡