Translate

Monday, August 27, 2012

የመለስ ዜናዊ ለቅሶ ድራማ እና ዘላቂው መፍትሄ


Ginbot 7 weekly editorialየዘረኛውና የአምባገነኑ መለስ ዜናዊ መሞት በይፋ ታወጀ። ቤተሰቦቹና ባልደረቦቹ፤ አጨብጫቢዎችና አስመሳዮች እና በርካታ የዋህ ዜጎች  ሃዘናቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።
የመለስ ዜናዊ ሞት እወጃን ጨምሮ አብዛኛው ነገር የተለመደ ድራማ መሆኑ ቢታወቅም እንኳን፣ ደጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ “ነብስ ይማር፤ እግዚአብሄር ያጥናችሁ” ማለቱ አልቀረም።
የለቅሶው ድራማ ሰሜን ኮሪያን ቢያስታውሰንም እዚያ ከነበረው በላይ የሚያሳምም ነገር አለው።
ንጹሃን ዜጎችን በማሰቃየትና በመግደል የሚታወቁ፤ ትኩስ የሰው ደም በእጃቸው ላይ ያለ የወያኔ ሹማምንት በአለቃቸው ሞት ሲያነቡ ማየት የሚያስተዛዝብ ብቻ ሳይሆን የሚያሳዝን ነው። ይህ ተግባራቸው ብቻውን እነሱ “ሰው” ብለው የሚጠሩት ፍጡር የኢትዮጵያ ሕዝብን በሙሉ የማያጠቃልል መሆኑ ማረጋገጫ ነው። ለዚህም ነው ያለአንዳች ርህራሄ ህፃናትን ሲጨፈጭፉ የኖሩ ፋሽስቶች ለጌታቸው ሞት በአደባባይ ሲያነቡ የሚታዩት። እነዚህ ጨካኞች በየጎዳናውና በየጥሻው በግፍ ገድለው የጣሏቸው ኢትዮጵያዊያን፤ አሁንም በግፍ በየእስር ቤቱ ያጓሯቸው ንጹሃን የሚያዝኑና የሚያለቅሱ ቤተሰቦች  ያሏቸው መሆኑ አይታሰባቸውም።  የእነሱ ዘር አባል ያልሆነ፤ አሊያም ለእነሱ ያልገበረ ሁሉ “ሰው” አይደለምና ህመሙ አይታያቸውም፤ ለቅሶው አይሰማቸውም። ለእነሱ  “ሰው” ማለት የእነሱ የሆነ ሰው ማለት ብቻ ነው። እነሱ “ሰው” ከሚሉት ውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ መረገጡ፣ መገረፉ፣ መገፋቱ፣ መፈናቀሉ፣ መጋዙ፣ መገደሉ ተገቢ ነገር ነው። ከእነሱ አንዱ አደጋ ከደረሰበት ግን የሚያሳዝንና የሚያስለቅስ ነገር ነው። ይህ ነው በመለስ ዜናዊ የለቅሶ ድራማ ውስጥ እያየነው ያለ ሃቅ።
አዎ መለስ ዜናዊ ሞቷል። እሱ የዘረጋው ዘረኝነት እና ዘረኛ ፓሊሲው የቆመባቸው የአፈና መዋቅር አብረውት አልሞቱም። በዘር ተሰባስበው በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚያላግጡ፤ ሃገርን የሚግጡና የሚረግጡ ግለሰቦች ቡድን ዛሬም በስልጣን ላይ ነው። መለስ የዘራው የዘረኝነት መርዝ መዘዙ ብዙ ነው። ይህ መርዝ ነቅለን ካልጣን በስተቀር ከመለስ ሞት በኋላም ቢሆን በማኅበረሰባችን እና በሃገራችን ላይ ጉዳት ማድረሱ ይቀጥላል። ዘረኝነት በሁሉም ቦታ – በለቅሶም ጭምር – ኢትዮጵያዊያንን ማዋረዱ የማይቀር ነው። የመለስ አገዛዝ ከመለስ ዜናዊ ጋር እስካልቀበርነው ድረስ የሚደርስብን ጥቃት ይጨምር እንደሆነ እንጂ አይቀንስም። ስለሆነም ከዘረኝነት ጋር የገጠምነው ትግል አጠናክረን መቀጠል ግዴታችን ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ መለስ ዜናዊ ከጫነበት የዘረኝነት እና የባርነት ስቃይ ሳይገላገል የመለስ ዜናዊን ሞት ከቁብ ቆጥሮ ከጀመረው የነፃነትና የእኩልነት ትግል የሚዘናጋበት ምክንያት የለውም። የኢትዮጵያ ሕዝብ በመለስ ዜናዊ ሞት ዙሪያ የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገራት ጥቅም ተካፋዮቹ የሚሰሩትን ትዕይንት በማየትና በመስማት የሚያጠፋው ግዜ ሊኖር አይገባም።
በግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እምነት፣ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ ትኩረት መሆን ያለበት መለስ ዜናዊ ጥሎት የሄደው አፋኝና ዘረኛ ሥርዓት መለስ ዜናዊን ተከትሎ ወደ መቃብር እንዲሄድ ትግሉን ማጠናከር ነው። አሁን ትግላችንን የምናፋፍምበት እንጂ “በነፍስ ይማር” ከንፈር የምንመጥበት ጊዜ አይደለም።
ስለሆነም ግንቦት 7:

No comments:

Post a Comment