Translate

Thursday, November 30, 2017

መሀል ኢትዮጵያ – አዲስ አበባ፣ ፍርድ ቤት ውስጥ ህዝቡ በእንባ ይራጫል(መሳይ መኮንን)

Political prisoners in Ethiopia
ፍርድ ቤት ውስጥ ህዝቡ በእንባ ይራጫል። አንድ ሰውነቱ በግርፋት የተዘለዘለ እስረኛ ልብሱን አውልቆ ''እዩት ሰውነቴን። አኮላሽተውኛል። ዘር እንዳይኖረኝ አድርገውኛል።'' እያለ ሲቃና ለቅሶ ባሸነፈው ድምጽ ይማጸናል። ''የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ''ም አለ። ፍርድ ቤቱ በሀዘን ክው ብሎ ቀረ። ሁሉም ተላቀሰ። አሁንም እዚያው አዲስ አበባ ወጣቷ ንግስት 10ሩም የእጆቿ ጥፍሮች ተነቅለው በኪሶቿ ይዛለች። የደረሰባት ቶርቸር መልኳን አገርጥቶታል።

Wednesday, November 29, 2017

የአዜብ መስፍን ከህውሓት መታገድ፣ – ኤርሚያስ ለገሰ

አንደኛ: የመለስ ራዕይ ወደ ሥላሴ መቃብር ይወርዳል። HD ከዚህ በኋላ ” ታላቁ መሪያችን” ብሎ እንዳይናገር ከአርከበ ትእዛዝ ይደርሰዋል።

Tuesday, November 28, 2017

ዳኛ ዘርዐይ ወልደሰንበት ዛሬ ማሕሌት ፋንታሁንን በችሎት መሐል በወቀሳ አስጠነቀቋት

በፍቃዱ ዘ. ኃይሉ
ዳኛ ዘርዐይ ወትሮም ትዝብት የማያጣው የፌ/ከፍ/ፍ/ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ዳኛ ሆነው ከመጡ ጀምሮ ሌላ የውዝግብ መንስዔ ሆነዋል። Mahlet Fantahun, human rights activist and bloggerታዳሚውን በጥርጣሬ ይሁን በጥላቻ በማያስታውቅ ሁኔታ የሚገረምሙት እኚህ ዳኛ ከመጡ ወዲህ ችሎቱ ቁጡ እና ለተከሳሽ ቀርቶ ለታዳሚ አስፈሪ ሆኗል። በሚገርም ሁኔታ እሳቸው ገጽታ ላይ የሚነበበው ቁጣ ሌሎቹ ዳኞች ላይ አይነበብም። የችሎቱ ዳኞች ባለፈው ግዜ (ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራውን ጨምሮ የአውሮጳ ኅብረትን ወክለው ችሎቱን የሚታዘቡ) ታዳሚዎችን በማስነሳት “እነማን ናችሁ? ለምንድን ነው የመጣችሁት?” ብለው ጠይቀዋል። ይህ በሕግ አግባብ ተገቢ ይሁን አይሁን የሕግ ባለሙያዎች አስተያየት የሚሰጡበት ነው። ችሎቱን ለሚታደሙት እና በራሳቸው ከደረሰባቸው ኢፍትሐዊነት በመነሳት የሰብኣዊ መብት ጥሰት አቤቱታዎችን አድምጦ ለሕዝብ ለማጋለጥ እና የፍርድ ቤት ውሎዎችን በመዘገብ፣ ችሎቱን አክብረው፣ የሕግ የበላይነት እና የችሎቱ ነጻነት ላይ ያላቸውን ሁሉ ጥርጣሬ ቀብረው፣ ለፍትሕ ስርዓቱ የግልጽነት ድባብ ለማላበስ የለት እንጀራ ሳያምራቸው በብዙ መስዋዕትነት ለሚከፍሉት ወዳጆቼ ምን ያህል አስደንጋጭ እና የማስፈራራት ስሜት እንዳለው አውቃለሁ። በመሆኑም በጣም አዝኛለሁ!
ችሎቱ በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት የተለያየ ሰበብ ተለጥፎባቸው የተከሰሱ ሰዎች የሚበዙበት እንደመሆኑ ብዙ ቅሬታዎች ይቀቡበታል። ለዚህ ደግሞ ችሎቱ ማድረግ የሚችለው ዝቅተኛው ነገር ቅሬታዎቹን ማድመጥ ነው። ከዚህ በፊት የነበሩት ዳኞች ቢያንስ ይህንን ሞክረው ነበር። ነገር ግን እኚህን ዳኛ ጨምሮ አዲሶቹ ከመጡ ጀምሮ ችሎቱ የተከሳሾችን ቅሬታ ማቅረብ እንደጠብ ማጫር ነው የሚመለከተው።

ሕወሓት የቀድሞዋን የአባይ ጸሐዬ ሚስት (ሞንጆሪኖ) ሊቀመንበሩ ሊያደርግ ነው እየተባለ ነው

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት የድርጅቱን ሊቀመንበር አቶ አባይ ወልዱን ከስልጣኑ ማስወገዱን የገለጸው ሕወሓት በ እርሳቸው ቦታ የቀድሞዋን የአባይ ጸሐዬ ሚስት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር (ሞንጆሪኖ)ን ሊቀመንበር ሊያደርግ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች እየገለጹ ነው::
ለመሆኑ ሞንጆሪኖ ማናት? ለምትሉ:
ኤርሚያስ ለገሰ የመለስ ትርፉቶች በሚለው መጽሐፉ ላይ እንዲህ ጽፏት ነበር:: ተጨማሪ መረጃዎች እስኪመጡ መልካም ንባብ::
የሞንጆሪኖ ለቅሶ…
በሰፈሩት ቁና ሆነና ነገሩ የሕወሓት መሰንጠቅ የሞንጆሪኖን ፍጹማዊ አገዛዝ እንዲያከትም አደረገው:: በ እርግጥ የተስፈማሪያምን ያህል ውግዝ ከማርዮስ አልደረሰባትም:: ከአቶ መለስ ተግሳጽ ውጭ::

Sunday, November 26, 2017

“ዘጭ እንቦጭ የኢትዮጵያ ጉዞ” በፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም

No automatic alt text available.
ታደለ መኲሪያ
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ፣ ክኢሳቱ ጋዜጠኛ ማንአላቸው ስማቸው ጋር ስለ መጽሐፉ “ዘጭ እንቦጭ የኢትዮጵያ ጉዞ” ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ተከታትያለሁ፥ ይህን መነሻ በማድረግ አቶ አቻምየለህ ታምሩም “ንግግሩ ታሪክ መዝግቦ ከያዘው እውነት ጋር ይቃረናል“ በሚል ሐሣብ ይዘው ቀርበዋል፥ እኔም መላ መጽሐፉን አላነበብኩትም፥ ሆኖም የፕሮፌስሩን ያለፉ ሥራዎችን በከፊል አንብቤለሁ ፤ ለ52 ዓመታት በኢትዮጵያ ጉዳይ አንኳር አንኳር የሆኑ ሐሣቦችን ሲያቀርቡ ከማስታውሰው ሁለት ለኣብነት ልጥቀስ፣ በእኛ አቆጣጠር፣ 1964 ዓ.ም ነበር፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የወረዳና የአውራጃ ኣስተዳዳሪዎቹን እንዲመርጥ ያቀረቡት ሐሣብ እስከዛሬም እውን አልሆነም፥ በ 1970 ዓ ምህረትም፣ ስድስት ኪሎ ግቢ ነበር፤ አንድ ካድሬ እየተደረደረ መጥቶ ”ፕሮፌስር ብሎ ተጣርቶ ንቃት አለ፣ ውይይት ኣለ፥” ሲላቸው፣“ ለራስህ ንቃ “ብለውት ሄዱ፥ በወቁቱ አካባቢው በፍረሃት ድባብ ተውጧል፣ ፥ በላይ የሚባል የዩኒቨርሲቲ መምህር፣ ከአራት ኪሎ አስተምሮ ሲወጣ ቀበሌዎች ተከታትለው ከሰድስት ኪሎ መግቢያ ደጃፍ ላይ በኢህአፓ ስም ነፃ እርምጃ ወስደውበታል፣ ግቢው ተሸብሯል፣ ካድሬው ከነበሩት ሰዎች ሁሉ መርጦ ወደ ፕሮፌስር መሰፍን ወልደማሪያም መሮጡ አድኑኝ ይመስላል። ግርግሩ ለፕሮፌሰሩ ቁብ አልሰጣቸውም፥ እነዚህ ሁለት ክስተቶች በተለያዩ ሥራዓቶች ሰለነበሩ ስለ ፕሮፌሰሩ የሚሉት ቁምነገሮች አላቸው ። ወደ ተነሣሁበት ሐሣብ ልመልሳችሁ፥

Friday, November 17, 2017

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮች ከሱዳን ነዳጅ ጭኖ፣ በወታደሮች ታጅቦ ይጓዝ በነበረ መኪና ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ገለጹ


ዛሬ ህዳር 7 ቀን 2010 ዓ/ም ከምሽቱ 12 :48 ሲሆን በሰሜን ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ ጓንግ ወንዝ ድልድይ ከመድረሱ በፊት 100 ሚትር ሲቀረው መታጠፊያ ቦታ ላይ በህወሓት ወታደሮች ከፊትና ከኃላ ታጅቦ ሲጓዝ በነበረ ነዳጅ በጫነ ቦቴ መኪና ላይ በተፈፀመ ጥቃት ተሽከርካሪው ሙሉ በሙሉ አስከ ጫነው ነዳጅ ሲወድም በአሽከርካሪው እና በሚያጅቡት ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡

Thursday, November 16, 2017

”እኛ ደህና ነን፣ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም፣ የሚፈጠር ነገርም አይኖርም” ወ/ሮ ውባንቺ ቢሻው የመንግስቱ ኃይለማርያም ባለቤት

Mengistu Haile Mariam
Mengistu Haile Mariam, Ethiopian army officer and head of state (1974–91)
መሳይ መኮንን
የቢሮ ስልኬን አነሳሁ። ወደ ሀራሬ ደወልኩ። ከወዲያ ማዶ ትህትና የተሞላበት የእመቤት፣ የወይዘሮ፣ የእናትነት ግርማ ሞገስ የተላበሰ ረጋ ያለ ድምጽ ተሰማኝ። ይሄን ድምጽ አውቀዋለሁ።

የመቀሌው ሽኩቻና የህወሃት የውድቀት አፋፍ

ክንፉ አሰፋ
TPLF Mekelle meeting
መቀሌ ወሩን ሙሉ ውጥረት ውስጥ ከርማለች። ከተማዋ ላይ እየወረደ ያለው ዶፍ የሚያባራ አይመስልም። የህወሃቶቹ የዘንድሮ መሰባሰብ ለጤና እንዳልነበረ ግልጽ ነው። ሰዎቹ እንደወትሮው “በሃገር ጉዳይ ላይ” ለመዶለት ወደ መቀሌ አልተጓዙም። ቀደም ሲል ጠላታችን ድህነት ነው ሲሉን ነበር። አሁን ግን በለሁለት ተቧድነው አንዱ ሌላውን ጠላት ሲል ይሰማል።

Wednesday, November 15, 2017

የብሄራዊ ደህንነት ዕቅድ ወይስ የህወሀት የስንብት ደብዳቤ?

Azeb Mesfin and TPLF
በመሳይ መኮንን
መቀሌ
ይህን ጽሁፍ በማዘጋጅበት ሰዓት መቀሌና ሀራሬ ሁነኛ የፖለቲካ ክስተት ተፈጥሯል። የመቀሌው ይፋ የወጣ አይደለም። በህወሀት አፍቃሪያን ድረገጾች የተተነፈሰ ወሬ ነው። ወ/ሮ አዜብ መስፍን የመቀሌውን ህንፍሽፍሽ ረግጠው ወጡ የሚለው ከውስጥ አዋቂ ያፈተለከው ዜና በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በትክክል ከሆነ የሀራሬው ዓይነት መፈንቅለ መንግስት ልናይ የምንችልበት እድል ሰፊ ነው። የጄነራል/ፕሮፌሰር ሳሞራ የኑስ ቡድን በመቀሌው ስብሰባ ከተሸነፈ እጁን አጣጥፎ የሚቀመጥ አይሆንም። በአቶ ስብሃት ነጋ የሚመራው የአዲስ አበባው ህወሀት በአንዳች ተአምር መከላከያውን ከሳሞራ የኑስ እጅ ፈልቅቆ ካልወሰደ በቀር የወ/ሮ አዜብ መስፍን ኩርፊያና ረግጦ መውጣት የሚያስከትለው መዘዝ ለህወሀት ፍጻሜው ሊሆን ይችላል።

Sunday, November 12, 2017

የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚያስከትል አዲስ የጸጥታ እና የደህንነት ዕቅድ ይፋ ተደረገ

በሰብዓዊ መብት ላይ ከፍተኛ ወንጀል የሚፈጽም አዲስ ዕቅድ ይፋ ተደረገ፡፡ ዕቅዱ የብሔራዊ እና የክልል ደህንነት ጸጥታ ምክር ቤቶች የጋራ ዕቅድ የሚባል ሲሆን፣ ይህን ለማስፈጸምም ራሱን የቻለ አንድ ግብር ኃይል አለው፡፡ በውጭ ዲፕሎማቶች እና በእርዳታ ሰጪ ሀገራት ጫና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማንሳት ተገዶ የነበረው ገዥው ፓርቲ፣ አሁን ደግሞ ቆዳውን ገልብጦ ሌላ ጸረ ህዝብ አዋጅ ይዞ ብቅ ማለቱም ተነግሯል፡፡
ትላንት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በተደረገው ስበሰባ ላይ የፌደራል እና የከልል የደህንነት አባላት፣ የመከላከያ አዛዦች እና በጸትታ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ የገዥው ቡድን ሰዎች ተገኝተው ነበር፡፡ የመከላከያ ሚኒስትሩ እና የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ በውይይቱ ላይ እንደገለጹት፣ አዲስ የወጣው ዕቅድ ለቀጣይ አንድ ዓመት ይቆያል፡፡ ዕቅዱ በፌደራል እና በክልሎች የተቀናጀ ተሳትፎ እንደሚተገበር የገለጹት አቶ ሲራጅ፣ ዕቅዱም ከፌደራል እስከ ቀበሌ ድረስ እንደሚተገበር ተናግረዋል፡፡

Saturday, November 11, 2017

የመጨረሻው መጀመሪያ( መሳይ መኮንን)


የኢኮኖሚ ቀውስ ህወሀትን በአፍጢሙ ሊደፋው ተቃርቧል። የፖለቲካ ግለቱ ከቤተመንግስቱ አፋፍ ተጠግቷል። የኢኮኖሚና የፖለቲካ ቀውሶች አንድ ላይ ሲከሰቱ ደግሞ አይጣል ነው። አንዳቸው በተናጠል ቢመጡ እንኳን የመንግስት ለውጥ የማምጣት አቅማቸው ከፍተኛ ነው። እያየን ያለነው ደግሞ ሁለቱም ተያይዘውና ተደጋግፈው በፍጥነት እየገሰገሱ መሆናቸው ነው። ሌላም ቀውስ ከአጠገባቸው አለ። ማህበራዊ መናጋት። ይህም ቀውስ ስር ይዞ አድፍጧል። ለብዙዎች ይህ ወቅት የደርግን የፍጻሜ ዘመን ያስታውሳቸዋል። ወደ ኋላ ራቅ ላለው ትውልድ ደግሞ የ66ቱ አብዮት ኮፒ ሆኖባቸዋል።

Friday, November 10, 2017

ተጋለጠች!!! የነ ሚሚ ስብሃቱ ጉዳይ፦ ሙሰኝነት ወይስ ጋዜጠኝነት (የሳዲቅ አህመድ ልዩ ዜና ትንታኔ) | የሰበታው ሰፊ መሬት ተወሰደባት | ሌሎችም ምስጢሮች

ሚሚ ስብሃቱ ሰበታ ዉስጥ በህገወጥ መንገድ የያዘችዉ 35ሺ ካሬ ሜትር ተወሰደባት
የዛሚ ሚዲያና ተባባሪዎቻቸው አሰሪና ሰራተኛን በማገናኘት የሚያደርጉት ዘረፋ
ሰራተኞችን በማስቀጠር ለደህንነት መስሪያ ቤቱ የመሰለላቸው ሁናቴ
ዛሚ ሚዲያዉ ህዝብን ከህዝብ ለማጫረስ ከENN ቲቪ ጋር የመተባበሩ ምስጢር
የህወሃት የፕሮፓጋንዳና የስለላ መረብ ተባባሪዎች ሴራ ሲጋለጥ!
በሳዲቅ አህመድ | ቢቢኤን ሬድዮ
ይከታተሉት

Wednesday, November 8, 2017

እነ አላሙዲ በሳዑዲ “ቂሊንጦ”


ቅዳሜ ማታ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የሳዑዲ ልዑላንና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዲሁም አላሙዲ መሬት ላይ ተኝተው የሚያሳይ ፎቶ ዴይሊ ሜይል በድረገጹ ላይ ለቋል። “ቂሊንጦ” በሚሰኝ ሁኔታ “አገልግሎት” እየተሰጣቸው እንደሆነ ከዴይሊ ሜይል ዘገባ ለመረዳት ይቻላል።

Saturday, November 4, 2017

ህወሀቶች በማያቋርጥ ስብሰባ ውስጥ ናቸው / መሳይ መኮንን/

ህወሀቶች በማያቋርጥ ስብሰባ ውስጥ ናቸው። ልዩነታቸው ከመጥበብ ይልቅ እየሰፋ መጥቷል። የበላይነት ይዟል የተባለው በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ከሳሞራ የኑስ ላይ ወታደሩን የመንጠቅ ሙከራው የተሳካ ባለመሆኑ አንዳቸውም አንጃ ገዝፎ መውጣት ተስኖት በር ዘግተው መጠዛጠዛቸውን ቀጥለዋል። መጨረሻቸው አጓጊ ይመስላል። ቦታ እየቀያየሩ የቀጠሉት ህንፍሽፍሽ ለኢትዮጵያ መፍትሄ ለማምጣት እንዳልሆነ ይታመናል። ከችግር ፈጣሪ መቼም የመፍትሄ ሀሳብ አይፈልቅም። የመለስ ዜናዊ አይነት ብልጣብልጥና ሴረኛ መሀላቸው ባለመኖሩ አንደኛው አንጃ ነጥሮ የመውጣትና ሌላኛው ደፍልቆ ለማንበርከክ ያለው እድል እጅግ ጠባብ ነው። ዝሆኖች ሲጣሉ ጥሩ ነው።

Friday, November 3, 2017

ብሱን እየገሰጠርን ከላችንን እናውልቅ (በነጋ አባተ)

በነጋ አባተ
Professor Berhanu Nega
1) ከዓመት በፊት ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በዋሽንግተን ዲሲ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ንግግሩን በቀጥታ ስርጭት ከተከታተልኩ በኋላ “ብርሃኑ እንደቸርችል እኛ እንደ እንግሊዞች” በሚል ርዕስ ስር አንድ መጣጥፍ ማቅረቤን አስታውሳለሁ። ዘንድሮ በሲያትል ዋሽንግተን በተደረገው ስብሰባ የፕ/ሩን ንግግር ፊት ለፊት ቃል-ተአካል ተገጣጥመን ስለሆነ ብዙ ነገሮችን ለማስተዋል እድል አግኝቻለሁ። እንደ ዜጋ ከዚህ በፊት ደጋግሜ  ባቀረብኳቸው መጣጥፎቼ አንኳር አንኳር ናቸው የምላቸውን ፍሬ ሃሳቦች እየሸረከትኩ ወደ አንባቢዎቼ አምጥቻለሁ። በመክሊቴ ቆሜአለሁ ብዬም አስባለሁ። የቀረቡትን ሃሳቦች ወደ አትሮኑ አስጠግቶ ማድቀቅና ማላም ደግሞ  የፖለቲካውን መዘውር ለመያዝ የሚያታትሩት ወገኖች ድርሻ ይመስለኛል።

Wednesday, November 1, 2017

እነለማ መገርሳ /መሳይ መኮንን/


ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኦህዴድ መንደር የሚታየው ነገር የተለየ ነው። ስለዚህ ጉዳይ ለመግለጽ ትንሽ ወደኋላ መንደርደር ግድ ይላል። በ1982ዓም የኦሮሞን ህዝብ ለመቆጣጠር እነ መለስ ዜናዊ ሰሜን ሸዋ ደራ ላይ ጠፍጥፈው የሰሩት፡ ሳምባና ልቡ በህወሀት ቁመና ልክ የሚተነፍስና የሚመታ ድርጅት መሆኑ የአገላለጽ ልዩነት ካልሆነ በቀር በድርጅቱ የታሪክ ድርሳን ላይ የተጻፈ እውነት ነው።
ሻዕቢያ በምርኮ በያዛቸውና በኋላም ለህወሀት በጉዲፈቻነት በተሰጡት የደርግ ወታደሮች የተመሰረተው ኦህዴድ ባለፉት 26 ዓመታት የህወሀት ቅርንጫፍ ሆኖ ትዕዛዝ ከመቀሌ እየተቀበለ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ተፈናጦ መክረሙም የአደባባይ ሀቅ ነው። ለሩብ ክ/ዘመን የኦሮሞ ህዝብ በኦነግ ስም በጅምላ እስር ቤት ሲጋዝ፡ በየመንደርና ጫካው ሲገደል፡ በየማጎሪያ እስር ቤቱ ፍዳ መከራውን ሲበላ ኦህዴድ በስሙ እየማለ ፡ በግብር እየገደለ ከህወሀት ጎን ተሰልፎ ቆይቷል። ስለዚህ ጉዳይ በርካታ ጸሀፊያን ብዙ ነገሮችን ስለጠቀሱ ከዚህ በላይ መግፋት አያስፈልግም። በአጭሩ ግን ኦህዴድ ፈጣሪውና ጌታው ህወሀት መሆኑን፡ ሲያገለግል የከረመውም ህወሀትን እንደሆነ ማስታወስ ይገባል።