Translate

Friday, August 24, 2012

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ሞት ምክንያት ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግላጫ



አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

ቁጥር አንድነት /592/2ዐዐ4
        ቀን 16/12/2ዐዐ4 ዓ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ሞት ምክንያት

 ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

 የተሰጠ የሃዘን መግለጫ

እኛ እንደ ተቃዋሚ ፓርቲም ሆነ እንደ ዜጋ ሁልጊዜም የአገር ደህንነት፤ የሕዝብ ሠላም መረጋጋት፣ ብልጽግናና ነፃነት ያሳስበናል፡፡ ያስጨንቀናል፡፡ በመሆኑም ለሕዝቦች እኩልነት ወንድማማችነትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ በአለንበት ፈታኝ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ በድንገት ሕይወታቸው በማለፉ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እየገለጽን እግዚአብሔር መጽናናትን እንዲሰጣችሁ እንመኝላቸዋለን፡፡
በዚህ አጋጣሚ ኢህአዴግና በእሱ የሚመራው መንግሥት በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ ሕጋዊና ሠላማዊ የሥልጣን ሽግገር እንዲያከናውን እየጠየቅን የአገርን ልዑአላዊነት ደህንነት የሕዝብን ሠላምና መረጋጋት የማስጠበቅ ታሪካዊና አገራዊ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዲወጣ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡
ሠላምና ብልጽግና
ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ እንመኛለን!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ነሐሴ 16 ቀን 2ዐዐ4 ዓም
አዲስ አበባ
የቢሮ ስልክ  ዐ11 8 4ዐ ዐ8 11   ፖሣቁ 4222
  

No comments:

Post a Comment