Translate

Tuesday, December 29, 2015

ዮናታን ረጋሳ ታሰረ


Yonatan Regassa of Blue partyየሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረውና ብዙ ጓደኞቹ እንደሚስማሙበት እጅግ ታታሪ የመብት ተሟጋች እና ፖለቲከኛ ዮናታን ረጋሳ በወያኔ ደህንነቶች ታፍኖ በታዋቂው የማእከላዊ እስር ቤት እንደሚገኝ ታውቋል። ቀደም ሲል ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችም በተመሳሳይ መታፈናቸው ይታወሳል።
ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ አዲስ አበባን በማስፋት ስም በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የአዲስ አበባ አጎራባች ወረዳዎችን መሬት ለመቀራመት ሲሰናዳ በተቀሰቀሰበት ከፍተኛ ህዝባዊ አመጽ በመደናገጥ ከመቶ በላይ ንጹሃን ዜጎችን ሲገድል ከአምስት ሺህ በላይ ዜጎችን ደግሞ በየማጎሪያ ካምፖቹ በማሰር ላይ ይገኛል።

የወያኔው አገዛዝ ሰሞኑን የአፈና ድርጊቱን አጠናክሮ በመቀጠል የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አመራሮችንም ከያሉበት እንዲታፈኑ አድርጓል።
ወትሮውንም ጋዜጠኞችን እንደ ጦር የሚፈራው ወያኔ የነገረኢትዮጵያ ሪፖርተር ጌታቸው ሽፈራውንና ሌሎች ጋዜጠኞችንም በማሰር እና በማባረር ስራ ላይ ተጠምዶ ይገኛል።
ወያኔ ከአስር ዓመት በፊት ምርጫ 1997ን ተከትሎ ተነስቶበት የነበረውን ህዝባዊ እምቢኝነት ለማዳፈን ተመሳሳይ እርምጃ መውሰዱ ይታወሳል።
ይህ በዚህ እንዳል በኦሮምያ ክልል የተቀሰቀሰው ህዝባዊ እምቢተኝነት ጨርሶ እንዳልበረደ የሚያሳዩ መረጃዎች በመውጣት ላይ ይገኛሉ። ወያኔም በበኩሉ ህዝባዊ እንቅስቃሴውን ለማፈን ኦሮምኛም ሆነ አማርኛ ቋንቋን የማይናገሩ ገዳይ ወታደሮቹን ከቦታ ቦታ በማንቀሳቀስ ግድያና አፈናውን ተያይዞት ይገኛል።
ጨለማን ተገን አድርጎ፣ የኤሌክትሪክ ኃይልን በመቋረጥና ሂሊኮፕተሮችን በመጠቀም በድንገት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ጊቢ የዘረገፋቸው ገዳይ ወታደሮቹ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ ኢሰብአዊ ድርጊት ፈጽመዋል፣ ይህ ድርጊት እራሱን መንግስት እያለ የሚጠራው የወያኔ ቡድን እውነተኛ ማንነቱን የሚያሳይ ነው።
ሁኔታዎች ሁሉ እንደሚያመላክቱት ወያኔ በሽብር ተግባር ላይ የተሰማራ ቡድን ነው!

No comments:

Post a Comment