Translate

Tuesday, December 29, 2015

ዮናታን ረጋሳ ታሰረ


Yonatan Regassa of Blue partyየሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረውና ብዙ ጓደኞቹ እንደሚስማሙበት እጅግ ታታሪ የመብት ተሟጋች እና ፖለቲከኛ ዮናታን ረጋሳ በወያኔ ደህንነቶች ታፍኖ በታዋቂው የማእከላዊ እስር ቤት እንደሚገኝ ታውቋል። ቀደም ሲል ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችም በተመሳሳይ መታፈናቸው ይታወሳል።
ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ አዲስ አበባን በማስፋት ስም በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የአዲስ አበባ አጎራባች ወረዳዎችን መሬት ለመቀራመት ሲሰናዳ በተቀሰቀሰበት ከፍተኛ ህዝባዊ አመጽ በመደናገጥ ከመቶ በላይ ንጹሃን ዜጎችን ሲገድል ከአምስት ሺህ በላይ ዜጎችን ደግሞ በየማጎሪያ ካምፖቹ በማሰር ላይ ይገኛል።

Saturday, December 26, 2015

የ11ኛው ሰዓት ጥሪ እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ይመለከታል!

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracyየንቅናቄያችን መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባደረጉት የትግል ጥሪበ11ኛው ሰዓት ላይ እንደምንገኝ ገልጸዋል ። የ 11ኛው ሰዓት መልዕክት፣ አንደኛ፣ ወደ 12ኛው ሰዓት ወይም ወደ ፍጻሜው እየተቃረብን መሆኑን የሚነገረን ነው። የ11ኛው ሰዓት የትግል ጥሪ የአንድን የትግል ምዕራፍ ለመዝጋት እና አዲስ የትግል ምዕራፍ ለመጀመር የመጨረሻ የሞት ሽረት ትግል የምናደርግበት ጊዜ ላይ መድረሳችንን የሚገልጽ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ጥሪው ከትግሉ ፍጻሜ በሁዋላ ስለሚፈጠረው አዲስ ስርዓት ከአሁኑ ማሰብ መጀመር እንዳለብን የሚያነቃን ደወል ነው። 11ኛው ሰዓት ላይ ቆመን ከ12ኛው ሰዓት በሁዋላ ስለሚፈጠረው ነገር መጨነቅ ካልቻልንና በጊዜ ቤታችንን ካላሰናዳን ፣ ከትግሉ ፍጻሜ በሁዋላ ሊገጥሙን የሚችሉትን ተግዳሮቶች በጊዜና ብቃት ባለው መልኩ ለመፍታት መቸገራችን አይቀርም ። አንድ በእድሜ የገፋ ሰው 11ኛው ሰዓት ላይ መሆኑን ሲያውቅ ከህይወቱ ፍጻሜ በሁዋላ ስለሚኖረው ህይወት ማሰላሰሉ ተፈጥሯዊ ነው። የ11ኛው ሰዓት ጥሪም የአንድን አገዛዝ እርጅናና ፍጻሜ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን፣ በቦታው የሚወለደውን አዲስ ስርዓት ምንነትም የሚያሳይ ነው።

Wednesday, December 23, 2015

በነ ኦነግና ግንቦት ሰባት አታሳቡ ይላል ሪፖርተር ጋዜጣ – የሚሊዮኖች ድምጽ


ገዢው ፓርቲ ሕወሃት/ኢሕአዴግ በኦሮሚያና በጎንደር ለተከሰተው ቀዉስ ጣቶቹን በዉጭ ያሉ አመጽ ቀስቃሽ ኃይሎች በሚላቸው ላይ ማድረጉ ይታወሳል። አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ የመንግስት ቃል አቀባይም አፋቸዉን ሞልተው ተቃዉሞ ያሰሙትን በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን “ጋኔኖች” ፣ በዉጭ ያሉ “ጋኔኖችን” የሚያንቀሳቀሱ ያሉዋቸዉን ደግሞ “ጠንቁዋዮች” የሚል ከአንድ ትልቅ አገር የመንግስት ቃላቀባይ በጭራሽ የማይጠበቅ ርካሽ ንግግር መናገራቸው ይታወሳል።

Tuesday, December 22, 2015

በሰሜን በጌምድር (ጎንደር) ወልቃይት ፀገዴ፣ ፀለምት በአማራው ላይ ተስፋፊው ተሓህት/ህወሓት የፈጸመው የዘር ማጽዳት ወንጄል (ገብረመድህን አርአያ)

በገብረመድህን አርአያ

ይህ ታሪካዊ መረጃ በተቀነባበረ መልኩ የሚጀምረው ገና ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተሓህት) ሲፈጠር ጀምሮ አስቀድሞ ለማጥፋት ያነጣጠረው በአማራው ህዝብ ላይ እንደሆነ በማስገንዘብ ነው።Ato Gebremedhin Araya is one of former Tigray People Liberation Front (TPLF) leaders
ከዚህ በመነሳት የተሓህት ፕሮግራም ገና ከ1967 ጀምሮ የረቀቀው በዲማ ኮንፈረንስ በየካቲት ወር 1968 ከ150 ያነሱ የተሓህት ታጋዮችን በማሰባሰብ ሕጋዊ ሆነ ተብሎ ቢነገርም፣ ሁሉም ታጋዮች ግን አልተቀበሉትም። በመጥፎ መልኩ የተዘጋጀውና አማራውን በማውገዝና ጠላት ብሎ የፈረጀ ነው።

Sunday, December 20, 2015

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባቀረቡት ጥሪ ኢትዮጵያውያን ቅድሚያ ሰጥተው ሊተገበራቸው የሚገቡ ስድስት ተግራት

አርበኞች ግንቦት 7 በሚከተሉት ስድስት ነጥቦች ዙርያ የተቀናጀ ትግል እንዲካሄድ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የትግል ጥሪ ያደርጋል።

Thursday, December 17, 2015

ትግላችንን ተጠናክሮ በአንድነት ይቀጥል! (አርበኞች ግንቦት7)


የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱ በያቅጣጫው መነሳቱ የሚያኮራ ነው። ባለፉት 3 ዓመታት ብቻ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ያደረጉትን የመብት ትግል ጨምሮ በደቡብ፣ አማራ፣ አፋር፣ ጋምቤላና በሌሎችም አካባቢዎች በርካታ የነጻነት ትግሎች ተካሂደዋል። አሁን በኦሮምያ እና በአማራ በተለይም በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉት የነጻነት ትግሎች የአጠቃላዩ የነጻነት ትግል አካሎች ናቸው። በእነዚህ የነጻነት ትግሎች ገዢው ፓርቲ ከህዝብ ጋር ለምንጊዜውም መለያየቱን ለማየት ችለናል።

ከፍተኛ የወያኔ ባለስልጣናት በቋራ ህዝብ ውርደት ተከናንበው ተመለሱ

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ

አባይ ፀሐዬ፣ ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች በዛሬው ዕለት ወደ ቋራ አምርተው ህዝቡን ለመሰብሰብ ሲሞክሩ ህዝቡ በአንድነት አምፆ ከእነሱ ጋር ፈፅሞ መነጋገር እንደማይፈልግ ገልፆ የውርደትና ሀፍረት ጉንጉን አበባ አንገት አንገታቸው ላይ አስሮ መልሷቸዋል፡፡tplf-in-gondar
የጀግናው አፄ ቴዎድሮስ አጥንት ፍላጭ የሆነው ጀግናው የቋራ ህዝብ አሳፍሮ የመለሳቸው እነ አባይ ፀሐዬ በጎንደር ከተማ ሲኒማ አዳራሽ የፀጥታ ኃይሎችን፣ የዞኑን አመራሮች፣ ወሬ ለማዳመጥና እግር ጥሎት የገባውን ህዝብ ለማወያየት ሞክረው ነበር፡፡ ባለስልጣናቱ ፀረ ሰላም ኃይሎችና አሸባሪዎች ያሏቸውን ጠብመንጃ ያነሱ የነፃነት ድርጅቶች ህዝቡ እንዳይደግፍ ሲያሳስቡ ህዝቡ “ቢመጣ ቢመጣ ከእናንተ የባሰ አይመጣ…” ሲል ምላሽ ሰጥቷቸዋል፡፡ በጎንደር ከተማ የሚኖሩ የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በስማቸው እየነገደ ከሌሎች ቋንቋዎች ተናጋሪዎች ጋር እንዳቆራረጣቸው በመግለፅ ህወሓትን ከሰውታል፡፡ ከዚህ በኋላ የህወሓት ደጋፊም እንዳልሆኑ የአቋም ለውጣቸውን በይፋ አስታውቀዋል፡፡
የጎንደር ከተማ የፀጥታ ኃይሎች ደግሞ በበኩላቸው ከእንግዲህ ወዲህ ወደ ወጡበት ህዝብ አፈሙዝ አዙረው ምላጭ መስበር እንደማይሹና አገዛዙ ወደ ወገናቸው ተኩሱ የሚላቸው ከሆነ አስቀድሞ የጦር መሳሪያቸውን እንዲረከባቸው ጠይቀዋል፡፡

Monday, December 14, 2015

“ኤርትራ የትግራይ ናት”

“ትልቅ ነበርን ትልቅ እንሆናለን” - ህወሃት

eri-tigray

ኤርትራ የትግራይ አካል ናት የሚል አስተምህሮና የፖለቲካ ዝግጁነት ቅስቀሳ መጀመሩ ተሰማ። የጎልጉል ታማኝ ምንጮች ኤርትራ የትግራይ አካል ስለነበረች እንደገና መልሶ በመቀላቀል ታላቋን የአክሱም መንግስት ለመመሥረት የተያዘው አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ ይቻል ዘንድ አስፈላጊው ሥራ እየተሰራ መሆኑንንም ጠቁመዋል። ለኢትዮጵያ እንደሆነ የሚጠቀሰው “ትልቅ ነበርን ትልቅ እንሆናለን” የሚለው የህወሃት መፈክር ኤርትራን ከትግራይ በመቀላቀል የአክሱምን “ዳግም ልደት” (ህዳሴ) ለመተግበር የታቀደ ነው ተብሏል፡፡

ጨለማው በረታ!! የትግራይ ተገንጣዮች ወስኑ!!

ጠብ መንጃ መፍትሔ አይሆንም!

eth pic 1


ወተት ሊገዛ የወጣ ልጅ በድንገት መሃል ግንባሩን በአልሞ ተኳሾች ይመታና ይወድቃል። ግማሹ ይሸሻል። አላስችል ያለው ርዳታ ለመስጠት ይሞክራል። በመካከል እናት የልጇን መውደቅ ትሰማለች። ጨርቋን ጥላ እያለቀሰች አስፋልት መሃል ተዘርሮ የወደቀው ልጇ ላይ ተጠመጠመች። በደም ተጨማልቃ እያነባች ህይወቱን ለመመለስ ፈለገች። ልጅ መሃል ግንባሩን ተወግቶ ነበርና ሕይወቱ አልፋለች። እናት አበደች። “እኔን፣ እኔ ልደፋ … …” አነባች። አስከሬኑን ለመውሰድ ሚኒሊክ ሆስፒታል ተሰለፈች።

Sunday, December 13, 2015

አርበኞች ግንቦት 7 በህወሓት ሰራዊት ላይ ጥቃት በመሰንዘር ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱን ገለጸ

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)

ጀግናው የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በህወሓት አገዛዝ የጦር ኃይል ላይ ጥቃት በመሰንዘር ከፍተኛ ድልን ተቀዳጀ!!

Patriotic Ginbot7 attacked TPLF troops
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ተደጋጋሚ የሽምቅ ውጊያዎችን በማድረግ የህወሓትን መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ጦር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የህዝብ አለኝታነቱን እያስመሰከረ ይገኛል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 የመጀመሪያ ምክር ቤት ስብሰባ መግለጫ

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከህዳር 26 ቀን 2008 ዓ.ም እስከ ህዳር 30 ቀን 2008 ዓም ድረስ ሰራዊቱ በሚገኝበት የትግል ቦታ የመጀመሪያውን የምክር ቤት ስብሰባ አድርጎ በስኬት አጠናቋል::

Patriotic Ginbot7 Conference
ይህ ስብሰባ የቀድሞዎቹ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባርና ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ተዋህደው አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከተሰኘ ወዲህ የተደረገ የመጀመሪያው የምክር ቤት ስብሰባ ነው::

Wednesday, December 9, 2015

ለወያኔ ድርጊት፣ ምን ስም እናውጣለት (ይገረም ዓለሙ)

ወገንን ጨፍጫፊ ቆዳው የነጣ ነው
በአበሻ የሚጨክን ፈረንጅ ብቻ ነው፤
እያለ የሚያስብ የዋህ ፍጡር ማነው
ጨፈጫፊ ከሆነ አበሻም ጣሊያን ነው
እንቶኔም በተግባር ሲኞር እንቶኔ ነው፤
Police brutality in Ethiopia
በየግዜው እየከፋ የሄደውን የወያኔ አረመኔነትና የሀገራችንን ጉዞ ወዴትነት ሳስብ ትውስ ያለችኝን ይህችን ስንኝ ወደ ማስታወሻየ ገልብጬ ያኖርኳት በ1980ዎቹ መጨረሻ ግድም ለንባብ ይበቁ ከነበሩት መጽሄቶች ከአንዱ ነው፡፡ ወያኔ ዴሞክራት መስሎ ለመታየት በሞከረበትና ትክክለኛ ማንነቱ ገሀድ ወጥቶ ብዕርን ከጠመንጃ አስበልጦ መፍራት ባልጀመረበት በዛ ወቅት እንዲህ የጻፉት ሰው ዛሬ በህይወት ካሉ ምን ሊሉ እንደሚችሉ መገመት ይቸግራል፡፡

ዐይናችን ተከፍቷል ህሊናችን ነቅቷል (ከአንተነህ መርዕድ)

Protests in different Ethiopian cities and universities
የመጀመርያው የኬንያ ፕሬዝደንትና የነፃነት ታጋይ ጆሞ ኬንያታ ብዙ ጊዜ የሚጠቀስላቸው፣ ስለ ቅኝ ገዥዎች የተናገሩት እውነት ይህን ይመስል ነበር። “ሚሲዮኖች ወደ አፍሪካ ሲመጡ እነሱ መጽሃፍ ቅዱስ፤ እኛ ደግሞ መሬት ነበረን።

Tuesday, December 8, 2015

ESAT Latest News update Protest Dec 08 2015

የአምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ ግባት መሬት የመጨረሻው መጀመሪያ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በተካሄደባችው አካባቢዎች ሕዝብ የራሱን አስተዳደር እየመደበ ነው!!
ይህንን የሕዝብ ትግል በየትኛውም መልኩ ማገዝ የውዴታ ግዴታ ነው!!




“ትግራይ ወረዳ ውስጥ ያለ የመንግሥት አሰራር በኦሮሚያ ውስጥ … ይገኛል”

“ወደ እውነተኛው ፌደራሊዝም እንመለስ”

addis_oromia_sp_zone
* “የአዲስ አበባ መሬት በማለቁ ወደ ኦሮሚያ መሬት እጃቸውን መዘርጋት ጀመሩ”
* “ማስተር ፕላኑ መሰሪ ነው” በቀለ ገርባ
የአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላንን በተመለከተ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ያለውን ዝርዝር አቋም በተመለከተ የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባን አዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ በፅ/ቤታቸው ተገኝቶ አነጋግሯቸዋል፡፡

በገዛ አፈ-ሙዙ መቃብሩን የሚቆፍር የሽንፈትን ጽዋ ይጎነጫል! (ሰማያዊ ፓርቲ)

ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማንና ዙሪያን ለማከለል ከወጣው የማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ፤ ገቢራዊነትና ሃሳቡን የተቃወሙ የኦሮሞ ተወላጆች እና የዕቅዱ ተቃዋሚዎች፣ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሌጆች እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዲሁም የየከተማዎቹ ነዋሪዎች ላይ የኃይል እርምጃ እየተወሰደ እንዳለ የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡Semayawi party to welcome Andinet members
ዜጎች እያሰሙት ያለውን ተቃውሞና የሃሳብ ልዩነት በኃይልና በጠብ-መንጃ ለመመለስ የተደረገውም አግባብነትና ኃላፊነት የጎደለው ጭፍን ተግባር እንደሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት በጽኑ ያምናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ፣ መቶ-በመቶ ሁሉንም ተቋማትና መንግሥታዊ መዋቅሮች በጠቅላላ እንደልቡ የሚያዘውና ያሻውን የሚፈጽመው የኢህአዲግ መራሹ ኃይል፣ ልማትንና እድገትን በኃይልና በጉልበት እፈጽማለሁ እንዲሁም አስፈጽማለሁ ብሎ መነሳቱም መሠረታዊ የእብሪት ተግባር መሆኑም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሳምሮ ያውቀዋል፡፡

Sunday, December 6, 2015

የሰማያዊ‬ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ወጣት እንደግ አዳነ በረሃ ወርዶ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቀለ


Semayawi party member Endeg Adane joins patriotic Ginbot 7
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) — የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ድረጅት ጉዳይ ኃላፊና የሟቹ ሳሙኤል አወቀ የቅርብ ጓደኛ እንዲሁም የትግል አጋር የነበረው ወጣት እንደግ አዳነ በ2007 ዓ.ም በተካሄደው የይስሙላህ ምርጫ ሞጣ ወረዳ ላይ ለተወካዮች ምክር ቤት የተወዳደረ ሲሆን አሁን ደግሞ የህወሓትን አገዛዝ ፈፅሞ በሰላማዊ ትግል መለወጥ እንደማይቻል አምኖ ጫካ ገብቶ ብረት አንስቷል፡፡ 

Saturday, December 5, 2015

ልጆች በጥይት አይቀጡም፣ የትኛው መንግስት ዛሬ ተማሪዎችን በጥይት ይደበድባል?

ቢላል አበጋዝ – ዋሽግተን ዲሲ

ዛሬ የዓለም መሪዎች በፓሪ ፈረንሳይ ስለ ዓለማችን ያየር ንብረት ችግሮች እየመከሩ ነው።ችግሩ ደግሞ ቀድሞ ሰለባ ያደረገው ደሃ አገሮችን መሆኑ ግልጽ ነው።ኢትዮጵያም አንድዋ ናት።ከኢትዮጵያ ህዝብ አስራ አምስት ሚሊዮን ለራብ መጋለጡ መደበቅ የማይቻል እውነት ነው።ወያኔ ሃላፊነት ያለው መንግስት ቢሆን እዲህ ጊዜ የማይሰጥ ችግር ላይ ያተኩር ነበር።የአስራ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ለራብ መጋለጡን የአውሮፓ ህብረት ጉዳዬ ብሎ ሲመክርበት ህወሃት ይህን ችግር ከፖለቲካ ተቃውሞ መለየት ተስኖት ከውይይቱ እንኳን ለመሳተፍ አልመረጠም።ካአየር ንብረት ችግሩ እጅግ የከፋው የአስተዳደር ጉድለቱ የሚፈጸመው ግፍ ነው በኢትዮጵያችን።ኢትዮጵያ መንግስትዋ ሽብርተኛ ያየር ንብረት ችግሯ በጣም ፈታኝ የሆነበት ዘመን ዛሬ ነው።ያየር ንብረት ችግር ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ልጆችዋን እየገበረች ነው።ልጆች በጥይት ይቀጣሉ።የህወሃት ግፍ ይህ ነው።
TPLF killing Oromo students
ህወሃት የዛሬውን አይበለውና የትግራይ ህዝብን አታግልለታለሁ ሲል “ሃረሽታይ ሸቃላይ” ወይም አርሶአደር ላብአደር ይል ነበር። ለህዝብ እንደቆመ ሁሉ።ዛሬ “መሬት ላራሹ”ን ተረተረት አድርጎ የኢትዮጵያን አርሶ አደር መሬት ንብረቱን ቀምቶ እያራቆተው ይገኛል። ከአርሶ አደሩ አብራክ የወጡትን ልጆቹን ለአርሶ አደሩ በደል ቢነሱ በጥይት ይደበድባቸዋል። የዓለም ዜና ይህን ባያተኩርበትም ዛሬ የኢትዮጵያ ሁኔታ በከፋ መጠን እየተናጋ መሆኑን ማንም ሊክድው አይችልም።በዓለም ተበትነን ያለነው ዜጎች በየሰዓቱ የምንከታተለው ይህንኑ ነው።

Thursday, December 3, 2015

አርበኞች ግንቦት 7 – የወገኖቻችን ስቃይ፣ ችግርና ብሶት በያለንበት ይሰማን፤ ለመፍትሔውም በጋራ እንነሳ!

አርበኞች ግንቦት 7 – የወገኖቻችን ስቃይ፣ ችግርና ብሶት በያለንበት ይሰማን፤ ለመፍትሔውም በጋራ እንነሳ!

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracyበአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ሰበብ በከተማዋ ዙርያ ያሉ ወገኖቻችንን ማፈናቀል በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተፈፀመ ጥቃት ነው። በማስተር ፕላኑ ሰበብ የሚፈናቀሉ ገበሬዎች የሁላችን ወላጆች፣ ወንድሞችና እህቶች ናቸው። በማስተር ፕላኑ ሰበብ የምንፈናቀለው ሁላችንም ነን። ይህን መሰሪ ፕላን በመቃወም ላይ ያሉት የኦሮሞ ተወላጅ ወገኖቻችን ትግል ፍትሀዊ በመሆኑ አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ከጎናቸው ይቆማል።
በዚሁ ወቅት በጎንደር ሌላ አሳዛኝ ጉዳይ ተከስቷል። ህወሓት ከሶስት ሺህ በላይ ዜጎቻችንን ያጎረበት እስር ቤት በእሳት ሲጋይ ዜጎች ተቆልፎባቸው እንዲነዱ ተደርጓል። ከእሳቱ በእድል ያመለጡት በጥይት ታድነዋል። ኢትዮጵያዊያን እንዲህ ዓይነቱን ጭካኔ የሚያውቁት በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ጊዜ ነው። ይህን ጥቃት በመቃወም ላይ ያሉ የአማራ ተወላጅ ወገኖቻችን ትግል ፍትሀዊ በመሆኑ አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ከጎናቸው ይቆማል።

Wednesday, December 2, 2015

አንድ:- ከመጠምጠም መማር ይቅደም

(ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

priest 11
በፌስቡክ የምንሰባሰበው ለመወያየት፣ አንዱ ከሌላው እንዲማር፣ መረጃዎችን በነጻነት እንድንለዋወጥ፣ ይህንን ሁሉ በማድረግ ራሳችንን ለማሻሻል፣ የእኛ መሻሻል እየተራባና እየተባዛ የአገርና የሕዝብ መሻሻል እንዲሆን፣ ከተቻለንም ከአገራችንና ከሕዝባችን አልፈን የምንታይ የዓለም አካል እንድንሆን መስሎኝ ነበር፡፡ ሳየው በዚያ መንገድ ላይ ያለንና ፌስቡክን ለበጎ ዓላማ እየተጠቀምንበት ያለን አይመስለኝም፤ ስለዚህ ወይ መታረም፣ አለዚያም በፌስቡክ ጊዜ ማጥፋቱን መተው ምርጫ ሊሆንብን ነው፡፡

Tuesday, December 1, 2015

አማራ እንደምን አደርክ (ኄኖክ የሺጥላ – ግጥም)


Henoke Yeshitila's pottery
ኄኖክ የሺጥላ
ኄኖክ የሺጥላ
ስለ ስቃይህ ባወራ አማራ ይሉኛል ብዬ
የልቤን የልቦና ቃል ፣ በይሉኝታ ጨርቅ አፍኘ
ታሪክ ተማርኩ ብዬ
አንድነት እንዳልንድ ብዬ
የፍቅር የመቻቻሉ ፣ ባህል ይፈርሳል ብዬ
ትግሬ እንዳይቀየም ፣ እንዳይከፋው የኔ ነገር
አማራ ይሙት አልኩኝ ፣ ምስኪን ዘመዴ ይቀበር !

Monday, November 30, 2015

በምህራብ ኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው


በምዕራብ ወለጋ በመንዲ እና ጉሊሶ “መንግሥት አድማ በታኞችንና የአግዓዚ ጦርን አሠማርቶ ብዙ ተማሪዎችንና የከተማዪቱን ነዋሪዎች በቁጥጥር ሥር አውሏል” ሲል አንድ ስሙ እንዳይገለፅ የጠየቀ ነዋሪ ከቪኦኤ ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ገልጿል።
“በተጨማሪም ከላይ በተጠቀሰው ዞን ውስጥ ጉሊሶ በተባለ ከተማም እንዲሁ ዛሬው ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ እንደተሰባሰቡ ፖሊስ በአድማ በታኝ ጢስ ሠልፉን በትኗል” ስትል አንዲት ተማሪ ገልፃለች።

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቁስለኛ ወታደሮች ዳሽ-6 በተባለ አውሮፕላንና ኤም.አይ-17 ሄሊኮፕተር ከሶማሊያ አየተጫኑ ድሬ ደዋ ላይ በመራገፍ ላይ ናቸው፡፡

Patriotic Ginbot 7's photo.
ራሱን በመንግስትነት ስም የሚጠራው የማፍያው ቡድን ህወሓት የምዕራባዊያንን ቁሳዊና ፖለቲካዊ ድጋፍ በማግኘት ስልጣኑን ለማደላደል ሲል ብቻ ከ10 ዓመታት በፊት ማለትም ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ የድሃው የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ የሆኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ያለማቋረጥ ወደ ሶማሊያ በረሃማ ምድር እያስገባ እጅግ በጣም አሰቃቂ ለሆነ እልቂት እየዳረጋቸው ይገኛል፡፡ 

ሳዑዲ ዓረቢያና ዩናይትድ ዓረብ ኤምሬትስ በየመን ላይ እያደረጉት ላለው ጦርነት የአሰብ ወደብ ለ30 ዓመታት ተከራዩት

የተባበሩት መንግሥታት የቁጥጥር ቡድን ያወጣቸው መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ፣ ሳዑዲ ዓረቢያና ዩናይትድ ዓረብኤምሬትስ በየመን ላይ እያደረጉት ላለውጦርነት የአሰብ ወደብ 30 ዓመታት እንደተከራዩት፣ የኤርትራ ወታደሮች በየመኑ ውግያ ላይ እየተሳተፉ መሆናቸውንና የጦር መሣሪያም ወደ ኤርትራ እየገባመሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡

Thursday, November 26, 2015

አሜሪካ፡ የሰብአዊያን የመጨረሻ ታላቅ ተስፋ ከኢ-ሰብያዉያን ኪሳራ ማዳን

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ከናዚ ጀርመን ሰው ልጅ እልቂት የተረፉት እና የኖቤል ተሸላሚ የነበሩት ኤሊ ዊሰል በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ኢፍትሐዊነትን ለመከላከል የማንችልበት እና አቅመቢስ የምንሆንበት ጊዜ ሊኖር ይችላል፣ ሆኖም ግን ኢፍትሐዊነትን የምንቃወምበት ጊዜ በምንም ዓይነት ሁኔታ እና በምንም ዓይነት መንገድ በፍጹም ማጣት የለብንም፡፡“America: Saving the Last Great Hope of Humanity
እኔ ደግሞ እንዲህ የሚል አባባል እጨምርበታለሁ፣ ”በቢሮ ተወሽቀው የሚገኙትን የፖለቲካ አስመሳይ እብዶችን እና ምንም ዓይነት ሀሳብ ማመንጨት የማይችሉ እርባና ቢስ የሀሳብ ድሁር ፖለቲከኞችን የምንቃወምበት ጊዜ በምንም ዓይነት መልከኩ እና በምንም ዓይነት መንገድ በፍጹም ማጣት የለብንም፡፡“
የሬፐብሊካን ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶናልድ ትሩምፕ ባለፈው ሳምንት “በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪክ የሚገኙ የሙስሊሙን ማህበረሰብ የመረጃ ቁጥጥርን ፍጹም በሆነ መልኩ አካትቶ የሚይዝ የመረጃ ቋት ስርዓት በመንደፍ ተግባራዊ አደርጋለሁ“  ብሎ ነበር፡፡

Wednesday, November 25, 2015

“ረሃቡና ኢህአዴጋዊ እውነታዎች!” (ኤርሚያስ ለገሰ)

ኤርሚያስ ለገሰ

ህወሃት መራሹ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ረሃብ በተከሰተ ቁጥር የረሃቡን ዋነኛ ምንጭ “የአየር ንብረት መዛባት” በሚል ውጫዊ ምክንያት ማላከኩ የተለመደ ሆኗል። ለአብነት ያህል የዛሬ ዘጠኝ አመት በኢትዮጵያ ረሃብ በተነሳ ወቅት “የሰሞኑ የረሃብ ፖለቲካ” በሚል ረዕስ የውስጥ ድርጀት ሰነድ ተዘጋጅቶ ነበር ደራሲው ጓድ መለስ ዜናዊ ነበሩ። በማስከተልም የፓርቲው ከፍተኛ ካድሬዎች እና የመንግስት ባለስልጣናት ውይይት እንዲያደርጉበት ተደረገ። በዚህ ሰነድ ገፅ 6 ላይ የረሃቡን ዋነኛ ምንጭ እንደሚከተለው ይገልጻል።Ermias Legesse of ESAT
“ረሃቡ ከምን እንደሚመነጭ በትክክል ማስቀመጥ መፍትሄውን ለማስቀመጥ ወሳኝ ነው። የረሃቡ ቀጥተኛ ምንጭ ከአየር ንብረት መዛባት ጋር ተያይዞ የተከሰተው ድርቅ ነው። የአየር ንብረቱ መዛባትና ድርቁ እኛ ያልፈጠርነው ልናስተካክለው የማንችለው ነባራዊ ሃቅ ነው። በዚህ ነባራዊ ሁኔታ ማዕቀፍ ድርቁን ተቋቁመን ረሃቡን ለማስወገድ ያስቀመጥነው ስትራቴጂ ተዓምር ሰሪነቱ በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በተግባር ተረጋግጧል። የረሃቡ ዋነና ምንጭም የአየር ንብረት መዛባትና ድርቅ ነባራዊ ሁኔታን መቋቋም ረሃብን ለማጥፋት የቀየስነው ስትራቴጂ በሚፈለገው ፍጥነት በሁሉም አካባቢዎችን ስላልተፈጸመ ነው” ይላል።

Tuesday, November 24, 2015

“ገበሬው ነፃነት ካላገኘ ችጋር ሁልጊዜ በኢትዮጵያ ይኖራል” ፕሮፌሰር መስፍን

farmer
* “ችጋር የሰው ልጅ እንደ ማገዶ እንጨት ተለብልቦ የሚያልቅበት የውርደት ሞት ነው”
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (Institute of Development Research) ሥር ከ1967 ዓ.ም. ጀምሮ ለ10 ዓመታት ያህል በ102 የኢትዮጵያ አውራጃዎች ላይ ምርምር አድርገው ስለ ድርቅ በእርሳቸው አጠራር (ስለ ችጋር) (Rural vulnerability to famine in Ethiopia 1958-1977) የሚል መጽሐፍ ጽፈዋል። የእንቢልታ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በዛሬው እትማችን ለበርካታ ዓመታት በድርቅ ጉዳይ ያካሄዱትን የምርምር ሥራ መሠረት አድርገን በወቅታዊው የአገሪቱ የድርቅ ሁኔታ ላይ ከጽዮን ግርማ ጋር ቆይታ አድርገዋል። (ዓርብ መጋቢት 26 ቀን 2000 ዓ.ም)

Sunday, November 22, 2015

“የየጁ ደብተራ…” | በኤርሚያስ ለገሰ


ከቅርብ አመታት ወዲህ በአከባበር እየተለወጠ የመጣውን የህውሀት እና ልጆቹን ልደት አጨንቁሮ ለተመለከተ ብዙ ነገሮችን መናገር ይችላል። በልሙጡ ለሚያይ ሰው የብአዴን፣ ኦህዴድ እና ደኢህዴግ የልደት በአላት ” መወድሰ ህወሀት” እየሆኑ መሔዳቸውን በቀላሉ መታዘብ ይችላል። ህውሀቶች የየካቲት 11 እና እሱን ተከትሎ የነበሩት ሳምንታት አልበቃቸው ብሎ ህዳር 11 ( የኦህዴድ እና የሐይለማርያምን ልደት ቀን ረሳሁት) በቤቢ ሻወርነት እየተጠቀሙበት ነው። ርግጥ ነው ህውሀቶች ወገባቸውን ይዘው ” እኛ በልጆቻችን ውስጥ አድረን ቡራኬያችንን ብንወስድ እናንተን ለምን አሳከካችሁ?” እንደሚሉን ይገባኛል። ባያሳክከን ጥሩ ነበር። ፈር የሳተው ቡራኬ በኢትዬጲያ ህዝብ ላይ እያሳረፈ ያለው ጫና በአይናችን ላይ እየሔደ አላሳከከንም ማለት እንደ ብአዴን አባላት ቧልት ስለሚሆንብን ነው። እናም ቢያንስ የብአዴን አባላትን የውስጥ ጩኸት እኛ ብንጮኸው ምስጋናቸው ዘግይቶም ይደርሰን ይሆናል።

Thursday, November 19, 2015

ወንጌል እና ሰይጣን፣ ትግሬ እና ብርቱካን ( ሄኖክ የሺጥላ )

ወንጌል እና ሰይጣን፣ ትግሬ እና ብርቱካን ( ሄኖክ የሺጥላ )
የብርቱካን አሊ ልጅ አብዱ በራ’ብ እንዳልሞተ ወያኔ ነገረን ። በዛ ላይ ቢቢሲ ደሞ እንደ ኢሳት እንደዋሸ ተነገረን ። ይሁን !
እንበልና የብርቱካን ልጅ በራብ አልሞተም ፣ ቀጥሎም የብርቱካን ልጅ በቁንጣን ነው የሞተው እንበል ፣ እንደውም እንደ ወያኔ ባለ ስልጣን ልጆች ሰክሮ መንገድ ላይ ውስኪ እየደፋ ሲሄድ የደፋው ውስኪ አዳልጦት ነው የሞተው እንበል ፣ ከፍ ሲል ለቢቢሲ ጋዜጠኛ ያሳየችው ቅጠል የተሸፈነ የልጇ የአብዱ መቃብር ሳይሆን የእህል ማስቀመጫ ጎተራ ነው እንበል ፣ እነዚህ ሁሉ እውነት ሆኑ እንበል ፣ ከዚያስ ?
እርግጥ ነው ፣ ነገሩን በጥልቀት ከተመለከትነው የብርቱካን ልጅ የሞተው በራብ አይደለም ፣ ራብ ነብሱን ከስጋው የለየው የመጨረሻው ጉዳይ ይሆን ይሆናል እንጂ ፣ የብርቱካን ልጅ የሞተው ፣ እኛ ወንድነታችንን የተቀማን ግዜ ነው ፣ ብርቱካን ልጆቿን የቀበረችው የወለደቻቸው ቀን ነው ፣ እርግጥ ልጇን አፈር ያለበሰችው ዛሬ ነው ፣ መቃብሩ የተቆፈረው ግን ወያኔ ስልጣን ላይ ሲወጣ ነው ። ረሃቡ ሞትን ያስከተለ አንድ ምክንያት ሊሆን ይችላል እንጂ የብርቱካን ልጅ ረሃብ ባይኖርም አያድግም ! ሰው አይሆንም ! ሃገሩን አይጠቅምም ! ባገሩ አይጠቀምም !

Wednesday, November 18, 2015

ረሃቡን በሚመለከት የተሰጠ መግለጫ፣ ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት (Global Alliance for the Rights of Ethiopians – GARE)

Global Alliance for the Rights of Ethiopians (GARE)ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት ከተቋቋመበት ወቅት ጀምሮ ለኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ በያሉበት ለሚደርስባቸው ግፍና ችግር ያልተቆጠበ ጥረት በማካሄድ ላይ ይገኛል። በዚሁ መሰረት በሳውዲ አረቢያ፤ በየመን፤ በሊቢያ፤ በኬንያ፤ በሰሜን ሱዳንና በማላዊ ችግር ለገጠማቸው ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የገንዘብ፤ የዲፕሎማሲ፤ የምክርና ሌሎች ድጋፎች አድርጓል። ይኼ ግዙፍ ድጋፍ ስኬታማ ሊሆን የቻለበት ዋና ምክንያት ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በያሉበት የገንዘብ ድጋፍ ስላደረጉ ነው። ድርጅታችን እነዚህን ደጋፊዎች ያመሰግናል።

“15 ሚሊዮን ህዝብ መደበቅ ሰማይን በመዳፍ ለመሸሸግ እንደ መሞከር ይቆጠራል” (በውቀቱ ስዩም)

Ethiopian author and poet, Bewketu Seyoumባገራችን ኣብዛኛው ዜጋ ለቀን ጉርስና ላመት ልብስ ሲታገል የሚኖር ነው፡፡ ጌቶች ደግሞ ኣማርጠው ይበላሉ፡፡ ኣማርጠው ይለብሳሉ፤በለስ ሲቀናቸው ደግሞ የሃያ ኣምስት ሚሊዮን ብር ቪላ ይቀልሳሉ፡፡ እንዲያም ሆኖ ደግሞ መከበርና መደነቅ ይፈልጋሉ፡፡ ሰው ምንም በስጋው ቢመቸው በሌላው ተመዝኖ እንደቀለለ ሲሰማው ደስተኛ ኣይሆንም፡፡ ስለዚህ ጌቶች ያስንቀናል ብለው የሚያስቡትን ነገር በሙሉ ጠምድው ይይዙታል፡፡ ይዋጉታል፡፡ ኢትዮጵያ- ጌቶች ለኩራታቸው፤ ዜጎች ለራታቸው የሚታገሉባት መድረክ ናት፡፡

Tuesday, November 17, 2015

ለድርቁ አስቸኳይ ብሔራዊ ግብረኃይል ይቋቋም! “ህይወት ለማትረፍ በቅድሚያ መተማመን”

drought and hope





* ከአገዛዝ ለውጥ በፊት ችጋር ይቀድማል?
* “በአሁኑ ጊዜ ችጋሩ እንደ 1977 ሆኗል!”
በኢትዮጵያ ላለፉት ፴ ዓመታት ያለታየ ችጋር ተከስቷል። ድርቁና ረሃቡ ከዚህም በላይ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ኢህአዴግን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ተቋማት ይፋ እያደረጉ ነው። “የምግብ ዋስትናን አረጋግጫለሁ” በማለት ሲወተውት የኖረው ህወሃት ተገዶ ያመነው ችጋር ከ፩፱፯፯ ድርቅ በላይ የከፋ እንደሚሆን ስጋት አይሏል። ከዚህ በፊት እንደተከሰቱት ለውጦች ይህኛውም የአገዛዝ ለውጥ ሊያስከትል እንደሚችል ተነገረ። በአስቸኳይ ብሔራዊ ግብረኃይል መቋቋም እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ክፋት በዛ [ረሃብ እንደ ቀይ ሽብር፤ ህወሃት እንደ ደርግ]

ክፋት በዛ

[ረሃብ እንደ ቀይ ሽብር፤ ህወሃት እንደ ደርግ]
birtukan ali


ክፉ ቀን ብዙ ክፉ ምግባሮች ይዞ ይመጣል።
በቀይሽብር ወቅ በመቀሌ ከተማ ያጋጠመ አንድ የክፉ ምግባር ምሳሌ ነበር።
ዘስላሰ የተባለ ወጣት በፀረ ደርግነት ተጠርጥሮ የቀይ ሽብር ሰለባ በመሆን በባዛር እየተባለ የሚታወቀውና አሁን በስሙ ዘላሰ የተሰየመው የአፄ ዮሐንስ ቤተ መንግሥት ፊትለፊት የሚገኝ አደባባይ ይረሸናል። ወላጅ እናቱ በደርግ ወታደሮች ተገድደው እልልል እያሉ፣ እያጨበጨቡ ደስታቸው እንዲገልፁ ተደርገዋል።

ብልግናና እና ስልጣን ( ሄኖክ የሺጥላ )


ባለጌ ብልግናውን በትምህርት ፣ በሥርዓት በተገመደ ባህል ፣ በቤተሰብ እና በሚከተለው ሃይማኖት ካላረቀ ዱርዬ ይሆናል ። ይህ ዱርዬ ወታደር ከሆነ ደሞ ፣ የጠመንጃው አፈሙዝ እና ብልግናው ጥጋብ ይደርብለት'ና የወጣለት አምባገነን ይሆናል ። የኢትዮጵያ ችግር ይሄ ነው ። አመጸኛ ባለጌ ጀግና ሆኖ ፣ የሚፈራው አጣ ፣ የሚያከብረው አጣ ፣ የሚሰማው አጣ ።
ዛሬ ሀገራችን የገባችበት መከራ ምንጩ ፣ የስድ ጓዶች ፣ የመሃይም ጀነራሎች ፣ የባለጌ ሚንስትሮች ፣ የዱርዬ ጳጳሶች እና የወሮበላ ዳኞች ሀገር ስለሆነች ነው ። ባለጌ ብልግናው እሱ ጋ አይቆምም ፣ የ ባለጌ ትውልድ አባወራ ፣ የባለጌ ልጆች አባት ፣ የባለጌ ስርዓት ባለቤት ይሆናል ። ለዚህም ነው ባለጎችን የሚያግባባቸው እና የሚያመሳስላቸው ነገር ሁሉም አለመግባባታቸው ነው የሚባለው ። በባለጌ ስርዓት ውስጥ ይሉኝታ የለም ፣ ሰው ምን ይለኛል የለም ፣ ሀፍረት የለም ፣ ክብር የለም ፣ ታሪክ የለም ፣ ሕዝብ የለም ፣ እምነት የለም ፣ ነገ የለም !
ሕፍረቱን ያጣ ስርዓት ፣ ስርዓቱን የተነጠቀ ሕዝብ ፣ ጨዋነት የራቀው መንግስት ፣ የመዋረድ እና የማጎብደድ ርካሽነት የሚያይበት አእምሮም ነብስም የለውም ። ስለዚህ በሊቢያ መታረድም ሆነ በሱማሊያ ጦር መማገድ ሃገራዊ ውድቀት ሳይሆን እንደ አንድ የማህበረሰብ የለት ተለት ተራ ክንውን ተደርጎ የሚወሰደው ።

Sunday, November 15, 2015

ድርቅ ርሃብና ችጋር ምንና ምን ናቸው? ኢትዮጵያስ ለምን የርሀብ ሀገር ሆነች? (ፈቃደ ሸዋቀና)

ፈቃደ ሸዋቀና
ሀገራችን መሬት ላይ እንድ ሌላ ግዙፍ የርሀብና የችጋር ዳመና እያንዣበበ ነው። አንዳንድ ቦታም ግዳይ መጣል መጀመሩን እየሰማን ነው። ይህ ችግር በሰብዓዊMalnutrition hits record high in Ethiopiaዕውቀትና ሀይል የሚፈታ ሆኖ ለምንድነው እንዲህ እየተመላለሰ የሚጎበኘን? ሌሎች ሀገሮች ተመሳሳይ የአየር ሁኔታ ችግር እየገጠማቸው እንደኛ ለአዋራጅ ጉስቁልናና ልመና አልተዳረጉም። እኛ ጋ ምን የተሰወረብን ነገር አለ? የአፍሪካ የውሀ ሰገነት የምትባልና ከማንም የማይተናነስ የተፈጥሮ ጸጋ ያላት ሀገር ይዘን ለምን እንደዚህ አይነት ሕዝብ ሆንን? በጅጉ የሚደንቅ ነገር ብቻ ሳይሆን በንዴት የሚያቃጥል ነገር ነው። እንደሚመስለኝ ችግሩን የልፈታንበት አንዱ ምክንያት ተገቢና የበሰለ ውይይት የማናካሂድ ህዝብ መሆናችንና ይህንንም ለማድረግ የመወያያና መፍትሄ ፍለጋ ሁኔታ እንዳይፈጠር መንግስታቱ ተጠያቂነትን ለማምለጥ ሲሉ የሚፈጥሩት እንቅፋትነት ይመስለኛል። እስከመቼ በዚህ ውርደት እንደምንቀጥል ባሰብኩ ቁጥር የሚያመኝን ህመም ችዬ ነው ይህን ለውይይት የሚሆን ጽሁፍ የጻፍኩት።

Friday, November 13, 2015

የሞቱ ካሉ የሞቱት በረሃብ አይደለም ይላሉ ም/ጠ ሚኒስተሩ – የሚሊዮኖች ድምጽ

8c1e31b24cd68f93e746d072f1231338_XL
የኢትዮጵያ መንግስት 600 ሺህ ሜትሪ እህል አዟል ይሉት አቶ ደመቀ መኮንን 200 የሚሆነው ጅጅቡቲ ወደብ እንደደረሰ ለፋና ራዲዮ ተናግረዋል።ሄ መልካም ዜና ነው። ረፍዷል፤ ቢሆንም ረፍዶም እርምጃዎች መወሰዳቸው ጥሩ ነው።
“የተለያዩ የውጭ መገናኛ በዙሃን በድርቁ የተነሳ የሰው ህይወት አልፏል እያሉ እያሰራጩ ካለው ዘገባ አንጻር በተጨባጭ ያለው እውነታ ምን ይመስላል” በሚል ከፋና ለቀረበላቸው ጥያቄ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመልሱ፥ “የውጭ መገናኛ ብዙሃን ከተለያዩ አካላት ጋር እንደሚሰሩ ይታወቃል። ከዚያ በላይ ግን፣ አፍ ለማዘጋት አልያም ለማስተባበልና ምላሽ ለመስጠት ሳይሆን፣ ረሃብ የሚባለው ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ የለም” ይየሚል ማልሽ ነው የሰጡት።

Wednesday, November 11, 2015

ጉድ በል!!!!! ወገኔ. 15 ሚሊየን ሕዝብ በተራበበት ሃገር ውስጥ አልጠግብ ባይ የወያኔ ሕውሃት ቡድን የሚሰሩትን በራሳቸው ልሳን ስማ. ላረጁና ሕዝብና ሃገርን ሲያደሙ ለኖሩ ለያንዳዳቸው 25 ሚሊየን ብር የሚያወጣ መኖሪያ ቤት እየተሰራላቸው እንደሆነ. .

ጉድ በል!!!!! ወገኔ.  15 ሚሊየን ሕዝብ  በተራበበት ሃገር ውስጥ  አልጠግብ ባይ የወያኔ ሕውሃት ቡድን የሚሰሩትን በራሳቸው ልሳን ስማ.
ላረጁና ሕዝብና ሃገርን ሲያደሙ ለኖሩ ለያንዳዳቸው  25 ሚሊየን ብር የሚያወጣ መኖሪያ ቤት እየተሰራላቸው እንደሆነ. .




ወሮበሎች በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ሰርጎ መግባት? (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ጥንታዊ የሮማ ሰዎች እራሳቸውን ከወሮበላ አደጋ ጣዮች ለመጠበቅ ሲሉ የከተሞቻቸውን በሮች እና ግንቦች ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ይጠብቁ ነበር፡፡TPLF officials and VOA
የሮማ ሰዎች ወሮበላ አደጋ ጣዮች ምንም ዓይነት አደጋ ሳይጥሉ ቅድመ ዝግጅት አድርገው ገና ከበሩ ጋ በመጠበቅ ዓላማዎቻቸውን ያከሽፉባቸው ነበር፡፡
በአሁ ጊዜ ደግሞ የዘመኑ የፕሬስ ነጻነት አደጋ ጣይ ወሮበሎች እ.ኤ.አ መስከረም 26 /2015 በዋሺንግተን ዲ.ሲ የሚገኘውን የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት በድብቅ  ጭለማን ተገን አርገው ሰርጎ ገብተው ነበር ፡፡

አገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል፤ በአክሊሉ ወንበር ቴዎድሮስ ተቀምጧል (ይገረም ዓለሙ)

ይገረም ዓለሙ
Ethiopian foreign ministerበዕድሜአችን የደረስንባቸውንም ሆነ በታሪክ የምናውቃቸውን በዚህች ሀገር በመሪነትም ሆነ በከፍተኛ ሥልጣን ላይ የነበሩ ሰዎች ስናስብ የዘመናችን ባለሥልጣናት በብዙ መንገድ አንሰውና ቀለው ነው የሚታዩት፡፡ በውሸታምነታቸው በዘረኛነታቸውና ለሀገርና ለሕዝብ በአላቸው እኩይ አመለካከት ደግሞ አይደለም ትናንት ከነበሩት ወደ ፊትም ከሚመጡት የሚስተካከላቸው የሚገኝ አይመስልም፡፡ ነገረ ስራቸው ሲመዘን፣ የማይታመን የማይጨበጥ ንግግራቸው ሲሰማ እንዲህ የሚያደርጋቸው ከደደቢቱ እኩይ ዓላማቸው በላይ የተቀመጡበት እነዚያን ታላላቅ ኢትዮጵያውያንን ያስተናገደ ወንበር እያቃዣቸው ሳይሆን አይቀርም ያስብላል፡፡

Monday, November 9, 2015

ረሃብ የመንግሰት ፖሊሲ ብልሹነት እንጂ የዝናብ እጥረት ዉጤት አይደለም! (ኤፍሬም ማዴቦ)

በኤፍሬም ማዴቦ
Malnutrition hits record high in Ethiopia
ደርግ የቀዳማዊ ኃ/ሥላሤን ስርዐት ከደመሰሰ በኋላ ወሎ፤ ትግራይና ሰሜን ሸዋ ዉስጥ ህዝብ እንደ ቅጠል ሲረግፍ እሳቸዉ የልደት በዐላቸዉን ለማክበር ከዉጭ አገር ኬክ ያስመጣሉ ብሎ ነበር ንጉሰ ነገስቱንና ስርዐታቸዉን የከሰሰዉ።

Thursday, November 5, 2015

የኢትዮጵያ ወጣቶች ክልል፣ ቋንቋም ሆነ ሀይማኖት ሳይገድባቸው በጋራ ይቁሙ!

def-thumb
ከ1950ዎቹ ጀምሮ የተደረጉ ሕዝባዊ ንቅናቄዎች በሙሉ የተጠነሰሱትና የተመሩት እድሜያቸው ከሠላሳ አምስት ዓመት በታች በሆኑ ወጣቶች ነው። የ1997 ምርጫ ታሪካዊ እንዲሆን ያደረጉ፤ የሚያዝያ 30 ቀን 1997ን ታላቅ ሰልፍ ያደራጁ፤ ሕዝብን አደፈፍረው ለምርጫ በማሰለፍ ግንቦት 7 ቀን 1997 ታሪካዊ ዕለት እንድትሆን ያደረጉ፤ በኋላም “ድምፃችንን አናስነጥቅም” በማለት የአግዓዚ ፋሽስቶችን በድንጋይና ዱላ የገጠሙ የኢትዮጵያ ወጣቶች ናቸው። በዚህ ትግል ሽብሬ ደሳለኝን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች ሕይወታቸውን ሰውተዋል፤ በቁጥር የበዙት ደግሞ አካሎቻቸውን አጥተዋል፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች አሁንም በአገዛዙ እስር ቤቶች ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው ነው። ጥቃቱ ቢበዛም ትግሉ ደግሞ የዚያኑ ያህል ተጠናክሮ ቀጥሏል። የኢትዮጵያ ወጣት ጥቃትን አሜን ብሎ አይቀበልም።

‹‹የመጣነው የሚላስ የሚቀመስ ስለሌለ ነው፡፡ ከብቶቻችን አልቀዋል፡፡ አዝመራ የሚባል የለም፡፡ ሰው በርሃብ እያለቀ ነው፡፡››››




‹‹የመጣነው የሚላስ የሚቀመስ ስለሌለ ነው፡፡ ከብቶቻችን አልቀዋል፡፡ አዝመራ የሚባል የለም፡፡ ሰው በርሃብ እያለቀ ነው፡፡››››
መንግስት በርሃብ ለተጠቁት ዜጎች እርዳታ እየሰጠ እንዳልሆነ ታወቀ
• በርሃብ የተጠቁት ዜጎች ቀያቸውን ለቀው እየተሰደዱ ነው
• ‹‹ሰው በርሃብ እያለቀ ነው››
• ‹‹የሚላስ የሚቀመስ የለም፡፡ ቤተሰባችን ፈርሷል››
• ‹‹እርዳታ ቢሰጥማ ከዚህ ድረስ አንመጣም ነበር፡፡››

Tuesday, November 3, 2015

የታማኝ እዳ

እንግዳ ታደሰ – ኦስሎ
በቃል የምነት እዳ ሸክፎ ሸክሙን 
እንደ ሴባስቶፖል ሽቅብ ቁልቁለቱን
ሲወጣና ሲወርድ ቋጥኝ አቀበቱን 
እስቲ እንካፈለው የሃገር እዳውን ፡፡
Ethiopian activist Tamagne Beyene
እዳው በግል የናት አባት እዳ አይደለም ፡፡ የርሱ እዳ የዕምነቱ እዳ ነው ፡፡ ለሸክም የከበደ ፥ የሰው ፊት የሚያስገርፍ፥ ዕረፍት የሚነሳ ፥ ከወለዳቸውና ከሚወዳቸው ቤተሰቡ ለወራት የሚያቆራርጥ፣ እንደ አጼ ቴዎድሮስ መድፍ ሴባስቶፖል ሽቅብና ቁልቁል የሚያስሮጥ፣ ኢሳትን በግሩ ለማቆሞ የሚደረግ ትግል ፡፡

ለጥቅምት 22 ሰማዕታት የመታሰቢያ ፕሮግራም ተካሄደ (ነገረ ኢትዮጵያ)

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

The Ethiopian police massacre 2005
ምርጫ 1997 ዓ.ምን ተከትሎ ጥቅምት 22/1998 ዓ.ም በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ቀጥታ ትዕዛዝ በ‹‹ፀጥታ ሀይሎች›› በጭቃኔ ለተገደሉት ሰማዕታት እና ለቆሰሉት ኢትዮጵያውያን በሰማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት መታሰቢያ ተደረገ፡፡ የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች ጥቅምት 22/1998 ዓ.ም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የገጠማቸውን በተለይም ኢትዮጵያውያን ሲገደሉ ያዩትንና የራሳቸውን ገጠመኝም አካፍለዋል፡፡

Saturday, October 31, 2015

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የለሊቱ የቪኦኤ ሚስጥራዊ ጉባኤ (በአበበ ገላው)

በአበበ ገላው (ትርጉም በታኬ)
Tedros Adhanom and Ambassador Girma Birruበቅርቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድኃኖም እና አምባሳደር ግርማ ብሩ በዩናይትድ ሰቴትስ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲ.ሲ በሚገኘው የቪኦኤ ሬዲዮ ጣቢያ በሌሊት በድብቅ በመግባት ሕጋዊ ስልጣኑ ሳይኖራቸው ስለስርጭቱ ለጥቂት የድርጅቱ ሠራተኞች የኢዲቶሪያል መመሪያ ከሰጡ በኋላ በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው አገልግሎት (ቪኦኤ) እና በህወሀት የበላይነት በሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት መካከል ያለው የሻከረ ግንኙነት ያልተጠበቀ አቅጣጫ ይዟል፡፡ ስብሰባው በሚስጥር በተካሄደበት ጊዜ የአምባገነኑ አገዛዝ ባለስልጣኖች ለሬዲዮ ስርጭቱ ሰራተኞች ስለዜና አዘጋገብ፣ እንደዚሁም ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ስለሚተላለፈው የስርጭት ጥራት ሁኔታ መመሪያ የመስጠት ሙከራ ያደረጉ ለመሆናቸው ከታመኑ ምንጮች በተገኙ መረጃዎች ተረጋግጧል፡፡

አይኔ አያየ እዚህ ዉስጥ አልገባም – መሠረት ሙሌ (ኤፍሬም ማዴቦ ከአርበኞች መንደር)

ኤፍሬም ማዴቦ ከአርበኞች መንደር
Patriotic Ginbot7 fighters
መብራቱን አጥፍቼዉ አልጋዬ ላይ የወጣሁት በግዜ ነዉ። አለወትሮዬ እንቅልፍ የሚባል ነገር በአይኔ አልዞር ብሎኝ ከጨለማዉ ጋር ፊት ለፊት ተፋጥጠናል። የነፋስ ሸዉታ እንኳን የማይሰማበት ደረቅ ሌሊት ነዉ። ጨላማዉ አይን ይበሳል። እቤቱ ዉስጥ ያለዉ ሰዉ ሁሉ ተኝቷል። ቀኑን በሠላም ላዋለኝ አምላክ ምስጋና ሰጥቼ ሌሊቱንም አደራ ብዬዉ ፀሎቴን ጨረስኩ። ያ ምቀኛ እንቅልፍ ግን አሁንም እንደከዳኝ ነዉ። ትንሿ አልጋዬ ላይ ግራ ቀኝ እያልኩ ተገለባበጥኩ። እንቅልፍ ተጎትቶ የሚመጣ ይመስል አሁንም አሁንም ላይ ታች እያልኩ አልጋዉ ላይ እራሴን ጎተትኩት . . . እንኳን እንቅልፍ ሊወስደኝ ጭራሽ አይኖቼ መርገብገባቸዉን ያቆሙ ይመስል ቀጥ ብለዉ ቀሩ። ከተጋደምኩበት ብድግ ብዬ መብራቱን አበራሁና ለመንገድ ከያዝኳቸዉ ሁለት መጻህፍት አንዱን አዉጥቼ ማንበብ ጀመርኩ። እኔ ላንብበዉ ወይ መጽሀፉ ያንብበኝ አላዉቅም። ጧት ስነሳ ግን “The Architecture of Democracy” የሚል መጽሐፍ ደረቴ ላይ ተለጥፎ ነበር።

Thursday, October 29, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) በላንድ ክሩዘር መኪና ተሳፍረው ወደ አርባ ምንጭ ከተማ በፍጥነት ያመሩ የነበሩ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ፡፡


የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
በላንድ ክሩዘር መኪና ተሳፍረው ወደ አርባ ምንጭ ከተማ በፍጥነት ያመሩ የነበሩ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ፡፡
====================================================
በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ አስሩ የፌደራል ፖሊሶች መጀመሪያ አንድ አይሱዙ የጭነት መኪና በኃይል በማስገደድ አስቁመው የተሳፈሩ ሲሆን መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር "የጫንካቸውን ፖሊሶች አራግፍ አለያ ከነንብረትህ አብረህ ትጋያለህ!" የሚል የስልክ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ለአሽከርካሪው በመድረሱ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ ፖሊሶቹን "አልሄድም" ይላቸዋል፡፡ ቀጥሎም ፌደራል ፖሊሶቹ ሾፌሩን ለማንገራገር ሞክረው ትዕዛዛቸውን በቀላሉ ሊቀበል ባለመቻሉ ስልክ ተደዋውለው ሌላ ላንድ ክሩዘር መኪና እንዲመጣላቸው በማድረግ ተሳፍረው ጉዟቸውን ቀጥለው ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ሲደርሱ ቅፅበታዊ ጥቃት ተከፍቶባቸው ከነተሳፈሩበት መኪና ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ሙሉጌታ አባ፣ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ እና በኃይሉ ሲሳይ የተባሉ የህወሓት ጆሮ ጠቢዎችና የአካባቢው ቆራጭ ፈላጮች ፎቶግራፋቸው በማህበራዊ ሚዲያው መሰራጨቱን ተከትሎ ከትናንት ምሽት ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ ከከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ በፌደራል ፖሊስ ተጥለቅልቃ እየታመሰች ትገኛለች፡፡ 

Wednesday, October 28, 2015

(ሰበር ዜና) መምህር ግርማ ታሰሩ

Memeher-Girma
(ዘ-ሐበሻ) በአውሮፓ የተለያዩ ሃገራት በማጥመቅ ላይ ቆይተው ወደ ሃገራቸው የተመለሱት መምህር ግርማ ወንድሙ በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመምህሩ ቅርብ ሰዎች የሆኑ ታማኝ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ:: እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘገባ ከሆነ መምህር ግርማ ወንድሙ ፈቃድ ሳይኖራቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም ተጠቅመው በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር በማስተማር እና በማጥመቅ ሥራ ላይ ተሰማርተዋል በሚል በቤተክህነት በቀረበባቸው ክስ ነው የታሰሩት:: በአገልግሎታቸው የተነሳ በወንጀል እንደሚጠየቁ በፖሊስ እንደተነገራቸው የተገለጸው መምህር ግርማ በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ሥር ላይ ውለው ምርመራቸው እንደቀጠለ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል:: ምንጮቻችን የሚያደርሱንን መረጃዎች ይዘን እንቀርባለን::

ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ የተከሰተውን ረሀብ ማቆም ይችላልን? (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በአውዳሚ ረሀብ መካከል ተሰንጋ መያዟ ታላቅ ዓለም አቀፍ ሚስጥር ሆኖ ይገኛል፡፡Can the T-TPLF Stop the Famine in Ethiopia?
.. 1984-85 ወዲህ ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተ ታላቅረሀብ!
ባለፈው ሳምንት ግሎባል ፖስት/Global Post የተባለው የዜና ወኪል በርዕሰ አንቀጹ የመጀመሪያ ርዕስ በማድረግ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቅርቧል፡
“ኢትዮጵያ ባለፉት 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ በአስከፊነቱ የመጀመሪያ የሆነውን ድርቅ ተጋፍጣ ትገኛለች፡፡ መንግስት በአሁኑ ጊዜ የተከሰተውን ረሀብ ማስቆም ይችላልን?”
ግሎባል ፖስት መንግስት ረሀቡን ማስቆም ይችላል ወይ የሚል ጥያቄ ያቀረበለት እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ ለሚጠራው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) ነው፡፡

Tuesday, October 27, 2015

አይ ስብሐት ነጋ – ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

በኢትዮጵያ ውስጥ ሥልጣን ሳይኖረው ባለሙሉ ሥልጣን፣ እውቀት ሳይኖረው ባለሙሉ እውቀት የሆነ ሰው ስብሐት ነጋ ብቻ ነው፤ እንዲያውም ከዚያም አልፎ ራሱን የቻለ ሉዓላዊ ነጻነት ያለው ግለሰብ ነው ለማለት የሚቻል ይመስለኛል፤ በዚህ ግለሰብ ላይ የማደንቃቸው ሁለት ነገሮች ናቸው፤ በሉዓላዊነቱ የተጎናጸፈውን ሥልጣን ሙሉ በሙሉ ይጠቀምበታል፤ ይቆጣኛል ወይም ይቀጣኛል ብሎ የሚፈራው የለም፤ ስብሐት ነጋ የሚፈራው ምንም ነገር የለም፤ ሁለተኛ በሉዓላዊነቱ ያለውን ሙሉ ነጻነት በሙሉ ልብ ይጠቀምበታል፤ ናስ በላይ ከበደ እንዳለው ‹‹የቅብጠት መዘላበድ›› ሊሆን ይችላል፤ ስብሐት ነጋ የተናገረው ነገር ትክክል ይሁን አይሁን ጉዳዩ አይደለም፤ ዋናው ነገር መናገሩ ነው።

በቅርቡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከጋዜጠኛነት ተማሪዎች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ሁለት ሰዎች ጽፈው አይቻለሁ፤ ዶር. በድሉ ዋቅጅራ በፋክት ላይ፣ ናስ በላይ አበበ በኢትዮ-ምኅዳር ላይ፤ ሁለቱም ሰዎች አልወደዱለትም ማለት ያንሳል፤ የሚወዱለትና የሚያጨበጭቡለት መኖራቸውም ሳይታለም የተፈታ ነው፤ ነገር ግን ስብሐት ነጋም ሆነ ደጋፊዎቹ አደባባይ ወጥተው ለመከራከር አይችሉም፤ ናስ በላይ አበበ እንደሚነግረን ‹‹አቶ ስብሐት ነጋ የውጭ ሰው እንዳይገባ ከተማሪዎቹ ጋር ተደራድረው ነበር የመጡት፤ ስለሆነም ነበር ከፍተኛ ጥበቃ አልፈን የገባነው፤›› ብቻውን ተናግሮ በጭብጨባ የሚሸኝበት መድረክ በመፈለጉ በከባድ ጥያቄም ቢሆን የሚያጣድፉት ሰዎች እንዳይኖሩ ማረጋገጡ በተማሪዎቹም ቢሆን ውሎ አድሮ ትዝብት ላይ ይጥለዋል።

የተቦርነ የፈራረሱ ቅኝቶች (ከአርአያ ተስፋማርያም)

ከአርአያ ተስፋማርያም
ወዳጄ ተቦርነ በተመለከተ ግልፅ ያልሆኑልኝ ነገሮችን አንስቼ በጥያቄ መልክ አቅርቤ ነበር። አንተም ለኔ ጥያቄ የሚሆን የመልስ ፅሑፍ ለጥፈህ አነበብኩት። የመለስክልኝ መልስ በጣም አስገርሞኛል፣ ግራም አጋብቶኛል። ያንተኑ ተረት በመዋስ “ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ” ብየዋለሁ። ምክንያቱም ጥያቄዬን መመለስ ስላልቻልክ ወይም ስላልፈለክ እኔን በመሳደብ ጥያቄውን ለማድበስበስ ስትሞክር ነበር። ሃሳብን በሃሳብ መርታት ሲቃትህ ሃሳቡን ያቀረበውን ግለሰብ የማጥቃት የተባለ የክርክር ግድፈት ወይም ሎጂካል ፋለሲ ነው። ምን አልባት ጥያቄዬን ካልተረዳኸው ደጋሜ ላንሳው።
ዘረኛ፣ ኣምባገነንና ሙሰኛ የሆነው የኢህአዴግ መንግስት ህዝባችንን ከፍላጐቱ ውጭ በሀይል፣ በማስፈራራትና በዘር በመከፋፈል እየገዛ 24 አመታት አለፈ። ይህ መንግስት የስልጣን ዘመኑ እንዲቀጥል ህዝቡን በዘር መከፋፈል፣ በሀይል ማፈንና አዲሱ ትውልድ በተለያዩ የማይረቡ ጉዳዮች ማደንዘዝ ዋና አላማዬ ነው ብሎ እየሰራ ይገኛል። ለብዙ ኢትዮጵያዊያን ሞት፣ እስራት፣ ግርፋት፣ ድህነትና ስደት ተጠያቂ ከሆነው ከዚህ መንግስት ጋር የጥቅም ተካፋይ ሆነው ስልጣኑ እንዲረዝም በገንዘባቸውና በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ከሚረዱት ሰዎች አንዱ ሼኽ አልሙዲ ናቸው። ሼኹ በኢትዮጵያ ፖለቲካ በፈፀሙት ደባ፣ የሀገሪቱን ሃብት በመበዝበዝ የሃገራችንን ባህልና ወግ የሚያናጋ የማህበራዊ ቀውስ በህብርተሰቡ ውስጥ በማምጣት የሚጠየቁ ሰው ናቸው።
ከላይ እንደጠቀስኩት የዚህ መንግስት ዋና አላማው ህዝቡን ከፋፍለህ መግዛት ብቻ ሳይሆን ትውልዱን ስለሃገሩ ታሪክ፣ ስለማንነቱ፣ ስለሰብዓዊና ዴሞክራሲ መብቶቹ እንዳያውቃና እንዳይጠይቅ ማደንዘዝ ነው። ለዚህ አላማ መሳካት የፖለቲካ፣ የታሪክ፣ የፍትህ፣ ፍልስፍናና የማንነት ጥያቄ የማያነሱትን እንዲሁም ህዝብ እንዲነቃ የሚያደርጉትን የመገናኛ ብዙሃን እየዘጋ፣ ሽብርተኛ እያለ ጋዜጠኞችንም እያሰረ፣ እያሸማቀቀ፣ ከሀገር ያሰድዳል። በተቃራኒው ደግሞ ህዝቡ ከሀገሩ ጉዳይ ጋር እንዲፋታ የፖለቲካም ሆነ የመብት ጥያቄ ሲያነሳ የተባለውን አድራጊ፣ የተጠየቀውን ፈፃሚ ይሆን ዘንድ እንደ ሰይፉ ፋንታሁን አይነት ትውልዱን የሚያደነዝዙ ዝግጅቶችንና መገናኛ ብዙሃንን “የመዝናኛ ፕሮግራም” በሚል ስም ይለፈልፋል።
አነተ ገለልተኛ እያልክ የምታወድሰው ጓደኛህ ሰይፉ ፋንታሁን ይህንን የኢህአዴግን አላማ ግንባር ቀደም አስፈፃሚ ከመሆኑ በተጨማሪ አሁን በስልጣን ላይ ያለውን አምባገነን መንግስት የሚደግፍ ካድሬ መሆኑን አገር ያውቃል። ከዚህ በተጨማሪ ሰይፉ የኢሃዴግ መንግስትን እድሜ ለማርዘም ሌት ተቀን የሚለፉትና የአገርን ሃብት ያለአግባብ የሚዘርፉት የሼኹ ሎሌ ነው። በቅርቡ በሸራተን ሆቴል ሲያገባ የሰርጉን ወጪ ሙሉ በሙሉ በሼኹ የተሸፈነለትም በዚሁ የኢህአዴግ ካድሬነቱና ታማኝነቱ የውለታ ምላሽ ነው። ከሼኹና ከገዢው ፓርቲ ጋር አልተባበርም ያሉና ከተፅዕኖ ውጭ የሆኑ አርቲስቶች ፈተና ሲገጥማቸው አይተናል። ህዝብ የጀግንነት ክብር ከሰጣቸው ታማኝ በየነና ቴዲ አፍሮ ይጠቀሳሉ።
ኢ.ሴ.ኤፍ.ኤን ከኢህአዴግና ከሼኽ አልሙዲ ተፅዕኖ ራሱን አላቆ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በመስራቱ ምን ያክል የህዝብ ድጋፍ እንደነበረውና ውጤታማ እንደነበረ አይተናል። እኔ ለአንተ የማቀርበው ጥያቄ የሚነሳው እዚህ ላይ ነው። እዚህ አሜሪካ አላሙዲ ከፈጠሩት የስፖርት ፌዴሬሽን ጋር የተባበሩትን አርቲስቶች እያወገዝክና ሌላ ስራ እንዳይሰሩ እያሳደምክ፣ በአንፃሩ ቀንደኛ የገዥው ፓርቲ ካድሬና የሼኹ ወዳጅ በመሆን ከኢትዮጵያ ህዝብ ከተዘርፈው ገንዘብ ተካፋይ የሆነው ሰይፉ ፋንታሁንን የአንተ ጋዷኛ በመሆኑ ብቻ አላሙዲ በሸራተን ደግሰው ሲድሩት ለምን ለማውገዝ ተሳነህ?..ማውገዝ እንኳ ቢቀር የሼኹ ሎሌ የሆነው ሰይፉን በምን መለኪያ ገለልተኛና በእመነቱ የሚፀና ለማለት ደፈርክ?.. ወይም ገለልተኛነትና በእምነት መፅናት ምን እንደሆኑ አታውቅም! አለበለዚያ ለአንተ ገለልተኛነትና በእምነት መፅናት ማለት ከአንተ ጋር የሚመሰረት ጓደኝነት ነው ማለት ነው። ሌላው ጥያቄ እዚህ አሜሪካ አገር ከአልሙዲ ጋር የተባበሩትን አርቲስቶች ከተቃወምክ አዲስ አበባ ላይ ከዚያው ግለሰብ (ሼኹ) ጋር የሚተባበሩትንና የቅርብ ወዳጅ የሆኑትን ሰዎች ማንቆለጳጰስ እንዴት ትችላለህ?..በተጨማሪ በአላሙዲ የሚረዳውን ፌዴሬሽንና ሸራተን ለየብቻ እንደሆኑ አድርገህ ለመግለፅ ሞክረሃል። እጅግ አስቂኝ ነው።ሁለቱም በሼኹ የሚዘወሩ ናቸው!
ከአምባገነኑ መንግስት ኢህአዴግና መንግስትን ከሚደግፉት እነሼኽ አላሙዲ ጋር መተባበር አይገባም ካልክ አቋምህ ወጥ ሊሆን ይገባል። አዲስ አበባም ሆነ አሜሪካ፣ ሰርግም ሆነ ስፖርት ጓደኝነት ኖረም አልኖረ፣ የግል ጥቅም ተገኘም አልተገኘ፣ አቋምህ ወጥ መሆን ይገባዋል። ስትቃወም፣ ስትደግፍ፣ ወጥ የሆነ አቋም ይኑርህ!
በእነኚህ ጉዳዮች ላይ የምታንፅባርቀው ወጥ ያለሆነ አቋም ሳስብ አንድ ጥንታዊ የቻይና ተረትን አስታወሰኝ። ሰውዬው በመንደሩ ውስጥ ሱቅ ከፍቶ ጦርና ጋሻ አንድ ላይ ይሸጣል። የሚገርመው ግን ጦሩን ሲያሻሽጥ “ሁሉንም ነገር ይበሳል” እያለ ሲሆን ጋሻውንም ሲያሻሽጥ “ምንም ነገር አይበሳውም” እያለ ነበር። አንተም፣ ያንተም ጓደኛም ሰይፉ ፋንታሁን ከአልሙዲ ተሻርኰ እየሰራና ሸራተን ሰርግ ሲደገስለት እያየህ ገለልተኛና በእመነቱ የሚፀና ብለህ ታወድሰዋለህ! አሜሪካ አገር ያሉ አርቲስቶች ከአልሙዲንና አላሙዲ ከፈጠሩት ፌዴሬሽን ዝግጅት ላይ ሲዘፍኑ ደግሞ “ባንዳና ከሃዲ” ብለህ ታወግዛለህ፤ እንዴት ነው ነገሩ?..የባንዳነትና የኢትዮጵያዊነት መለኪያው የአንተ ፍቃድና ጓደኝነት ሆነ እንዴ?..ለነገሩ የአንተን የአቋም መዘባረቅ በተመለከተ ግራ የሚያጋቡኝን አንድ ሁለት ነገሮች ልጠቃቅስልህና ወደ ዋናው ሃሳቤ ልመለስ። ድምፃዊ ቴዴ አፍሮ ከአልሙዲ ጋር ላለመስራት ወስኖ የኢትዮጵያ ህዝብ ጀግና እያለ ሲወድሰው ኢህአዴግ ደግሞ እንደጠላት ሲያዋክበው በነበረት ጊዜ አንተም ከሰይፉ ጋር ሆነህ ቴዲ አፍሮን በማዋከቡና የድምፃዊውን መልካም ስም በማጠልሸት ዘመቻ ላይ ከሰይፉ ጋር ተሳታፊ ነበርክ። ሁለተኛ የሰይፉን በመዝናኛ ስም ህዝብ የማደንዘዝ ተግባር ላይ አካልና አጋር ነበርክ። አንተ የእኔን የትላንት፣ የዛሬና የነገ አቋም ለመጠየቅ አንዳችም ማስረጃ ባይኖርህም እኔ ግን እነዚህንና ሌሎች ለጊዜው የማልገልፃቸውን ስህተቶችህን እያወቅኩ ኢትዮጵያዊነትህን አልተጠራጠርኩም።

Sunday, October 25, 2015

“ዘመድነህ ንጋቱ የኩባንያው ሳይሆን የህወሃት አገልጋይ ናቸው”

ዓለምአቀፉ ኧርነስትና ያንግ ኩባንያ ጉዳዩን እንዲመረምር ተጠየቀ

E&Y


የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃት) በሚገዛት ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ስም የኧርነስትና ያንግ የተሰኘውን የንግድ ሒሳብና ኦዲት ሥራ የሚያከናውን ኩባንያ ከፍተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት ዘመድነህ ንጋቱ በኦባንግ ሜቶ ለዓምአቀፉ የኧርነስትና ያንግ ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች አቤቱታ ቀረበባቸው፡፡

Friday, October 23, 2015

የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንደሌሉ ገለፀ (ነገረ ኢትዮጵያ)

• ‹‹የስርዓቱን ሽፍትነት ያመላክታል›› 3ኛ ተከሳሽ አቶ ደናሁን ቤዛ
• ‹‹የሚቀርብልን ምግብ ለእንሰሳትም መቅረብ የማይገባው ነው›› 2ኛ ተከሳሽ አቶ አሸናፊ አካሉ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
Ato Andargachew Tsige, Ginbot 7በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ -5ኛ መዝገብ ለተከሰሱት አቶ አሸናፊ አካሉ (2ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) እና አቶ አንሙት የኔዋስ (5ኛ ተከሳሽ) በመከላከያ ምስክርነት የተጠቀሱት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንደሌሉ ማረሚያ ቤቱ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛው ወንጀል ችሎት በላከው ደብዳቤ ገልፆአል፡፡ 19ኛ ወንጀል ችሎት ሀምሌ 29/2007 ዓ.ም የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አቶ አንዳርጋቸውን ለምን እንዳላቀረበ እንዲያብራራ፣ እንዲሁም ለምስክርነት እንዲያቀርብ ለዛሬ ለጥቅምት 12/2008 ዓ.ም ለአራተኛ ጊዜ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ አቶ አንዳርጋቸው ቃሊቲ እንደሌሉ በደብዳቤ አሳውቋል፡፡

እናመሰግናለን! የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች

እናመሰግናለን
Thank You! Zone9 bloggers
በድንገት ከያለንበት ተይዘን እንደታሰርነው አፈታታችንም ግራ የሚያጋባ ነበር፡፡ ተመሳሳይ ክሶች ቀርበውብን እያለ ግማሾቻችን ‹ክስ ተቋርጦላችኋል› ተብለን ተፈታን፣ ግማሾቻችን ደግሞ ‹ነፃ ናችሁ› (ከሳሽ በነፃነታችን ላይ ይግባኝ መጠየቁ እንዳለ ሁኖ) ተብለን ይሄው ወጥተናል፡፡ ቀሪ ክስ ይዘን በዋስ ወጥተን እየተከራከርንም ያለን አለን፡፡ በዚህ ሁሉ መሃል የሁላችንም ዕምነት ግን አንድም ቀን ሊያሳስረን የሚገባ ወንጀል አለመፈፃችን ማመናችን ነው፡፡ መፈታታችን ጥሩ ሁኖ፤ መታሰር በፍፁም የማይገባን ነበርን፡፡ መፃፋችን እና ሕግ እንዲከበር መጠየቃችን ሀገሪቱ አገራችን እንድትሻሻል እና ሁላችንም ዜጎች የተሻለ ህይወት አንዲኖራቸው ከመሻት ባለፈ ሌላ ነገር አልነበረውም/የለውም፡፡ ነገር ግን ይህን በማድረጋችን ተገርፈናል፣ ተዘልፈን-ተሰድበናል፣ ታስረናል ተሰደናልም፡፡ ይህ በፍጹም አይገባንም ነበር፡፡