Translate

Tuesday, November 28, 2017

ሕወሓት የቀድሞዋን የአባይ ጸሐዬ ሚስት (ሞንጆሪኖ) ሊቀመንበሩ ሊያደርግ ነው እየተባለ ነው

(ዘ-ሐበሻ) ትናንት የድርጅቱን ሊቀመንበር አቶ አባይ ወልዱን ከስልጣኑ ማስወገዱን የገለጸው ሕወሓት በ እርሳቸው ቦታ የቀድሞዋን የአባይ ጸሐዬ ሚስት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር (ሞንጆሪኖ)ን ሊቀመንበር ሊያደርግ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች እየገለጹ ነው::
ለመሆኑ ሞንጆሪኖ ማናት? ለምትሉ:
ኤርሚያስ ለገሰ የመለስ ትርፉቶች በሚለው መጽሐፉ ላይ እንዲህ ጽፏት ነበር:: ተጨማሪ መረጃዎች እስኪመጡ መልካም ንባብ::
የሞንጆሪኖ ለቅሶ…
በሰፈሩት ቁና ሆነና ነገሩ የሕወሓት መሰንጠቅ የሞንጆሪኖን ፍጹማዊ አገዛዝ እንዲያከትም አደረገው:: በ እርግጥ የተስፈማሪያምን ያህል ውግዝ ከማርዮስ አልደረሰባትም:: ከአቶ መለስ ተግሳጽ ውጭ::

አቶ መለስ እንዲህ አላት:-
“ሞንጆሪኖ አዲስ አበባን የለውጥ ማዕበል ውስጥ አስገብተሽ ታስተካክያለሽ ብለን ነበር የላክንሽ:: አንቺ ግን የድርጅቱን አደራ በልተሽ ከጀርባ ስታደራጂ ከረምሽ:: ኸረ ለመሆኑ ምን ጎድሎብሽ ነው? እነስዬን ስታውቂያቸው ቀርተሽ ነው; አብረሽ ድርጅቱ ላይ ገመድ ልታጠልቂ የነበረው?”
ሞንጆሪኖ ተንሰቅስቃ አለቀሰች:: ስጋ ስው አትን ጠርታ ሁለተኛ እንደማይለመዳት ቃል ገባች:: እግሩ ላይ ተደፍታ ይቅርታ ጠየቀች:: ከነተወልደ ጋር እንዲኤት እንደተመሳጠረች ዘከዘከች:: የህቡዕ እንስቃሴው ከስድስት ወር በፊት በአዲሳባ መጀመሩን አስረዳች:: በአዲስ አበባ ያሉት የዞን ሊቀመናብርት ትልቁ ሥራቸው መሆኑን ገለጸች:: ካድሬዎቹ አባዝተው ስለበተኑት ወረቀት ዘከዘከች:: አመናት::
ፊቱን ወደ እሷ አነሳ… ራራላት::
እንደቀድሞ ባሏ አባይ ጸሐዬ የምህረቱ ተቋዳሽ አደረጋት:: የዘመናዊ ዕውቀት ማነስ የፈጠረው ችግር ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ የቀለም ትምህርት እንድትማር ፈረንጅ ሃገር ሰደዳት:: ትምህርቷን አጠናቃ እንደመጣች ጓዟን ጠቅልላ መቀሌ ገባች:: የትግራይን ካቤኔ ተቀላቀለች:: ለአቶ መለስ ያላትን ታማኝነቷን በተግባር አሳየች:: እሱም ካሳውን በቁሙ ተቀበለ:: በዚህ ሳይወሰን በሕወሓት ሁለተኛ ትውልድ ውስጥ እንድትታቀፍ የመጀመሪያው ምርጫ አደረጋት::
(ሞንጆሪኖ ፈትለወርቅ ሆናለች:: የአዲሷ ፈትለ ወጣትነት የድሮዋ ሞንጆሪኖ ነው:: አፍታም ሳይቆይ የሕወሓት ድርጅታዊ ጉባኤ በመቀሌ ተካሄደ:: ፈትለወርቅ የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነች::
(የመለስ ትርፉቶች መጽሐፍ ገጽ 56 – 57)

No comments:

Post a Comment