Translate

Monday, December 14, 2015

“ኤርትራ የትግራይ ናት”

“ትልቅ ነበርን ትልቅ እንሆናለን” - ህወሃት

eri-tigray

ኤርትራ የትግራይ አካል ናት የሚል አስተምህሮና የፖለቲካ ዝግጁነት ቅስቀሳ መጀመሩ ተሰማ። የጎልጉል ታማኝ ምንጮች ኤርትራ የትግራይ አካል ስለነበረች እንደገና መልሶ በመቀላቀል ታላቋን የአክሱም መንግስት ለመመሥረት የተያዘው አጀንዳ ተግባራዊ ለማድረግ ይቻል ዘንድ አስፈላጊው ሥራ እየተሰራ መሆኑንንም ጠቁመዋል። ለኢትዮጵያ እንደሆነ የሚጠቀሰው “ትልቅ ነበርን ትልቅ እንሆናለን” የሚለው የህወሃት መፈክር ኤርትራን ከትግራይ በመቀላቀል የአክሱምን “ዳግም ልደት” (ህዳሴ) ለመተግበር የታቀደ ነው ተብሏል፡፡

አጀንዳው ባልታሰበ ወቅት ብቅ ያለው በመሃል አገርና በተለያዩ አካባቢዎች እየተነሳ ያለው ተቃውሞ መበራከቱ ያሳሰባቸው ለሚያነሱት የስጋት ጥያቄ መልስ ለመስጠት ነው። የሻዕቢያን ተቃዋሚዎች በማደራጀት፣ በመደገፍና የስደት ፓርላማ በማቋቋም በህወሃት እየተካሄደ ያለው ሥራ የዚሁ ዕቅድ አካል እንደሆነ መረጃውን የሰጡት ክፍሎች አመልክተዋል። ህወሃት ውስጥ ያሉ ኤርትራዊ ደም ያላችው ባለሥልጣኖች የዚህ ዓላማ አካል ናቸው ተብሎ እንደሚገመትም አክለው ይናገራሉ።eritrea opposition conference
ስለ ኤርትራ ከተወላጆቹ በበለጠ በልበሙሉነትና ባለቤትነት መንፈስ በገሃድ የሚሟገቱት የቀድሞው የህወሃት መሪና የነፍስ አባት ስብሃት ነጋ አሁን የሚመሩት የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ተቋም “የሃገሪቱን ገፅታ ለመገንባት የኢትዮ-ኤርትራን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማድረስ የሚያስችሉ ስራዎችን እያከናወነ” ሲሉ ኢህአዴግ በፓርላማ ስም ለሚመራው የምክርቤት ኮሚቴ መናገራቸውን ሰኔ 5፣2007 የታተመው የኢቲቪ (ኢብኮ)ዘግቧል፡፡ የውጭ መከላከያና ደህንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮቴውም የስብሃትን ዘገባ ካደመጠ በኋላ “ኢንስቲትዩቱ የኢትዮ-ኤርትራ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንዲቀጥል” ማሳሰቡ ጨምሮ ተገልጾዋል፡፡
“የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ የሚለውን ስም የማትቀይሩት ለምንድን ነው?” የሚል ጥያቄ ለሴት ጓደኛው ሲያቀርብ “መጀመሪያ ኤርትራን ወደ ውድ እናት አገሯ መመለስ ይቀድማል” የሚል መልስ ማግኘቱን ትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሰራ የተናገረ የጎልጉል ደንበኛ ከሁለት ወር በፊት ገልጾ ነበር። ይህ ለትግራይ ሕዝብ የማይጠቅም እንዲያውም ለከፍተኛ ችግር የሚዳርግ እና በስሙ የሚፈጸም ሤራ ተቃዋሚዎች እንዳሉት ቢገመትም በግልጽ ደጋፊዎችም አሉት፡፡
በዴንማርክ የምትኖር አንዲት የትግራይ ተወላጅ እዚያው ለሚገኝ የጎልጉል አምደኛ ተመሳሳይ መልስ ሰጥታለች። “ደሚት (የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) የሚባለው ሃይል የህወሃት ልዩ አጀንዳ አስፈጻሚ እንጂ የህወሃት ተቃዋሚ አይደለም” ስትል ስሜት በተቀላቀለበት ሁኔታ ተናግራለች። ስዊድን አገር ለትምህርት ተልካ ዴንማርክ የቀረችው ይህቺው የትግራይ ልጅ “ኢሳያስ በቅርብ ይወገዳል” ስትል መሃላ የተቀላቀለበት ትንቢት ተናግራለች። “እጁን ሰጥቷል፤ ፈርሷል፤ ወደ ልማት ተመልሷል፤…” የሚባልለት የሞላ አስገዶም ደሚት በቃል ለኢትዮጵያ ነው የምታገለው እያለ በትግራይ ስም መቋቋሙና መቀጠሉ ገና ከጅምሩ ለብዙዎች ጥያቄ የፈጠረ ጉዳይ ነበር፡፡
ህወሃት ደሚትን “አሸባሪ” በሎ ያላስፈረጀው ብቸኛ ነፍጥ ያነገበ ድርጅት መሆኑ የዘወትር መወያያ መሆኑ ይታወቃል።
የኢትዮጵያን ታሪካዊ ታላቅነት በማሰብ እንደገና ገናና አገር እንደምትሆን የሚያመላክቱ ናቸው የሚባልላቸው ሕዝብን ቀስቃሽ መፈክሮች ህወሃት ለራሱ ድብቅ ዓላማ ሊጠቀምበት ያሰበ ስለመሆኑ ሲነገር ቆይቷል፡፡ “ህዳሴ” (ዳግም ልደት – renaissance)፣ “ትልቅ ነበርን ትልቅ እንሆናለን”፣ … እየተባሉ የሚለፈፉ መፈክሮች የኢትዮጵያን ሳይሆን የአክሱምን ገናናነት እንደገና እንዲወለድ በማድረግ በድጋሚ ትልቅ ለመሆን የተወጠነ ነው በማለት የሚከራከሩ፤ ትግራይ ካለ ዓቅሟ የምታካሂደው የኢኮኖሚ፣ የትምህርት፣ የወታደራዊ፣ ወዘተ “ልማታዊ እንቅስቃሴ” በተያያዥነት ሊጠቀስ እንደሚገባ በአስረጂነት ይጠቅሳሉ፡፡
ኤርትራ የትግራይ ታሪካዊ አካል ስለመባሏ አስተያየት የተጠየቀ በአውሮፓ የኢሳያስ ተቃዋሚ ኃይሎች አመራር አባል የሆነ የኤርትራ ተወላጅ የዴንማርክ ነዋሪ “እኛና የትግራይ ህዝብ አብርን ልንኖር አንችልም። ምኞታቸው ይገርማል። ከሚመለከታቸው ጋር ተነጋገሬ አስተያየት እሰጣለሁ” የሚል መልስ ሰጥቷል።
ህወሃት ታላቋን ትግራይ የመመስረት (ነጻ የማውጣት) ፕሮግራም ይዞ የሚንቀሳቀስ ተገንጣይ ድርጅት ነው።

No comments:

Post a Comment