Translate

Sunday, March 31, 2013

የህወአት ታላላቅ የታሪክ ክህደቶች ከ“ፍኖተ ገድል” (ገብረመድህን አርአያ )


ለአነባበብ ይረዳ ዘንድ ጽሁፌን ከመጽሃፉ እያጣቀስኩ ለመልሱ ከራሴ እና አስረጅ ይሆናሉ ካልኳቸው ዋቢ ማስረጃዎች ጋር አድርጌ የራሴን እነሆ እላለሁኝ።
የታሪክ ክህደት ቁጥር 1:
ይህ ጉዳይ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ የትግሪኛ ፕሮግራም ላይ አረጋዊ በርሄ እና ስብሃት ነጋ ቀርበው የተወያዩበት/የተከራከሩበት እና እና ስለ መጽሃፉ በተለይ እኛ ከአገር ውጪ ያለን ኢትዮጵያውያን ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማንበት ጭብጥ ነው -የአክሱም ስልጣኔ ጉዳይ።
ከመጽሃፉ እጠቅሳለሁ:-
<< በርካታ ተመራማሪዎችና ጸሃፊዎች “አክሱም አሁን በሰሜን ኢትዮጵያ የአማራ ነዋሪዎች ወዳሉበት ደቡባዊ ክፍል ስለመስፋፋቷ የጽሁፍ ማስረጃዎች የሉም። እንደኢትዮጵያ(አማራ) አባባል ሳይሆን የአክሱም ታሪክ ከሁሉ በላይ የደቡብ ኤርትራና የሰሜን ትግራይ ታሪክ ስለ መሆኑን(sic) ማስረጃዎች ያሳያሉ። ከዚህ በተጨማሪ አማራ የአክሱም አፄአዊ ግዛት አካል የነበረ ስለመሆኑ ምንም አይነት ታሪካዊ ጥቁምታ የለም:

ኢህአዴግ የሠላማዊ ሰልፍ መብታችንን ማረሳሳቱ ነው እንዴ?

ኢህአዴግ የሠላማዊ ሰልፍ መብታችንን ማረሳሳቱ ነው እንዴ? 

eprdf 9th meeting 

እኔ የምላችሁ…ኢህአዴግ 9ኛውን የፓርቲውን ጉባኤ ያካሄደበትን እጅግ የተንቆጠቆጠ “ባለ 7 ኮከብ” (ኮከብ የመስጠት ኮፒራይቱ የራሴ ነው!)
የስብሰባ አዳራሽ አይታችሁልኛል? (በኢቴቪ ማለቴ ነው!) በአካልማ ማን አስደርሷችሁ! (አዳራሹ ከ2ሺ ሰው በላይ አይችልማ!) ለነገሩ አዳራሹም ቢበቃ ሌላም የመግቢያ መስፈርት እንደነበረው ሰምቻለሁ።

Prisoners of conscience in Ethiopia: By Birtukan Mideksa


Al Jazeera

Birtukan Mideksa is a fellow at Harvard University’s WEB Du Bois Institute for African and African American Research and a former prisoner of conscience in Ethiopia.
Birtukan Mideksa a prisoner of conscience now a Reagan-Fascell Democracy Fellow
Birtukan Mideksa
Although Ethiopia has its first new prime minister in 17 years – so far, the government has failed to right a long history of wrongs. With prisoners of conscience still languishing in its prisons, Ethiopia must receive the clear message – especially from allies like the United States – that continued human rights violations will not be tolerated.
My journey to become a political prisoner in Ethiopia began as a federal judge fighting to uphold the rule of law. Despite institutional challenges and even death threats, I hoped to use constitutional principles to ensure respect for basic rights.

Saturday, March 30, 2013

ሃይማኖት፣ ፖለቲካና ህብረተሰብ!


(ፈቃዱ በቀለ)

politics and religion
የዐለማችን ሁኔታ በጣም እየተወሳሰበ መጥቷል። በየአገሮች ውስጥ የማህበራዊና የፖለቲካ ጥያቄዎች ሳይፈቱ የሃይማኖት ጥያቄ ራሱን የቻለ አጀንዳ ሆኖ በመምጣት ብዙ አገሮችን እያተራመሰ ነው። በተለይም የሶስተኛው ዓለም ተብለው በሚጠሩ አገሮች ውስጥ ያለው የፖለቲካ አወቃቀር ምሁራዊ ብስለት ስለሚጎድለው፣ አፍጠው አግጠው የሚመጡ እንደ ሃይማኖት የመሳሰሉ ጥያቄዎችን በውውይትና በክርክር ከመፍታት ይልቅ ግብግቡ ወደ አመጽ በማምራት አክራሪዎች በሚባሉትና በመንግስታት መሀከል የሚደረግ ዐይነት ፍጥጫ እየሆነ በመምጣት ላይ ነው። መንግስታት ወደ ዕምነት ያመራውን የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍል በጭፍኑ በአክራሪነት በመወንጀል በተለኮሰው እሳት ላይ ቤንዚን እየነሰነሱበት ነው። (ሙሉው ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል)

የመንግስት ባለስልጣናት እያስፈራሩዋቸው መሆኑን በፍኖተሰላም ከተማ ሜዳ ላይ ወድቀው የሚገኙት ተፈናቃዮች ተናገሩ


መጋቢት ፳  (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

Ethiopian Satellite Television (ESAT)ኢሳት ዜና:-ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ሜዳ ላይ ወድቀው የሚገኙት አማራ ተወላጅ አርሶደአሮች ከክልሉ ዋና ከተማ እና ከዞኑ የተውጣጡ ባለስልጣናት ዛሬ ሰብስበው ያነጋገሩን ቢሆንም ፣ ተስፋ የሚያስቆርጥ መልስ ሰጥተውናል በማለት ለኢሳት ተናግረዋል።
አርሶአደሮቹ እንደሚሉት ባለስልጣናቱ ከተማውን ለቀው ወደ ወረዳቸው እንዲሄዱ፣ የተቀሙትን ሀብትና ንብረት በተመለከተ ጥያቄ ሲያቀርቡም ” ቀድሞ ማን ሂዱ አላችሁ አናውቅም” ብለው እንደመለሱላቸው ተናግረዋል።
ያለምንም መጠለያ 2 ሺ አባወራ ሜዳ ላይ ተጥሎ እንደሚገኝ የተናገሩት ተፈናቃዮች፣ ከንጽህና ጉድለት ጋር በተያያዘ በሽታ ተነስቶ ህጻናትና ሴቶች ሊያልቁ ይችላሉ በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል። ተፈናቃዮች ምግብ እየቀረበላቸው መሆኑን ተናግረዋል፣ ምግቡን የሚያቀርብላቸው ግን ቀይ መስቀል ይሁን መንግስት አላወቁም።

ለማያዉቅሽ ታጠኚ


ለማያዉቅሽ ታጠኚ

ማስረሻ መኮንን ነኝ ከቃሊቲ
እንደምን ሰነበታችሁ ግንቦቶች -  እቺ ደብዳቤዬ እንደምትደርሳችሁ አልጠረጠርም፤ ካልደረሰችም እርግጠኛ ነኝ እናንተዉ ፈልጋችሁ ታገኟታላችሁ።  ለመሆኑ እንደምን ከረማችሁ? ዘረኞቹ የወያኔ ካድሬዎች በዚያ ሰሞን ዉጭ አገር ካሉ ሽብርተኞች ጋር ትገናኛለህ ብለዉ ዘብጥያ ወርዉረዉኝ ይሄዉና ሳላናግራችሁ ሳታናግሩኝ ድፍን አንድ አመት አለፈን። መቼም የማይለመድ ነገር የለም መታሰርም ኑሮ ሆኖ ይሄዉና እስር ቤቱን ለመድኩት። ደሞስ የወያኔ እስር ቤት ለምን አይለመድ! ባልታሰር የማላገኛቸዉን ጓደኞቼን፤ ምሁራንንና፤ የእስልምናና የክርስትና እምነት ሊቃዉንትን እዚህ እስር ቤት ዉስጥ ነዉ እንዳሰኘኝ የማገኛቸዉ። ለሁሉም ምን አለፈችሁ ምን አነበብክ፤ ምን ጻፍክ፤ ምን አሰብክ፤ ማንን አሳደርክ እያለ የወያኔ ካድሬ በየቀኑ ከሚጨቀጭቀኝ እዚህ የአገሪቱ ምሁርና አዋቂ የበዛበት እስር ቤት ዉስጥ ብኖር ይሻላል ብዬ አትፍቱኝ ብያቸዋለሁ . . . . . . .  የሚሰሙኝ ከሆነ!
ግንቦቶች የዛሬዉ ጉዳዬ  የእስር ቤት ኑሮዬን መተረክ አይደለም፤ ጉዳዬ ሌላ ነዉ። ግን ስለ ልጅነት ጓደኛዬ ስለ ታሪኩ ሳልነግራችሁ ባልፍ ቅር ይለኛል። ታሪኩ የወያኔን ፖሊሶች ግልምጫ ከምንም ሳይቆጥር ሁሌ እየመጣ የሚጠይቀኝ የልጅነት ጓደኛዬ ነዉ። ታሪኩ የሚበላ ምግብ ብቻ ሳይሆን የሚነበብ ጸሁፍም ይዞልኝ ይመጣል፤ እኔም የጻፉኩትን ለአንባቢ ያደርስልኛል። የሚገርመዉ ታሪኩ የኮድ ስሙ ሳይሆን እናቱ ያወጡለት ትክክኛ ስሙ ነዉ፤  ስሙን ልደብቅለት ስሞክር  . . .   ስሜን ይወቁት ምን ያደርጉኛል ብለህ ነዉ . . . .  አንተዉጋ ነዉኮ የሚያመጡኝ. . . . . . ደግሞስ በየቀኑ ከምመላለስ አንዱኑ አብሬህ ብታሰር ይሻላል የሚል ቆራጥ ሰዉ ነዉ ታሪኩ።

ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው


ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው

አምባገነን መንግስታት አገዛዛቸውን ለማቆየት ከሚጠቀሙበት ዋነኛ መሳሪያቸው ከሆነው የጦርና የደህንነት ሃይል ውጭ በርካታ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። ልዩነትን ማራገብና ህዝብን መከፋፈል፣ ማስፈራራት፣ ዜጎች መረጃ እንዳያገኙ አማራጭ ሚዲያዎችን ሁሉ ማፈንና መዝጋት ብሎም የጥቂቶቹን ስብእና በጥቅማጥቅም  በመግዛት ሎሌና ጋሻ ጃግሬ በማድረግ፤ እንዲሁም በአገዛዛቸው የተማረረውን ህዝብ የተስፋ ዳቦ ላያድሉት እየጋገሩ ነገ የተሻለ ቀን ይመጣል እያሉ መስበክ ከብዙ ጥቂቶቹ ዘዴዎቻቸው ናቸው።
የሰሞኑን የወያኔ ጉባኤና ያወጣቸውን መግለጫዎች ልብ ብሎ የሚያጤን ኢትዮጵያዊ ሁሉ አንድ ነገር በግልጽ ማየት ይችላል። እሱም የጉባኤዉ ተሳታፊዎችና የወያኔ/ኢህአዴግ መሪዎች የሚጋሩት፤ አብሮ ያቆማቸዉና ከምንም በላይ የሚያያይዛቸው አንድ ነገር ቢኖር ፍርሃታቸው መሆኑ ነው። በአለም ዙሪያ በከፍተኛ ፍጥነት እየናኘ አምባገነኖችን እንደማእበል ከወዲያ ወዲህ እያናወጠ፣ እየጠራረገ በማስወገድ ላይ ያለው የህዝብ የዴሞክራሲና የሰበአዊ መብት መከበር ጥያቄ፣ የእነሱንም በር እያንኳኳ መሆኑ ከፍተኛ ፍርሃት ለቆባቸዋል።
እነዚህ ዘረኛ ቡድኖችና ግፈኞች የሚጋሩት ህዝባዊነት ያለው መርህና የሀገር ራእይ የላቸውም። ለዚህም ነው ጉበኤያቸዉን ሞቶ በተቀበረ ሰዉ መሪ ቃል ጀምረዉ በዚሁ በሞተ ሰዉ ራዕይ የጨረሱት። የዚህ ሰዉ ራዕይ ደግሞ ዘረኝነት፤ስደት፤ እስር፤ ግድያ፤ንቀት፤ዘለፋና ህዝብን ማዋረድ ነዉ። የኢህአዴግ/ወያኔ መሪዎች የሚያስተዉል አዕምሮ ስለሌላቸዉ አልተረዱትም እንጂ ለኢትዮጵያ ህዝብ በዚህ በዘጠነኛ ጉባኤያቸዉ በግልጽ የነገሩት ነገር ቢኖር ፓርቲያቸዉ ኢህአዴግ የራሱ የሆነ ራዕይ የሌለዉ ጭራሽ በሞተ ሰዉ ራዕይ የሚንቀሳስ ሙት ፓርቲ መሆኑን ነዉ።

አዜብ መስፍንና የቼኮሌቱ ታሪከ

Click here for PDF
ሰለሞን ታረቀኝ
ድሮ ነው አሉ፤ አንዲት በናዝሬት ትምህርት ቤት ትማር የነበረች ተማሪ ጥርሷን ጣፋጭ ጨርሶት ነበርና ወላጆቿ በፍጹም ቼኮላት እንዳትበላ ያስጠነቅቋታል፤ ከዚያም አንድ ቀን አንዲትAzeb Mesfin for refusing to leave the palace. ጓደኛዋ ቼኮሌት አምጥታ ኖሮ በእረፍት ሰዓታቸው ጓደኛዋ የሰጠቻትን ጥቂት ቼኮሌት ታናሽ ወንድሟ እንዳያሳብቅባት ተደብቃ ስትበላ ያ ከውካዋ ወንድሟ ድንገት ቢደርስባት እጅዋ ላይ የቀረውን በድንጋጤ ወደ አፍዋ አስግብታ ቁልቁል መስደድ፤ ወንድምየውም ቼኮሌት እንድትሰጠው ቢጠይቃት እንዳለቀባት ትነግረዋለች። እሱም ይናደድና አሳብቃለሁ ብሎ ያስፈራራታል። ከዚያም ከትምህርት ቤት ወጥተው ቤታቸው እንደደርሱ ወንድሟን ለመቅደም ብላ ማንም ሳይጠይቃት፥ እማዬ፥ እማዬ እኔ እኮ ዛሬ ቼኮሌት አልበላሁም አለች ይባላል።
ቀየድሞዋ ቀዳማዊትም እንዲሁ ቀደም ቀደም ብላ ሳትጠየቅ ተክለፍልፋ ለሁለተኛ ጊዜ ባሌ የ፮ ሺህ ብር የወር ደመወዝተኛ፥ ከዚህም ተቆራርጦ ፬ ሺህ ብር ያገኝ ነበር ስትል አበሰረችን። የቼኮሌቱ አይነት መሆኑ ነው።

“የኢህአዴግ እብሪትና ትዕቢት አገርንና ህዝብን የሚያጠፋ ነው”


አቶ ግርማ በቀለ 33ቱ ፓርቲዎች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ

የዛሬው እንግዳችን አቶ ግርማ በቀለ ይባላሉ ፡፡ አቶ ግርማ በቀለ በቅርቡ የትብብር ሠነድ የተፈራረሙት 33ቱ ፓርቲዎች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ እና የኦሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት /ኦህዴህ/የተባለ ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡-  ፔቲሽን ፈራሚ ፓርቲዎች አሁን በምን እንቅስቃሴ ላይ ናቸው?
Ato Girma Bekele opposition politician based in Ethiopia
አቶ ግርማ በቀለ 33ቱ ፓርቲዎች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊ
አቶ ግርማ፡- የፔቲሽን ፊርማው ወደ ትብብር ሠነድ ከተሸጋገረ በኃላ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ የቀጣይ 6 ወራት ተግባር እቅድ ተዘጋጅቷል፡፡ ትብብሩን ለሚቀጥለው 6 ወራት የሚመራ ቋሚ አስተባባሪ ኮሚቴ ለማስመረጥ በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡ እስከ አሁን ድረስ ስንቀሳቀስ ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ አልነበረም፡፡ ከውስጥም ከውጪም የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመቋቋም እዚህ ደርሰናል፡፡ አሁን የደረስንበት ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ነው፡፡

ሳዑዲና ዓባይ ምን አገናኛቸው?


Source:-  Fitih le Ethiopia

በዘሪሁን አበበ ይግዛው
ሳዑዲ ዓረቢያንና አፍሪካን (ዓባይን) የከፈለውን ቀይ ባህርን ስናስብ እንዴት ሳዑዲ ዓረቢያ ከዓባይ ጋር ልትያያዝ የምትችለው ብለን ላናስብ እንችላለን፡፡ ምንም ዓይነት መቀራረብም ሆነ ጉርብትና የላቸውም፡፡ የሰውየውን መልዕክት አዘል ንግግር ስናስብ ደግሞ ሳዑዲ ዓረቢያ ለግብፅና ለሱዳን ጠበቃ ለመቆም የተናገረችው ሊመስለን ይችላል፡፡ ይህንንም ከተለያዩ መላምቶችና ምክንያቶች ብለን ከምናስባቸው ጉዳዮች እየተነሳን ልናትት እንችላለን፡፡Abay fallsሆኖም ግን የዓባይ ውኃ ፖለቲካን ጠለቅ ብለን ስንመረምር የምናገኘው እውነት ሳዑዲ ዓረቢያ በአንድም በሌላም መልኩ በዓባይ ውኃ ፖለቲካ ውስጥ እጇን ለማስገባት መፈለጓን እንረዳለን፡፡ ይህንም ከኢትዮጵያው ባሮ (ጋምቤላ) በተከዜ አትባራ (ፖርት ሱዳን) እስከ ቶሽካ ፕሮጀክቶች እንደሚከተለው እንቃኛለን፡፡

እንገፋበታለን እየተባለ ከበሮ የሚደለቅለት እዉነተኛዉ የመልሰ ዜናዊ ራእይ ተልእኮ፣ ግብና የአፈጻጸም መሳሪያዎቹ


ከአየነዉ ብርሃኑ

እንደ መንደርደሪያ
መለስ ዜናዊ ላይመለስ ሄዷል። አገርን የማፈራረስ እቅዱና ዘርን የማጥፋት አላማዉ ግን ዛሬም አለ።ወደፊትም እንደሚቀጥል የመለስ ምልምሎች ደግመዉ ደጋግመው እስኪገለማን ድረስ እየነገሩን ነው።
ባለ ራእዩ መሪ፣ ሊቁ መሪ፣አርቆ አሳቢዉ መሪ፣ የአፍሪካ ጠበቃ እንዲያዉ በአጠቃላይ ስለ መለስ ምን ያልተባለ አለ !! ሀይማኖቴን ቀይሬ በመለስ ማመን ጀምሬአለሁ ያለም አለ። ይባስ ብለዉም ፖሊስ ሲያባርረዉ የተወረወረዉን ወጣት በመለስ ሞት ምክንያት ከአስረኛ ፎቅ ላይ በመዉደቅ ራሱን አጠፋ ይሉናል። ምን ይህ ብቻ መለስ ዜናዊ አሁንም በመንፈስ እየገዛ ነዉ በሚል የሰበካ ስራ የተሰማራዉ የአዳዲስ ካድሬ ብዛት የትየለሌ መሆኑም ይነገራል።
ሁሉንም ማለት መብት ነው።ይመኑበትም ይስገዱለትም ይሙቱለትም ምንም ይሁን ምን መለስ አሁን የለም።ወደፊትም አይኖርም። ይቅበሩትም ያቃጥሉትም ለጊዜው ባይታወቅም እሱና እርኩስ ተግባሩ አሁን የሉም።

ኢህአዴግን “አድርባይ” አመራሮች አስግተውታል


አባላት “አድርባይነት የመመልመያ መስፈርት ነው” አሉ!!

eprdf 9th meeting
ኢህአዴግ አመራሮቹን “አድርባይነት የተጠናወታቸው” ሲል ፈረጀ። የከፍተኛ አመራሮች የግምገማ ውጤት የሆነውን ፍረጃ የሰሙ “የኢህአዴግ አባል ለመሆን አንዱና ዋናው መስፈርት አድርባይነት ነው” በማለት አድርባይነትን የፈጠረውና ያስፋፋው ራሱ ኢህአዴግ፣ በተለይም ህወሃት እንደሆነ አመለከቱ።

ወ/ሮ አዜብ ተጨንቀዋል!


“ከሁሉም ነገር ጽድት ብለን እንታገል”

azebb mesfin
አቶ መለስ ከሞቱ ጀምሮ በተለያዩ መድረኮች ንግግርና መዕልክት የሚያስተላልፉት ወ/ሮ አዜብ መስፍን መረጋጋት እንደማይታይባቸው ተገለጠ። አሁንም በባለቤታቸው ስምና መንፈስ ሙግትና ማብራሪያ ከማቅረብ አልተላዘቡም። ይህን የሚያደርጉት ከጭንቀት የተነሳ እንደሆነ ተመልክቷል።
ሰሞኑንን በተጠናቀቀው የኢህአዴግ ጉባኤ አቶ መለስን አስመልክቶ ወ/ሮዋ የተናገሩት ንግግር በጭንቀት ውስጥ ስለመሆናቸው ማሳያ እንደሆነ የተናገሩት አብረዋቸው ባህር ዳር ስብሰባ የተቀመጡ የድርጅታቸው ኢህአዴግ “ባልደረቦቻቸው” ናቸው።

ስለ አባይ ግድብ “አድርባይ” እንሁን?


ስለ አባይ ግድብ “አድርባይ” እንሁን?

cant keep quiet
ሰሞኑን ኢህአዴግ ጉባኤውን ሲጨርስ “አድርባይነት አሰጋኝ” ብሎናል። አባላቶቼ አድርባይ ሆነዋልና በዚህ ከቀጠልኩ እሰምጣለሁ የሚል ስጋት እንዳለበትም አስታውቆናል። ከፍርሃቻው ብዛት የተነሳ አድርባይነትን ለመዋጋትና “መድረክ ላይ ለመጥለፍ” በቁርጠኛነት እንታገላለን ብለው አቋማቸውን ነግረውናል። የሚገርመው ግን አድርባይነትን የፈጠረና ያነገሰው ራሱ ኢህአዴግ መሆኑን መዘንጋቱ ነው።

“እያንጓለለ” የአዜብ ኮሜዲ


“እያንጓለለ” የአዜብ ኮሜዲ

ከቴድሮስ ሐይሌ (TADYHA@GMAIL.COM)
“መለስ ወደዚህ ዓለም ጭንቅላቱን ይዞ ለዝህች አገር ለዚህች ምድር የሚጠቅም ሃሰብ አመነጨ ለግሌ ለቤተሰቦቼ ሳይል አንድ ቀን ለራሱ ሳይሆን መንግስት በሚሰጠው ደመወዝ በፔሮል የሚከፈል መሪ በዓለም ላይ መለስ ብቻ ነው።” አዜብ መስፍን
የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ዝናው ገኖ የነበረው የቀድሞው መንግስት ተራ ወታደር የነበረው ታምራት ገለታ የተባለ አባይ ጠንቋይ ሴት ወንዱን መሃይም ምሁሩን ብቻ ከተራውAzeb Mesfin, the wife of Meles Zenawi ዜጋ እስከዘመኑ ባለስልጣናት ሲያሰግድ ለቃልቻ ጣዖቱ ግብር ሲያስገባ የበረታ መንፈሳዊ ሃይል የተቀዳጀ እንደሆነ በአንድ ግዜ በተለያየ ቦታ እንደሚገለጽ ለተማጠነው ሃብት ጤና ትዳር እንደሚሰጥ በመስበክ ብዙ የዋሃንን አሳምኖ እስከ መመለክ ደርሶ የእግሩን እጣቢ እነደ ጠበል ሲያስጠጣ የነሆለሉለትን ሃብታሞች መድሃኒት በማጠጣት ገድሎ ሃብታቸውን የወረሰበትን የዩንቨርስቲ ምሩቃንን ሳየቀር ሳር እያስጎዘጎዘ ቡና እያስወቀጠ ይካደም የነበረበትን ሞራል አልባ የእውነት ድራማ በፍርድ መቋጫ እስካገኘበት ድረስ ያለውን የግለሰቡን የአጭበርባሪ ጥንቆላ ተውኔት ያንድ ወቅት መነጋገሪ ሆኖ የድርጊቱ ሰለባዎችና ራሱ ወንጀል ፈጻሚው ጭምር ለፖሊስ ይሰጡ የነበረውን መረጃ በየፌስቡኩና በዩትዩብ ተለቆ ጉድ ሲባል ነበር።

ታምራት ላይኔና አማረ (ክፍል-2)


ታምራት ላይኔና አማረ (ክፍል-2)

ከኢየሩሳሌም አ.
አማረ አረጋዊ በማስታወቂያ ሚ/ር የኢቲቪ ስራ አስኪያጅ ሃላፊ እያለ በጣም አፀያፊ ተግባራትን በየእለቱ ይፈፅም ነበር። እሱን ጨምሮ አራት የሕወሐት ሃላፊዎች ተመሳሳይ ወራዳ ተግባር ይፈፅሙ ነበር፤ አንዱ ዋሽንግተን የሚገኝና የፓርቲው ሰላይ ሲሆን አንዱ የሻዕቢያ ተላላኪ ሆኖዋል፤ ሌላው ሹም በርካታ ሴቶችን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በሽታ ሆን ብሎ በማስያዝ አገር ቤት እንዳለ (እስከ 2000ዓ.ም) አውቃለሁ፤ አሁን ግን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ መረጃው የለኝም።…
በወቅቱ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ ጉዳዩን ሰምተው አማረን ግምገማ ይጠራሉ፤ ቃል በቃል እገልፀዋለሁ፥ «አማረ ቢሮ ውስጥ (office sex) ትፈፅማለህ፤ ..» በማለት በማስረጃ አስደግፈው ሲነግሩት፣ የሰጠው መልስ ፥ «በረሃ አይደለም ያለሁት፤ ስራዬን እስካልበደልኩ ድረስ የፈለኩትን ማድረግ እችላለሁ፤ መብቴ ነው..» የሚል ነበር። በዚህም ምክንያት በታምራት ትእዛዝ አማረ ከሃላፊነት እንዲነሳ ተደረገ።

የአማረ ገመና ሲገለጥ!(ክፍል-1)


የአማረ ገመና ሲገለጥ!(ክፍል-1)

(ከኢየሩሳሌም አ.)
አዲስ አበባ አየር ማረፊያ፣ ነሃሴ 13 ቀን 1997ዓ.ም ፣ ምሽት 2 ሰዓት…ለእረፍት መጥቶ የነበረ ጓደኛዬን ለመሸኘት በስፍራው ተገኝቻለሁ። ..እንዳጋጣሚ በቅርብ ርቀት የ<ሪፖርተር> ጋዜጣ ባለቤት አማረ አረጋዊን አየሁት፤ ወደርሱ አምርቼ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ < ወደ አሜሪካ ለእረፍት የላከውን ልጁን ለመቀበል እንደተገኘ > ገለፀልኝ። …ከዛም ወደ ወቅቱ የፖለቲካ ትኩሳት በመግባት ወሬ ቀጥልን፤ በመሃከሉ አማረ ፥ « ..ሲሳይና እስክንድር የጋዜጠኝነት ካባቸውን አውልቀው ለምን በግልፅ ፖለቲከኛ አይሆኑም? » ሲል በሹፈት አይነት ጠየቀኝ። « ምን ማለት ነው?» ስል መልሼ ጠየቅኩት፤ ..« በግልፅ የሚፅፉትን አታይም እንዴ?..የቅንጅት ዋና አቀንቃኞች ሆነዋል እኮ..» ካለ በኋላ አያያዘና « ..ይህችን አገር ልደቱና ሃይሉ ሻውል እንዲመሯት ነው የሚፈልጉት?…ልደቱ ነው አገር ለመምራት የሚቀመጠው?..» ሲል ያቺ የማውቃት የአማረ ፌዝና ሹፈት ፈገግታ በስሱ እያሳየኝ፤ …በዛ ሰሞን አማረ <አቋሙን> ይፋ አውጥቶ በቅንጅትና በጋዜጦች በተለይም በኢትኦጵና ምኒልክ ጋዜጦች ላይ በየሳምንቱ ..ለገዢው ፓርቲ የወገነ የቃላት ጦርነት የገጠመበት ወቅት ነበር።

Friday, March 29, 2013

Oromo struggle pioneers embrace Ethiopian struggle for justice & democracy

The following is a statement they sent out today to the media:

Leencoo Lataa
DECLARATION OF THE OROMO DEMOCRATIC FRONT (ODF)

We, members of the Founding Congress of the Oromo Democratic Front (ODF), announce the launching of a new Oromo political movement that advocates justice for the Oromo and all other nations in Ethiopia. The founding of ODF ushers in a new phase in the Oromo nationalist struggle with the objective of working for the transformation of the Ethiopian state into a truly democratic multinational federation equitably owned by all the nations.

Ethiopia: EPRDF, no identity and no vision


FOR  IMMEDIATE  RELEASE

March 28 2013
For the past twenty one years, the Tigray People Liberation Front (TPLF) that has no mandate to rule Ethiopia hasGinbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy actually ruled Ethiopia with iron fist dashing on the  Trojan horse,  the  EPRDF ( Ethiopian People Revolutionary Democratic Front).  The EPRDF, a political front; composed of a hodgepodge of ethnically assembled organizations, is a hollow group of ethnic demagogues created by its late leader to materialize his lifelong dream of dividing Ethiopia along ethnic lines. Ironically, the EPRDF that blatantly boasts to have averted the disintegration of Ethiopia, firmly stood up to the dreams of its creator and augmented the fragmentation of Ethiopia, the very country it calls home.

ነገን የተሻለ ቀን ለማድረግ፤ ዛሬ ነው መነሳት፤ ይድረስ ለሀገሬ ወጣቶች


ሉሉ ከበደ

ከዘር ማንነታችን በፊት ሰብአዊ ሰውነታችን፤ ከጎጠኝነታችን በፊት ኢትዮጵያዊነታችን፤ ከሸፍጥ፤ ከተንኮል፤ ከመሰሪነታንችን በፊት ቅንነታችን፤ ከፍርሀታችን በፊት ድፍረታችን፤ እርስEthiopian flag, Green, yellow and red በርስ ከመጠራጠራችን በፊት መተማመናችን፤ ከመፍረክረካችን በፊት በጽናት መቆማችን፤ ከልዩነታችን በፊት አንድነታችን፤ ወያኔ ዛሬ ኢትዮጵያውያንን ከከተተበት መቀመቅ ውስጥ የሚያወጣን ብቸኛ መፍትሄ ከላይ የደረደርኩት ነገር ብቻ የመስለኛል።
ነጻ አውጭ ነን የሚሉ የዘር ፖለቲከኞች፤  ህዝብ መክሮ ዘክሮ ከዚህ ዘር ነጥሉን፤ ከዚያ ዘር ነጥሉን፤ ነጻ አውጡን፤ ብሎ ባይመርጣቸውም፤  በስራቸው ለማሰባሰብ ለፈለጉት ህዝብ ታሪክ እየፈጠሩ መስበካቸው እንዳለ ሆኖ፤  እንዲዋጋላቸው፤ እንዲታገልላቸው ሲያደርጉም የዚያኑ ያህል የውሸት ተስፋ እየመገቡም ነው። ለምሳሌ በትግሉ ዘመን የሻእቢያ ካድሬዎችና ፕሮፓጋንዳ ሰራተኞች ዘወትር ህዝቡን ሲሰብኩ፤ ኤርትራ ነጻነቷን ስታገኝ እያንዳንዱ ኤርትራዊ ዜጋ ምንም ስራ ሳይሰራ ከወደቦች በሚገኝ ገቢ ብቻ በቀን ከሰላሳ እስከ አርባ ብር ገቢ ይኖረዋል እያሉ ይሰብኩ ነበር።  ከነጻነት በኋላ ኤርትራ የምስራቅ አፍሪካ ሲንጋፑር ትሆናለች ይሉ ነበር።

ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል ሶስት)


ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል ሶስት)

ሀገሬ ሙች፣ ገንዘብ ወዳድ ሆነሻል!
addis-ababa
ሀገሬ አንዳንዴ ከሰሜን ወደ ደቡብ፣ ከምስራቅ ወደ ምእራብ የዘረጋሻቸውን ጎዳናዎች፣ ልታነጥፊያቸው ደፋ ቀና የምትይላቸውን ሀዲዶች ስመለከት ደስ ይለኛል። የአዲስ አበባን አስፋልትና በየአስፋልቱ ዳር ያቆምሻቸውን ህንፃዎች አዲስነት ስመለከት ደግሞ፣‹‹ቆይ ሀገሬ፣ መንገድም፣ ህንፃም አልነበራትም እንዴ?›› ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ። እውነቴን ነው የምልሽ ሀገሬ ግንባታሽን ለተመለከተ ፈርሶ የሚሰራ ሀገር ነው እኮ የምትመስይው! ግን እኔ ልማትሽን፣ እድገትሽን፣ ትራንስፎርሜሽንሽን . . . አልነግርሽም! እንደነገርኩሽ ጉዳዬ ከገመናሽ ነው። ለልማት ለትራንስፎርሜሽንማ ራዲዮና ቲቪሽ መች አነሰሽ! ዋናው ራዲዮና ቲቪ አልበቃ ብሎ ኤፍ.ኤም፣ ኢቲቪ1፣ ኢቲቪ 2 . . .  ልማትና እድገትሽ ራስምታትሽ እስኪሆን ይነግርሽ የለ! ነጋሪ ያጣው እኮ ገመናሽ ነው! እና እኔ ልጅሽ ልንገርሽ! በትልልቅ ህንፃና በተንጣለለ ጎዳና እንኳን አልሸፈን ያለውን ገመና ልንገርሽ!

Thursday, March 28, 2013

እስር ቤቶቻችን በሕገ-መንግሥት ወይንስ በ‹‹ሕገ-አራዊት››?


እስር ቤቶቻችን በሕገ-መንግሥት ወይንስ በ‹‹ሕገ-አራዊት››?




ምንጭ፣ ዞን ዘጠኝ ጦማር
በጌታቸው ሺፈራው
 የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትን እንዲጸድቅ በበላይነት የመሩት አቶ መለስና አቶ ሌንጮ ለታ መሆናቸው ይነገርላቸዋል፡፡ ይህ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ ቀጥተኛ ተሳታፊ ባልሆኑት የተገንጣይ መሪዎች ጠንሳሽነት የጸደቀው ሕገ መንግሥት ለአገር ሉኣላዊነት፣ አንድነትና ታሪክ ክብር የሌለው ቢሆንም ዓለማቀፋዊ የሰብኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን አጠቃልሏል፡፡ ሆኖም እነዚህ ሰብኣዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ለእርዳታ ማሰባሰቢያ የተቀመጡ እንጂ ወደመሬት ወርደው ተግባራዊ መሆና ባለመቻላቸው የይስሙላህ ሕግ ሆኗል፡፡ ከሕገ መንግሥቱ ይልቅ የገዥዎች ጊዜያዊ ሥልጣን ጥቅም ለማስጠበቅ በየጊዜው ትርጉሙ የሚቀያየረው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ‹‹መርሕ›› ሕዝብ ላይ የተጫነ ገዥ ሕግ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ይህን ስርዓት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ‹‹ሕገ አራዊት›› ሲሉ ይገልጹታል፡፡

ዳንኤል ክብረት በአርቲስት ጀማነሽ ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴ ዙሪያ ያቀረበው ጽሁፍ ስንቶቻችሁ እንዳነበባችሁት አላውቅም፡፡ እኔ ግን…


የኢትዮጵያዊነት ድምጽ-Ethiopiawinet
ዳንኤል ክብረት በአርቲስት ጀማነሽ ሀይማኖታዊ እንቅስቃሴ ዙሪያ ያቀረበው ጽሁፍ ስንቶቻችሁ እንዳነበባችሁት አላውቅም፡፡ እኔ ግን በጣም ተገርሜበታለሁ፡፡መጀመሪያም ከፕሮፌሰር መስፍን ጋ እንደዛ ያጠማመደው ለካ ይህ ኖራል?ቀጥታ ወደ ዲያቆናችን ከመግባቴ በፊት ትንሽ ስለ እነ ታምራት ነገራ የሆነ ነገር ብል ደስ ይለኛል፡፡ ታምራት የት እንደ ተወለደ አላውቅም ግን ልክ እንደ መስፍን ነጋሽ እንደ አብርሀም ደቦጭም ሀገር ያለው አይመስልም፡፡እሱ ኢትዮጵያም ውስጥ ኖረ ከኢትዮጵያ ውጪ ያው ልክ እንደ ጓደኞቹ የሰው ሀገር ሰው ነው፡፡ምናልባት እድሉ ካጋጠመው አሁን በሚኖርበት ሀገር እንደምንም የመኖሪያ ፈቃድ አግኝቶ እንዲህ ከማያውቃትና ከአፈጣጠሯ ጀምሮ እንከንና ብክነት ከሞላባት ሀገር እንዲገላገል በጣም የዘወትር ጸሎቴ ነው፡፡ግን አንድ ነገር እንዳይረሳ ልጆች ካሉ ወደ ኢትዮጵያ ይላካቸው ፣ የኢትዮጵያ አፈር ብቻ ሳይሆን አለትም መሰረትም ጭምር ካባት ካያቶቻቸው እንደ ተሰራች እንደምንም እናስተምራቸዋለን፡፡ በዚህ አመሉ እሱ ካስተማራቸው ነገ አድገው ተመንድገው በተንሻፈፈ ተረትተረት ሀገር ፍለጋ ጫካ እንዳይገቡ ያሰጋልና፡፡አበርሃም ደቦጭ ..ታሪክና..ተመራማሪ ..የሚሉ ትልልቅ የሰማይ ስፋት ያህል የእውቀት ይዘት ያላቸው ስሞችን ተሸክሞ የአንድ ነገር ምንነት ከግል አስተያየት በውጣ መልኩ ሙያና ስርአት ባለው መንገድ የአንድን ነገር መግለጽ አለመቻሉ ይገርመኛል፡፡ስም ተጭኖ አይገለም የሚባለው ተረት በሙሉ አካል ምን እንደሆነ ያሳየኝ ሰው ስለሆነ ባመሰግነው አይከፋኝም፡፡ግን ይህን አካል የያዘው አካለ ቢስ ስለሆነ አይደለም ትክከለኛ አካሉ ለነጮች ተረት ተረት አሳልፎ ሰጥቶ እነሱ በሱ ማንነት ወርቅ አውጥተው ማር ቆርጠው ካለ ማንነታቸው ባገኙት ነገር ሲደሰቱ እሱ ግን የነሱን ኩበት ተሸክሞ አገሪጻን ኩበት በኩበት ከብትበከብት ለማድረግ በወዶ ገብነት በመሰለፉ ነው፡፡ በተለይ ቢትል ኢንቲሞሎጂ.. የምትለው አስተሳሰብ ጎትቶ ጎትቶ የጎጠኝነት ቅርጫት ስላደረጋትና ፕሮፌስር መስፍንንም በዛ አንተልልጥሎ ለመሄድ በማሰቡ በጣም አዝኛንቶኛል፡፡

! ……. የትግራይ ህዝብን ዝምታ ሲተረጎም ……!


! ……. የትግራይ ህዝብን ዝምታ ሲተረጎም ……!

ባለፈው እንዲህ ፅፌ ነበር፣

“… የትግራይ ህዝብ በሙሉ የህወሓት ደጋፊ ነው ማለት ኣይቻልም። ብዙ የሚቃወም ኣለ። ብዙ የሚጨቆን ኣለ። በትግራይ የሌለው ጭቆናን የሚያጋልጥ ሰው ነው። በሌሎች ኣከባቢዎች (ከትግራይ ውጭ) ሰው ሲታሰር ወይ ሲገደል የሚናገርለት ወይ የሚጮህለት ወገን ኣለው። በትግራይ ግን የለም። ኣንዱ ሲታፈን ሌላው ኣብሮ ዝም ይላል። ይሄ ነው ልዩነቱ እንጂ በትግራይ ጭቆና ስለሌለ ኣይደለም።”

ከዚህ በመነሳት Prof. Mesfin Wolde-Mariam እንዲህ ጠየቁ:

“አብርሃ ደስታ፤ ያልከውን አምናለሁ፤ ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህና አንተ በተመቸህ መንገድ መልስልኝ፤ በትግራይ ሰዎች ሲበደሉና ሲጠቁ ሌላው ሰው ዝም የሚለው በምን ምክንያት ነው?”

መልስ

ኣብዛኛው የትግራይ ሰው የህወሓት መንግስት በዜጎች በደል ሲያደርስ ከመቃወም ይልቅ “ብኡ የሕልፎ” የሚል ብሂል (ወይ ኣባባል) ተግባራዊ ያደርጋል። “ብኡ የሕልፎ” የትግርኛ ኣባባል ሲሆን Literally ‘በዛ ይለፍልን’ (ወይ ‘የባሰ ኣታምጣ’) ዓይነት ትርጉም ኣለው። 

! …… የመተካካት ሙስና በህወሓት …….!


! …… የመተካካት ሙስና በህወሓት …….!

ጥያቄ

“የምትፅፈው ነገር የተወሰነ እውነት ኣለው። ግን ከውጭ ሁኖ ህወሓት ለት ተቀን ከመውቀስ በህወሓት ውስጥ ሁነው ማስተካከል ኣይሻልም?” (ኣንድ የህወሓት ኣባል)።
መልስ
ኣንድ!
ህወሓት በቤተሰባዊነትና ሙስና (ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ) የተጨማለቀ ድርጅት ሆነዋል። ኣብዛኛው መዋቅሩ በስብሰዋል። በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል ኣይደለም። የመዋቅር ሙስናው በጭቃ እንመስለው፤ ኣብዛኞቹ የህወሓት ባለስልጣናት በሙስና (በጭቃው) ተጨማልቀዋል። ይሄንን ለማስተካከል ታድያ በ’መተካካት’ ስም ኣዲስ ሰው ወደ ጭቃው በመወርወር ጭቃው ማስወገድ ኣይቻልም። የሚያስፈልገው ኣዳዲስ ሰዎች ወደ ጭቃ መክተት ሳይሆን ጭቃው ማስወገድ ነው።
ሁለት
በህወሓት ዉስጥ ግለሰዎች ድርጅቱን የማስተካከል ዕድ ል ኣያገኙም። ምክንያቱም ድርጅቱ ከተዘፈቀበት ዓዘቅት ለማስወጣት ባለ ኣዲስ ራእይ ኣዲስ ወጣቶች፣ ኣዲስ ኣመለካከትና ኣሰራር ኣስገብተው ድርጅቱን መምራት ኣለባቸው። ኣሁን ያለው የህወሓት ኣመራር ይሄንን ይፈቅዳል??? 

የዘገየው አብዮት (ተመስገን ደሳለኝ)


የዘገየው አብዮት (ተመስገን ደሳለኝ)

images (1)
‹‹አረብ ስፕሪንግ››ን ተከትሎ በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ፖለቲካ ተንታኞች በዘርፈ ብዙ ቅሬታ በተሞላችው ኢትዮጵያም ተመሳሳይ ነገር መከሰቱ አይቀሬ እንደሆነ ደግመው ደጋግመው መተንተናቸው ይታወሳል፡፡ ለድምዳሜያቸው ገፊ ምክንያት አድርገው ከወሰዷቸው ችግሮች ውስጥ ስርዓቱ ለሁለት አስርታት በስልጣን ላይ መቆየቱ፣ አስከፊ ድህነት መስፈኑ፣ የስራ አጥ ቁጥር ማሻቀቡ፣ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ክብር አልባ መሆናቸው፣ የፍትህ እጦት… ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ቁጥራቸው የበዛ ምሁራኖች እነዚህ ችግሮች በጊዜ መፍትሄ ካላገኙ አብዮት ወደ ሚያቀጣጥል ‹‹ካምሱር››ነት ለመቀየራቸው የተለያዩ ሀገራትን ታሪክ ጭምር ጠቅሰው በርካታ ፅሁፎችን አስነብበዋል፡፡ የሆነ ሆኖ የሰሜን አፍሪካ ሀገራት ህዝቦች ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸውን ተከትሎ፣ በኢትዮጵያ የተፈጠረውን መነቃቃት ለማደብዘዝ ስርዓቱ ራሱን ለተጋነነ ወጪ መዳረጉ ይነገራል፡፡ በተለይም የደህንነት ተቋሙን፣ መከላከያ እና የፖሊስ ሠራዊትን ለማጠናከር የሀገር ሃብት ባክኗል፡፡

አቶ አዲሱ ለገሰ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን በሀሜተኝነት ነቀፉ፤ አስጠነቀቁም


መጋቢት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:- “ስለዴሞክራሲያዊ ድርጅትም ስናወራ በአስተሳሰብም በተግባርም ወደ አንድ መምጣት መቻል አለብን። አሁን ባለው አቀራረብ ከሄድን ግን መቀራረቡ አይደለም የሚጨምረው”ሲሉ አቶ አዲሱ ለገሰ  የ ኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን አስጠነቀቁ።
 የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ አመራር የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ አባል ድርጅቶቹን ያስጠነቀቁት “መተካካቱ በብአዴን ውስጥ በተቀመጠው እቅድ አልተተገበረም” በማለት  እርሳቸውና ድርጅታቸው በሌሎቹ ድርጅቶች አመራሮች በመታማታቸው ነው።
ሰንደቅ እንደዘገበው የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ሰሞኑን በተናጠል ባካሄዱት ጉባዔ ነባር አመራሮችን ወደማዕከላዊ ኮሚቴ መልሶ የመምረጥ ሁኔታ መታየቱ ከመተካካት መርህ አንጻር በግንባሩ አባላት ሳይቀር ጉዳዩ መነጋገሪያ ሆኗል።
ህወሃት አቶ አባይ ጸሐዬን፣ ብአዴን እነአቶ አዲሱ ለገሰን እና አቶ ህላዊ ዮሴፍን በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የመረጡ ሲሆን፤ ሌሎችም በአዲስ መተካት ያለባቸው ነባር አባላት በአመራርነት መቀጠላቸው ጥያቄ አጭሯል።

Ethiopia’s Human Rights Crisis Worsened


Ethiopia’s Human Rights Crisis Worsened

Betre Yacob Ethiopian Journalist and blogger
by Betre Yacob
The human rights situation in Ethiopia, the most important strategic and security ally of the Western powers, has worsened drastically, according to the 2013 Human Rights Watch’s World Report, which summarizes the human rights situation of more than 90 countries worldwide—drawing on events from the end of 2011 through November 2012.
The 665 page report says that Ethiopia’s dictatorial regime has deliberately continued to severely restrict fundamental rights of freedom of expression, association, and assembly. In addition, the report indicates that intimidation, arbitrary arrest, torture, forced displacement, and killing remain routine throughout the country.
The report, which reflects extensive investigative work that Human Rights Watch undertook in collaboration with local human rights activists, was released in the beginning of February 2013. Providing heartbreaking examples, cases, and photographs, the report explains enough how dramatically the human rights crisis in Ethiopia has been worsening.

“ሀገሬ ገመናሽ” (ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ፣ ክፍል ሁለት)


በየፍርድ ቤቶችሽ የፍትህ ውርጃ ሲፈፀም ዝም አልሽ።

ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ
ልዕልና ጋዜጣ
ምንጭ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም ብሎግ
በቀደም ሳት ብሎኝ፣
ለመጀመሪያ ልጄ ብቻ የፈረንጅ ሸራ ጫማ ገዝቼ ገባሁ። ያለወትሮዬ ማለቴ ለወትሮው ገበያ የምወጣው ሁለቱንም ልጆቼን ይዤ ስለነበረ ነው። ታዲያ ያን እለታ ማታ ትልቅዋ ልጄ ጫማውን ስትለካ፣ የታናሽ እህትዋ አይን ከሚለካው ጫማ ጋር ሲንከራተት ተመለከትኩ፤ ወይም የተመለከትኩ መሰለኝ። ‹‹ከወደድሽው ላንቺም ይገዛልሻል›› አልኳት፤ የትንሽዋን ልጄን አይን እየሸሸሁ። በውስጤ አድሏዊነት ተላወሰ። በልጅትዋ ህሊና ውስጥ ይህ ስሜት እንደማያድር ባውቅም፣ የእኔን ሃሳብ ግን ቶሎ ላስወግደው አልቻልኩም። አየሽ ሀገሬ? እንኳን ህዝበ አዳምና ሔዋንን በእኩልነት ቤት ሆኜ አኖራለሁ የሚል ሀገር፣ አንድ ተራ ምስኪን ወላጅ እንኳን በጎጆው አድሏዊነት እንዳይሰፍን ይጥራል። አንቺ ግን ሀገሬ! … አንቺ ግን ዝሆንና ጥንቸል እያፋለምሽ ለአሸናፊው ታጨበጭቢያለሽ፤ ትሸልሚያለሽ።

መልካም መሪ ማግኘት ምንኛ መታደል ነው?!


በታምሩ ገዳ

በየትኛውም የእድገት  ደረጃ  ይሁን የፖለቲካ  አመለካከት ወይም የሃይማኖት  ስርአት  ውስጥ ለሚገኝ ማህበረሰብ ሁነኛ መሪ ማግኘት ከእድሎች ሁሉ ትልቁ እድል ነው  ቢባል ማጋነንPope Francis breaks with tradition and refuses to move into a palatial apartment  አያስብልም፡፡
ለዚህ ይመስላል የሮማ  ካቶሊክ ቤ\ክርስቲያን   በቀርቡ 266ኛዋን  መሪ (ፓፓ ) ለመምረጥ የሃይማኖቱ አባቶች  በቫቲካን ከተማ  በተሰባሰቡበት  ወቅት በ 150,000ዎች  የሚቆጠሩ ምእመናን ቀጣዩ የሃይማኖታችን አባት  ማን ይሆኑ? በማለት  የምርጫው ውጤቱን ለማወቅ  በታላቁ  የቅዱስ  ጴጥሮስ  አደባባይ ተሰባስበው የነበረው፡፡ በዚህ የምንፈስ  ቅዱስ መሪነት  በተካሄደው  የመጪው  የቤተክርስቲያኒቱ  መንፈሳዊ አባት መረጣ    ላይ  የብዙዎቹ ምርጫ ሆነው  የቀረቡት  ከ120 ሚሊዮን  በላይ የእምነቱ ተከታዮች  ያሏት አገር  ብራዚል  ከሳኦ ፖሎ ከተማ  የመጡት  አርክቢሾፕ ኦዲሎ ሺረር ነበሩ፡፡

Wednesday, March 27, 2013

“ሀገሬ ገመናሽ” በፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም (ክፍል ሁለት)


በየፍርድ ቤቶችሽ የፍትህ ውርጃ ሲፈፀም ዝም አልሽ።

በፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም (ክፍል ሁለት)
በቀደም ሳት ብሎኝ፣
ለመጀመሪያ ልጄ ብቻ የፈረንጅ ሸራ ጫማ ገዝቼ ገባሁ። ያለወትሮዬ ማለቴ ለወትሮው ገበያ የምወጣው ሁለቱንም ልጆቼን ይዤ ስለነበረ ነው። ታዲያ ያን እለታ ማታ ትልቅዋ ልጄProfessor Mesfin Woldemariam is one of Ethiopia's well-known intellectuals ጫማውን ስትለካ፣ የታናሽ እህትዋ አይን ከሚለካው ጫማ ጋር ሲንከራተት ተመለከትኩ፤ ወይም የተመለከትኩ መሰለኝ። ‹‹ከወደድሽው ላንቺም ይገዛልሻል››አልኳት፤ የትንሽዋን ልጄን አይን እየሸሸሁ። በውስጤ አድሏዊነት ተላወሰ። በልጅትዋ ህሊና ውስጥ ይህ ስሜት እንደማያድር ባውቅም፣ የእኔን ሃሳብ ግን ቶሎ ላስወግደው አልቻልኩም። አየሽ ሀገሬ? እንኳን ህዝበ አዳምና ሔዋንን በእኩልነት ቤት ሆኜ አኖራለሁ የሚል ሀገር፣ አንድ ተራ ምስኪን ወላጅ እንኳን በጎጆው አድሏዊነት እንዳይሰፍን ይጥራል። አንቺ ግን ሀገሬ! … አንቺ ግን ዝሆንና ጥንቸል እያፋለምሽ ለአሸናፊው ታጨበጭቢያለሽ፤ ትሸልሚያለሽ።

ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ


(በሰሎሞን ተሰማ ጂ.)

Email: solomontessemag@gmail.com
ማንም በዕድሜው ብዛት አያስጠራም ስሙን
በጥቂቱም ዕድሜው ይሠራል ሐውልቱን፡፡
ታሪክ ሲያበላሸው ረጅሙም ያጥራል፣
ታሪክ ሲያሳምረው አጭሩም ይረዘማል፤
ብዙ ዘመን ቢኖር ዕድሜውም ቢበዛ፤
በሳቅ በጨዋታ ዋዛን በፈዛዛ፣
ሲለዋውጥ ኖሮ ሃሳቡን ሳይገዛ፣
እንዲሁ ይቀራል እንዲያው እንደዋዛ፡፡
(“ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ” (2004)፤ ገጽ 191)
ከላይ የተጠቀሱት ስንኞች የማንን “ዕድሜ” እና “ታሪክ” ለማሳመር እንደሚበጁ ለመወሰን አያዳግትም፡፡ ሥንኞቹ ጉልሕ አጽንዖት የሚሰጡት ዕድሜው ስላልበዛው ሰው ነውና፤ የዚህ መጽሐፍ ደራሲም ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ “38 ዓመት ከ10 ወር ሊሞላው 4 ቀን ጎደል ነበር”፡፡ ለአንድ “ሩቅ አስቦ፣ ቅርብ ላደረ” ሰው የሚስማማ ዐርኬ ነው፡፡ ሌሎቹ በዚህ የመጽሐፍ ግምገማ ውስጥ የምናወሳቸው ሁለት ሰዎች፣ ከዚህ “አታላይ ዓለም” ሲለዩ ሃምሳ ሲደመር ሦስትና ለሰባ አንድ ፈሪ ነበሩ፡፡

Ethiopia: Prime Minister Bereket Simon


Ethiopia: Prime Minister Bereket Simon

by Amanuel Biedemariam
After the late genocidal dictator Meles Zenawi was rumored to have been sick, incapacitated or dead, Bereket SimonBereket Simon direct Ethiopian political direction to suit his needs. used the time cunningly to direct the course of the current Ethiopian political direction to suit his needs and the needs of few of his close allies. I have in the past written that “the End of TPLF is here”; and current political developments in Ethiopia prove that in deed, has happened. TPLF revolution, Gedli Tigray is over, caput because Bereket Simon is the undisputed victor for now.

በምንሊክ ሆስፒታል የኩላሊት ስርቆት ይካሄዳል ተባለ !


ኩላሊት ለመስረቅ ሙሉ መሳሪያና የኩላሊት ባለሙያ ያስፈልጋል – የሆስፒታሉ ባለሙያ በምንሊክ ሆስፒታል ኩላሊት ተሰርቋል በሚል በቀረበ አቤቱታ የተነሳ በሆስፒታሉ የአስክሬን ምርመራ ክፍል ላይ ምርመራ እንደተካሄደ ምንጮች የገለፁ ሲሆን፣ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች የኩላሊት ስርቆት ሊካሄድ አይችልም ሲሉ አስተባበሉ፡፡ የመኪና አደጋ ደርሶበት በምንሊክ ሆስፒታል ሲታከም የነበረ ሰው ህይወቱ በማለፉ የሟች ቤተሰቦች ለፖሊስ የሚቀርብ ማስረጃ ከሆስፒታሉ ጠይቀው ነበር በማለት የገለፁ ምንጮች እንደሚሉት፤ ከዚህ ጋር ተያይዞ የተካሄደው የአስከሬን ምርመራ በቤተሰቦች ላይ ቅሬታና ጥርጣሬ እንደፈጠረ ይጠቁማሉ።
ጉዳዩም ወደ ፖሊስና ወደ ፀረ ሙስና ኮሚሽን እንዳመራ ምንጮቹ ጠቁመው፣ መርማሪዎች በሆስፒታሉ ተገኝተው ቅኝት እንዳካሄዱና ባለሙያዎችን እንዳነጋገሩ ገልፀዋል። ከፖሊስና ከፀረ ሙስና ኮሚሽን መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ፣ በሃላፊዎች አለመገኘት ምክንያት ባይሳካም፤ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች በበኩላቸው መርማሪዎች ወደ ሆስፒታሉ መጥተው እንዳነጋገሯቸው ጠቅሰዋል። አስከሬን ላይ ተገቢውን ምርመራ እንደሚያከናውኑ የሚገልፁት የሆስፒታሉ ባለሙያዎች፤ “በህክምና ወቅት ያልተከፈተውን የሟች አካል፣ በአስከሬን ምርመራ ወቅት እንዴት ይከፈታል?” የሚል ቅሬታ ከሟች ቤተሰቦች በተደጋጋሚ ይቀርባል ሲሉ ተናግረዋል።

Tuesday, March 26, 2013

በአረመኔው የወያኔ አገዛዝ በግፍ እስር ቤት የታጎሩት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸው ታወቀ


በአረመኔው የወያኔ አገዛዝ በግፍ እስር ቤት የታጎሩት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸው ታወቀ

ድምጻችን ይሰማ የሚል መፈክር አንግበው ላለፉት አስራ ሶስት ወራት አፋኙን የወያኔ አገዛዝ መቆሚያና መቀመጫ በማሳጣታቸው በጭካኔ እስር ቤት የተጣሉት ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ባስተላለፈልን ሪፖርት ገለጸ፣ ፣ እንደዘጋቢያችን ሪፖርት በዘረኛውና አረመኔው የወያኔ አገዛዝ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ታፍሰውና ማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ በግፍ ታስረው የሚገኙት ሙስሊም የዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ፣ ቤተሰቦቻቸው ያሉበትን ቦታ ባለማወቃቸው በቀለብ እና በልብስ እጦት እየተቸገሩ ነው ብሏል።
ዘጋቢያችን እንደገለጠው በአቃቂ እስር ቤት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ተማሪዎችና መምህራን እስር ቤቱን አጨናንቀው እንደሚገኙ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ፣ ከነኝህ ታሳሪዎች ውስጥ እጂግ በርካቶቹ ቶርቸር ( አሰቃቂ ድብደባ) ተፈጽሞባቸዋል። ይህም አልበቃ ብሎ ተማሪዎቹ በአሁኑ ጊዜ የረባ ምግብ አጥተው በመሰቃየት ላይ እንደሚገኙና ልብሶቻቸው በላያቸው ላይ እያለቁባቸው ለእርዛት እየተዳረጉ እንደሆነም ታውቋል።

የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አብረን እንታገል የሚል የትግል ጥሪ አደረገ


የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አብረን እንታገል የሚል የትግል ጥሪ አደረገ

የኢትዮጵያ ህዝብ ሃያ አንድ አመት ሙሉ ከቀለደበት  የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ እጅግ በጣም የተሻለ አማራጭ ኃይል እንዳለዉና ይህንን ለኢትዮጵያ አንድት፤ ለህዝቦቿ እኩልነትና ነፃነት በቆራጥነት የቆመዉን አማራጭ ኃይል የኢትዮጵያ ህዝብ በፍጥነት እንዲቀላቀልና የትግሉን የመጨረሻ ምዕራፍ እንዲጀምር የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል አገራዊ ጥሪ አደረገ። የወያኔ ንቀት፤ጥላቻና ህዝብን ማሸበር ማብቃት አለበት ብለዉ አምርረዉ በተነሱ ወጣቶች፤ምሁራንና ወታደሮች በቅርቡ የተቋቋመዉ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል በላፈዉ ሳምንት እንዳሳወቀዉ በወያኔ ተራ ካድሬዎች መረገጥና እየተገፋ እስር ቤት መወርወር የሰለቸዉ ኢትዮጵያዊና በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ዉስጥ በህዝብ ነጻ ፍላጎት ተመስርቶ ህዝብን በታማኝነት የሚያገለግል ስርአት ለመመስረት ምትፈልጉ ኢትዮጵዉያን ሁሉ ወያኔ እስካለ ድረስ ይህንን ህዝባዊ ስርአት ካለመስዋዕትነት ማምጣት አይቻልምና ለድል ሊያበቃን የሚቸለዉን መስዋዕትነት ለመክፈል እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተጠንቀቅ እንዲቆም አገራዊ የአደራ ጥሪዉን አስተላልፏል። የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል ይህንን ጥሪ ያደረገዉ የወያኔ ህወሀት ተሸካሚ ፈረስ የሆነዉ ኢህአዴግ ካለፈዉ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን እስከዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 17 ቀን ድረስ ባህርዳር ላይ ጌታዉን ተሸክሞ ያካሄደዉን ትርጉም የለሽ የወሬ ጉባኤ አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላለፈዉ መልዕክት ነዉ።

“አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ባመዛኙ ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረበት ጊዜ የባንዳ ልጆች ነበሩ”


ፍኖተ ነጻነት መጋቢት 15 ቀን 2005 ዓ.ም.

የዛሬው እንግዳችን አቶ ታዲዎስ ታንቱ ይባላሉ፡፡ አቶ ታዲዎስ የታሪክ ምሁርና በኢትዮጵያ ፖለቲካ እና ነፃ ፕሬስ ውስጥ ትልቅ ሚና ያላቸው ሲሆን በአሁን ወቅት “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ዋና ሰብሳቢ ናቸው ፡፡ በተለይ ለፋሺስቱ ግራዚያኒ ከተሰራው ሐውልት ጋር በተያያዘ አጭር ቆይታ አድርገናል ተከታተሉን፡፡
በጣሊያን የሩዶልፍ ግራዚያኒንን የሐውልት ለመቃወም የሐሳቡ ጠንሳሽ ማን ነው?
አቶ ታዲዎስ፡- የፋሽቱ ጣሊያን የኢትዮጵያውያን ዋና ጨፍጫፊ የነበረውን ሩዶልፍ ግራዚያኒ ሐውልት መሰራት ለመጀመሪያ ጊዜ ተቃውሞው የተጀመረው በውጭ ሀገር ባሉ
Interview with Ato Tadiwos Tantu
አቶ ታዲዎስ ታንቱ
ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት
ኮሚቴ ዋና ሰብሳቢ
ኢትዮጵያውያን ነው፡፡ በሀገር ውስጥ ግን የሐሳቡ ጠንሳሽ “ለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ኮሚቴ” ነው፡፡ ከዛ በኋላ የባለዕራዕይ ወጣቶች ማኀበር ሰልፉን ለማስተባበር ፈቃደኛ መሆኑን ገለፀልን፤ በዚህም ላይ ሰማያዊ ፓርቲ እንደሚተባበረን ከገለፀ በኋላ መጋቢት 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ሰልፉን ለማካሄድmወሰንን፡፡

“ዘጠኝ ቦላሌ…” ከይኸነው አንተሁነኝ


ከይኸነው አንተሁነኝ

መጋቢት 26 2013
የክህደት ቁልቁለት አሉ ታላቁ ምሁር!!! የክህደት ውርስ የበቀል ዛር እያስጎራ፣ የሚሆነውንም የማይሆነውንም እያስቀባጠረ ሃያ አንድ ዓመት እያንደረደረ ወርውሮ እዚህ ያደረሰው ሕወሃት ስለመድረሱ እንጅ ወደ ፊት ስለሚሆነው ወይም ስለሚያደርገው ከግምት በላይ የሚያውቀው ነገር ያለ አይመስልም። አውቃለሁ ብሎ ያቀዳቸው ተማከርኩ ብሎ ያወራቸው ሁሉም እንዳይሆን እንዳይሆን እየሆኑበት መሆኑ ይሰማል። ብዙ የተነገረለት ስንት የተባለለት ”የሕወሃቱ የእድገት ትራንስፎርሜሽን”ም ብዙም እንዳልጨበጠ የሚወራው ሳይሆን እየሆነ ያለው የምድሩ ላይ እውነት እያሳበቀበት ነው። ወትሮም ያልነበረው የሁለት አሃዝ ተከታታይ የኢኮኖሚ እድገት ፉከራም ወደ ሗላ እየባረቀ ”ለነዚህ ያህል ዓመታት ሁለት አሃዝ ተከታታይ እድገት ለምን ድህነትንና ስደትን በመጠኑ እንኳ ሊቀርፍ አልቻለም?” የሚለውን የዓለም ማሕበረሰብ ጥያቄ ባልተሳከረ መልኩ ለመመለስ ለሕወሃት አስቸጋሪ ሆኖበታል። ምክንያቱም የኑሮ ውድነቱ፣ ርሃብ እና ችግር የሚያንገላታው የሕዝባችን ቁጥር፣ የተማረ የሰው ሃይል ስራ አጥነት እንደጉድ መጨመር፣ ሁሉን አቀፍ ስደት ለመናገር ከሚያስቸግር በላይ መሆን እንዲሁም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ከምንም ጊዜ በላይ ዋጋው  ረክሶ የታየባቸው ዘመናት በሙሉ በሕወሃት የአገዛዝ ዘመን በተለይም ሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት አመጣሁ እያለ በሚለፍባቸው በነዚሁ ዓመታት ነበርና ነው።

ዕውን ኢትዮጵያን የሚመሯት ኢትዮጵያውያን ናቸው?



ETHLየኢትዮጵያ ክብር ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽ ኮሚቴና ባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር በመሆን ያዘጋጁት ሰላማዊ ሰልፍ አላማ ለፋሺስቱና ለጦር ወንጀለኛው ግራዚያኒ በጣሊያን ሀገር የተገነባውን መናፈሻ ስፍራና ሀውልት ለመቃወም ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ ታሪክ አይዘነጋውም፡፡

እጅግ አስደንጋጭ ቭዲዮኢትዮጵያውያን በመደበኛነት ከቆሻሻ ገንዳ የተደፉ ምግቦችን በመሰብሰብ ይመገባሉ::

ከዘመናት በፊት ለስብህናው ዋጋ የሚሰጠው፣ በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢያልፍ የሰው እጅ አይቶና ለምኖ ማደርን የማይፈቅደው የሃገሬ ሰው፣ ለእምነቱና ለክብሩ ሟች የነበረው ወገኔ ይኸው በዚህ ዘመን በሃገሩ በልቶ የመኖር ዋስትና አጥቶ፣ ድርሻውን በጥቂት ዘረኞች ተነጥቆ ኑሮው የምድር ሲኦል ሆኖበት ክብሩን አዋርዶና ነውር ትቶ ነብሱን ለማቆየት ይህንን የመሰለ ዘግናኝ የለት ከለት ኑሮ ይገፋል በመሃል አዲስ አበባ፡፡ ስለልማት፣ ስለተሰራው መንገድ፣ ባለጊዜዎች ስለገነቡት ህንፃ የምናወራ ጉደኞች፣ እድገት ምናምን እያልን የምናዜም አንድ ትውልድ ያመከንን  ከንቱዎች፣ ወገኖቻችን በእንደዚህ አይነት የሰቀቀን ህይወት ውስጥ እያይን ከራሳችን ባለፈ ማሰብ ተስኖን እንደቀትር እባብ ከደሃው ቀምተን ባገኘነው ሃብት የምንንፈላሰስ ከንቱዎች ጥሩም ሆነ መጥፎ መንግሰታት ያልፋሉ ሃገርና ሕዝብ ግን ህያው ናችው፡፡ ያኔ ምን ይውጣችሁ ይሆን . . . . . . . .

ከ100.000 በላይ ኢትዮጵያውያን በመደበኛነት ከቆሻሻ ገንዳ የተደፉ ምግቦችን በመሰብሰብ ይመገባሉ::ይህ የሚያሳየው ሃገራችንን የሚያስተዳድረው የወያኔ ጁንታ 11% እድገት አለ እያለ ቢሆንም ዉሸት መሆኑን ነው ::ወያኔ እየደረሰበት እያለው ኪሳራ መውድቂያው በመሆኑ ህዝቡን ለከፋ ችግር ዳርጎታል::

ነጋሶ ሞገቱ ወይስ ተሞገቱ?


“ኢህአዴግ በህዝብ (ያልተመረጠ) ስለሆነ እውቅና አንሰጠውም”

N G
“ … አንተም ሆንክ ማንም ኢትዮጵያዊ ውጪ ያሉትን ጨምሮ ቢደግፉን ደስ ይለናል። በዚህ መንገድ ሂዱ ብለው እንዲጠመዝዙን ግን አንፈልግም። … ሰላማዊ ትግል የምትሉት ለውጥ አያመጣም ይሉናል። እንደዚህ የምትሉ ከሆነ ከፈለጋችሁ ገንዘብ አትርዱን እንላቸዋለን … ኢህአዴግን እንደ መንግስት እውቅና አንሰጠውም” ከዶ/ር ነጋሶ የተመረጡ መልሶች መካከል የተጠቀሱ ናቸው። በዚህና በሌሎች ምክንያቶች ዶ/ር ነጋሶ ሊሞገቱ ሄደው ሞገቱ የሚል ርዕስ ለጽሁፌ መረጥኩ።

ከእሁድ እስከ እሁድ


ከእሁድ እስከ እሁድ

(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)
bottle


አንድ ላስቲክ ውሃ 10 ብር!!
በአፋር የቡሬ ነዋሪዎች ለከፍተኛ የውሃ ችግር መዳረጋቸውን ውሃ የሚሸጥበትን ላስቲክ በፎቶ በማያያዝ የጎልጉል የአይን ምስክር ከስፍራው አስታውቋል። በክልሉ የጎልጉል ተከታታይ የሆኑ እንደገለጹት በመጠጥ ውሃ ችግር እየደረሰ ያለው ችግር ከፍተኛና ህይወትን የሚፈታተን ነው። አካባቢው የጦር ቀጠና ከመሆኑ አንጻርና የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር አሳሳቢ እንደሆነ ያስታወቀው የአይን ምስክር “እባካችሁ የሚሰማ ካለ ንገሩልን” ሲል ጥሪ አስተላልፏል።