Translate

Thursday, October 11, 2012

ዜና በጨዋታ፤ ኢሳት ከለንደን ኢትዮጵያውያን ለአንድ ሚሊዮን ብር ሩብ ጉዳይ ብር አገኘ አሉ!


Abe Tokchaw
እንደምን አደራችሁ ያልነገርኳችሁን ዜና አቀርባለሁ። ለዝርዝሩ ከስር እንገናኝ፤
የሆኑ ኢትዮጵያውያን፤ “ህዝቡ ነፃ እና ገለልተኛ የዜና ምንጭ ይኑረው ይኑረው” ብለው ተመካከሩና መሰረቱት። መሰረቱት እና ለህዝቡ ሰጡት። ህዝቡም መረጃዎቹ አንጀት ላይ ጠብ የሚሉ መሆናቸውን ሲመለከት ጊዜ ዳዴ ሲል የነበረውን መገናኛ ብዙሃን በአንድ እግሩ እንዲቆም እገዛ ማድረግ ጀመረ። የማወራው ስለ ኢሳት ራዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት ነው።
የኢህአዴግ መንግስት ኢሳት ቴሌቪዥን ወደ ኢትዮጵያ የሙከራ ስርጭት ሲያደርግ ምንም አላለውም። በዚህ ጊዜም በርካታ ኢትዮጵያውያን ዲሽ ለመግዛት ሲሯሯጡ እኔም አስታውሳለሁ። ወድያውም የዲሽ ዋጋ እንዳሻቀበ እርስዎም ትዝ ይልዎታል።

ቴሌቪዥን ጣቢያው አንድ እና ሁለት ፕሮግራሞችን ሲያስተላልፍ ግን መንግስት “ኢሳት”ን የእሳት ያህል ፈራው። ከዛም በእጅም በእግርም በፋራም በአራዳም “እፍፍ…” ብሎ ለብዙ ጊዜ ከኢትዮጵያውያን ቴሌቪዥን ላይ አጠፋው።
በመንግስት ግዝገዛ እና በህዝብ እገዛ መካከል የሚገኘው ኢሳት አሁን ግን እንደምንም ብሎ ድጋሚ ወደ ኢትዮጵያ አየር ተመልሷል።
በተለይ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ዜና ሞት ቀድሞ ከተናገረ በኋላ በህዝብ ዘንድ ታላቅ አመኔታ እየተጣለበት የመጣው ኢሳት በተለያዩ ሀገሮች የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞችን እያደረገ ይገኛል። በዚህም መሰረት ባለፈው ሳምንት ውስጥ በለንደን ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለአንድ ሚሊዮን ሩብ ጉዳይ የሆነ ብር ገቢ አግኝቷል።
በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከአረብ ሳት ተባሯል አሉ። ለመባረሩ ምክንያት የኢቲቪ ባለቤት የሆኑት እነ አቶ በረከት ኢሳትን ለማጥፋት በሚያደርጉት ጥረት በርካታ ቴሌቪዥኖችን ከአረብ ሳት ላይ እያጠፋ እና እያወኩ በማስቸገራቸው  እንደሆነ ተሰምቷል።
አረ እንደውም የአረብ ሳት ባለስልጣኖች አሉ እንደተባለው  ከሆነማ “ከዚህ በኋላ ከኢትዮጵያ ጋር የተገናኘ ማንኛውንም ቴሌቪዥን አናስተናግድም” ብለው ራሱ ኢቲቪን፤ ኦሮሚያ ቲቪ እንኳን ሌላ ቀርቶ ኢቢኤስ የተባለውን የግለሰቦች ቴሌቪዥን ሁሉ አስወግዷል አሉ።
ታድያልዎ አሁን በቅርቡ ኢቲቪን በኢንተርኔት ለማየት ጎራ ብዬ ነበር። ከአረብ ሳት ተባረሩ የተባሉትን ኢቢኤስ፣ ኦሮሚያ ቲቪ እና ኢቲቪ በአንድ ላይ ቁጭ ብለው አገኘኋቸው። አንጀቴንም በሉኝ።
ለማንኛውም ኢሳት ቴሌቪዥን አሁን ያለ ሀሳብ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ ነው። …ረስቼው አቶ በረከት ስሞን አንድ ሰሞን “ኢሳት ከሚገባ ቢላ በአንገቴ ይግባ” ብለው ነበር!. የአቶ በረከት ቤተሰቦች የሆናችሁ ቢላ ከአካባቢያቸው አርቁ…! እንበል ይሆን!?

No comments:

Post a Comment