Translate

Wednesday, December 21, 2016

ሰበር መረጃ — የላክናቸው ሁሉ አይመለሱም የሰሜን ዕዝ ስምሪት ማዘዣ!


በልኡል አለም 
በሕወሃት ኮማንድ ፖስት ቁጥጥር ስር የወደቀው የሰሜኑ እዝ ወደ ሰሜን እና ደቡብ ጎንደር የላካቸው በወታደራዊ ደህንነት እና በወታደራዊ ምህንድስና የተሰማሩ አባላቶቹ መገደላቸውንና መሰወራቸውን ለኮማንድ ፓስቱ በላከው ሪፖርት ለማወቅ ተችሎአል። በሪፓርቱ መሰረት፣

Monday, December 12, 2016

ወያኔ የመከላከያ ሰራዊቱ ወደ አርበኞች ግንቦት 7 እየተቀላቀሉ መሆኑን አመነ።

(ዘርይሁን ሹመቴ)
የወያኔን አገዛዝ በመክዳት ወደ ትጥቅ ትግሉ እየተቀላቀሉ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። በቅርቡ በሰሜን ጎንደር ለነጻነት እየተዋደቁ ያሉትን ጀግኖች የአማራ ተወላጆችን ለመጨረስ ወያኔ ከላካቸው ወታደሮች አብዛኞቹ ወደ አርበኞች ግንቦት ግንባር መቀላቀላቸው ይታወቃል።በቆራጥነት ቤተሰባቸውን ጥለው በየጫካው የሽምቅ ውጊያ በማድረግ ወያኔን እያርበደበዱ ያሉትን የአማራ ታጋዮችን ትጥቅ ለማስፈታት የሚልካቸው ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው ወያኔን እራሱን ለመውጋት ከህዝቡ ጎን ለመቆም ግንባሩን ተቀላቅለዋል።

Thursday, December 8, 2016

አርበኞች ግንቦት 7 የወያኔን ሰራዊት በሁመራ አዲስ አለም ዲንሻ አብደራፊ በካበታና በሰሜን ጎንደር አርበደበደ።

አባይ ሚዲያ ዜና
የአርበኞች ግንቦት የፖለቲካ ጉዳዮች ዋና ሃላፊና የግንባሩ ቃለ አቀባይ የሆኑት አቶ መንግስቱ ወልደስላሴ በወያኔ አገዛዝ ጋር ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ እንደሆነ ተናገሩ። እንደ ቃለ አቀባዩ ገለጻ የአርበኞች ግንቦት ወታደሮች በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በጥልቀት ሰርገው ገብተዋል። የፓለቲካ ጉዳዮች ዋና ሃላፊውም በማከልም እነዚህ ሰርገው የገቡት ወታደሮች ከወያኔ ጦር ጋር የሚያደርጉትን ውጊያ አጠናክረው እንደቀጠሉ ይናገራሉ።