Translate

Friday, August 31, 2012

የዋልድባ አብረንታንት መነኰሳት መሰደድ ጀምረዋል



  • ባለፉት ጥቂት ቀናት ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት ተሰደዋል
  • “ታጋይ ገድላችኹ እናንተ አትኖሩም” (የፀለምት - ማይ ፀብሪ ወረዳ ሓላፊዎች)።
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 21/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 27/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በዋልድባ አብረንታንት ገዳም መነኰሳት ላይ ባተኰረውና ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ እየተባባሰ በቀጠለው እስርና እንግልት ሳቢያ ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት የፀለምት - ማይ ፀብሪ የፀጥታ ኀይሎች በሚያደርሱባቸው ግፍ ሳቢያ ወደ ሌሎች ገዳማት መሰደዳቸውን፣ በተቀሩትም አባቶች ላይ ድብደባ እየተፈጸመባቸው መኾኑን የሥፍራው ምንጮች እየገለጹ ናቸው፡፡
የዜናው ምንጮች እንደሚያስረዱት÷ የወረዳው ፖሊሶችና ታጣቂዎች በገዳሙ መነኰሳት ላይ የሚፈጽሙት እንግልትና ድብደባ የተባባሰው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ኅልፈተ ሕይወት መሰማቱን ተከትሎ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽኑ ሕመም እና ኅልፈት ገዳማውያኑን ተጠያቂ በማድረግ ነው፡፡ ቀደም ሲል በየጊዜው እየታሰሩ በተለቀቁት አበው መነኰሳት ላይ ያነጣጠረው ይኸው ርምጃ በአሁኑ ወቅት ደግሞ መነኰሳቱ ጨርሶ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ከማዘዝና ከማስገደድ ጋራ የተያያዘ መኾኑም ተመልክቷል፡፡

Ethiopian POW in Eritrea "could be freed soon"


Colonel Bezabih Petros

Ethiopian prisoners of war (POW) in Eritrea such as Colonel Bezabeh Petros (younger brother of opposition politician Prof. Beyene Petros), Colonel Tadesse Muluneh and many others arrested during the 1998-2000 Ethio-Eritrea border war and other times by the Eritrean regime could soon be freed, a member of the exiled Ethiopian Orthodox synod, His Eminence Abune Mekarios indicated. 

The Abune, who heads Ethiopian Ortodox churches in North America and Asutralia said this in a recent interview he held with ESAT Radio from Eritrea. Abune Mekarios said that he went to Eritrea to seek amnesty for Ethiopian  prisoners arrested in Eritrea from the Eritrean regime.  The religious figure said,

በመለስ ሞት ምክንያት… ሰርግ ተሰረዘ፣ የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ተዛወረ፣ የምሽት ክለቦች ተዘጉ… ሌላስ?


(ኢ.ኤም.ኤፍ) የቀድሞውን ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ ከአዲስ አበባ አካባቢ የሚደርሱን ዘገባዎች በየ እለቱ የሚያስደምሙ ሆነዋል። ከደረሱን ዘገባዎች መካከል… ቴዲ አፍሮ ለአዲስ አመት በጊዮን ሆቴል ሊያደርገው የነበረው የሙዚቃ ዝግጅት ተሰርዟል፤ ላልታወቀ ጊዜ ተዛውሯል። በምሽት አዲስ አበባን ያዳምቁ የነበሩ ክለቦች ሙዚቃ ማጫወት ስለተከለከሉ፤ ደንበኞችም ስለሌሉ በራቸውን ለመዝጋት ተገደዋል። በአዲስ አበባ በየትኛውም ስፍራ የሚገኙ ሙዚቃ ቤቶች መሸጥ እንጂ ሙዚቃ ማጫወት ተከልክለዋል። ታክሲዎች እንደድሮው አዲስ የወጣ ዘፈን መክፈት አይችሉም። ዝርዝሩ በዚህ አይነት ይቀጥላል።
አንድ ነገር እንጨምር። አዲስ አበባ የሚገኘው ዘጋቢያችን የሰርገኞቹን ስም እንዳናወጣ ነግሮናል። ባለፈው እሁድ ስለሆነው ነገር እንዲህ አጫውቶናል። “ሰርገኞች እና ቤተሰብ ለሰርጋቸው ከአመት በላይ ሲዘጋጅ ቆይቷል። ለሰርጉ ስርዓት ማከናወኛም ጦር ኃይሎች ጋር የሚገኘውን የመኮንኖች ክለብ አዳራሽ በ13ሺህ ብር ተከራይተዋል። እናም የሰርጉ ቀን ከመድረሱ በፊት ቦታውን ለማዘጋጀት ሲሄዱ ሰርግ ማድረግ እንደማይችሉ ተነገራቸው።

Thursday, August 30, 2012

ሳይደረጁ እንደርጅ



ከተስፋዬ ዘነበ (ኖርዌይ በርገን)


”አምላክ ሲቆጣ ልምጭ አይቆርጥም ያረጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም”  ይሉ ነበር ልጅ እያለን  አንድ የሰፈራችን አዛውንት ፡፡ ይህው እንግዲህ ለሃገር ለምድር ከብደውም ይሁን? እራሳቸውን አክብደው፣ በህሊና ቢሶችና ለሆዳቸው ባደሩ ጥቂት ሰዎች እስከ መመለክ የደረሱት ፈላጭ ቆራጮች አምላክ ለኢትዮጲያና ለህዝቡዋ አስቦ  ወይም የምድሩን ፍርድ እንዳያዩ እርሱ ፈቅዶ የጥፋት ዘመናቸውን ጨርሰው እስከ እኩይ ስራቸው የፈነጩባትን ምድር ተሰናብተዋል፡፡
እንደ  ሰማነው  ከሆነ እንግዲህ በአብዛኛው የዛኛው መንደር ጉልቤዎች የመቃብር ጠርዝ ላይ ሆነው አንዱ  ለአንዱ ሳይሆን  ሁሉም ለየራሱ እያለቀሰ  እና እያስለቀሰ በሚመስል ሁኔታ አገሪቱን የሙሾ ተቋም አድርገዋታል፡፡

“መለስ መጀመሪያ እናቴን አገባ፤ ቀጥሎ አባቴን አስገደለ” – የክንፈ ገ/መድህን ልጅ በረከት።…አዜብ መስፍንን ለማጽናናት በቤተመንግስት ይገኛል እውነት ለአባቱ ገዳይ ያለቅስ ይሆን ?


ወላጅ እናቱን ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ለመጎብኘት ወደ ቤተ መንግስት እንዳይገባ በደህንነት ሚ/ሩ ጌታቸው አሰፋ የተከለከለው የሟቹ ክንፈ ገ/መድህን የጀመሪያ ልጅ “መለስ መጀመሪያ እናቴን አገባ ቀጥሎ አባቴን አስገደለ፤ መለስ ዜናዊን እፋረደዋለሁ”ብሎ በአደባባይ መናገሩ በርካታ ሲኒየር የሕወሓት አባላትን ማሳፈሩን ሆርን ታይምስ የተባለው መጽሄት ዘገበ።
አቶ መለስ ዜናዊ ከቀድሞው የደህንነት ሚ/ሩ ክንፈ ገ/መድህን የአሁኑ ባለቤቱን አዜብ መስፍንን በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ እንደወሰደ የዘገበው መጽሄቱ በረከት ክንፈ ያን ጊዜ የ2 ዓመት ሕጻን ልጅ ነበር ብሏል።   በረከት ክንፈ ወላጅ አባቱ አቶ ክንፈ ገ/መድህንን በ8 ጥይት መትተው የገዱሉት ሻለቃ ጸሐዬ የመለስ ቀኝ እጅ ናቸው በማለት ለ6 ዓመታት በ እስር ላይ በቆዩበት ጊዜ በተደጋጋሚ ሊጎበኛቸው ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ እንደሆነበርና የሻለቃ ጸሐዬ ባልታሰበ ለሊት ድንገት መገደል ምስጢሩን ለመደበቅ የተደረገ ሙከራ ነው በማለት ጥያቄ ማንሳቱን ሆርን ታይምስ መጽሄት አጋልጧል።

ሳይደረጁ እንደርጅ

Author and writer Tesfaye Zenebe from Norway
ከተስፋዬ ዘነበ (ኖርዌይ በርገን)
30-08-2012
“አምላክ ሲቆጣ ልምጭ አይቆርጥም ያረጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም”  ይሉ ነበር ልጅ እያለን  አንድ የሰፈራችን አዛውንት ፡፡ ይህው እንግዲህ ለሃገር ለምድር ከብደውም ይሁን?
እራሳቸውን አክብደው፣ በህሊና ቢሶችና ለሆዳቸው ባደሩ ጥቂት ሰዎች እስከ መመለክ የደረሱት ፈላጭ ቆራጮች አምላክ ለኢትዮጲያና ለህዝቡዋ አስቦ  ወይም የምድሩን ፍርድ እንዳያዩ እርሱ ፈቅዶ የጥፋት ዘመናቸውን ጨርሰው እስከ እኩይ ስራቸው የፈነጩባትን ምድር ተሰናብተዋል፡፡
እንደ  ሰማነው  ከሆነ እንግዲህ በአብዛኛው የዛኛው መንደር ጉልቤዎች የመቃብር ጠርዝ ላይ ሆነው አንዱ  ለአንዱ ሳይሆን  ሁሉም ለየራሱ እያለቀሰ  እና እያስለቀሰ በሚመስል ሁኔታ አገሪቱን የሙሾ ተቋም አድርገዋታል፡፡

“ቴዲ ለመለስ ነጠላ ዜማ ለመስራት ሀሳብ የለውም”


Tewodross Kassahun Ethiopian pop singer “ቴዲ ለመለስ ነጠላ ዜማ ለመስራት ሀሳብ የለውም” ዘካርያስ ጌታቸው (የቴዲ አፍሮ ማናጀር)

ፍኖተ ነጻነት
ታዋቂው አርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የሟቹን ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት አስመልክቶ ነጠላ ዜማ አዘጋጅቷል መባሉን የድምፃዊው ማናጀርና የአዲካ ኮሙኒኬሽን ሚዲያ ማናጀር ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ አስተባበሉ፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ነሐሴ 15 ቀን 2004 ዓ.ም አቶ መለስ ከዚህ አለም በሞት የመለየታቸውን ዜና መንግስት ይፋ ካደረገ በኋላ ላለፉት ሰባት ቀናት ብሔራዊ ሀዘን መታወጁን ተከትሎ ታዋቂው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የአቶ መለስ ዜናዊን ሀዘን ምክንያት በማድረግ ነጠላ ዜማ ለቋል የሚሉ መረጃዎች ሲሰራጩ ሰንብተዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም ድምፃዊው በብሄራዊ ቤተመንግስት በመገኘት ሀዘኑን ለመግለጽ በሞከረበት ወቅት በስፍራው የተገኘው ህዝብ ጩኽት በማሰማቱ ወደ ውስጥ ሳይዘልቅ እንደተመለሰ ተናግሯል፡፡

ሴተኛ አዳሪዎች በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ


Postby ቅዱስ » Thu Aug 30, 2012 12:34 am
ትናንት በስቲያ ስራ ልገባ እየተጣደፍኩ ስለነበር የላኩላችሁን መልዕክት መልሼ እንኳን ሳላነበው እንደወረደ ነው ጣል አድርጌላችሁ የበረርኩት። በወቅቱ ኢቲቪን እያየሁ ስሜቴ ክፉኛ ተጎድቶ ስለነበር የሰዓቱ ነገር ባይገድበኝ ውስጤን ያላውሰው የነበረውን ስሜት በቀላሉ ከትቤ የምጨርሰው አልነበረም። ታዲያ ዛሬ ኢትዪ ትዪብ ድረ ገጽ ላይ “የአዲስ አበባ ጎዳና ተዳዳሪዎች በአቶ መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ” የሚለውን የኢትዮጵያን ቴሌቭዥን ዘገባ ስመለከት እነበረከት የተቆጣጠሩት ስርዓት ምን አይነት ጨዋታ በመጫወት ላይ እንዳሉ ወለል ብሎ ታየኝና መፅናናት ያዝኩ። ሕዝባችን በግዴታ ሃዘኑን እንዲገልጽ የተላለፉት የጥሪ ደብዳቤዎችንም አንዳንድ ድረ-ገፆች ላይ ለመመልከት ችያለሁ።

ይህ ከአሳዛኝነቱ ይልቅ አስቂኝነቱ የሚጎላው የዜና ዘገባ፣ የኢቲቪ ጋዜጠኞች ብቃት ምን ያህል የወረደ መሆኑን ከማመላከቱ በተጨማሪ ለምስል ቀረፃው የመረጧቸው የጎዳና ተዳዳሪ ተብዬዎች ፊት ላይ የሚነበበው ስሜትና በእጅጉ የሚያደምም ሆኖ ነው ያገኘሁት። እኛ የምናውቀው አዲስ አበባ ላይ በርሳቸው ዘመን ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ላይ ጎዳና ላይ እንኳን ማደር እየተከለከሉ እየተከለከሉ ሲሳደዱ ነው። በተለይም አላሙዲ ፒያሳ ላይ እስካሁን አጥሮ ያስቀመጠው ቦታ አጥር ስር ከነቤተሰባቸው ለዓመታት ተጠልለው ይኖሩ የነበሩ ምስኪን ወገኖቻችን መጨረሻ ላይ የመንግስት ታጣቂዎች በምን አይነት መልኩ ከቦታው ላይ እየደበደቡ እንደነቀሏቸው ምንጊዜም የማይረሳኝ የቅርብ ጊዜ ትዝታዬ ነው።

I am happy for the death of Zenawi, Says Gebremedhin Aray

I am happy for the death of Zenawi, Says Gebremedhin Aray

የጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የአገዛዝ ዘመን እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ


በመጀመሪያ የአክብሮት ሰላምታዬን እያቀረብኩ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ውስጥ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መርማሪ በመሆን ለስምንት አመታት ሳገለግል በቆየሁበትEthiopian pm Meles Zenawi ጊዜ ካገኘሁት መረጃና ልምድ በመነሳት በጠ/ሚ መለስ ዜናዊ የ21 አመት የአገዛዝ ዘመን በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጸሙ ዋና ዋና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የሚዳስስ መጠነኛ ጽሑፍ አዘጋጅቼ ከአባሪ ሰነዶች ጋር በማያያዝ ልኬያለሁ። ለሕዝብ እንድታደርሱልኝ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
ከታላቅ ምስጋና ጋር!
ያሬድ ኃይለማሪያም
የቀድሞ የኢሰመጉ የምርመራ ሰራተኛ

Woyane Cadres are saying “Meles Zenawi is Jesus Christ”


TPLF cadres are working hard to portray Dictator Meles Zenawi as a Jesus like figure soon after his death. At AwassaMeles Zenawi is Jesus Christ University in Southern Ethiopia, Eskindir Loha, a Wolayta Woyane cadre, has been telling students that “Meles is Jesus” and students needed to workship him as such. When two students refused to accept this ridiculous assertion by Eskindir Loha, they were beaten and put in prison.
Two days later, Mulugeta Jarso, a well known Ethiopian gospel singer, who refused to accept Meles as a Jesus like figure was told to sing about Meles in his gospel songs. When Mulugeta Jarso refused, he was also beaten and put in prison in the town of Leku in Southern Ethiopia. Several people in Yirgalem, Dila, Shebedino and Alata Wondo have refused to accept Meles as Jesus and they are currently suffering because of their stand against the TPLF cadres.
These are developing stories and we will update you with more information.
Abdissa Aga from Southern Ethiopia

Wednesday, August 29, 2012

INTERVIEW WITH DR GETACHEW BEGASHAW 26 AUGUST 2012


ESAT Ethiopian News August 29, 2012


የመድረኩ ሊቀመንበር ስለ አቶ መለስ ዜናዊ ምንም አይነት ምስክርነት እንዳልሰጡ ገለጡ::


ነሀሴ ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ጋዜጠኞች የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ የሰጠሁትን የሐዘን መግለጫ ወደ ጎን ጥለው የራሳቸውን የፈጠራ ድርሰት አዘጋጅተው አስተላልፈዋል ሲሉ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን እንዳሻው ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
አቶ ጥላሁን የሀዘን መግለጫውን ባስተላለፉበት ወቅት የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ጋዜጠኞች ስለ ጠቅላይሚኒስትሩ የስራ ሁኔታ አስተያየት ለመቀበል ጥያቄ አቅርበው ጥያቄያቸው ተቀባይነት እንደሌለው በመግለፅ ምንም አይነት አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን መግለጻቸውን አውስተዋል።
የማዕከሉ ሰዎች ግን ከሌሎች ሚዲያዎች በተለየ ሁኔታ የራሳቸውን የፈጠራ ድርሰት በማዘጋጀት ከእርሳቸውም ሆነ ከመድረክ አቋም ጋር ተፃራሪ የሆኑ ኀሳቦችን ማስተላለፋቸውን ገልፀዋል። “የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ሰዎች እኔየሰጠሁትን መግለጫ በመተው የራሳቸውን ኀሳቦች በማካተት እጅግ አስነዋሪ በሆነ መልኩ በእኔ ስም ፅፈው ነሐሴ 23 ቀን 2012(እ.ኤ.አ) በኢንተርኔት ድረ-ገፃቸው ላይ ለቀውት መመልከት ችያለሁ” ያሉት አቶ ጥላሁን፤ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሄራልድ ጋዜጣ ይህንኑ ጠቅሶ ነሐሴ 24 ቀን 2012 እትሙ መዝገቡን ገልፀዋል።

መኢአድ ህዝብ የሥልጣን ባለቤት የሚሆንበት ኮንፈረንስ እንዲጠራ ጠየቀ::


ነሀሴ ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያ ህዝብ በኢህአዴግ አገዛዝ እየተፈፀመበት ካለው አፈናና ረገጣ ተላቆ በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበት ሁሉን አቀፍ ኮንፈረንስ እንዲጠራ ሲል የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጥያቄ አቀረበ።
ፓርቲው ሰሞኑን ባቀረበው ጥሪ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የተቋቋሙ ፓርቲዎች በሙሉ እንዲሁም ሲቪክ ማኅበራት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ አርሶ አደሮች፣ነጋዴዎች፣ ሠራተኞችና የገዢው ፓርቲ ተወካዮች እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላትም በሀገራዊ ኮንፈረንሱ ላይ ተገኝተው በመመካከር ሀገሪቱ ወደ ሁከትና የእርስ በርስ ብጥብጥ ሳትገባ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን መፍትሄ ሊያበጁ ይገባል ብሏል።
በኮንፈረንሱ ላይም ህዝብን ከእልቂት ኢትዮጵያንም ከውድቀት ለማዳን የሚችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ይደረጋል።
በሚዘጋጀው ብሔራዊ ኮንፈረስ ላይ ተሳታፊዎች ያለፉትን ጊዜያት ፖለቲካዊ ሁኔታዎች በመገምገም አዲስ የፖለቲካ አቅጣጫዎችን የመቀየስ፣ አሁን ያሉትን የኢህአዴግ ኃላፊዎች ለመተካት ጊዜያዊ የሽግግር ካውንስል መምረጥ እና መተካት፣ለሙስሊሞች እና ለመምህራን ጥያቄ ምላሽ መስጠት፣ የዋልድባ ገዳም ይዞታ በነበረበት እንዲመለስ የማድረግ የመፍትሄ ሀሳብ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ በተጨማሪም ከቴሌ ኮሙኒኬሽንና ከሌሎችም መስሪያ ቤቶች የተባረሩ ሰራተኞች ወደ ስራቸው እንዲመለሱ እንዲሁም ገለልተኛ የሆኑ የፍትህ ተቋማት፣ የሚዲያና የማስታወቂያ ተቋማት፣ የብሔራዊ ምርጫ አስተባባሪ እና የደህንነት ተቋም ይቋቋማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ፓርቲው ገልጿል።

የአዲስ አበባ አስተዳደር የኮንዶሚኒየም ቤቶች ባለዕድለኞችን ዝርዝር “አገሪቱ ሐዘን ላይ ናት” በሚል ለሕዝብ እንዳይሰራጭ አገደ፡፡


ነሀሴ ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የአዲስ አበባ አስተዳደር የጠ/ሚኒስትር መለስ ሞት ጋር በተያያዘ በዕጣ የለያቸውን የኮንዶሚኒየም ቤቶች ባለዕድለኞችን ዝርዝር “አዲስ ልሳን” የያዘውን ጋዜጣ “አገሪቱ ሐዘን ላይ ናት” በሚል ለሕዝብ እንዳይሰራጭ አገደ፡፡
ነሃሴ 13 ቀን 2004 ዓ.ም በሕዝብ ፊት በአዲስአበባ ማዘጋጃ ቤት ለ7 ሺ 300 የኮንዶሚኒየም ዕድለኞች ዕጣ የወጣ ሲሆን ዕድለኞች የዕጣውን ውጤት ከአዲስአበባ አስተዳደር ድረገጽ መመልከት ወይም የአስተዳደሩ ልሳን በሆነው
“አዲስልሳን” በተባለ ጋዜጣ ላይ ሲወጣ ጠብቀው መመልከትና በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አስፈላጊውን ፎርማሊቲ እንዲያሟሉ ተጠይቀው ነበር፡፡
ሆኖም የጠ/ሚኒስትር መለስ ሞት ነሐሴ 15 ቀን በይፋ መነገሩን ተከትሎ ነሐሴ 19 ቀን 2004 ዓ.ም የታተመውና የኮንዶሚኒየም ባለዕድለኞችን ዕጣ የያዘው ጋዜጣ ከቀብር በፊት ለሕዝብ እንዳይሰራጭ በመወሰኑ ሕትመቱ ወደመጋዘን እንዲገባ ተደርጎአል፡፡ በአስተዳደሩ ድረ ገጽ  ላይም “በቅርብ ቀን ይጠብቁ” የሚል መረጃ በማስቀመጥ ዕጣው ይፋ ሳይሆን ቀርቶአል፡፡
ምንጫችን አስተዳደሩ ይህን እርምጃ የወሰደው በአ/አ ከተማ ከ300ሺ በላይ ሕዝብ ኮንዶሚኒየም ተመዝግቦ ዕጣ የሚጠባበቅ በመሆኑ ዕጣው ይፋ ቢደረግ የጠ/ሚኒስትሩ ሞት የሕዝብ ትኩረት ሊያጣ ይችላል ከሚል ሥጋት የተነሳ መሆኑን ጠቁሞአል፡፡
ነሐሴ 13 ቀን 2004 ዕጣቸው የወጣው ቤቶች አስተዳደሩ በልደታ መልሶ ማልማት እና በሌሎች ነባር ሳይቶች የገነባቸውን 7ሺ300 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሲሆኑ ቤቶቹ የተገቡት በልደታ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ ቦሌ፣ ኮልፌ ቀራንዮ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ አዲስ ከተማ፣ ቂርቆስና የካ ክፍለ ከተሞች ውስጥ ነው።

እንግዲያስ የመለስ ገዳይ ማነው… ኢህአዴግ አይደለምን!?

እንግዲያስ የመለስ ገዳይ ማነው… ኢህአዴግ አይደለምን!?
አቤ ቶኪቻው
ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህመም ዋና ምክንያት ሆኖ ከመንግስት ባለስልጣናት የተነገረን “የስራ ጫና እና ረጅም ግዜ የቆየ የስራ ኃላፊነት ነው።” እኛም አምነናቸዋል። እንኳንስ ይሄንንና “መለስ ከመስከረም በፊት ይመጣል” ሲሉም “አምነናቸዋል” እነርሱም የሚሆነውንም የማይሆነውንም ነገር የሚነግሩን “እንደምናምናቸው” ርግጠኞች ስለሆኑ ነው። ታድያ ለምን እናሳፍራቸዋለን…!? “እንመናቸው” እንጂ!
ሰባኪው ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስብከቱን ቀጥሏል።
“መለስ ጌታ ነው!” እያለን ይገኛል። “ሁሉ በእርሱ ሆኗል።” በማለትም የተለያዩ “ማስረጃዎችን” ሊነግረን እየተጋ ነው። እንግዲህ የዚህ ጥቅሙ ምን ይሆን!? በስማቸው ቤተስኪያን እንድናቋቁም ታስቦ ይሆንን? ግራ ነው የሚያጋባው፤ ብቻ የሆነው ሆኖ በኢትዮጵያችን የሁሉ ነገር ፈላጭ ቆራጭ መለስ እንደነበሩ ቴሌቪዥናችን አረጋግጦልናል።

Bahir Dar University forced to attend Zenawi’s memorial services


Dear Editors, I hope you all are alright.
Bahir Dar University Zenawi’s memorial services
I am certain that you are following the drama which is orchestrated by the shameless TPLF cadres. It is pretty obvious that tyrant Meless Zenawi is the most hated person in Ethiopia. However, as you can follow the everyday activity in Ethiopia now, the TPLF cadres are trying to paint the Butcher’s ugly picture in a positive way though it is a futile attempt. History know Meless not only as a tyrant, but also as the first leader in the world’s history who hates the country he rules. Thus far in world’s history there was no a leader who bitterly hated his own country that he ruled except tyrant Meles Zenawi

ESAT: Ethiopian Defence Engineering College Corporal(CPL) Nigusu Worku Ethiopia


እንግዲያስ የመለስ ገዳይ ማነው… ኢህአዴግ አይደለምን!?


ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህመም ዋና ምክንያት ሆኖ ከመንግስት ባለስልጣናት የተነገረን “የስራ ጫና እና ረጅም ግዜ የቆየ የስራ ኃላፊነት ነው።” እኛም አምነናቸዋል። እንኳንስ ይሄንንና “መለስ ከመስከረም በፊት ይመጣል” ሲሉም “አምነናቸዋል” እነርሱም የሚሆነውንም የማይሆነውንም ነገር የሚነግሩን “እንደምናምናቸው” ርግጠኞች ስለሆኑ ነው። ታድያ ለምን እናሳፍራቸዋለን…!? “እንመናቸው” እንጂ!
ሰባኪው ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስብከቱን ቀጥሏል።
“መለስ ጌታ ነው!” እያለን ይገኛል። “ሁሉ በእርሱ ሆኗል።”  በማለትም የተለያዩ “ማስረጃዎችን” ሊነግረን እየተጋ ነው። እንግዲህ የዚህ ጥቅሙ ምን ይሆን!? በስማቸው ቤተስኪያን እንድናቋቁም ታስቦ ይሆንን? ግራ ነው የሚያጋባው፤ ብቻ የሆነው ሆኖ በኢትዮጵያችን የሁሉ ነገር ፈላጭ ቆራጭ መለስ እንደነበሩ ቴሌቪዥናችን አረጋግጦልናል።

የዋልድባ አብረንታንት መነኰሳት መሰደድ ጀምረዋል


  • ባለፉት ጥቂት ቀናት ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት ተሰደዋል
  • “ታጋይ ገድላችኹ እናንተ አትኖሩም” (የፀለምት - ማይ ፀብሪ ወረዳ ሓላፊዎች)።
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 21/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 27/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በዋልድባ አብረንታንት ገዳም መነኰሳት ላይ ባተኰረውና ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ እየተባባሰ በቀጠለው እስርና እንግልት ሳቢያ ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት የፀለምት - ማይ ፀብሪ የፀጥታ ኀይሎች በሚያደርሱባቸው ግፍ ሳቢያ ወደ ሌሎች ገዳማት መሰደዳቸውን፣ በተቀሩትም አባቶች ላይ ድብደባ እየተፈጸመባቸው መኾኑን የሥፍራው ምንጮች እየገለጹ ናቸው፡፡
የዜናው ምንጮች እንደሚያስረዱት÷ የወረዳው ፖሊሶችና ታጣቂዎች በገዳሙ መነኰሳት ላይ የሚፈጽሙት እንግልትና ድብደባ የተባባሰው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ኅልፈተ ሕይወት መሰማቱን ተከትሎ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽኑ ሕመም እና ኅልፈት ገዳማውያኑን ተጠያቂ በማድረግ ነው፡፡ ቀደም ሲል በየጊዜው እየታሰሩ በተለቀቁት አበው መነኰሳት ላይ ያነጣጠረው ይኸው ርምጃ በአሁኑ ወቅት ደግሞ መነኰሳቱ ጨርሶ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ከማዘዝና ከማስገደድ ጋራ የተያያዘ መኾኑም ተመልክቷል፡፡

Ethiopia After Meles Zenawi – (analysis)


Ethiopian Dictator Meles ZenawiThe death of Prime Minister Meles Zenawi on 20 August has triggered a constitutional succession mechanism which he personally designed, having led the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front for 21 years. His chosen successor, Hailemariam Desalegn, takes over in the first non-violent transition in Ethiopia’s modern history.
Hailemariam was Deputy Prime Minister, Foreign Minister and Deputy Chairman of the EPRDF.
An EPRDF Executive Committee meeting on 21 August endorsed his leadership and agreed to set aside any differences for now. He had been expected to take over only in 2015, when Meles was due to retire.

Tuesday, August 28, 2012

ESAT DC Daily News August 28 2012


ኃይለማሪያም ሆይ ቶሎ ና!


Abe Tokchaw
ኢትዮጵያን ላለፉት ሃያ አንድ አመታት የገዙት መለስ ዜናዊ አሁን በሞት የተነሳ ከስልጣናቸው ገለል ብለዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሀዘን የሚገልፁ አንዳንድ ግለሰቦች ሲናገሩ “አንድ ቀን እንኳ ሳያርፉ… እንዲሁ እንደለፉ… አለፉ” በማለት ሲቆጩ ተመልክቻለሁ። ይሄ ነገር ነቀፌታ ነው ወይስ ውዳሴ ነው የሚለውን ለማወቅ ገና ጥናት እያደረግሁ ነው።
ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ 21 ዓመታት “ሀገሪቷን ከኔ በቀር የሚመራት የለም” በማለት በስልጣን ላይ ቁጭ ብለው መክረማቸው እኔ እንዳመላከተኝ ከሆነ ትልቅ ስህተት ነው። (ምንም ማድረግ አይቻልም ካመላከተኝ እንግዲህ መናገር ነው…) ከእርሳቸው ውጪ የሆኑ ሰዎችም ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን እንደሚችሉ ስልጣኑን ለቀው ቢያሳዩን ኖሮ ዛሬ ሲሞቱ ሰማይ የተከደነብንን ያኽል ባልተሰማን ነበር።  (እሺ ይሄንን እንተወው ሙት መውቀስ አግባብ አይደለም!)

የፖለቲካ እስረኞች፤ በመለስ ሞት የተነሳ ማስፈራሪያ እየተደረገባቸው ነው!


የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲነገር ሌላው ሲያለቅስ አንተ ስቀሃል ተብሎ አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚአብሔር በእስር ቤት መደብደቡን ሰምተን ተደንቀናል። ተሳቀናልም።
አሁንም እስር ቤት ከሚገኙ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች አካባቢ እየተሰማ ያለው ነገር ይህንኑ የሚያጠናክር ነው። ስሙን ከምገልፅላችሁ ባልገልፅላችሁ የሚሻል አንድ የተፈረደበት ጋዜጠኛ በፊት ከታሰረበት ቦታ የተዛውረ ሲሆን “ጠቅላይ ሚኒስትሩን እኛ የገደልናቸው ይመስል ከባድ የሆነ ማስፈራሪያ እና ዛቻ እየደረሰብን ነው!” ሲል ሊጠይቁት ለሄዱ ቤተሰቦቹ ተናግሯል።
ባለፈው ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙ የዋልድባ መነኮሳት “መለስን እንዲታመም ያደረጋችሁት እናንተ ናችሁ መተተኞች” እየተባሉ በፖሊስ እንደተደበደቡ ሰምተን ተገርመናል። እንግዲህ አሁንም መገረማችንን እንቀጥላለን ማለት ነው!
እስቲ ቸር ያሰማን!
ይህ በእንዲህ እንዳለ አርብ ዕለት ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹን እንዳያገኝ ተከልክሎ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ቅዳሜ እና እሁድ ወዳጆቹ እና ቤተሰቦቹ ሊጠይቁት መቻላቸውን ሰምቻለሁ።

የምናዉቀዉ ህወሀት ዘመን ላይመለስ አክትሟል፤ በፍስሀ አሸቱ (ዶ/ር)


በፍስሀ አሸቱ (ዶ/ር)
ጊዜ የማያሳየን ነገር የለም፤ ትግስት ካለና አምላክ ከፈቀደ ደሞ የማይሆን ነገር የለም። እስኪ ራሳችንን ወደሗላ መለስ ብለን ሥድስት ወራት በምናባችን እንመለስና ጊዜን የሗልዮሽ እንቃኘዉ። በዚያን ግዜ እኔ ለዉጥ በምን ያክል ቅበጽነትና ሁኔታ ሊመጣ እንደሚችል አናዉቅም፤ ሰርገኛ መጣ ብለን ከምንሯሯጥ ተሰባስበን ለማናቸዉም አጋጣሚ እንዘጋጅ ብዬ ስናገር በርካቶች ሰዉዬዉ አበደ እንዴ ሲሉ ነበር። አንዳንዶቹ አስጠንቁሏል ሲሉ፤ ሌሎቹ ደሞ የሚያዉቀዉ ነገር አለ እያሉ በትንታኔ ዉድ ጊዜን አሳለፍን። ወደፊት ሄደን ዛሬ ላይ ቆም ብለን ያለፉትን ስድስት ወራት ስንመለከት ለማመን የሚያስቸግሩ ስንት ታአምሮች አየን። እኛ ስንዳክር አምላክ ግን ስራዉን ሰራና ታምራቱን አሳየን። እስኪ ስንቶቻችን ነን መለስ ለዚህ ይበቃል ብለን ቅንጣት እንኳን ጥርጣሬ የነበረን? የአቡነ ጳዉሎስና አጠቃላይ የሃገሪቱ ጉዳይስ? ሁሉም ነገር ፈጽሞ የማይታመንና እምነት ካለ የማይሆን ነገር እንደሌለ በተጨባጭ ያየንበት የበረከት ወቅትን አሳልፈናል። የዚህ ጽሁፌ አላማ ስለህልፈተ መለስ ወይንም አሁን እየታየ ስላለዉ ቴያትር ግለሰባዊ ትንተና ለመስጠት አይደለም። በአንጻሩ ግን ከጊዜዉ ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት ስለመጪዉ ሁኔታ እንደ አንድ ዜጋ ሚሰማኝን ለወገኖቼ ለማካፈል ነዉ።

በመለስ አጥንት ይሁንባችሁ፣ አለ በረከት ስሞኦን

Abune Paulos funeral in Ethiopia
ሄኖክ የሺጥላ
የሰሞኑ ዜና እንደ እስር ቤት ወጥ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ይፈጥራል አይደል? ካንዱ ዜና ወደ ሌላው ስሄድ በቃ ግራ ገባኝ… ETV በቃ  ስራ ጀመረ::  እኔ እንደውም ከአሁን በሁዋላ ኢሳትን አልመለከትም::  ምክንያቱም ETV ይግደለኛ::
በመጀመሪያ አቡነ ጳውሎስ እንደ ልደት ኬክ መስታወት ውስጥ ሆነው ብቅ አሉ:: happy birth day የሚል ነገር ለማንበብ ሳተኩር… አንድ  ኮስተር ብሎ የተኛ  ነገር ተመለከትኩ… እንደ አጋጣሚ የኮምፒዩተሬ ድምጽ ማውጫ  (Speaker) ስለተበላሸ… ምስሉን ብቻ ነበር  የተመለከትኩት::

Dagem Ahunem

የአቶ መለስ አስከሬን ለአንድ ወር ሙሉ ከተቀመጠበት ማቀዝቀዣ ፍሪጅ ውስጥ አውጥተው አዲስ አበባ በገባበት ምሽትና ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን አስከሬን በተረከቡበት ወቅት፣ ……. ወይኔ ተቀጣሁ፣ እንኳን ደህና መጣችሁ፣ …… መለስ ግን የለም፣ ….. ቤታችን ቀዝቅዟል፣ …… አልጋው ባዶ ነው፣ ሲሉ የተሰሙት ትራሱን በእጃቸው አቅፈው ይዘው ነበር። በመሪር ሀዘን ውስጥ ለምትገኙት ለአቶ መለስ ዜናዊ ቤተሰቦች፣ ዘመዶች፣ ጓደኞችና ወዳጆች የማቀርበው አንድ መሠረታዊ ጥያቄ አለኝ፤- በአቶ መለስ፣ በሕወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና በእርሳቸው እውቅና (ወ/ሮ አዜብ መስፍን) የወልቃይ ጠገዴ እና ጠለምት ጀግና ሕዝብን የእኩይ ተግባራቸው ተባባሪ ባለመሆኑ ወንዶች እየተመረጡ፣ የአልጋ ቁራኛ (በሽተኛ) ሳይቀር የወያኔ ስቆቃ መፈፀሚያ ባዶ-6 በተባለ እስር ቤት በማጎር በተፈፀመባቸው ስቃይ ብዛት ሰውነታቸው እስኪተላ ተገርፈው ዘር ማጥፋት በሚባል መልኩ የተጨፈጨፉ፣ በ21 ዓመታት ብልሹ አስተዳደር ሳቢያ በወለጋ፣ በአርሲ፣ በጋምቤላ፣ በሶማሊያ፣ በቤንሻንጉል፣ በሐረር፣ በሞያሌ፣ ወዘተ… በብሔርና ጎሳ ግጭት ምክንያት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የአንድ ቤተሰብ አባላት የተጨፈጨፉ፣ ዋጋቢስ ለሆነ ኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በአገር ሉዓላዊነት ስም ተግዘው ደመ- ከልብ የሆኑ፣ በቀናነት አገራቸውንና ወገናቸውን ሲያገለግሉ በአቶ መለስ ዜናዊ ፀጥታ አስከባሪ ተብየዎች በጠራራ ፀሐይ በጥይት የተገደሉት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አመራር የነበሩት የአቶ አሰፋ ማሩ፣ በወያኔ እሥር ቤት ማቀውና በሽተኛ ተደርገው የሞቱት የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን አለኝታ የነበሩት የፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስና የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት አባላትን በማናለብኝና እብ
ሪት የተገረፉ፣ የተሳደዱ፣ በአደባባይ ላይ የተረሸኑና እስካሁንም ያሉበት ያልታወቁ፣ እንደነ ሸብሬ ደሳለኝ ዓይነት ለጋ ወጣቶች፣ ሕፃናት ልጆች፣ ሽማግሌዎችና አሮጊቶች፣ በአቶ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ
ትዕዛዝ ርህራሄና ስብዕና እንደሌለው በሚነገርለት በአረመኔ አጋዚ የትግርኛ ተናጋሪ ቅልብ ወታደር በጎዳና፣ በበር፣ በመጫዎቻ ሜዳ ላይ ጭንቅላት ጭንቅላታቸው እየተመታ የተገደሉ፣ አካላቸው የጎደለ፣ የተገረፉ፣ የተሰደዱና የአዕምሮ በሽተኞች የሆኑበት የ1997 ብሔራዊ ምርጫ ተጎጂዎች፣ በሚደርሰው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ሳቢያ ወደ አረብ አገራት በመሰደድ የሚሰቃዩ፣ ህይወታቸውን የሚያጠፉና በአሠሪዎቻቸው የሚገደሉ ለጋ ሴት እህቶቻችን፣ በአቶ መለስ ዜናዊ አምባገነን አስተዳደር ስቃይ፣ ግርፋት፣እስርና ግድያ ሲሸሹ ውሀ ያስቀራቸውና በሰውነት የውስጥ አካል ነጋዴዎች እየተገደሉ በሰሃራ በረሃ ያለ ቀባሪ አሸዋ ውስጥ ተቀብረው የቀሩ፣ የወያኔው ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለቅፅበት እንኳን ያላያቸው እንዲሁም የትኛውም የዜና አውታር ያልዳሰሳቸው ነገር ግን
ቤት የሚቆጥራቸው፣ በተረሪስት ስም በውሸት ድራማ ተቀናብሮ በቃሊቲ፣ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኘው ቀሌንጦና የተለያዩ እስር ቤቶች ታስረው የሚማቅቁና በእስር ቤቶች በስቃይ ብዛት ህይወታቸው ያለፈ፣ ወዘተ…… ቤተሰቦች፣ አፍቃሪዎች፣ ወላጆች፣ ዘመዶች፣ጓደኞችና ወዳጆችስ ስቃይ፣ መሪር ሀዘን፣ እሮሮ፣ ደም እንባ ማንባት፣ የመሳሰሉት ለአንዲት ሰኮንድ ትዝ ብሏችሁ ያውቅ ነበርን???
እንግዲያውስ እንደናንተው ወይም ከእናንተ እጅግ በላቀ መጠን ተንሰቅስቀዋል፣ ሀዘናቸውን በቀል ለሚመልስ አምላክ ተንበርክከው በዓይናቸው ያሳያቸው ዘንድ አንብተዋል፣ እስካሁንም እያነቡ ይገኛሉ። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ተጎጂ ቤተሰቦች ሐዘን ከአቶ መለስ ቤተሰብ የከፋ የሚያደርገው ወ/ሮ አዜብ መስፍን ሙሾ እንዳወረዱት ዓይነት ብቻ ሳይሆን ልጆች ያለ አሳዳጊ መቅረት፣ የእለት ጉርሳቸውን በማጣት ወንዶች ልጆች የጎዳና ተዳዳሪ መሆንና ሴቶች ልጆቻቸው በመንገድ ዳር በመቆም ክብረ-ሥጋቸውን ለመሸጥ መገደዱ፣ በድህነት ተቆራምደው ያሳደጓቸው ልጆቻቸው በመገደላቸውና ከአረመኔው
ሥርዓት ሲሸሹ ከታሰበበት ቦታ ሳይደርሱ በመንገድ ላይ የቀሩ የስደተኛ እናቶች ጧሪ አልባ መሆን ወዘተ፣ ወዘተ፣ ወዘተ፣….ነው።
ስለዚህ እናንተ የዚህ ሀዘን ተጠቂዎች የሆናችሁና በዚህ ሥርዓት ስም ሕዝብን ያሳዘናችሁና የበደላችሁ ሆይ የኑሮ አጋር ያደረጉት፣ ያፈቀሩት፣ የወደዱት፣ የወለዱትና ያሳደጉት ሲገደል ወይም ሲሞት እንደዚህ ከማሳዘን፣ መሪር እንባ ከማስነባቱም በላይ ብቸኝነትን፣ ጎደሎነትን፣ ረዳት አልባነትን፣ አለመረጋጋትን፣ በሽተኝነትንና እብደትንም ስለሚያስከትል ነገም በእኔ በማለት ካለፈው ስህተት ተምራችሁ በመተሳሰብና በመተዛዘን ለመኖር ፍርድን የማያጓድል እግዚያብሔር ማስተዋልን ይሰጣችሁ ዘንድ ምኞቴ ነው።ኢትዮጵያንና ሕዝቧን እግዚያብሔር ይባርክ!!!!
August 26, 2012,
ፀሐፊውን በ belete_z@yahoo.co.uk ሊደርሱት ይችላሉ፤፤

Wikileaks - Meles Zenawi gets money from Piracy


ስብሐት ነጋ የቀድሞ የህወሓት አመራር አባላትን እያደራጁ ነው


TPLF power broker, Sibehat Negaአውራምባ ታይምስ (አዲስ አበባ) – የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ መስራችና የድርጅቱ የሞራልና የፍልስፍና አባት ተደርገው የሚወሰዱት አቶ ስብሐት ነጋ በ1993 ዓ.ም ክፍፍል ወቅት ከድርጅቱ የተሰናበቱ አባላትን አንድ በአንድ በማነጋገር ድርጅቱ በአዲስ መልክ ህልውናውን እንዲያጠናክር በማደራጀት ላይ እንደሚገኙ የአውራምባ ታይምስ አስተማማኝ ምንጮች ከአዲስ አበባ ገልጸዋል፡፡
‹‹መለስ እራሱን ብቻ ሳይሆን ሀወሓትንም ጭምር ገድሎ ነው የሞተው››Nየሚሉት ስብሐት ነጋ ‹‹በትጥቅ ትግሉ ወቅት የጎላ ድርሻ የነበራቸውና ችግርና መከራን ተጋፍጠው ህወሓት ውስጥ በጽናት የዘለቁ አመራሮች ወደ ጎን ተገፍተው፤ ዛሬ ድርጅቱ የእነ አዜብ መፈንጫ ሆኗል››Nማለታቸውን ጠቅሰው ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

ሰበር ዜና፡ የፍትሕ ዋና አዘጋጅ ክስ ተቋረጠ


BY TAMIRU TSIGE
የፌደራል ዓቃቤ ሕግ በመሠረተበት ሦስት ክሶች ምክንያት ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. ዋስትና ተከልክሎ በማረሚያ ቤት እንዲቆይ የተደረገው የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅሰበር ዜና፡ የፍትሕ ዋና አዘጋጅ ክስ ተቋረጠ ተመስገን ደሳለኝ በዛሬው ዕለት ክሱ እንዲቋረጥ ተደረገ፡፡
ክሱ እንዲቋረጥ ያዘዘው ከሳሹ የፌደራል ዓቃቤ ሕግ ሲሆን፣ ለክሱ መቋረጥ በምክንያትነት ያቀረበው ተጨማሪ ምርመራ አደርጋለሁ በማለቱ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዓቃቤ ሕግ በዛሬው ዕለት ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 16ኛ የወንጀል ችሎት በጻፈው ደብዳቤ በጋዜጠኛ ተመስገን ላይ ያቀረባቸውን ክሶች ማቋረጡን አስታውቋል፡፡ በዚህ መሠረት ተመስገን በዛሬው ዕለት ከእስር እንደሚለቀቅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ክስ የተመሠረተበት በ2003 እና በ2004 ዓ.ም. ራሱ በዘገባቸውና በጋዜጣው ዓምደኞች በተዘገቡ አመፅ ቀስቃሽ ናቸው በተባሉ ሦስት ጽሑፎች ሳቢያ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ፍትሕ ጋዜጣ ሐምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስር መለስ ዜናዊ ሕመም ጋር በተገናኘ ዘገባው ምክንያት ከታተመ በኋላ እንዳይሠራጭ በፍትሕ ሚኒስቴር መታገዱም ይታወሳል፡፡ ጋዜጣው ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት አላትምም በማለቱ ምክንያት ሕትመቱ ተቋርጧል፡፡

Monday, August 27, 2012

የዋልድባ አብረንታንት መነኰሳት መሰደድ ጀምረዋል


  • ባለፉት ጥቂት ቀናት ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት ተሰደዋል 
  • “ታጋይ ገድላችኹ እናንተ አትኖሩም” (የፀለምት - ማይ ፀብሪ ወረዳ ሓላፊዎች)። 
 (ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 21/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 27/ 2012)፦  በዋልድባ አብረንታንት ገዳም መነኰሳት ላይ ባተኰረውና ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ እየተባባሰ በቀጠለው እስርና እንግልት ሳቢያ ከስድስት ያላነሱ መነኰሳት የፀለምት - ማይ ፀብሪ የፀጥታ ኀይሎች በሚያደርሱባቸው ግፍ ሳቢያ ወደ ሌሎች ገዳማት መሰደዳቸውን፣ በተቀሩትም አባቶች ላይ ድብደባ እየተፈጸመባቸው መኾኑን የሥፍራው ምንጮች እየገለጹ ናቸው፡፡

የዜናው ምንጮች እንደሚያስረዱት÷ የወረዳው ፖሊሶችና ታጣቂዎች በገዳሙ መነኰሳት ላይ የሚፈጽሙት እንግልትና ድብደባ የተባባሰው የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ኅልፈተ ሕይወት መሰማቱን ተከትሎ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽኑ ሕመም እና ኅልፈት ገዳማውያኑን ተጠያቂ በማድረግ ነው፡፡ ቀደም ሲል በየጊዜው እየታሰሩ በተለቀቁት አበው መነኰሳት ላይ ያነጣጠረው ይኸው ርምጃ በአሁኑ ወቅት ደግሞ መነኰሳቱ ጨርሶ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ ከማዘዝና ከማስገደድ ጋራ የተያያዘ መኾኑም ተመልክቷል፡፡

ESAT DC Daily News 27 August 2012 Ethiopia


ESAT News 28 August 2012 Ethiopia


ወ/ሮ አዜብ በለቅሶ ላይ በሚወረውሯቸው ድንገተኛ ቃላቶች የተበሳጨው ኢህአዴግ ፣ ከካሜራ ቀረጻ ውጭ እንዲሆኑ አዘዘ::


ኢሳት ዜና:- (Aug. 28) የአቶ መለስ ዜናዊን እረፍት ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ድራማ እየሰራ ያለው ኢህአዴግ፣ ወ/ሮ አዜብ ከካሜራ ቀረጻ ውጭ እንዲሆኑ ለጋዜጠኞች ትእዛዝ ማስተላለፉ ታውቋል።
በተወሰነ ጊዜ ሰው በሚሰባሰብበት ሰአት ላይ ብቅ እያሉ የሚያለቅሱት ወ/ሮ አዜብ መስፍን፣ በድንገት በሚወረውሩት ቃላት ያልተደሰተው ኢህአዴግ ከካሜራ ቀረጻ ውጭ እንዲሆኑ ማድረጉን ታማኝ ምንጮቻችን ገልጠዋል።
ወ/ሮ አዜብ መስፍን በለቅሶአቸው ጊዜ የሚያወጡዋቸው ቃላቶች የኢህአዴግ ባለስልጣናትን ክፉኛ እያበሳጨ፣ በመካከላቸውም ጥርጣሬ እንዲፈጠር እያደረገ መሆኑን ነው ምንጫችን የገለጡት።
የአቶ መለስ ሁለተኛ ልጅ የሆነችው ማርዳ መለስ በበኩሏ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና የግል ሚዲያ ጋዜጠኞች እናቱዋን በሚቀርጹበት ሰአት የግል ጠባቂዎቿን ጠርታ ከቤተመንግስት ተገፍትረው እንዲወጡ ማስደረጉዋን የአይን እማኞች ለኢሳት ዘገባ ገልጠዋል።

ከአቶ መለስ ሞት ጋር በተያያዘ በበርካታ ዜጎች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመ እንደሚገኝ ተገለፀ።


ኢሳት ዜና:- (Aug. 28) የአብዴፓ ፕሬዚዳንት ተደብድበዋል፤የአንድነት ፓርቲ አባላትም እየታሰሩ ነው።
በቂሊንጦ እስር ቤት፡የሚገኙት የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ ዘሪሁን ገብረ እግዚአብሔር፦“መለስ መሞታቸው በቴሌቪዥን በተነገረበት ጊዜ ሌሎቹ ሲያለቅሱ፤ አንተ ስቀሀል” ተብለው ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።
አቶ ዘሪሁን ከደረሰባቸው ከፍተኛ ድብደባ ብዛት ፊታቸው አባብጦና መንቀሳቀስ አቅቷቸው ሲያነክሱ መታየታቸውን ነው ፍኖተ-ነፃነት ቤተሰቦቻቸውን ጠቅሶ የዘገበው።
ለምን ይህ  ዘግናኝ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ሲጠይቁ፦ “ገና እንገለዋለን!” መባላቸውንም ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።
ቤተሰቦቻቸው ጠይቀዋቸው ከተመለሱ በሁዋላ  አቶ ዘሪሁን  በሰንሰለት ታስረው እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ከቂሊንጦ እስር ቤት የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል።

ህዝቡ ለአቶ መለስ ሀዘኑን እንዲገልጽ ጫናዎች እየተደረጉበት ነው

(Aug. 27) የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝቡ ሀዘኑን እንዲገልጽ የተለያዩ ጫናዎች እየተደረጉበት እንደሆነ ከኢትዮጵያ የሚመጡት መረጃዎች አስረዱ።
ለጎንደር ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ የተጻፈ ደብዳቤ እንደሚያሳየው የጎንደር ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ በመስቀል አደባባይ ተገኝቶ ሀዘኑን እንዲገልጽ ታዞ እንደነበር ታውቋል።
በዚህም መሰረት፤ ባለፈው አርብ በጎንደር መስቀል አደባባይ በተዘጋጀው የሀዘን መድረክ ላይ፤ የመንግስት ሰራተኞች በሙሉ ከስራ መግቢያ ሰዓት ቀደም ብለው ከጠዋቱ 1 ሰዓት ከ40 ጀምሮ በስራ ገበታቸው በመገኘት፤ ወደ ሀዘን ስፍራው እንዲሄዱ ተነግሯቸዋል።
በደብዳቤው ላይም፤ በእለቱ ምንም አይነት ስራና ትምህርት እንደማይኖር የተጠቀሰ ሲሆን፤ ሰራተኞችና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ፤ የሀዘን መግለጫ ልብስ ለብሰው እንዲመጡም ማሳሰቢያ እንደተሰጣቸው ደብዳቤው ያሳያል።

A Farewell to Meles Zenawi


by Alemayehu G. Mariam
For over two hundred seventy five weeks, without missing a single week, I have written long expository commentariesThe cause of Meles Zenawi's death remains a closely guarded state secret on the deeds and misdeeds of the man who has been at the helm of power in Ethiopia for over two decades. Meles Zenawi has now passed on. The cause of his death remains a closely guarded state secret.
There is little I can say about what Meles has done or not done in death that I have not said in life. But his death saddens me, because as John Donne said, “Any man’s death diminishes me, because I am involved in Mankind. Death comes equally to us all, and makes us all equal when it comes.” As a committed human rights advocate, even the death of a tyrant diminishes me because I am involved in the cause of  humanity– justice, fairness, equality, dignity, benevolence, compassion, forgiveness, honesty, integrity and magnanimity.

‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ለቅንጅት ሰዎች የተወሰኑ የሚኒስትርነት ቦታዎችን ለመስጠት ቃል ገብተውልን ነበር››


1_256
ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ፣ የአገር ሽማግሌዎች ኅብረት ሊቀመንበር
የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዜና ዕረፍት ከተነገረበት ከነሐሴ 14 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሊያስብል በሚችል ሁኔታ ሐዘናቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ በአፍሪካና በዓለም ላይ ያሉ መሪዎችም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት ተከትሎ የሐዘን መግለጫቸውን በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ቆንስላዎቻቸው አማካይነትና በተለያዩ የዜና አውታሮች እየገለጹ ይገኛሉ፡፡
የኢትዮጵያ የአገር ሽማግሌዎች ኅብረትም ነሐሴ 16 ቀን 2004 ዓ.ም. በሸራተን ሆቴል ለተለየዩ የመገናኛ ብዙኅን የሐዘን መግለጫውን አስተላልፏል፡፡ በዛሬው የቆይታ አምዳችን ላይ እንግዳ ያደረግናቸው የ75 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ የሆኑትን ምሁርና የኢትዮጵያ የአገር ሽማግሌዎች ኅብረት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅን ነው፡፡ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር የተዋወቁበትን ጊዜና እስከ ዕረፍተ ዜናቸው ድረስ የነበራቸውን ግንኙነትና ስለሳቸው ያላቸውን አስተያየት በሚመለከት ታምሩ ጽጌ አነጋግሯቸዋል፡፡

የምናዉቀዉ ህወሀት ዘመን ላይመለስ አክትሟል በፍስሀ አሸቱ (ዶ/ር)

ጊዜ የማያሳየን ነገር የለም፤ ትግስት ካለና አምላክ ከፈቀደ ደሞ የማይሆን ነገር የለም። እስኪ ራሳችንን ወደሗላ መለስ ብለን ሥድስት ወራት በምናባችን እንመለስና ጊዜን የሗልዮሽ እንቃኘዉ። በዚያን ግዜ እኔ ለዉጥ በምን ያክል ቅበጽነትና ሁኔታ ሊመጣ እንደሚችል አናዉቅም፤ ሰርገኛ መጣ ብለን ከምንሯሯጥ ተሰባስበን ለማናቸዉም አጋጣሚ እንዘጋጅ ብዬ ስናገር በርካቶች ሰዉዬዉ አበደ እንዴ ሲሉ ነበር። አንዳንዶቹ አስጠንቁሏል ሲሉ፤ ሌሎቹ ደሞ የሚያዉቀዉ ነገር አለ እያሉ በትንታኔ ዉድ ጊዜን አሳለፍን። ወደፊት ሄደን ዛሬ ላይ ቆም ብለን ያለፉትን ስድስት ወራት ስንመለከት ለማመን የሚያስቸግሩ ስንት ታአምሮች አየን። እኛ ስንዳክር አምላክ ግን ስራዉን ሰራና ታምራቱን አሳየን። እስኪ ስንቶቻችን ነን መለስ ለዚህ ይበቃል ብለን ቅንጣት እንኳን ጥርጣሬ የነበረን? የአቡነ ጳዉሎስና አጠቃላይ የሃገሪቱ ጉዳይስ? ሁሉም ነገር ፈጽሞ የማይታመንና እምነት ካለ የማይሆን ነገር እንደሌለ በተጨባጭ ያየንበት የበረከት ወቅትን አሳልፈናል። የዚህ ጽሁፌ አላማ ስለህልፈተ መለስ ወይንም አሁን እየታየ ስላለዉ ቴያትር ግለሰባዊ ትንተና ለመስጠት አይደለም። በአንጻሩ ግን ከጊዜዉ ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት ስለመጪዉ ሁኔታ እንደ አንድ ዜጋ ሚሰማኝን ለወገኖቼ ለማካፈል ነዉ። 

Seyoum Mesfin, Sufian Ahmed and Indrias Eshete critically ill

Elias Kifle | August 27th, 2012
Indrias EsheteUPDATE: A local newspaper is reporting that Prof Indrias Eshete is dead. Read here.
Acting head of the ruling TPLF junta in Ethiopia, Seyoum Mesfin, Finance Minister Sufian Ahmed and former Addis Ababa University President Indrias Eshete are critically ill, according to an Ethiopian Review correspondent in Addis Ababa.
The armed forces chief of staff Samora Yenus is also sick and unable to attend meetings, our sources are reported.

ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ጠቅላይ ሚንስትሩን ተከትለው ሄደዋል መሞታቸው በአዲስ አበባ በስፋት እየተነገረ ነው።


ዘንድሮ ወያኔን እና ወያኔን አፍቃሪያን ምን ነካቸው ያሰኛል በከፍተኛ አመራሮች ላይ ክፉኛ የሞት ጥላ ጥላውን አድርቶባቸዋል።በዚህ ወር ብቻ ሶስት ታላላቅ ወያኔ እና ወያኔ አፍቃሪያንን በሞት ጥላ ተነጥቀናል። የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚዳንት ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ከዚህ አለም በሞት ተለየ ፣በአዲስ አበባ በአሁን ሰአት በከፍተኛ ደረጃ እየተናፈሰ ያለው ወቅታዊ ወሬ ከመለስ ዜናዊ ሞት ባሻገር  የፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ መሞት እንደሆነ ተገልጾአል ። ለረጅም ዘመን በበሽታ ሲሰቃይ የከረመው አንድርያስ እሸቴ የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አማካሪ በመሆን ሲያገለግል ነበር  ። በአዲሱ የአፍሪካ ህብረት መሰረተ ድንጋይ ሲጣል የአፍሪካ የሰበአዊ መብቶች ጥሰትን የሚያስታውሰውን ማእከል ለመገንባት ጊዜአዊ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠው ነበር ።

የ21 ዓመታት መከራን ያላገናዘበ የወ/ሮ አዜብ መስፍን መሪር ሀዘን፡ በፍቅሬ ዘለቀው (ኖርዎይ)




የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ም/ቤት ታማኝ ምንጮችን ጠቅሰው የአቶ መለስ ዜናዊን ዜና እረፍት ካወጁ እነሆ ከአርባ ቀናት በላይ አለፈው። ይሁን እንጂ አቶ በረከት ስምዖን የሚመሩት የኮምኒኬሽን ሚኒስቴር ቢሮ ሲያቀናብረውና ሲያሰራጨው ከነበረው የውሸት ድራማ፣ አይቀሬነቱ ደርሶ እነሆ በ15/12/04 ዓ.ም ውዥንብር ውስጥ ከተውት ለነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ተደርጓል። ይህንንም ተከትሎ የአቶ መለስ ቤተሰቦች፣ ዘመዶች፣ ወዳጆች፣ ደጋፊዎችና የስርዓቱ ተጠቃሚዎች መሪር ሀዘናቸውን እየገለፁና በማስገደድ እያስለቀሱን ይገኛሉ።
የኢህአዲግ አጋር የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የክልል መስተዳድር አካላት፣ በአምሳላቸው ተጠፍጥፈው የተሰሩ የተለያዩ የሲቪክ ማህበራት ሐላፊዎች፣ የመንግስት ሠራተኞች፣ ታዋቂ ነጋዴዎች፣ ግለሰቦችና ከመቼውም በላይ በሥርዓቱ ተጠቂ የሆኑውን ብዙሀን ማሕበረሰብ በካድሬዎች እየተገደዱ፣ እንደ ጣዖት ለሚያመልኩት መሪያቸው ሕዝቡን በማስፈራራት በርሀብ በጠበሰ አንጀት እያስለቀሱና ድራማ እያሰሩት ይገኛሉ።

የመለስ ዜናዊ ለቅሶ ድራማ እና ዘላቂው መፍትሄ


Ginbot 7 weekly editorialየዘረኛውና የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ መሞት በይፋ ታወጀ። ቤተሰቦቹና ባልደረቦቹ፤ አጨብጫቢዎችና አስመሳዮች እና በርካታ የዋህ ዜጎች  ሃዘናቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።
የመለስ ዜናዊ ሞት እወጃን ጨምሮ አብዛኛው ነገር የተለመደ ድራማ መሆኑ ቢታወቅም እንኳን፣ ደጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ “ነብስ ይማር፤ እግዚአብሄር ያጥናችሁ” ማለቱ አልቀረም።
የለቅሶው ድራማ ሰሜን ኮሪያን ቢያስታውሰንም እዚያ ከነበረው በላይ የሚያሳምም ነገር አለው።

ህወሃት – በሞተ አባቱ በሬ ዝና የሚኖር ጥጃ!


ላለፉት ሃያ አንድ አመታት የወያኔ ቁንጮ የነበረው መለስ ዜናዊ ሞት በመንግስት ደረጃ ይፋ ከተደረገ እነሆ ቀናት ተቆጥረዋል።ይሁንና በአንድ ሰው አምባገነንነት ላይ የተመሰረተው
Dawit Fanta Author and writer
Dawit Fanta /Eng./
የወያኔ መንግስት ከወዲሁ ግራ መጋባቱን የሚያሳብቁ ሁኔታዎች ከመከሰታቸውም ባሻገር ይህንን የዕውር ድንብር ግራ መጋባት ለመሸፈንና ብሎም በቀጣይ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት /Legitimacy/ ለማግኘት ወያኔ እየወሰደ ያለውንና ሊወስድ እየተዘጋጀባቸው ስላሉ እርምጃዎች እና የእርምጃዎቹን የአጭር እና የረጅም ጊዜ አንድምታ መፈተሽ የዚህ ፅሑፍ ዋና አላማ ይሆናል።

የፖለቲካ እስረኞች፤ በመለስ ሞት የተነሳ ማስፈራሪያ እየተደረገባቸው ነው!


አቤ ቶኪቻው

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲነገር ሌላው ሲያለቅስ አንተ ስቀሃል ተብሎ አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚአብሔር በእስር ቤት መደብደቡን ሰምተን ተደንቀናል። ተሳቀናልም።የፖለቲካ እስረኞች፤ በመለስ ሞት የተነሳ ማስፈራሪያ እየተደረገባቸው ነው!
አሁንም እስር ቤት ከሚገኙ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች አካባቢ እየተሰማ ያለው ነገር ይህንኑ የሚያጠናክር ነው። ስሙን ከምገልፅላችሁ ባልገልፅላችሁ የሚሻል አንድ የተፈረደበት ጋዜጠኛ በፊት ከታሰረበት ቦታ የተዛውረ ሲሆን “ጠቅላይ ሚኒስትሩን እኛ የገደልናቸው ይመስል ከባድ የሆነ ማስፈራሪያ እና ዛቻ እየደረሰብን ነው!” ሲል ሊጠይቁት ለሄዱ ቤተሰቦቹ ተናግሯል።
ባለፈው ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙ የዋልድባ መነኮሳት “መለስን እንዲታመም ያደረጋችሁት እናንተ ናችሁ መተተኞች” እየተባሉ በፖሊስ እንደተደበደቡ ሰምተን ተገርመናል። እንግዲህ አሁንም መገረማችንን እንቀጥላለን ማለት ነው!
እስቲ ቸር ያሰማን!
ይህ በእንዲህ እንዳለ አርብ ዕለት ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹን እንዳያገኝ ተከልክሎ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ቅዳሜ እና እሁድ ወዳጆቹ እና ቤተሰቦቹ ሊጠይቁት መቻላቸውን ሰምቻለሁ።

ዘመቻ ተመስገን ድስ አለኝ


ከተጠቀምንበት ትንሽ ቀዳዳ ይታየኛል።
ከምርጫ 97 በሗላ በአደባባይ ምንም አይነት ተቃውሞ ማድረግ ለወያኔ ካልሆነ ክልክል ነው። ሰልፍ ለለቅሶም የሁን ለተቃውሞ ወያኔዎች ብቻ ናቸው ባደባባይ የሚሰለፉት። ያለንTemesgen Desalegn Feteh newspaper editorአማራጭ የነሱን የሰልፍ ጠሪ ተቃውሟችንን ለማሰማት መጠቀም ነው። ቀብሩ ከተጠቀምንበት ከታላቁ ሩጫ የሚሻል አጋጣሚ ነው። ከደህንንት አኳያም ለምንቃወመው ይመረጣል።
በሬሳው ምክንያት ህዝብ በአደባባይ ወጥቶ  ሀዘኑን እንዲገለጽ በማስገደድ ላይ ናቸው። ታዲያ ምን ችግር አለው ለማመን ቢሚያስቸግር ብዛት ወጥቶ እሬሳው ላይ እንደፈለጉት አፈር ማልበስ ነው። ሬሳውን ለፖለቲካ መጠቀሙን እነሱ ስለጀመሩት አያስወቅሰንም።

Sunday, August 26, 2012

በመለስ ዜናዊ ሞት ደስታዋን የገለጸችው ወጣት በአደባባይ ተገደለች


ባሳለፍነው ሳምንት የህይወት እልፈታቸውን የሰማነው የህወሃት ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር እና የኢትዮጵያ የቁጭ በሉ ጠቅላይ ሚንስትር የሆኑትን የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት አስመልክቶ ከፍተኛ እና ሳዛኝ ዜና ከሃገራችን የደረሰን ሲሆን በደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች መካከልም ከፍተኛ ቅራኔን እየፈጠረ ነው ። በተለይም  የጠቅላይ ሚንስትሩን ሞት የዜናን እወጃ ስመልክቶ እንኳን ሞተ ጨካኝ ነበር በማለት የውስጥ ፍላጎቷን በድንገተኛ ሰሜት የገለጸችውን ወጣት ከሜሪካ ለጉብኝት የሄደው የወያኔ ቀንደኛ ደጋፊ እየተዝናኑ ባሉበት ካፍቴሪያ ውስጥ  በጠርሙስ ጭንቅላቷ ላይ በመምታት የገደላት መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል ።በ21ኛው ክፍለ ዘመን የፖለቲካ ልዩነታቸውን አቻችለው መኖር ሲገባቸው በግልፍተኝነት እና በማን አለብኝነት የሚደረገው የግፍ አስተዳደር ህዝብን ከጭቆና የማያወጣ መሆኑ ይታወቃል።

በኢትዮጵያችን የጨለማው ዘመን አብቅቶ የብርሃን ጎህ እንዲቀድ


አንዱ አምባገነን አልፎ በሌላው እየተተካ የመከራውና የችግሩ ዘመን ሳያቋርጥ ሕዝብ ፍዳውን ሲያይ የኖረባት ሀገራችንን የሚገዛው የዘመናችን አገዛዝ፣ በመለስ ዜናዊ ቁንጮነት የጨለማETHIOPIAN FLAGዕድሜውን ከጀመረ ሃያ አንድ ዓመት አለፈው። ይህ አምባገነን ቡድን በሥልጣን ላይ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲን ተቀብያለሁ፣ እንዲሁም የሰብዓዊ መብትን አከብራለሁ እያለ ቢመጻደቅም፣ ይህ ሁሉ ከተፃፈበት ወረቀት በላይ የማያልፍ ለመሆኑ የአገዛዙ የሃያ አንድ ዓመታት እኩይ ተግባራት ምስክሮች ናቸው። የዛሬይቱ ኢትዮጵያችን በዴሞክራሲና በሰብዓዊ መብት መከበር ምትክ፤ የመሰብሰብ፣ የመጻፍ፣ የመናገር፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ፣ በአጠቃላይም ዜጎች ሃሳባቸውን በነጻነት የመግለጽና የመደራጀት መብቶቻቸው የታፈኑባትና የአንድ ፓርቲ አምባገነንነት የሠፈነባት፤ የፍትህ አካላት የዜጎችን ደህንነት ከመጠበቅ ይልቅ የመጨቆኛና የማፈኛ መሣርያ በሆኑበት ሁኔታ ላይ ትገኛለች።

Bereket Simon forcing Teddy Afro to sing for Meles Zenawi

Elias | August 25th, 2012
Teddy AfroWoyanne propaganda chief Bereket Simon, aka Addis Bob, sent his goons to pressure popular Ethiopian singer Teddy Afro to sing a song in memory of the deceased dictator Meles Zenawi, Ethiopian Review has learned.
Teddy has two choices: 1. Sing praises of the genocidal dictator and stay safe for now, but be hated for ever by the people of Ethiopia; or 2) Not sing and get harassed and persecuted by the Woyanne junta. Teddy has so far chosen to stay loyal to the people, unlike Haile Gebreselassie and other Ethiopian celebrities who have betrayed the people of Ethiopia for Woyanne crumbs.
Meanwhile, TPLF junta security forces are roaming the streets of Addis Ababa and other cities forcing people to set up tents, hang the late dictator’s photos, and beat their chest. The scene in Gonder today, in particular, was bizarre — some thing that could be right out of the Twilight Zone. Wealthy Woyanne businessman were observed going to Tej Bet (bars) and pay azmaris (singers) to come up with songs for Meles, Ethiopian Review contact in Gondar reported.

ዜና እና ደብዳቤ፤ በሀዋሳ ከተማ የአቶ መለስን ፎቶግራፍ ሲያሳይ የነበረ “ስክሪን” በመብረቅ ተመታ!


አንድ ወዳጄ አሁን ከሀዋሳ ባደረሰኝ መልዕክት በሐዋሳ መስቀል አደባባይ የመለስን ፎቶግራፍ እና ቪዲዮ ሲያሳይ የነበረ ስክሪን በመብረቅ ተመቷል። እንደው መረጃውን ላድርሳችሁ ብዬ እንጂ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም የምሰጠው አስተያየት የለኝም።
ሀዋሳ ካልኩ አይቀር እና ከመጣሁ አይቀር ግን ትላንት ከዚሁ ከሀዋሳ የደረሰኝ ኢሜል “እንደ ወረደ” እንደሚከተለው ይቀርባል።

በሕግ አምላክ! ፓትሪያሪክ በህይወት እያለ ሌላ ፓትሪያሪክ አይሾምም! ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል


መግቢያ:
አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያሪክ የሆኑት አባ ጳውሎስ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨገ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ድንገተኛና አነጋጋሪ ሞት ተከትሎ መንበሩ በማን ይተካለሚለው ጥያቄ ባለፈው ሳምንት ፓትሪያሪክ መርቃሪዮስ ወደ መንበራቸው ይመለሱ!” ስል ለንባብ ማብቃቴ የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ስርዓትና ቀኖና በጠበቀ መልኩ በምትካቸው ከነባር ሊቃነ ጳጳሳት መካከል መርጣ መሾምና ሹመቱንም ማጽደቅ አዲስ ነገር አይደለም። ሆነም ግን የቤተክርስቲያኒቱ መሪዎች የውጭ ተጽእኖዎችና እክሎች በሚገባ መቋቋም ተስኖአቸው ከከፈቱት ክፍተት የተነሳ ላለፉት ፪፰ ዓመታት ለሰሚ በሚያሳፍር መልኩ እርስ በርስ ሲተረማመሱና መሪው ወደ ወሰደው የሚሄደው ሕዝብም ሲታመስ እዚህ መድረሳቸው የሚታወስ ሆኖ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ግን የቤተክርስቲያን መሪዎች በሚወስዷቸው እርምጃዎችና በሚያስተላልፍዋቸው ውሳኔዎች ቀደም ሲሉ የተፈጠሩ ችግሮች በመቅረፍ ረገድም ሆነ በአንጻሩ ጉዳዩን በማወሳሰብ ቁልፍ ሚና መጫወታቸው የማይቀር ነው።