Translate

Monday, August 27, 2012

ዘመቻ ተመስገን ድስ አለኝ


ከተጠቀምንበት ትንሽ ቀዳዳ ይታየኛል።
ከምርጫ 97 በሗላ በአደባባይ ምንም አይነት ተቃውሞ ማድረግ ለወያኔ ካልሆነ ክልክል ነው። ሰልፍ ለለቅሶም የሁን ለተቃውሞ ወያኔዎች ብቻ ናቸው ባደባባይ የሚሰለፉት። ያለንTemesgen Desalegn Feteh newspaper editorአማራጭ የነሱን የሰልፍ ጠሪ ተቃውሟችንን ለማሰማት መጠቀም ነው። ቀብሩ ከተጠቀምንበት ከታላቁ ሩጫ የሚሻል አጋጣሚ ነው። ከደህንንት አኳያም ለምንቃወመው ይመረጣል።
በሬሳው ምክንያት ህዝብ በአደባባይ ወጥቶ  ሀዘኑን እንዲገለጽ በማስገደድ ላይ ናቸው። ታዲያ ምን ችግር አለው ለማመን ቢሚያስቸግር ብዛት ወጥቶ እሬሳው ላይ እንደፈለጉት አፈር ማልበስ ነው። ሬሳውን ለፖለቲካ መጠቀሙን እነሱ ስለጀመሩት አያስወቅሰንም።

የጊዜ እጥረት ይኖራል መሞከሩ ግን አይካፋም። ኪሳራም ያሌለው ጉዳይ ነው። ህዝብ በገፍ ለቀብሩ እነዲወጣ መንገሩን ካዛሬ ይጀመር። እንዳሉት ቤተመንግስትም  ለመፈረም እንዲጎርፍ ቢደረግ ጥሩ ነው። ጉዳዩ መረጃ የማድረስ አቅማችንንም መፈተሻም ይሆናል። ወያኔዎች ከሬሳው ድራማ ጀርባ ልቡ ከዚህ መንግስት ጋር ያልሆነውን ህዘብ(ተቃዋሚውን) ለመለት እየተጠቀሙበት ስለሆነ  እርምጃው የህዝባችንን ደህንንተ ከመጠበቅም አኳያ ጠቀሜታ አለው። እዝንተኛው ቀድሞ ልዩ የሚያደርጋችሁን አለባበስም ሆነ ምንም ነገር ማድረግን  አያስፈልጋቸውም። መለያ አደባባዩ ላይ መፍጠር ይቻላል።
የነሱን መድረክ ለተቃውሞ ምጠቀሙ ውጤታማ እንደሆነ በውጪ አገር ያሉ ወገኖቻችን በተለያየ ጊዜ ተጠቅመውበት አይተናል። ባገር ቤት በጠበበ ሁኔታ ውስጥ በታላቁ ሩጫ ተደጋግሞ ተሞክሮ ሰርቷል። ይህ ሙከራ የተለየ ውጤት ባያስገኝም  ባህሉ ለማሳደግ የጠቅማል።
መቃወም ማለት የተለየ ያልተለመደ ነገር ማድረግ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። ቅዱስ ግብርኤልን ባስራ ሁለት ማንገስም ሆነ ለቀብር ወጥቶ እልል ማለት ተቃውሞ ሊሆን ይችላል። ውጤታማ የሚያደርገው ተቃውሞ ሆኖ እንዲሰማ መደረግ መቻሉ ነው።  የግድ እንደግብፆች ለሳምንታት አደባባይ  መቀመጥ የለብንም። ትንሽ ልትባል የምትችል ነገር ግን ፈንግል የሆነች ተቃውሞ የሁለት አውራ ባላንጣችንን ፍጻሜ እንዳረገች መዘንጋት የለብንም። ለዛው አንድ ደፋር ዜጋ በግሉ የደረገው ተቃውሞ። ስለዚህም ሁሌም ማጨናነቁ ጥሩ ነው።
ይህ የህዝብ ማሟቂያ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሊሆን ይችላል። ወጥታችሁ ቅበሯቸው ነው የቅስቀሳው መፈክር።
ካመኑበት ሀሳቡን የመግፋት አቅሙ ያለው መወያያ መድረኮች አካባቢ ስለሆነ ፈጣን ከሆነ ውሳኔ ጋር ተነጋገሩበትና እባካችሁ ግፉት።
ልንሞክረው ከወሰንን ለለውጥ የሚታገሉ ሜዲያዎች እገዛ እንደሁሌውም ይኖራል። ያሉን መረጃ ማድረሻ መንገዶች በሙሉ ሀይለቸው መጠቀምም አለብን። በድጋሚ ኪሳራ የለውም።
ሰርካለምንም የተመስገንንም እናት ፎቶቸውን ይዘው ቀብሩ ላይ ለናገኛቸው እንችላለን።
ደንፎ ከአዋሳ።

No comments:

Post a Comment