Translate

Wednesday, October 31, 2012

የሙስሊም ችግር መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አዲስ የትግል ስልት መቀየሱን አስታወቀ


ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ተወካዮች የ ኢህአዴግ መንግስት ከ ህገመንግስት እውቅና ውጭ በሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ለማስቆም እና በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የአህባሽን አስተምሮ በግድ የሚጭንበት ፣ እንዲሁም በቅርቡ በወረዳዎች ባካሄደው ምርጫ ካድሬዎቹን በሙስሊሙ ላይ የሾመበትን ሁኔታ ለ አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመግታት አዲስ ስልት መቀየሱን አስታውቋል።

እስካሁን በተደረገው መብትን የማስከበር ሁኔታ ህዝበ ሙስሊሙ የከፈለው መስዋትነት ታላቅ ነው ያሉት የኮሚቴው ተወካዮች ፣ ትግሉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ከማስተላለፍ ባሻገር  በአዲስ አበባ፣  በአንዋር  እና በቤኒ መስጊዶች ይደረግ የነበረው ተቃውሞ ተጠናክሮ በከተማዋ በሚገኙ መስጊዶች ሁሉ በፈረቃ በየሳምንቱ እንዲካሄድ መወሰኑን አስታውቀዋል።

በክልል ከተሞችም በተወሰኑ መስጊዶች ብቻ ይደረጉ የነበሩ የመብት ማስከበር ትግሎች በክልሉ በሚገኙ ሁሉም መስጊዶች በየሳምንቱ በፈረቃ እንዲካሄድ ፣ የኮሚቴው ተወካዮችም ለህዝብ ሙስሊሙ ማህበረሰቡ  ስለትግሉ በየወቅቱ እንደሚያሳውቁ ገልጠዋል።

በኢህአዴግ ውስጥ በተፈጠረው አለመግባባት የተነሳ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ካቢኔያቸውን ሊመሰርቱ አልቻሉም


ኢሳት ዜና:-አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የኢህአዴግ ባለስልጣን ለኢሳት እንደተናገሩት  ኢህአዴግ የድርጅቱን አባላት የአመለካከት መዛባት ለማጥራት በሚል ከክልል ጀምሮ ግምገማ የጀመረ ሲሆን፣ ግምገማውን ወደ ወረዳ ለማድረስ ማቀዱም ታውቋል።

በአሁኑ ጊዜ የአባላቱ አመለካከት እየተጣራ ፣ አዲሱን የጠቅላይ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት አይቀበሉም የተባሉትን ለማግለል እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው።

በድርጅቶች መካከል በተነሳው አለመግባባትም አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ እስካሁን ድረስ ካቢኔያቸውን ሊሰይሙ አልቻሉም። በተለይም የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅትን የሚያረካ ስልጣን መጥፋቱ ፣ አቶ ሀይለማርያም ስልጣናቸውን ተጠቅመው ካቢኔያቸውን እንዳይሾሙ እንዳደረጋቸው ባለስልጣኑ ጠቁመዋል።

Tuesday, October 30, 2012

ኢትዮጵያ ለግብጽ አንድ ሚሊዮን ስኩዌር ሜትር መሬት ልትሰጥ ነው


ኢሳት ዜና:-እየተገነባ ባለው የህዳሴው ግድብ ሳቢያ ግብጽ ችግር ልትፈጥርብን ትችላለች የሚል ስጋት በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ መንግስት ደጋፊ ሚዲያዎች ሲስተጋቡ  ቢሰሙም፤ የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትር  ግን በተቃራኒው  በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል ያለው የልማት ግንኙነት እየተሻሻለ መምጣቱን ነው ይፋ ያደረጉት።

የግብጹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሺም ካንዲ በቅርቡ በአልጀሪያ ባደረጉት የሁለት ቀናት ጉብኝት ላይ ፤አገራቸው ፤ በአልጀሪያና በኢትዮጵያ ሁለት የኢንዱስትሪ  ዞኖችን ለመገንባት ማቀዷን አስታውቀዋል።

የግብጽ የማስታወቂያ ሚኒስቴር እንዳለው ፤ግብጽ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር  2014 ዓም ከመድረሱ በፊት በ አልጀሪያ 2 ጥብ 5 ሚሊዮን የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ማቀዷን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ይፋ አድርገዋል።

<<አህራም ኦንላይን>>የተሰኘው የግብጽ ተነባቢ ድረ-ገጽ በፎቶ አስደግፎ ያወጣው ዘገባ  እንደሚያመለክተው ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያ ለግብጽ 1 ሚሊዮን ስኩዌር ሜትር መሬት እንደምትሰጥ አስታውቃለች።

በማረቃ ወረዳ የየኔሰው ገብሬ ጓደኛ የሆነው ወጣት ራሱን በአደባባይ ሰቀለ


ኢሳት ዜና:-በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል የሜዳሊያ ተሸላሚ  የነበረው ወጣት ግርማ ወ/ማርያም ራሱን በአደባባይ ለመስቀል የተገደደው በአካባቢው ያለውን የመልካም አስተዳዳርና የፍትህ እጦት በመቃወም መሆኑን ጓደኞቹና ቤተሰቦቹ ለኢሳት ገልጠዋል።

በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል ፣ በዳውሮ ዞን ፣በማረቃ ወረዳ ፣ በዋካ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ወጣት ግርማ ወ/ማርያም፣ በ1980 ዓም ነበር የተወለደው ። የ10ኛ ክፍል ትምህርቱን 3 ነጥብ 8 በማምጣት  በአንደኝነት አጠናቆ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ መግባቱንና የኢኮኖሚክስ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት ማጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል።

ትምህርቱን እንዳጠናቀቀም በማረቃ ወረዳ በታክስና አስተዳዳር ተቀጥሮ መስራቱን፣  ይሁን እንጅ በስራ ላይ እያለ ከፍተኛ የሆነ የአስተደዳር በደል እንደደረሰበት በተለይም ወጣት የኔሰው ገብሬ ራሱን በማቃጠል ከገደለ በሁዋላ ወጣቱ የየኔሰውን ጥያቄዎች ያቀነቅናል በሚል ከፍተኛ ጫና ሲደርስበት እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ።

የኦሮሞ ፖለቲካ ጉዳይ (ከትናንት እስከ ዛሬ)


አቶ  ቡልቻ ደመቅሣ

የኦሮሞ የፖለቲካ ጉዳይ በየዘመኑ አንድ እርምጃ ወደፊት ሁለት እርምጃ ወደኋላ ሲመሏ ለዘመናት ቆይቷል፡፡ ይህ የሆነው ከአፄ ሚኒሊክ ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ ከዚያ በፊት፣ የኢትዮጵያ ነገስታት ኦሮሞን ለማሸነፍ ስላልቻሉ በየጊዜው እየተጋጩ እንደምንም አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ ፋዘር አልሜዳ የሚባለው የፖርቱጋል ቄስ በዚህ ጉዳይ በሰፊው ጽፏል፡፡ ነገር ግን አብሮነታቸው እንደ ገዥና ተገዥ አልነበረም፡፡ ከአጼ ልብነድንግል ጀምረው እስከ ንጉስ ሳህለ ስላሤ የነበሩት አፄዎች ሁሉ ኦሮሞን ለማሸነፍ እና ለመግዛት ያላደሩጉት ጥረት አልነበረም፡፡
 የኦሮሞ ፖለቲካ ጉዳይ (ከትናንት እስከ ዛሬ)
ኦሮሞንና ሀገሩን አሸንፈው ለማስገበር የቻሉት አፄ ሚኒሊክ ብቻ ነበሩ፡፡ እሳቸውም ኦሮሞን ለማሸነፍ የቻሉት ከኦሮሞዎች ቀደም ብለው ከፈረንጆች የጦር መሳሪያ ስላገኙ ነበር፡፡ መሣሪያ ያገኙበትም ምክንያት ከእሳቸው ቀድሞ የነበሩት አንዳንድ አፄዎች ለአውሮፓ መንግስታት “ኢትዮጵያ ብቻዋን ክርስቲያን ሆና በአፍሪካ ውስጥ የምትኖር ሀገር ነች” ብለው የአውሮፓውያን መንግሥታትን ስለለመኑና ስላስረዱ የጦር መሣሪያ ማግኘት ቻሉ፡፡ በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አፄ ሚኒሊክ ሸዋን በሙሉ ለመቆጣጠር ሲነቃነቁ ደብረብርሃን አጠገብ በምትገኘው አብደላ በምትባል መንደር ውስጥ ከጎበና ዳጬ ጋር ተገናኙ፡፡

የኢትዮጵያዋ፡ ርእዮት ‹‹የጥንካሬዬ ዋጋ››


ከፕሮፌሰር  ዓለማየሁ  ገብረማርያም
ትርጉም  ከነጻነት ለሃገሬ

Click here for PDF

ስለስልጣን ብልግና አለያም ስለ ስልጣንን በማንአለብኘነት አለ አግባብ ስለ ከመጠቀም ከመናገር ይበልጥ አስቸጋሪ የሆኑ bezu ነገሮች yelum፡፡ ለ31 ዓመቷ ወጣት ኢትዮጵያዊት አይበገሬ ርዕዮት ዓለሙ ግን፤ የመጻፍ ነጻነት፤ የመናገር ነጻነት፤ ሃሳብን በነጻ የማንሸራሸር ነጻነትን ድምጻቸው በመሳርያና በስለላ መዋቅር ለታፈነባቸው ድምጽ ከመሆን ምንም አይነት ጋሬጣ ቢደረደር ሊያደናቅፋት ጨርሶ አይችልም፡፡  አሁንም ቢሆን ባለችበት ክፉ ሁኔታም ሆና ስለግፍ ስልጣን ቁልጭ ያለ ሃቅን ትናገራለች፤ ‹‹ለጥንካሬዬ ዋጋ እንደምከፍል ብገነዘብም የሚቃጣብኝን ለመቋቋም ዝግጁ ነኝ››፡በማለት ካለችበት ገሃነማዊ የቃሊቲ ጉረኖ ባመለጠው የእጅ ጽሁፏ መልእክቷን  ለአለም አስተላልፋለች፡፡

“ጥንካሬ ለሁሉም ድርጊት ታላቅ ዋጋ አለው፡፡ ጥንካሬ ከሌለ ማንኛውንም አይነት ዋጋ ያለው ተግባር ማከናወንም ሆነ ማቀድ አይቻልም” ያለችው ታላቋ የአሜሪካ የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ጸሃፊ ማያ አንጀሉ ናት፡፡ ባለፈው ሳምንት የዓለም አቀፉ ሜዲያ ፋውንዴሽን (IWMF) የ2012ን  ታላቁን “የጋዜጠኝነት ጀግንነት” ሽልማቱን  ለአይበገሬዋ ርዕዮት ዓለሙ ሸልሟል፡፡ ባለፈው ሜይ ርዕዮትን ወደ ወህኒ ለመወርወርና ዝም ለማሰኘት ስለተከናወነው ሂደት ጽፌ ነበር፡፡

Monday, October 29, 2012

ትንሽ ወግ ብጤ፤ የተቀበረው ባንዲራ “እየተከበረ” ነው


የኢትዮጵያ ባንዲራ በኢህአዴግ መንግስት አበሳውን ያየውን ያህል ማንም ጊዜ አበሳ አላየም ብንል ማጋነን አይሆንም። ማጋነነን ቢሆንም ማጋነን በኛ አልተጀመረም እና ወጋችን ይቀጥላል።

ባለፈው ጊዜ የዞን 9 ብሎግ ልጆች “የመለስ  አስር የአፍ ወለምታዎችን” አስነብበውን ነበር። ከእነርሱ ውስጥም “ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር አንድ ሰዓት ቁጭ ብሎ ማውራት ዩንቨርስቲ ገብቶ ከመውጣት እኩል ነው!” ብለው መለስ ኢሳያስን ያንቆለጳጰሱበት ካሳቁኝ መካከል ነበር።

ካሳቀቁኝ መካከል ደግሞ “ባንዲራ ጨርቅ ነው!” ብለው የተናገሩት ይጠቀሳል።

መለስ ባንዲራን ጨርቅ ብለው ያንቋሸሹትን ያህል ታድያ እድሚያቸው ወደ ሞት ሲቃረብ ፀፀት ተሰምቷቸው ነው መሰል የባንዲራ በዓል ይከበር ብሎ አንድ የተባረከ ሰውዬ ሲጠይቅ “እሺ” አሉ… አወጁም። ጎሽ…! ይኸው ዛሬ ለአምስተኛ ጊዜ ባንዲራ ቀን እየተከበረ ነው።

መስማት የተሳነው፡ ስብሃት ነጋ


ከማተቤ መለሰ ተሰማ

በአጼ ምኒልክ ዘመን፡ አንድ ኢትዮጵያዊ፡ በድንገት መስማት ይሳነዋል አሉ፡ ሰውየው እድሜ ጠግቦ እስከሚሞት፡ የምኒልክ፣ የእያሱ፣ የዘውዲቱ ንግስና አልፎ፡ ከሀይለ ስላሴ የግዛት ዘመን አጋማሽ ድረስ ቆይቶ ነበርና፡ ጆሮው መስማት ከማቆሙ በፊት የነበረው ሁሉ እንዳለ፡ የቀጠለ መስሎት፡ በምኒልክ አምላክ እንዳለ ነው የሞተው ይባላል። በአጠቃላይ ስነምግባሩ፡ ሲታይ ከሰው ተወልዶ ከእንስሳት ጋር እንዳደገ፡ በግልጽ የሚመሰክርበት፡ ስብሃት ነጋም፡ እንዳይሰማ ጆሮው የደነቆረው፣ እንዳያነብ አይኑ የታወረው፡ ደደቢት ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን የሚቀር አይመስለኝም። ምክናያቱም ዛሪ ሕዋሃት የማስመሰያ ካባውን አጥልቆ፡ ኢትዮጵያዊ ለመባል እየጣረ ባለበት ወቅት ስብሃት ከ21 አመት በሗላ የሚናገረው ሁሉ፡ በምኒልክ ሲል እንዳለፈው ሰው ደደቢት በነበረበት ጊዜ ሲሰበክ የነበረውን፡ የኢትዮጵያን ህዝብ ማዋረድንና አማራንና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን  ማጥላላት፣ ስለአከተመለት ስርአት ሰለደርግ ማውራትን ነው። ከዚህ አንጻር ሲታይ፡ በአሁኑ ወቅት ሰውየውን በጥሞና ለሚከታተለው ሰው፡ ዘመናት ጥለውት ከንፈው እሱ አንድ ቦታላይ ቆሞ ለብቻው እየቆዘመ እንዳለ ለመገንዘብ አያዳግተውም።

ባለፉት 30 አመታት ከኢትዮጵያ ተዘርፎ ወደ ውጭ አገራት ባንኮች የተሻገረው ገንዘብ 450 ቢሊዮን ብር ደረሰ


ኢሳት ዜና:-አሜሪካ የሚገኘው የማሳቹሴትስ ዩኒቨርስቲ በያዝነው ወር ባወጣው አዲስ ጥናት ከኢትዮጵያ እየተዘረፈ ወደ ውጭ አገራት ባንኮች የተሻገረው ገንዘብ ባለፉት 30 አመታት ውስጥ 25 ቢሊዮን ዶላር ወይም 450 ቢሊዮን ብር መድረሱን ይፋ አድርጓል። ይህ አሀዝ  አገሪቱ ካላት አጠቃላይ ገቢ ውስጥ 84 በመቶ የሚሆነውን የሚሸፍን ነው።

ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር ሲተያይ የ8ኛ ደረጃነት ብትይም ነዳጅ ከማያመርቱ አፍሪካ አገሮች ጋር ስትወዳደር ደግሞ ቀዳሚ ሆናለች።

አብዛኛው ገንዘብ የሚዘረፈው ወደ ውጭ አገራት ከሚላኩና ከውጭ አገራት ከሚገቡ እቃዎች እንዲሁም በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ከሚልኩት ገንዘብ ነው፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ስፖንሰርነት ጥናቱን ያካሄደው ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ባለፉት 7 አመታት ከኢትዮጵያ ከ 11 ቢሊዮን ዶላር  ወይም ከ200 ቢሊዮን ብር በላይ መዘረፉን ይፋ ባደረገ አመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ነው ማሳቹሴትስ ዩኒቨርስቲ አዲሱን አስደንጋጭ ሪፖርት ይፋ ያደረገው።

አቃቢ ህግ በሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ላይ ክስ መሰረተ


ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 4ኛ ወንጀል ችሎት ዛር ከጧቱ 4፡30 ላይ ጀምሮ ማእከላዊ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ሙስሊም ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እና የሀይማኖት መብታችን ይከበርልን ባሉ ሼሆችናኡላማዎች ላይ የፌደራሉ አቃቢ ህግ የመሰረተውን ክስ ተምልክቷል።

ብርሀኑ ወንድማገኘሁ ፣ ዘረሰናይ ምስግናው እና ቴዎድሮስ ባህሩ አቃቢ ህጎች ሆነው የቀረቡ ሲሆን ለተከሳሾች ማለትም ለ29 ግለሰቦችና ሁለት ግብረሰናይ ድርጅቶች ጠበቃ ሆነው የቀረቡት ደግሞ አቶ ተማም አባቡልጋ፣ አቶ ብርሀኑ ፣ አቶ ሞሀመድ አብደላና ናቸው።

የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከቀኑ 4፤30 ላይ ዘግይቶ የጀመረ ሲሆን የ31 ሙስሊም ተከሳሾችን ማየት ሲጀምር አቃቢ ህግ የክስ ፋይሉ ማህተም ይቀረዋል በማለቱ ችሎቱ ለ40 ዲቂቃ ተቋርጦ የክስ ፋይሉ ከመጣ በሁዋላ እንደገና ተሰይሟል።

የ“አዲሱ መንግስት” ተግዳሮት እና የአቶ ኃይለማሪያም አጣብቂኝ


ዘሪሁን ተስፋዬ
(የቀድሞ የአዲስ ነገር ጋዜጣ ባልደረባ)
አዲስ ታይምስ
mስከረም 2፤ 2005 ዓ.ም ሎንዶን። ከእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ የተወከሉ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተናል ከሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች፣ ጋዜጠኞች እና የምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተወካይ ግለሰቦች ጋር ለውይይት ተቀምጠዋል። ወቅቱ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ማን ይተካ ይኾን የሚለው ጉዳይ የሚብሰለሰልበት ነበር። በርግጥ ለእንግሊዝ ተወካዮች የሚያብሰለስል ጉዳይ አልነበረም፤ ምስጢራቸውን በልባቸው ሸሽገው ከባለሞያዎቹ ተጨማሪ ሃሳቦችን ይሰበስባሉ። ሁሉም ባለድርሻ የሚመስለውን እና ጥናቱ ያመላከተውን ሐሳብ ሰነዘረ። ተንታኞችን በሚያስማማ መልኩ የአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ተተኪነት አነጋጋሪ አልነበረም። በጠቅላይ ሚኒስትር ተተኪ ማንነት ላይ ላይ ጥርጣሬ የነበረው ማንም አልነበረም። የድሕረ መለስ የፖለቲካ ኹኔታ እንዲሁ ትኩረት ያገኘ ነበር።

በእስራኤል የተደበደበው የሱዳን ሚስጢራዊ የጦር መሣሪያ ፋብሪካ ለኢትዮጵያ ሥጋት መሆኑ ተጠቆመ


በጋዜጣው ሪፖርተር
ባለፈው ማክሰኞ ሌሊት ከሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በስተደቡብ የሚገኘው ሚስጥራዊ የጦር መሣርያ ፋብሪካ በእስራኤል የሚሳይል ጥቃት እንደተፈጸመበት ከታወቀ በኋላ፣ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ሥጋት መሆኑን ዜጎችና የፖለቲካ ተንታኞች እያስረዱ ነው፡፡
እስራኤል በዚህ እጅግ ሚስጥራዊ ነው በተባለለት ወታደራዊ የጦር መሣርያ ፋብሪካ ላይ ጥቃቱን የፈጸመችው በቅርቡ በሒዝቦላህ የተላከባት ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን (Drone) ግዛቷ ውስጥ መትታ ከጣለች በኋላ መሆኑ ታውቋል፡፡ የእስራኤል ወታደራዊ ባለሥልጣናት ሰው አልባው የጦር አውሮፕላን የተመረተው በካርቱም የጦር መሣርያ ፋብሪካ ውስጥ መሆኑን፣ በግብፅ በኩል ተጓጉዞ ለኢራን ከደረሰ በኋላ ሊባኖስ ውስጥ ለመሸገው ሒዝቦላህ መሰጠቱን መግለጻቸው በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኅን ተገልጿል፡፡

ምንም እንኳን እስራኤል የጦር መሣርያ ፋብሪካውን በሚሳይል ማጥቃቷን በቀጥታ ባታስተባብልም፣ የሱዳን መንግሥት ከጠላቶቿ ጋር እያሴረባት መሆኑን ወታደራዊ ባለሥልጣናቷ እየገለጹ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጥርስ ውስጥ ገብቷል


“አቶ መለስ፣ በረከትና ኃይለማርያም የቤተሰብ ያህል ነበሩ”
polis


የኦሮሚያን ክልል በውክልና የሚያስተዳድረው ኦህዴድ አቶ መለስ ህይወታቸው ካለፈ በኋላ ውስጥ ውስጡን ሲንተከተክ የቆየው የድርጅቱ “የመስመር” ችግር ይፋ መሆኑን ተከትሎ በተፈጠረ ስጋት የኦሮሚያ ልዩ የፖሊስ ተወርዋሪ ሃይል እንደ ቀድሞው እንደማይታመን ተጠቆመ።

ከሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች

girma seyifu


አቶ ግርማ ለጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ዘለፋ መልስ ሰጡ
በተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ መድረክ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ መድረክ የምርጫ ስነምግባር ኮዱን ላለመፈረሙ ያቀረቡትን ምክንያትና ዘለፋ አጣጣሉት። አቶ ግርማ ኦክቶበር 22 ቀን 2005 ዓ ም ከሪፖርተር  ከጋዜጠኛ ዮሐንስ አምበርብር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት “ከአይ ዲ ኤ በቀጥታ ተቀዳ የተባለው የምርጫ ስነ ምግባር ኮድ ሁለት ፓኬጆች የተካተቱበት አይደለም” ብለዋል።

“በፖለቲካ ቂም” የተመሰረተ ክስ ውድቅ ሆነ


ዳኞቹና ዓቃብያነ ህጉ በፖለቲካ ውሳኔ ተባረሩ
gambella


በጋምቤላ ሁለት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችና ሁለት ጠበቆች “በፖለቲካ ቂም ውሳኔያችንን አናዛባም” በማለታቸው ከስራና ከሃላፊነታቸው መሰናበታቸው ታወቀ። ሁለት የክልሉ የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃብያነ ህግም በተመሳሳይ ውሳኔ ከሃላፊነታቸው መባረራቸው የተጠቆመ ሲሆን ውሳኔው የክልሉ ፕሬዚዳንት ወንድም የሆኑትን ዓቃቤ ህግ አላካተተም።

Saturday, October 27, 2012

ወያኔ/ኢህአደግ ውስጥ የተፈጠረው ክፍፍል ግንባሩን ከማዳከም አልፎ ወደ መግደል እያመራ መሆኑን የወያኔ ልሳን የሆነው ሪፖርተር አስጠነቀቀ


የህወሃት የቀድሞ ታጋይና በመጀመሪያዎቹ የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴለቪዥንን መሥሪያቤትን ለረጅም ጊዜ በሃላፊነት ሲመራ የቆየው አማረ አረጋዊ ንብረት የሆነው ሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው ረቡዕ ር ዕሰ አንንቀጹ እንዳሰፈረው ህዝብ በሃዘን ወቅት ስላዘነና በደስታም ጊዜ በጋራ ስለ ጨፈረ ከወያኔ / ኢህአዴግ ጋር ያለውን ግንኙነት በአወንታዊ መልኩ አንጸባረቀ ማለት አለመሆኑንና ይልቁኑም በበርካታ ችግሮች ምክንያት ልቡ ከድርጅቱ መራቁን በመግለጽ የቀድሞ ጓዶቹ ሳይመሽባቸው መልሰው የሚጠናከሩበትን ዜዴ አጥብቀው እንዲሹ አሳስቦአል።
ወያኔ ዛሬም እንደ ትናንቱ ጠንካራ ነኝ እያለ ራሱንና አንዳንድ የዋሆችን ለማታለል ቢሞክርም እውነታው ግን ፍጹም የተለየና በሌላ ጽንፍ ያለ መሆኑ ያሳሰበው ሪፖርተር ወያኔ / ኢህአዴግ ደፋርና ቆራጥ የውስጥ ትግል አካሂዶ ካልተስተካከለ በስተቀር በስብሶ መደርመሱና የነበረው እንዳልነበረ መሆኑ አይቀርም በማለት አስጠንቅቆአል።
ሪፖርተር የቀድሞ የትግል ጓዶቹንና እስከ ደርግ መውደቅ የታገለለትን ፓርቲውን ከውድቀት ለማዳን ተጨንቆ በጻፈው በዚህ ርዕሰ አንቀጽ በእርግጥ ከተቃዋሚዎች አንጻር ሲታይ ግንባሩ የተሻለ አንድነት ቢኖረውም ወቅቱ ከሚጠይቀው አኳያ ግን የውስጥ አንድነቱ ደካማ  ስለሆነ ይህንን  እውነታ ከግንዛቤ በማስገባት እራስን ከማታለል ተቆጥቦ የቀድሞ አንድነትን በቶሎ መመለስ የተገባ ነው ብሎአል።

በወያኔ መዳፍ ውስጥ ያለችው ኢትዮጵያ በገለልተኛ ተቋማት ሚዛን


ዘረኛውና አምባገነኑ ወያኔ ሥልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች በመመንጠቅ ላይ ያለች ለማስመሰል ይጥራል። ይባስ ብሎም በሌሎች አገራት እድገት የሌለ በማስመሰል ስለ መለስ ዜናዊ “ተዓምራዊ” አመራር ይደሰኩራል። በፍትህ፣ በዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ረገድም የሚደርስብኝ የለም እያለ ይፎክራል።
“ይሉሽን በሰማሽ …” ለማለት ያህል ገለልተኛ የምርምር ተቋማት ስለኢትዮጵያ ካሉት ጥቂቶችን ለአብነት እናቅርብ።

1.     በአፍሪቃ የመልካም አስተዳደር መለኪያ /Mo Ibrahim Governance Index/

“ሞይ ኢብራሂም ፋውዴሽን” በአፍሪቃ ውስጥ መልካም አስተዳደርን ለማበረታታት የተቋቋመ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ነው። ከፋውንዴሽኑ ፕሮግራሞች አንዱ አገራቸውን በመልካም ሁኔታ አስተዳድረው የሥልጣን ሽግግር ላደረጉ የአፍሪቃ መሪዎች 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በመሸለም መልካም አስተዳደርን ማበረታት ነው። ይህ ፋዉንዴሽን ሥራውን ከጀመረ ስድስት ዓመታት ቢሞሉትም እስካሁን ለመሸለም የታደለው ግን ሶስት የአፍሪቃ መሪዎችን ብቻ ነው። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2007 የሞዛቢኩን ፕሬዚዳንት ጃኩም አልቤርቶ ቺሳኖ፣ በ2008 የቦትስዋናውን ፕሬዚዳንት ፌስተስ ጎንተባንዬ ሞጋዬ እና አምና በ 2011 የኬፕ ቨርዴውን ፕሬዚዳንት ፔድሮ ቬሮና ፓይረስ ይህን ታላቅ ሽልማት አግኝተዋል። ወያኔ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና አፍቃሪ ወያኔዎች “ታላቁ የአፍሪቃ መሪ” እያሉ የሚያሞካሹት ሰው መለስ ዜናዊ በዝርዝሩ ውስጥ ገብቶ እንደማያውቅ  ልብ ይበሉ።

“ቃሊቲ”ን በጨረፍታ – በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (ክፍል ሁለት)



ቃሊቲን በጨረፍታ – ክፍል ሁለት

በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

. . . እድሜዋ በግምት ወደ 50 የሚጠጋ፤ በክንዷ ላይ የአስር አለቃ ማዕረግ የለጠፈች (ሳጅን) በጥያቄ ታጣድፈኝ ጀመር፤ ለነገሩ በጥፊ ከመጣደፍ በጥያቄ መጣደፍ በብዙ የተሻለ ነው ብዬ ስለገመትኩ ያለቅሬታ ነበር የጠየቀችኝን ሁሉ የመለስኩላት፡፡ “ስምህ ማነው?” የተረከብሽበት ወረቀት ላይ አለልሽ ልላት አሰብኩና ተውኩት፡፡  በምትኩ ሙሉ ስሜን ነገርኳት፡፡

“ብሔርህ ምንድን ነው?” “እግዜር ይይልህ ኢህአዴግ!” በሆዴ ያልኩት ነው፡፡  በአፌ ግን እንደምንም ቀጣጥዬ እና ሰፋፍቼ ብሄሬን ተናገርኩ፡፡

ቃሊቲን በጨረፍታ – በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ (ክፍል አንድ)




በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

ተወዳጁ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና “የቃሊቲው መንግስት” በሚል ርዕስ በፃፈው መፅሐፍ እስረኞች በቃሊቲው ማረሚያ ቤት የሚኖራቸውን የህይወት ገፅታ ጨርፎ አሳይቶናል፡፡  ጋዜጠኛ ወሰንሰገድ ገ/ኪዳን ደግሞ “የቃሊቲ ሚስጥሮች” በተሰኘው መፅሐፉ የቅንጅት አመራሮች በቃሊቲ እስር ቤት በታሰሩ ወቅት እርስ በእርስ ምን እየተባባሉ እንደሚጎናነጡ እንዲሁ ጨርፎልናል፡፡  መቼም የቃሊቲ ጉድ በእነዚህ ሁለት መጽሐፍት ብቻ የሚገደብ እንዳልሆነ ለደቂቃም ቢሆን ግቢውን የረገጠ ይገባዋል፡፡  እናም በአርኪዎሎጂ ጥበብ ከተገኙ ጥንታዊ ከተሞች አንዱን የመሰለ ገፅታ በተላበሰው እስር ቤት ከየትኛውም ብሔር እና የሀገሪቱ ድንበር ያልተወከለ የለም- በእስረኝነት ማለቴ ነው፡፡

Friday, October 26, 2012

አጫጭር ወሬዎች


አቤ ቶኪቻው

አንድአጫጭር ወሬዎች
በመጀመሪያ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወዳጆቼ እንኳን ለኢድ አልድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ነገ የአረፋ በዓል በሚደረግባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች በሙሉ ለኢህአዴግ ሁለተኛው ቢጫ ሊሰጠው መሆኑን ሰምቻለሁ።
አዲሳባ ስታድየምን ጨምሮ በየክፍለ ሀገሩ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች “መንግስት ከሀይማኖታችን ላይ እጁን ያንሳ” ብለው ለብዙኛ ጊዜ ደግመው ሊነግሩት ተነስተዋል። ትላንት ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ይመሰረትባቸዋል ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ አባላት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በመዋላቸው “ሊለቀቁ ይሆን” የሚል ተስፋ በብዙዎች ዘንድ አጭሮ ነበር። ነገር ግን ክሱ ወደ ከፍተኛው ፍርድ ቤት መዛወሩን ዛሬ ሰምተናል።

የአላሙዲ ኪስ በወርቅ ሲታጨቅ፤ አዶላ ኑሮ በጭንቅ!


(አሥራደው ከፈረንሳይ)
gold

ከሳምንታት በፊት የለገደንቢ ወርቅ ሽያጭ ድራማ!! ወርቃችን እንዴት አላሙዲ እጅ ገባ? በሚል ርዕር ላቀረብነው ጽሑፍ የድረገጻችን አንባቢ አሥራደው የሚከተለውን በግጥም የተከሸነ መልዕክት ልከውልናል፡፡

“መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ…”

the hole


ይህንን ቃለምልልስ ያደረግነው ለበርካታ ዓመታት ለኢህአዴግ ሲሰራ ከነበረና በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ትምህርት ውጪ አገር ከሚገኝ ኢትዮጵያዊ ጋር ነው፡፡ ለደኅንነት ሲባል ስሙን ከመጥቀስ ተቆጥበናል፡፡
ጎልጉል ፦ የጠ/ሚኒስትር መለስ መታመም ድንገተኛ ነው የሚሉ አሉ፤ አሟሟታቸውም ድንገት ነው የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አጋጣሚው መልካም እንደሆነ የሚጠቁሙ አሉ አንተ ከየትኛው ወገን ነህ?
መልስ፦ ቅድሚያ አቶ መለስ ድንገት አልታመሙም። በሽታቸው የቆየ እንደሆነ ይታወቃል። ምስጢርም አይደለም። ለዚሁ እኮ ነው ቤተ መንግስት ውስጥ በአዋጅ የተፈቀደላቸውን ቤት አሰርተው በቅርብ ርቀት እየተቆጣጠሩ ለመኖር ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ የነበረው። በዚህ ቢስተካከል ለማለት ነው። መለስ ለኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች ሁሉ የጋራ ነጠብ ናቸው። በድልድይም ይመሰላሉ። በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች፣ በተለይም ዋናዎቹ አራት ፓርቲዎች በውስጣቸው የያዙት 21 ዓመትና ከዚያም በላይ የታመቀ ቁርሾ አለ። የመለስ ማለፍ በየድርጅቱ ታፍኖ የኖረውን ቁርሾ ማፈንዳቱ አይቀርም። ከዚህ አንጻር ሳየው የመለስ ሞት አጋጣሚው መልካም የሚሆንበት አግባብ ከምን እንደሆነ ልረዳው አልችልም።

ከሲና የተረፉት የሲኦል ነዋሪዎች ጩኸት!!


“አሁን ጉዳያችን ለዓለም መድረሱን ሰማን” እስረኞቹ
refugees crossing southern israel


“ላለፉት ሶስት ዓመታት ማንም ሳያውቀን ታስረናል። አሁን ጉዳያችን ለዓለም መድረሱን ሰማን።የተፈታን መስሎናል” የሚሉት እስራኤል ራምሌ በሚባ እስርቤት ከሶስት ዓመት በላይ ታስረው ያሉት ወገኖች ናቸው። ይህ የሆነው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር በርዕስ ለእስራኤል ጠ/ሚኒስትር በግልባጭ ደግሞ ከጉዳዩ ጋር አግባብ ላላቸው ለተለያዩ የአገሪቱ ባለስልጣናት፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የመገናኛዎች አውታሮች ያሰራጩትን ደብዳቤ ተከትሎ በእስር ላይ ያሉት ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በመንቀሳቀሱ ነው።

እራሱን ያልሆነው ጠ/ሚንስትር


ጌዲዮን ደሳለኝ ከኖርዎይ
Ethiopian Author and writer from Norway
ጌዲዮን ደሳለኝ
ለሁለት  አስርተ አመታት በኢትዮጲያና  በህዝቦቿ ላይ ነግሶ በማን አለብኝነት አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ በሁሉም ያገሪቱ አቅጣጫዎች ሰላማዊውን ህዝብ ለሞትና ለስደት እንዲሁም ለእስር ሲዳርግ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በፈፀመው ግፍና ሰቆቃ ለምድራዊ ፍርድ ሳይበቃ ይችን አለም ሲሰናበታት የብዙዎቻችን ነፃነት ናፋቂዎች ተስፋ ቢለመልምም ስርዓቱ ካለው እኩይ ተፈጥሯዊ  ባህሪ አንፃር የናፈቅነውንና የተመኘነውን ነፃነትም ሆነ ለውጥ ሳይመጣ እነሆ ሌሎች ንፁሃን ሲገደሉና ሲሰደዱ እንዲሁም ሲታሰሩ አየን ሰማን፡፡

Thursday, October 25, 2012

”ላለመማር መማር.. ፤ ከራስ ክህደት እስከ ሀገር ማፍረስ…”


ከፊልጶስ / ጥቅምት 2005
በመጀመሪያ ‘ራሳቸውን ከዱ፣ ከዚያም በጥላቻ ታውሩ፣ ከዚያም ኢትዮጵያዊነትን ኢትዮጵያን አምርረው ጠሉ፣ ከዚያም  በታሪካዊ ጠላቶቻችን እየተመሩና እየታገዙ፣ የገንዛ ወገናቸውን ‘ርስ-በ’ርስ እያበጣበጡና እያለያዩ፣ ኢትዮጵያን እያፈራረሱ፣ ለባዕዳንና ለታሪካዊ ጠላቶቻችን እየቸበቸቡ አሁን ካሉበት ደረጃ ደረሱ። ወያኔ/ኢሕአዴጎች።
የተከበሩት ኔልሰን መንዴላ እንዲህ ይሉናል ”….. ፍቅር አብሮን የተወለደ በተፈጥሮ ያገኘነው ነው። ጥላቻ ግን በትምህርት ያገኘነው ነው። ስለዚህ ጥላቻን በትምህርት ልናስወግደው እንችላለን።….”። ግን በ’ኛ ሀገር  ለወያኔ ገዥዎቻችን ጥላቻና ክህደት አብሮ’ቸው የተፈጠረ ይመስላል። ያለፈው አልበቃቸው ብሎ አሁንም የጥላቻንና የዘረኝነትን መርዝ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በህዝብ ላይ ይረጫሉ። ”ለምን?..” ያለውን ደግሞ ያስራሉ፣ ያሳድዳሉ፣ ይዘርፋሉ፣ ይገላሉ፣ ያስገድላሉ። እንደ’ነሱ ጠበንና አንሰን፣ ሀገራዊነትን አውግዘን፣ ስብእናችን ሁሉ ”ጎጠኝነት” አንዲሆን ሌት ተቀን ይደክማሉ። ለመሆኑ ከዘመናት በፊት ”ዘሬ የሰው ልጅ ነው፤ ሀገሬም ዓለም ነው።” ያለው ደራሲ (ስሙን ማስታወስ ስላልቻልኩ ይቅርታ።) በዚህ ዘመን ወያኔወችን እጅ ቢጥለው ምን ይል ይሆን? እነሱስ ምን ያደርጉት ይሆን?

Wednesday, October 24, 2012

የአይን ቀለም አንመረምርም


ጥያቄ : - ጠ /ሚኒስትር አቶ ኃ /ማሪያም አዲሱን ስልጣን እንዴት አዩት ?
ጠ /ሚኒስትር ኃ /ማሪያም : - እንግዲህ ከጌታ ጋር ሁሉንም ለመወጣት ተያይዘናል ያስጀመረን ጌታ ከግቡ ያደርሰናል የሚል ዕምነት አለኝ ::
ጥያቄ : - እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አልፎ አልፎ በከባድ ጥበቃ እየታጀቡ ወደ ቤ /ክርስቲያን እንደሚሄዱ ባለቤቴ ትነገረኛለች :: ይህ እውነት ነው ?
ጠ /ሚኒስትር ኃ /ማሪያም : - አዎን ለእኔና ለቤተሰቤ መሰረታችን እምነታችን ስለሆነ የዘውትር ሕይወታችን በቤተክርስቲያን ዙሪያ ነው :: ጊዜ ሳገኝ አልፎ አልፎ እሁድን እንደምንም ቸርች ለመሄድ ጥረት አደርጋለሁ : ካልሆነም ቄሶችና የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እኛ ቤት ድረስ እየመጡ የጌታን ቃል ያካፍሉናል :: በቤታችን ውስጥ ግን ማታ ማታ ሁሌም የቤተሰብ ፕሮግራም እናደርጋለን :: እንዘምራለን እናመልካለን :: መጽሐፍ ቅዱስ ከፍተን ሁላችንም ጥቅሶች አንብበን ተንበርክከን ጸሎት አርገን ወደ መኝታ እንሄዳለን ::
ጥያቄ : - አብረዋችሁ የሚሰሩ የኢሕአዴግ ሰዎች ባልሳሳት ኤትየስት / ኃይማኖት አልባ ናቸው : ሲባል እሰማለሁ ይህ ሁኔታ ለእርሶ በሥራዎት ላይ ፈተና አልሆንቦትም ?
ጠ /ሚ ኃ /ማሪያም :- በኢሕአዴግ ፖሊሲ ኃይማኖትን የግል አርገህ በውስጥህ የምትይዘው ነገር ስለሆነ በአመራር ውስጥ ያለነው የራሳችንን ኃይማኖት በሌሎቹ ላይ ማንጸባረቅ ወይም ጫና ማድረግ ባይፈቀድልንም አንዳንዶቹ ስለእኔ እምነት ለማወቅ የሚፈልጉት ነገር ሲኖር ከመጠየቅ ወደ ኋላ ብለው አያውቁም :: እኔም በመጠኑ መንገድ ለማስረዳት እሞክራለሁ :: በተረፈ ከሥራ ጓዶቼም ጋር ሆን ብለን በሥራ ቦታ ስለ ግል እምነት አንስተን ተወያይተን አናውቅም :: ይህን ስል በአገሪቱ በኃይማኖቶች ዙሪያ በሚፈጠሩት ችግሮች መንግሥት ምን ማድረግ አለበት በሚለው ላይ አንወያይም ማለቴ አይደለም ::
ጥያቄ :- ለመሆኑ ከአቶ መለስ ዜናዊ ጋር ስለ ኃይማኖትዎ አንስተው ተወያይተውበት ያውቃሉ ?

ይህ ከአዲሳባ ወዳጆቼ ጋር የተጨዋወትኩት ጨዋታ ነው።


Abe Tokchaw
ኢህአዴግ አቅም እንደሌለው ግለሰብ እዚህም እዛም ደጋፊ ሁኑኝ እያለ ሰዎችን እያስቸገረ ነው አሉ!
ባለፈው ጊዜ አንዷ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኛ አለቃዋ መጥሪያ አንቃጭለው ጠሯት። እርሷም፤ “አቤት ጌታዬ ምን ልታዘዝ” ብላ ሄደች! ጌታዋ ግን “ኢህአዴግ ጌታ ነው! አሜን በይ!” አሏት። ነገሩ እንዲገጣጠምልኝ ብዬ እንጂ አባል መሆን እንዳለባት ሰበኳት ለማለት ፈልጌ ነው። “ገብቶኛል ባክህ…” ካሉኝ “ድሮም የገባዎት እኮ ኖት” ብዬ አቆላምጪዎ እቀጥላለሁ።
ልጅት ግን ነገሩ የሚያመጣው ጦስ ጥንቡሳት አልገባትም ነበርና “እምቢኝ” አለች። “ውድ አለቃዬ ይቅርታ ያድረጉልኝና ስብሰባ ምናምን ደስ ስለማይለኝ የኢህአዴግ አባል ለመሆን ፍላጎት የለኝም።” ብላ ለአለቃ በሚገባ ትህትና ነገረቻቸው። እሳቸውም “ይቻላል ጥርግ በይ!” ብለው አሰናበቷት።
ቀጥላ ጓደኛዋ ተጠራች። ጓደኛዋ ከመግባቷ በፊት በጆሮዋ ለምን እንደተፈለገች አንሾካሾከችላት… እርሷም “አረ ባክሽ…!  ደ…ፋር! በያቸው!” ብላ ገባች።

ወ/ሮ አዜብ ቤተ-መንግስቱን ለቀቁ


ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ በ አቶ መለስ ምትክ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ከመረጠች ወራት ቢቆጠሩም ፤ ተሿሚው አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ለረዥም ቤተ-መንግስት መግባት ሳይችሉ መቆየታቸው ይታወሳል።
ከ አቶ መለስ ሞት ከረዥም ጊዜ በሁዋላ ዘግይቶ የተሾሙት አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር  ወደ ቤተ-መንግስቱ መግባት ያልቻሉት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እንደነበርም ይታወቃል።
በዚህም ምክንያት አቶ  ሀይለማርያም ከመኖሪያ ቤታቸው እየተመላለሱ ለመሥራት በመገደዳቸው ወደ ሥራ ሲወጡና ሲገቡ በሚደረግላቸው አጀባ መንገዶች እየተዘጉ፤ ህብረተሰቡ ለእንግልት ሲዳረግ መቆየቱ በ ኢሳትና አገር ቤት በሚታተሙ ጋዜጣዎች የተዘገበው ከሳምንት በፊት ነበር።
የወይዘሮ አዜብ፡የቅርብ ጓደኛ እንደሆኑ የሚነገርላቸው  የዛሚ ኤፍ ኤም ባለቤት ወይዘሮ ሚሚ ስብሀቱም  የአቶ መለስ 40 ሳያልፍ የዚህ ዐይነት ነገር መነሳቱ  አግባብ እንዳልሆነ በመጥቀስና በጋዜጦቹ ዘገባ በመቆጣት፦<<መረጃውን ለጋዜጣ የሰጡት እርሳቸው ከሆኑ የሚያሳዝን ነገር ነው>> በማለት አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ወቅሰዋል።
የ ኢዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤተ መንግስት አለመግባት ከኢትዮጵያውያን አልፎ የውጪ ሚዲያዎችን ሁሉ ትኩረት ስቧል።

Tuesday, October 23, 2012

Breast Cancer Awareness for Ethiopian Women and Men


by Alemayehu G. Mariam
October is international Breast Cancer Awareness month. Throughout the month, public and private organizations inBreast Cancer Awareness for Ethiopian Women and Men many countries promote programs and activities aimed at breast cancer risk reduction, early detection, treatment and research. It is well-established that breast cancer is one of the most common cancers affecting women throughout the world. Millions of women are diagnosed with the disease every year and hundreds of thousands die needlessly. Breast cancer is the second leading cause of death among African American women in the U.S., according to the Komen for the Cure organization. There is little reliable data on the incidence and prevalence of breast cancer in Africa because of the absence of reporting, diagnostic and treatment processes. Breast cancer cases in Africa are likely to be documented only when patients come to  hospitals, health centers, clinics and laboratories for diagnostic and treatment services.

Ginbot 7 urges Ethiopians to stand with Muslim brothers and sisters


Brutal Killings Inside Mosques Will Not Deter The Resolve Of The Ethiopian Muslim Community

Ginbot 7 Press Release
Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and DemocracyIn the twenty one years of the TPLF rule, the Ethiopian people and the world at large have witnessed mass killings, targeted killings, and indiscriminate killings of the young, old, women and children as young as 8 years old. In 2005, the mass killing in Ethiopia reached its climax when special security forces under the direct order from the late Prime Minister Meles Zenawi savagely killed over 200 people as the world watched quietly. When Deputy PM Haile Mariam Desalegn took the oath of office and promised to walk on the same path as his predecessor, many Ethiopians lowered their expectation of witnessing a free, just and democratic Ethiopia in their life time.

የህወሀቱ መስራች አቶ ስብሀት ነጋ፦”የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዲሞክራሲ ብቁ አይደለም” አሉ


ኢሳት ዜና:-አቶ ስብሀት ይህን ያሉት   <የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ከ አቶ መለስ ሞት በሁዋላ ምን ለውጥ ይኖረዋል?>በሚል ርዕስ ከጀርመን  ምክር ቤት አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።በበርሊን በተደረገውና ኢትዮጵያ፤ኬንያ እና ማላዊ ላይ ባነጣጠረው በዚሁ ስብሰባ ኢትዮጵያን ወክለው የተገኙት አቶ ስብሀት ነጋ አቶ መለስ ቢሞቱም ፖሊሲን በተመለከተ ምንም ዓይነት ለውጥ እንደማይኖር ተናግረዋል።
<<መለስ አንድ ሰው ነው፤በ አንድ ሰው ሞት የድርጅቱ ዓላማ አይቀየርም፤ስለዚህ በ ኢትዮጵያ መንግስት በኩል የፖሊሲ ለውጥ አይኖርም” ነው ያሉት አቶ ስብሀት።
መንግስታቸው የደርግ ተከታዮችንና የፊውዳል ርዝራዦችን ለመቆጣጠር ብዙ ዓመታት እንደሠራ የጠቀሱት አቶ ስብሀት፤<<በደርግ የተበላሸውን የ ኢትዮጵያ ህዝብ ለማስተማር ብዙ ጊዜ አጥፍተናል>ብለዋል።
ንግራቸውንም የዘጉት፦<የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዲሞክራሲ ብቁ አይደለም>> በማለት ነው።
መድረኩ ለውይይት ክፍት መሆኑን ተከትሎ በስፍራው የተገኙት ኢትዮጵያውያን በ አቶ ስብሀት ላይ ጠንካራ የተቃውሞ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ሰንዝረዋል።

በገርባ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ በርካታ ወጣቶች እየታሰሩ ነው


ኢሳት ዜና:-የፌደራል ፖሊስ አባላት 4 ንጸሁን ዜጎችን ፣ ሁለቱን አስረው በመውስድና በመረሸን ሁለቱን ደግሞ በተቃውሞው ቦታ ላይ ከገደሉ በሁዋላ ፣ ሌሊቱን የቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ በርካታ የገርባ ቀበሌ ወጣቶችን ማሰራቸው ታውቋል።
ትናንት ምሽት በርካታ ወጣቶች ከተደበቁበት ቦታ በመሆን ስልኮችን ወደ ኢሳት ቢሮ እየደወሉ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቤቶችን እያስከፈቱ ሲሰፈትሹ እንደነበር ድምጻቸውን ዝቅ በማድረግ ሲናገሩ አምሽተዋል።
እስካሁን ድረስ የታሰሩትን ሰዎች ቁጥር በውል ለመለየት ባይቻልም፣ የ106 ሰዎችን ዝም ዝርዝር የያዙ የፌደራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ በአህባሽ አስተምህሮ ተከታይነታቸው ከሚታወቁ ሰዎች ጋር በመሆን ቤቶችን እየፈተሹ አንዳንድ ወጣቶችን ይዘው አስረዋል።
የታሰሩ ሰዎችን ስም ዝርዝር በማጠናቀር  ላይ ያሉ የአካባቢው ወጣቶች እንደገለጡት እስካሁን ድረስ ባጠናከሩት መረጃ እስማኤል አብዱ አዎል፣ አብዱላሂም፣ ኡስማን አህመድ፣ ሼህ አብዱ፣ አህመድ ዳሊ ፣ ኑሩ አህመድ፣ ሳሊም ኬሌና አብዶ አህመድ የተባሉ የገርባ ነዋሪዎች ታስረዋል። የእስረኞች ቁጥር ግን ከዚህም አሀዝ እንደሚበልጥ በእርግጠኝነት ተናግረዋል።

ከሃገር ወዳድ የትግራይ ተወላጆች የተሰጠ ጥብቅ ማሳሰቢያ


መጽሐፈ ኢያሱ 3:9 “ለእስራኤል ልጆች የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ አለ” ሲል አውጇል::

ሕወሃት ከተመሠረተ ጀምሮ የትግራይን ሕዝብ ከእግዚአብሔርና ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሲያጋጨው መቆየቱን: እኛ አገር ወዳድ የትግራይ ተወላጆች በየአጋጣሚው ስናስጠነቅቅEthiopian flag (Alemayehu G. Mariam)መቆየታችን ይታወሳል:: እግዚሃብሔር ግን ዛሬ በሕዝብና በቤተክርስቲያን ላይ ችግር ሲፈጥሩ የነበሩትን እርሱ ወስዷል::ለቀሪዎቹ “ወደዚህ ቀርባችሁ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ” ይላል::ስለዚህ የሕወሃት መሪዎች ካለፈው ጥፋታችሁ ተምራችሁ ወድ ሕዝባችሁና ወደ አገራችሁ እንድትመለሱ አጥብቀን እናሳስባለን::
ከዚህ በፊት በተለያዩ ዌብሳይቶች ላይ አንዲት ገጽ ጽሁፍ አስነብበን ነበር::ዛሬም የሕወሃት አባላትና ደጋፊዎች ልብ እንዲገዙ እንመክራለን::ምክንያቱም ሕወሃቶች በእድሜአቸው ትልቅ ቢሆኑም ከአለፈው ጥፋታቸው ሊማሩ አልቻሉም::ይህን ጽሁፍ እንድናውጣ ያስገደደን ነገር ቢኖር ባለፈው አቶ ስብሃት ነጋ በተናገሩት ላይ ተንተርሰን ሲሆን እርሳቸው አሁንም ውጭ እንደሚመጡ ስላወቅን የሕወሃትን ደጋፊዎችና ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ለማስጠንቀቅ ነው::

ጥፋቱ የማን ነው?


“ባድመ የኛ አይደለም!” በረከት ስምዖን
bereket and badme


ኤርትራዊ ሆነው በኢትዮጵያ ከፍተኛ የስልጣን ሃላፊነት የተሸከሙት አቶ በረከት ስምዖን በኢትዮጵያ ላይ የሚፈርድ፣ ዜጎችን የሚያሸማቅቅ፣ ለአገራቸው የተሰውትን የሚያናንቅና በተለይም በውድ አገራቸው የሚመኩ ወገኖችን የሚያኮስስ ንግግር ማድረጋቸው በህወሃት ነባር ታጋዮች ዘንድ ቅሬታ ማስነሳቱ ታወቀ። አቶ ስዬ አብርሃ፣አቶ ገብሩ አስራት፣ እነ አቶ ተወልደን በስም በመጥራት በኤርትራ ጉዳይ ላይ ጥፋተኛ ያደረጉት አቶ በረከት “አንድነትና አንድ አገር” የሻዕቢያ መዝሙር መሆኑን በመናገር ኢትዮጵያ ውስጥ መገንጠል ለሚፈልጉ ጊዜው ሲደርስ እንደ ኤርትራ መገንጠል መብታቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ያስፈራል፤ ግን ኢትዮጵያ አትፈርስም!


(ፕሮፌስር መስፍን ወልደማርያም)
sendeq


ይቺ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ስንት የመከራ ወንዞችን ተሻግራለች! ገና ስንት ትሻገራለች! ስንት የግፍ ተራራዎችን አቋርጣለች! ገና ስንት ታቋርጣለች! ስንት የበደል ሰይፎችንና ጦሮችን አምክናለች! ገና ስንት ታመክናለች! ስንት የውጭ ኃይሎችን አሳፍራለች! ገና ስንቱን ታሳፍራለች! ስንት አምባገ- ነኖችን እያለቀሰች ቀብራለች! ገና ስንቱን ትቀብራለች! ጭቆና ከኢትዮጵያውያን ደም ሙልጭ ብሎ ወጥቶ በነፃነት፣ በእኩልነት፣ በዳኝነት በጠራ ደም እስቲተካ ድረስ “ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ” ትጸልያለች! እግዚአብሔርም ቃል ኪዳን አለበት ይሰማታል! የኃያላን ኃያል ኢትዮጵያ እንድትፈርስ አይፈቅድም!

እባካችሁ ይህንን “ኢትዮጵያዊነት” አክብሩት!!


(ርዕሰ አንቀጽ)

sendeq
ኢትዮጵያዊነት ከአጭበርባሪነት፣ ከሸፍጥ፣ ከሴራ፣ ከኩርፊያ፣ ከበቀል፣ ከተንኮል፣ ከደባ፣ ከድብቅ ዓላማ፣ ከአድማ፣ ከባንዳነት፣ ከአቃጣሪነት፣ ከከሃዲነት፣ ከተቀጣሪነት፣ ከማወናበድ፣ በተለይም ከማስመሰለና ከተራ የፖለቲካ ንግድ በላይ መሆኑንና ማንም ሊበርዘው ቢደክምም ሊሸረሽረው የማይችለው የልብ ማህተም መሆኑን ሰሞኑን አየን።

Monday, October 22, 2012

ወያኔ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን መጨፍጨፉን ቀጥሏል

ከዚህ በታች የቀረበው ጽሁፍ ሶሻል ሚዲያዎችን በመጠቀም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በማሰራጨት ላይ ያሉት ወቅታዊ ዘገባ ነው።

ሠላማዊ ትግላችን አሁንም አይቀለበስም!!
ትግላችን ወንድሞቻችንን በመግደል አይገታም!!!
Ethiopian muslim killed by government forces
በገርባ ከተገደሉ ወንድሞቻችን አስከሬን መካከል
በትናንትናው ዕለት በደቡብ ወሎ በደጋን እና ገርባ ከተማዎች የተፈፀመው ጥቃት ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው እና ለበርካታ ወራት ይዘን የዘለቅነው ፍፁም ሠላማዊውን የመብት ጥያቄ በምንም መልኩ ወደ ሌላ አቅጣጫ አይቀለብሰውም፡፡

ኃይለማርያም ከመድረሱ፤ የንፁሃንን ሕይወት መቀንጠሱ!


Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracyኃይለማርያም ደሣለኝ ምስለኔ ነው። ዋናው ባለሥልጣን ገና በውል አልታወቀም። ለሽያጭ ገበያ እንደወጣ ፈረስ ተስፈኛ ገዢዎች ኃይለማርያምን ለሙከራ እየጋለቡት ነው። በእርግጠኝነት የሚታወቀው ኃይለማርያም ደሣለኝ ምስለኔ እንጂ ዋናው ባለሥልጣን አለመሆኑ ብቻ ነው። እሱም ይህን ተቀብሎታል። የኃይለማርያም አዲስ ጌታ ነጥሮ ባለመውጣቱ ከቀድሞ ጌታው የተረከባቸውን ሹማምንት ይዞ ይቀጥል ወይም ጥቂት ለውጦችን ያድርግ ለጊዜው በውል የሚታወቅ ነገር የለም። ምን ያህል ሥልጣን በእጁ እንዳለም እንኳንስ ሌላው ሰው እሱም አያውቀውም። የመኖሪያ ቤትም ስላልተለቀቀለት ገና ወደ ቤተመንግሥት አልገባም።
እንዲህ ብዙ ነገሮች ገና ያልለየላቸው ቢሆንም ኃይለማርያም የቀድሞ ጌታው የመለስ ዚናዊን “ሌጋሲ” ለማስፈፀም ሲል ከአሁኑ ኢትዮጵያዊያንን መግደል ጀምሯል።

በገርባ የፌደራል ፖሊስ አባላት 2 ሰዎችን ረሸኑ፣ የሟቾች ቁጥር 4 ደርሷል


ኢሳት ዜና:-በገርባ የፌደራል ፖሊስ አባላት 2 ሰዎችን ረሸኑ፣ የሟቾች ቁጥር 4 ደርሷል :: የአካባቢው ነዋሪዎች ግን የማቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ይላሉበአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በገርባ ቀበሌ በትናንትናው እለት የወረዳው ፖሊስ አባላት ሆን ብለው በጫሩት ግጭት 4 ሰዎች ሲገደሉ 2ቱ በልዩ ሀይሎች ተወስደው መረሸናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የኢሳት ዘጋቢ የተለያዩ የአካባቢው ነዋሪዎችን አነጋግሮ ለማረጋገጥ እንደቻለው 2ቱ ሰዎች ማለትም ሼህ ሁሴን እና አቶ ሰይድ አብደላ የተባሉት ሰዎች በገርባና በባቲ መካካል በመትገኘዋ ዱሪ ከተማ ላይ ሁለቱም አንገታቸው አካባቢ በጥይት ተመትተው ተገድለዋል። ሁለቱ ግለሰቦች በፌደራል ፖሊስ አባላት ከተያዙ በሁዋላ በመኪና ተጭነው ወደ ባቲ መወሰዳቸውን፣ መንገድ ላይም እንደተረሸኑ፣ ፖሊሶችም የአካባቢውን ሰዎች ጠርተው ” ሁለቱ ሰዎች መንገድ ላይ ሞተውብናልና መጥታችሁ ውስዱ” በማለታቸው ህዝቡ ወደ ቦታው ሄዶ እንዳመጣቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ሁለቱ ግለሰቦች በተያዙበት ወቅት ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባቸው የአካባቢው ሰዎች አስረግጠው የተናገሩ ሲሆን፣ አስከሬናቸው መስጊድ ላይ ተወስዶ ሲታይ ሁለቱም ከአንገታቸው አካባቢ መመታታቸውን ህዝቡ ለማረጋጋጥ መቻሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

“የጥቁርም የነጭም ደም ቀይ ነው” የመለስ ድራማ!!


ኢህአዴግ ለመክሰስ ሲፈልግ ፊልም እንደሚደርስ ተረጋገጠ
swidish journalists in addis


የኦጋዴን ጉዳይ ሲነሳ ኢህአዴግ ይደነግጣል። ስለ ኦጋዴን አንዳችም ጉዳይ እንዲነሳበት አይፈልግም። የቢቢሲ የምርመራ ዘገባ በኦጋዴን ተፈጽሟል ያለውን ይፋ ሲያደርግ ኢህአዴግ በተለዩት መሪው፣ በህዝብ ግንኙነቱና እንግሊዝ አገር ባሉት አምባሳደሩ በኩል የማስተባበያ ዘመቻ ከፍቶ ነበር። በኬንያ ስደት ጣቢያ የሚገኙትን የክልሉ ነዋሪዎችን ያነጋገረው የቢቢሲው መርማሪ ጋዜጠኛ ሪፖርት ብቻ ሳይሆን ሂውማን ራይትስ ዎችም የከረረ መግለጫ አውጥቶ ነበር። ከአገር በቀል የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች መካከል የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄም በተመሳሳይ የኦጋዴንን አጀንዳ በማንሳት ጥሪ በማስተላለፍ ቅድሚያ እንደነበረው መረጃዎች ያመለክታሉ።

ሥራ አስፈጻሚ ወይስ ጉዳይ አስፈጻሚ?


በቁጥር 1 መቀመጫ የአቶ ሃይለማርያም የመጀመሪያው ውሎ


meles and hailemariam“ከአያያዝ ይቀደዳል ከአነጋገር ይፈረዳል” እንዲሉ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ፓርላማ ተራ ቁጥር አንድ መቀመጫ ላይ ተሰይመው ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎ አዲስ ክስተት ተስተውሏል። የቅናት፣ የተንኮል፣ የንቀት፣ ያለመታዘዝ፣ ተቃውሞን የማሳየት… ይሁን የሌላ እስካሁን በውል አልታወቀም። በመጀመሪያ ንግግራቸው መዛለፋቸውን ግን ብዙዎች ከእርሳቸው የጠበቁት ባለመሆኑ ተገርመውባቸዋል። በሌላ በኩል ግን ገና ከጅምሩ አክርረው የመጡት “ተለሳላሽ” ናቸው የሚባለውን ለመስበር እንደሆነም አስተያየት ተሰጥቷል።
የህወሃት፣ የብአዴን፣ የኦህዴድ፣ የደኢህዴን ሰዎችና ወ/ሮ አዜብ አቶ መለስ ንግግር ካላቸው ማታ እንኳን አያመሹም። ሲያንቀላፉ እንዳይታዩ በጊዜ ተኝተው ጠዋት ፓርላማ ናቸው። ሚኒስትሮችና ከፍተኛ ባለስልጣናት አንዳቸውም አይቀሩም። በሽተኛ እንኳን ቢሆኑ እንደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ወሳኝ ተጫዋች ደረቅ መርፌ ተወግተው መለስን ከማጀብ ወደኋላ አይሉም። ድርድራቸውን አሳምረው ይኮለኮላሉ። አቶ መለስን በሳቅና በማድነቅ አጅበው ይውላሉ።

ኬኒያን በድርበቡ! (አቤ ቶኪቻው)



ይህ ጨዋታ በአዲሳባዋ አዲስ ታይምስ (ፍትህ) መፅሔት ለንባብ የበቃ ሲሆን መፅሔቷን ለማግኘት ላልቻሉ ወዳጆች “በአዲሱ የትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችን” መሰረት “ወሬ ለሁሉም” እንዲዳረስ የተለጠፈ ነው። የኔታ “ለወሬ የለውም ፍሬ!” ይሉን ነበር። የኔታ ይቺን ብቻ ተሳሳቱ!
ወሬያችን ይቀጥላል!



አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን፦”በመኪና ሰው ገጭተህ ገድለሀል” ተብሎ ለእስር በተዳረገበት ጊዜ፦”ቴዲ ገድሏል፤ምሥክር ነኝ” በሚል ርዕስ አቅርቤው ከነበረው ረዘም ያለ ግጥም ውስጥ የተወሰነውን ክፍል ዛሬ ላስታውሳችሁ ፈለግኩ።እነሆ፦
ፍልሚያው ባህሪያዊ ነው – ስር የሰደደ ዘመቻ-
የፅልመትና የብርሀን- የፍቅርና የጥላቻ…….
…እናም ጎልያድ ሲመጣ- እየፎከረ በሰይፉ፦
የፍቅር ጠጠር ቢተፋ -የብላቴናው ወንጭፉ_
የክፋት ራስ ሰከረ-ወደቀ ከነመርገፉ፣
የጥላቻ አንገት ተቀላ- ምድያም ተረታ ሰልፉ፣
ቆነጃጅት ከበሮ አንሱ- በዕልልታ ምድርን ሙሉ፣
አንድ ሰው ብቻ አይደለም- ቴዲ ዕልፍ ገድሏል በሉ፣
ገዳይ ጨካኝ ነህ ተብሎ- ቴ’ድሮስ በከሳሽ ተከሷል፣
አዎ! ቴዎድሮስ ገዳይ ነው-የጥላቻን ግንብ ደርምሷል፣
አዎ! ቴዎድሮስ ጨካኝ ነው-እልፍ ክፉ ልብ አስለቅሷል፣
በቀዘቀዘ ጎጆ ላይ- የፍቅር እሳት ለኩሷል።

ትግላችን ወንድሞቻችንን በመግደል አይገታም!!!



በገርባ ከተገደሉ ወንድሞቻችን አስከሬን መካከል፡፡ በጉዳዩ ላይ የወጣነውን ዘገባና አቋም ከታች ይመልከቱ፡፡
ሠላማዊ ትግላችን አሁንም አይቀለበስም!!
ትግላችን ወንድሞቻችንን በመግደል አይገታም!!!
541271_284440988340479_2003171429_n(1)በትናንትናው ዕለት በደቡብ ወሎ በደጋን እና ገርባ ከተማዎች የተፈፀመው ጥቃት ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው እና ለበርካታ ወራት ይዘን የዘለቅነው ፍፁም ሠላማዊውን የመብት ጥያቄ በምንም
መልኩ ወደ ሌላ አቅጣጫ አይቀለብሰውም፡፡ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድነት ስሜት ህገ መንግስትዊ ስርዓቱን ባከበረ መልኩ ያነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ያገኙ ዘንድ ለተቃውሞ አደባባይ ላይ በዋለባቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ሂደቱ መልኩን ቀይሮ ኹከትን እንዲላበስ ብሎም ወደ ብጥብጥ እንዲያመራ ተከታታይ ሙከራዎች ተደርገውበት አልፏል፡፡ በእነዚህ ሙ
ከራዎቻቸው ዛቻ፣ ድብደባ፣ እስራት እና የህይወት መስዋዕትነትን ከፍለናል፡፡

 ይህ ሁሉ እየሆነ እያለ ያለ ምንም የአቋም መዋዠቅ ትገሉ ሠላማዊነቱን ጠብቆ እንዲዘልቅ ሙስሊሙ ኡማ ያላሰለሰ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ በመስከረም 27 ምርጫ እንኳን እነሱ ያለ ከልካይ በሕገ ወጥ ድርጊታቸው እንዳሻቸው ሲፈነጥዙ ሙስሊሙ ፍፁም ሠላማዊነቱን አስመስክሯል፡፡ በደቡብ ወሎ ደጋን እና ገርባ አካባቢዎች በትናንትናው ዕለት የተስተዋለውም የመንግስት ጸብ አጫሪነት የዚሁ የትንኮሳ እና ጸረ ሕዝብነት አንዱ ማሳያ ነው፡፡ክስተቱ የመላ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን ሰላማዊ የመብት ማስከበር ትግል አቅጣጫ በማስቀየር ወደ ብጥብጥ እና ኹከት በመለወጥ ብሎም ሙስሊሞች በዚህ ሂደት ተደናግጠው ከመታሰር፣ ከመደብደብ ብሎም ከመሞት አርፎ መቀመጥን እንዲመርጡ ከያዙትም አቋም እንዲያፈገፍጉ የታለመ መሆኑን በእርግጠኝነት መናገር እንችላለን፡፡

Saturday, October 20, 2012

አቤ ቶኪቻው! - ፀረ ኢትዮጵያ?


የቅዳሜ ማስታወሻ




ሰሞኑን “አይጋ” የተባለ የወያኔ ድረገፅ ግብረአበሮች ያላቸውን ሶስት ጋዜጠኞች በተከታታይ ፅሁፍ ሲደበድብ ሰንብቶአል። እነዚህ ሶስቱ ጣምራ ጠላቶች፣ አቤ ቶክቻው፣ ተመስገን ደሳለኝ እና እኔ ነበርን። ፀሃፊው እንቅልፍ በተጫጫናቸውና ውሃ በጠማቸው ቃላት ረጅም ሃተታ ፅፎአል። የአቤ፣ የተመስገን እና የኔ ስሞች ያለበትን እየመረጥኩ እየዘለልኩ ነው ያነበብኩት። ምክር ነክ ሃተታዎችን ዘለልኳቸው።

ከሶስቱ ተከታታይ ፅሁፍ ቀልቤን የሳበችው፣ አቤ ቶኪቻውን  ፀረ -ኢትዮጵያ ብለው መፈረጃቸው ነው። እኔን ቢሉኝ ያምርባቸዋል።

ለካስ ኢህአዴግ ፈሪ ናት!


Abe Tokchaw
ሽመክት ውድነህ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቴኳንዶ ክለብ ምክትል አሰልጣኝ ነበር። በቴኳንዶ “ሶስተኛ ዳን” በሚባል ደረጃ ኢንተርናሽናል ቀበቶ አግኝቷል። በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2009 ዴንማርክ የቴኳንዶ ስፖርት ክለቡን ይዞ ሄዶ ተስፋ ሰጪ የሚባል ውጤት ይዞ ተመለሶ ነበር። (ይቺ ተስፋ ሰጪ… ከስፖርት ጋዜጠኞቻችን ኮርጄ ነው። ብቻ ከተስፋ አስቆራጭ ተቃራኒ የሆነ ውጤት ማለት ናት!)
በአዲስ አበባ ከተማ ወደ አስራ አምስት ሺህ የሚጠጉ ወጣት ልጆችን በቴኳንዶ ማሰልጠኑን አውግቶኛል። ሽመክት ከአምና በፊት የነበረው አምና (ካቻምና ማለት ነው)  ግንቦት ሃያ ሊቃረብ አካባቢ ግን አንድ ፈታኝ ነገር ገጠመው።
በግል ክለቡ ቴኳንዶ የሚያሰለጥናቸውን ተማሪዎች ጠርጣራው መንግስት “ግማሹን በኦነግነት ግማሹን በግንቦት ሰባትንነት እጠረጥራቸዋለሁ” አለው። በዚህም የተነሳ የደህንነት ሰዎች ነን የሚሉ ሰዎች “የምታሰለጥናቸው ለግንቦት 20 ላሰባችሁት አመፅ እና ብጥብጥ ነው” ብለው ስለጥናውን እንዲያቆም አስጠነቀቁት።

መሳቂያው ፓርላማ!


እንደሚታወቀው የፓርላማ አባላቱ የምክር ቤት ስብሰባ ለማድረግ ሲሄዱ ወረፋ አይጠብቁ እንጂ የሆነ ኮሜዲ ፊልም ለመታደም ሲኒማ ቤት እንደሚገቡ አድርገው እንደሚያስቡት የታወቀ ነው። ይሄ ካልታወቀ ትልቅ የመረጃ ክፍተት አለ ማለት ነው!

“የጥቁርም የነጭም ደም ቀይ ነው” የመለስ ድራማ!!


ኢህአዴግ ለመክሰስ ሲፈልግ ፊልም እንደሚደርስ ተረጋገጠ
swidish journalists in addis

ኢትዮጵያ “የአፍሪካ ኢኮኖሚ ፓወር ሃውስ” ሆናለች የሚለውን ቀልድ እናንታም እንደኔ ሰምታችሁ ይሆን?


ከዶ/ ር ዘላለም ተክሉ
10/18/ 2012
በቅርቡ የቻይና ቲቪ ኒውስ1(China CCTV News) ኢትዮጵያን “የአፍሪካ ኢኮኖሚ ፓወር ሀውስ” ሆናለች ብሎ ሲያሞካሽ “ሊበሉዋት ያሰቧትን ጅግራ ቆቅ ነሽ ብለው ይሏታል” ዓይነት ፉገራ መስሎኝ ችላ ብዬ ተቀምጬ ነበር:: ነገር ግን “የመለስን ራዕይና ተክለ ሰውነት ወራሹ” አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ሰሞኑን ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር ተመሳሳይ ፉከራ ማድረጋቸውን ስሰማ በዝምታ የሚታለፍ ጉዳይ እንዳልሆነ ተረዳሁኝ:: በሳቸው አባባል ኢትዮጵያ በቴሌኮምና በኢንተርኔት ዝርጋታ ዘርፍ ባለፈው አመት ባደረገችው ልማት ከደቡብ አፍሪካና ግብጽ ቀጥሎ በሶስተኝነት ደረጃ እንድትሰለፍ ማድረጋቸውን አረጋግጠውልናል2::

መሬት ዘረፋ ኢትዮጵያዊያኖችን በ‹‹ዓለም የረሃብ ቀን›› ወቅት ለችጋር እያጋለጠ ነው፡፡


ልጁ በታችኛው ኦሞ ወንዝ ጠርዝ ላይ
በኢትዮጵያ በታችኛው ኦሞ ሸለቆ በውጭ አገር ባለሃብቶች የሚካሄደው የመሬት ዘረፋና ሽሚያ ተወላጆቹን እያፈናቀለ እና መሬታቸውን እንዳያርሱ እንቅፋት እየሆነ በርካታዎችንምSuvival International PR Release Translationበችጋር እያመሰ ‹‹ሞታቸውን እንዲጠብቁ›› እያደረገ ነው፡፡
በኦክቶበር 16 የ “ዓለም የምግብ ቀን”ን  በማክበርና ከድህነት በስተጀርባ ያለውን ችጋር በሕዝብ ሕሊና ውስጥ ለማስረጽ ደፋ ቀና በሚባልበት ወቅት፤ኢትዮጵያን በሚገዙት ኢሰብአዊዎች፤ 200 000 በራሳቸው የሚተማመኑትን ዜጎች የምግብ ዋስትና ለማሳጣት ደንቃራ እየሆኑ ነው፡፡

Friday, October 19, 2012

‹‹ለእኔ አንዱዓለምና (አንዱዓለም አራጌ የተባሉ የፓርቲያቸው አባል) ጓደኞቹ አሸባሪ ሳይሆኑ ለዚች አገር ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የሚደክሙ የነፃነት አርበኞች ናቸው፤›› ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ (መድረክ) ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ‹‹እነዚህ ለእኛ አርበኞች ሳይሆኑ አተራማሾች ናቸው›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም


የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የዘንድሮ ዓመት የሥራ ዘመንን ለመጀመር መስከረም 28 ቀን 2005 ዓ.ም. ባደረጉት የጋራ ስብሰባ ላይ የአገሪቱ

ሲሆን፣ በዚሁ ንግግራቸው መንግሥት ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት በበጀት ዓመቱ ሊያከውናቸው ይገባቸዋል ያሏቸውን ጉዳዮችም አብራርተው ነበር፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሠራር ደንብ መሠረት የምክር ቤቱ አባላት ፕሬዚዳንቱ በቀረቧቸው ሐሳቦችና ቅድሚያ ትኩረት ሊያገኙ ይገባቸዋል ባሏቸው ነጥቦች ላይ የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ አስተያየት እንዲሰጡ ይፈቅዳል፡፡ በሥነ ሥርዓት ደንቡ መሠረት የፕሬዚዳንቱ ንግግር ላይ ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል የተባሉት ነጥቦች ላይ ለሚቀርብ ተቃውሞ፣ እንዲሁም ትኩረት ሊያገኙና ሊካተቱ ይገባቸዋል በሚል ለሚቀርቡ ሐሳቦች የአገሪቱ ጠቅላይ ማኒስትር አስተያየትን ካዳመጠ በኋላ የፕሬዚዳንቱ ንግግር ተሻሽሎ አልያም ባለበት ሁኔታ እንዲፀድቅ ይደረጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በፕሬዚዳንት ግርማ ንግግር ላይ ከስድስት የምክር ቤቱ አባላት አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ አምስቱ አስተያየቶች የቀረቡት በኢሕአዴግ አባላት ሲሆን የማብራሪያ እንጂ ምንም ዓይነት የማሻሻያ ጥያቄ የላቸውም፡፡
ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ (መድረክ) ተወካይ በሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ የቀረቡት ሐሳቦች ግን ሁለት ዓይነት ይዘት አላቸው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ያነሷቸው ነጥቦች በፕሬዚዳንቱ ንግግር ውስጥ ሊካተቱ አይገባም ያሏቸውን ሲሆን፣ በመቀጠል ደግሞ በፕሬዚዳንቱ ንግግር ውስጥ ሊካተቱና መንግሥትም ትኩረት ሊያደርግባቸው ይገባል ያሏቸውን ነበር፡፡
ፖለቲካዊ ይዘት ካላቸውና በፕሬዚዳንቱ ንግግር ውስጥ ሊካተቱ ይገባል በሚል የጠቀሷቸው ነጥቦች የአንድ ፓርቲ የበላይነት በአገሪቱ መስፈን፣ የፖለቲካ ምኅዳሩ መጥበብ እንዲሁም ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሕዝባዊ ምርጫ እንዲሳተፉ በሕግ የተፈቀዱ ሥርዓቶች መከበር ይገባቸዋል የሚል ይዘት ያላቸው ናቸው፡፡

ቱጃሯ ሱራና ኦህዴድ


ከጫት ንግድ በስተጀርባ ያለው ቁማር!!
khatlines and sura

ኦብነግና ኢህአዴግ ንግግር አቆሙ!


ህዝበ ውሳኔ በብቸኛ አማራጭነት ቀረበ!
onlf eprdf

የጌታቸው እና የደብረፅዮን ቢሮ (ከተስፋዬ ገብረአብ)


ከተስፋዬ ገብረአብ
ስለ ጌታቸው አሰፋ ወይም ደብረፅዮን ምንም ልፅፍ አልችልም። ጌታቸውን በቅርብ አላውቀውም። የአማረ አረጋዊ የቅርብ ጓደኛ ስለነበር፣ አንድ ሁለት ጊዜ በአጋጣሚ ቡና ጠጥተናል። ጌታቸው አሰፋ ነባር የህወሃት አመራር አባል ሲሆን፣ በአቅም ደረጃ ሲመዘን ከላይኛው የህወሃት አመራር አባል አንዱ መሆኑ የሚታወቅ ነው።
ደብረፅዮንን በቅርብ አውቀው ነበር። ደርግ ከመውደቁ በፊት በሃገረሰላም የህወሃት ሬድዮ ጣቢያ በአንድ አካባቢ ነበርን። ሆኖም ደብረፅዮን ሰሞኑን እንደሚፃፍበት፣ ተራ የሬዲዮ ኦፕሬተር አልነበረም። የሬድዮ ስርጭቱ የቴክኒክ ሃላፊ ነበር። ደርግ ከወደቀ በሁዋላ ወዲያውኑ የተቋረጠ የዩንቬርሲቲ ትምህርቱን እንደቀጠለ አስታውሳለሁ። ከደብረፅዮን አንድ የሜዲያ ኮሚቴ ውስጥ አብረን ሰርተን ነበር። ብሩህ አእምሮ የነበረው፣ ባተሌ አይነት ሰው ነበር። ደብረፅዮንን የህወሃት ምክትል እና የፀጥታው መስሪያ ቤት ሁለተኛ ሰው አድርገው ማምጣታቸው በአጋጣሚ አይመስለኝም። ተጠንቅቀው አስበውበት ያደረጉት ነው። ደብረፅዮን በግማሽ ጎኑ ኤርትራዊ ስለመሆኑ ሰምቻለሁ፣ በጋብቻ ከስብሃት ነጋ ጋርም እንደሚዛመድ የተፃፈ አንብቤያለሁ። ርግጠኛ መረጃ ስለመሆኑ ግን አላውቅም።

እኛ “ነጋሲ” ስንልዎ እርስዎ “ሌጋሲ” እያሉ… እየተያየን ተለያየን!?


አቤ ቶኪቻው

ትላንት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ (በቅንፍም ቢያንስ ሌላ ጠቅላይ ሚኒስትር በመጥራቴ እኔም ደሳለኝ…!) በፓርላማ ጥያቄዎችን ለመመለስ ለመጀመሪያ ግዜ ቀርበው ነበር።  በዚህ የመጀመሪያው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርላማ ላይ በርካታ ዋና ዋና የሟቹ ወዳጆች አልተገኙም ነበር አሉ። ወሮ አዜብም ካልተገኙት ውስጥ ናቸው። ወሮዋ ድሮ በሟቹ ጊዜ ስብሰባ ሲቀሩ ከፓርላማው ስብሰባ መልስ ለቀጣዩ መጂሊስ ስብሰባ ቤቱን ሞቅ ሞቅ አድርገው ሊጠብቋቸው ነው የቀሩት ብለን እናስብ ነበር። አሁን ደግሞ ምን ሆነው ቀሩ…? ብለን ስንጠይቅ “ላልተወሰነ ጊዜ ቤተመንግስቱን አምነው ርቀው አይሄዱም አሉ!” የሚል ሽሙጥ እናገኛለን።እኛ “ነጋሲ” ስንልዎ እርስዎ “ሌጋሲ” እያሉ… እየተያየን ተለያየን!?
የሆነው ሆኖ ግን አቶ ሃይለማሪያም በትላንቱ ፓርላማ መለስን ሆነው ሲተውኑ ነው የተመለከትናቸው። እንደውም አንድ ወዳጄ ሲናገር እንደሰማሁት አፈ ጉባኤው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲያስተዋውቁ “ቀጥሎ እንደ መለስ ዜናዊ ሆነው እንዲተውኑልን አቶ አርቲስት ሃይለማሪያም ደሳለኝን እጋብዛለሁ!” ማለት ነበረባቸው ብሎኛል።፡
የምር ግን ሰውዬው መለስን ለመምሰል በሚያድርጉት ጥረት ራሳቸውንም መለስንም ሳይሆኑ መቅረታቸው ነው ያሳዘነኝ።

ኢትዮጵያ፡- ከረጂም ርቀት ሯጮቻችን የምንማረው


ከፕሮፌሰር  ዓለማየሁ  ገብረማርያም
ትርጉም  ከነጻነት ለሃገሬ
ኢትዮጵያ በመልካም ስሟም፤በአስከፊ ገጽታዋም ትታወቃለች:: ኢትዮጵያ በመልካም እንግዳ ተቀባይነቷና አስተናጋጅነቷ፤በሕዝቦቿ መልካም ባሕሪ፤ በመልክአ ምድሯ ውበት፤እናEthiopian Long Distance Runnersበግሩሙ ቡናዋና በማይደፈሩት ጅጋኖች ረጂም ርቀት ሯጮቿ ትታወቃለች፡፡ ተወዳዳሪ በሌለው የሰብአዊ መብት ጥሰት፤የፕሬስ ማፈኛ ተቋሟም፤በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፖለቲካ እስረኞች የሚገኙባት ሃገርም ሆና ኢትዮጵያ ትታወቃለች፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ችጋር (ኤክስፐርቶቹ እንደሚሉት፤ “ሥር የሰደደ የማይነቀል የምግብ እጥረት”) ከውቢቷ ኢትዮጵያ ጋር ከተሳሰረ ዘመናት አልፈዋል፡፡ የሆነው ሆኖ አትዮጵያ ከጭቆና የፈላጭ ቆራጭ አስተዳደር ወደ ዴሞክራሲ ጉዞዋን ጀምረለች፤ ወይስ ኢትዮጵያዊያኖች ከአምባገነኖች አገዛዝ ወደ ነጻነት እየሮጡ ነው ብል ይሻላል?

ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች፡ “የኢትዮጵያ ፍርድ ሂደት ቀልድ ነበር” አሉ


ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ በእስር ላይ ቆይተው የተለቀቁት የስዊዲን ጋዜጠኞች የታሰሩበት እስር ቤት በእስረኛ ብዛት ከ200 በመቶ በላይ የተጨናነቀና በሽታ የበዛበት መሆኑን ጋዜጠኞቹ አስታወቁ::
በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች የታሰሩበት እስር ቤት ከ200 በመቶ በላይ መያዝ ከሚችለው በላይ የተጨናነቀና ፍጽም ቆሻሳ መሆኑ ተገለጸ::
በእስር ቤቶቹ አይጦችና ዝንቦች ለታሳሪዎች መከራ መሆናቸውንም ቢቢሲ ጋዜጠኞቹን ጠቅሶ ዘግቧል::
በኢትዮጵያ እስር ቤቶች 400 ቀናት አሳልፈው የተፈቱትን ስዊዲናዊ ጋዜጠኞችን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ እንደዘገበው ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች የታሰሩባቸው እስር ቤቶች፤ ውሀ የሌለባቸው፣ በከፍተኛ ወበቅ የነደዱና ተባይ የበዛባቸው በመሆናቸው፤ ብዙ ሰዎች ይታመማሉ የሳምባ ነቀርሳም ሌላው ችግር ነው ብለዋል::

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬም በአንዋርና በበኒ መስጊዶች ተቃውሞአቸውን አሰሙ


ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ በኢህአዴግ መንግሥት ደረሰብን ላሉት የሕገ-መንግሥትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዛሬ ከጁምዓ የጸሎት ፕሮግራም በኋላ ፒያሳ በሚገኘው የበኒ መስኪድ እና መርካቶ በሚገኘው አንዋር መስኪድ ተቃውሟቸውን ገለጹ፡፡
በከፍተኛ ቁጥር ፒያሳ በሚገኘው በኒ መስኪድ እና መርካቶ በሚገኘው አንዋር መስኪድ የተሰባሰበው የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ከጸሎተ ሥግደት በኋላ ለ30 ደቂቃ ያህል እጅ ለእጅ በመያያዝ አንድነታቸውን ያሳዩ ሲሆን፣ እጃቸውንም በመቆላለፍ የኢህአዴግ መንግሥት አፍኖናል- አስሮናል ያሉ ሲሆን እጃቸውን ያለ ድምጽ በማውለብለብ መንግሥት በሃይማኖታችን ጣልቃ እየገባ ካድሬዎቹን መሾሙን እና የአህባሽን አስተምህሮ ካልተቀበላችሁም የሚለውን የግፍ አካሄዱን እስካላቆመ ትግላችን ይቀጥላል ሲሉ በአካላዊ እንቅስቃሴ ተቃውሟቸውን መግለፃቸውን የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ተወካዮች ለዘጋቢያችን ገልጸዋል፡፡

Tuesday, October 16, 2012

አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች መልስ ሰጡ


ኢሳት ዜና:-ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተመራጩ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ከአቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ አዲስ ነገር አለመጠበቃቸውን ሲናገሩ፣ እውቁ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ደግሞ፣ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር “ከእነስታይላቸው ” አቶ መለስን መስለዋል ብለዋል።
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከፓርላማ አባላቱ ለተነሱት በርካታ ጥያቄዎች መልሶችን የሰጡት፣ የቀድሞው ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር  ፎቶ ግራፍ ፊት ለፊታቸው ተሰቅሎ በሚታይበት ሁኔታ ነው።
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በመልሶቻቸው ሁሉ ላይ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒሰትር ይህን ብለው ነበር በማለት ደጋግመው ሲናገሩ ተስምቷል።
አቶ ሀይለማርያም ዲሞክራሲያዊ ስርአት በኢትዮጵያ በመገንባቱ ለህዝብ ተጠያቂ የሚሆን ስርአት መፈጠሩን በአንድ በኩል ሲገልጹ፣ ዲሞክራሲ እየጎለበተ የሚሄድ ባህል መሆኑን፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ተበጥብጦ የሚጠጣ አለመሆኑን በመጥቀስ ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ ተገንብቷል በማለት የተናገሩትን ንግግር ማፍረሳቸውን ውይይቱን የተከታተለው ዘጋቢያችን ገልጧል።

ለግርድና የሚሄዱት እህቶቻችንን ልንደርስ የምንችልባቸው 4 መንገዶች – ገለታው ዘለቀ


በኣረብ ኣገራት ለግርድና የሚሄዱትን እህቶቻችንን የሚደርስባቸውን ስቃይ መናገር መነሻዬ ኣይደለም። ያልፍልኛል፣ እናት ኣባቴን እጦራለሁ እያሉ ወደ ሊባኖስና ሌሎች የኣረብAlem Dechasa’s only crime is coming to Lebanon to make some money for her poor family back in Ethiopia. ገልፍ ኣገራት የሚጎርፉት እህቶቻችን ከሰባዊነት ደረጃ ዝቅ ብለው ሲሰቃዩ ሌላው በተለያየ የኣለም ክፍል ያለው ኢትዮጵያዊ ከንፈሩን ከመምጠጥ ያለፈ ብዙ ነገር ሲያደርግ ኣይታይም። እግዚኣብሄር ይባርካቸውና የተለያዩ ሰባዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የቻሉትን ሁሉ እየታገሉ ነው። ግን ኢትዮጵያዊው የበኩሉን ለመወጣት ከማንም በላይ የሞራልም የዜግነትም የውዴታ ግዴታ ኣለበት።
የዛሬው ጽሁፌ በሌላው ኣለም ያለው ኢትዮጵያዊ ምን ሊያደርግ ይችላል? በሚል ተግባራዊ ዘዴዎችን ለመጠቆም ነው።
በመሆኑም ለእህቶቻችን በሚከተሉት መስመሮች ልንደርስላቸው እንችላላን።

ዜና በጨዋታ፤ የኢቲቪው ጋዜጠኛ “ፕሮፖጋንዳ በቃኝ” ብሎ “ነካው!”


Abe Tokchaw
ሰለሞን መንግስት ይባላል። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ውስጥ የእንግሊዘኛው ክፍል ባልደረባ ነው። ዛሬ በፌስ ቡክ ግድድዳው ላይ “I have said “enough is enough“ and decided to never be back in that dirty propaganda factory called ERTA.”  የሚል ለጥፎ አስነብቦናል።
መቼም ሰው ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን “በቃኝ ብያለሁ በቃኝ” ብሎ ቢማረር ምን ሆኖ ነው? ተብሎ አይጠየቅም። ምክንያቱም ቤቱ ኢቲቪ ነው!
ይልቅስ በኢቲቪ አሁን ድረስ እየሰሩ ያሉ ወዳጆቻችን ምን ሆነው ነው የማይለቁት? ኢቲቪው ላይ ምነው ወይዘሮ አዜብ ሆኑበት? የሚለው ጥያቄ መልሱ ግር ይላል።
በነገራችን ላይ አንድ ወደጄ ነው ይቺን አዲስ ፈሊጥ የነገረኝ። አንድ ሰው የሆነ ቦታ ገብቶ አልወጣ ካለ “ምነው አዜብ መስፍንን ሆንክ!?” እያሉ መጠየቅ በከተማው ተለምዷል አሉ። ይሄ ያነጋገር ፈሊጥ መፀዳጃ ቤት ገብቶ አልወጣ ላለ ሰው፣ ከመኝታው አልነሳ ላለ እንቅልፋም ሁሉ አገልግሎት ላይ ይውላል።