Translate

Saturday, November 24, 2012

ኢትዮጵያ አደጋ ውስጥ ከገቡ አገሮች ተርታ ተመደበች



-ፎሬን ፖሊሲ መጋዚን ባወጣው የፌልድ ሰቴትስ ኢንዴክስ ኢትዮጵያን ከአለም አገሮች በ17ኛ ደረጃ በማስቀመጥ፣ለአደጋ የተጋለጠች አገር ሲል ፈርጇታል። ለኢትዮጵያ ህልውና አስጊ ሆነው ከቀረቡ ችግሮች መካከል የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የስደተኞች መብዛት፣ የህዝብ ብሶቶች መጨመር፣ ዜጎች አገራቸውን ጥለው መሰደድ፣ የፖለቲካ መሪዎች ልዩነት እና የጸጥታ ሀይሎች ጣልቃ ገብነት የሚሉት ይገኙበታል።
ከሁለት አመት በፊት ኢትዮጵያ እንደ ዘንድሮው ሁሉ በ17 ኛ ደረጃ ላይ ትገኝ የነበረ ሲሆን፣ አምና ግን ደረጃዋን በማሻሻል ወደ 20ኛ ዝቅ ብላ ነበር።

 በዚህ አመትም በአገሪቱ ውስጥ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መክፋቱን መረጃው ያሳያል። ከአንድ እሰከ 20 ባለው ዝርዝር ውስጥ የሚገኙ አገሮች የመፈራረስ አደጋ ያንዣበበባቸው አገሮች ናቸው። ሶማሊያ አሁንም በቀደማነት ትመራለች። ኤርትራ ከአንድ እስከ 20 ካሉት አገሮች ተርታ በመውጣት በ23 ደረጃ ላይ ትገኛለች።
አዲሱ መረጃ የኢትዮጵያን ማህበራዊ እና ኢኮሚያዊ ችግሮች እያሻሻልኩ፣ አገሪቱን ወደ መካከለኛ ገቢ ለማሳደግ ግስጋሴ ላይ ነኝ ለሚለው የመለስ መንግስት የሚያቀርበውን ተደጋጋሚ ፕሮፓጋንዳ የሚቃረን ነው። የኢትዮጵያ ህለውና ከጊዜ ወደ ጊዜ አደጋ ውስጥ መውደቁን አለመቃፉ የግጭቶች አስወጋጅ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት መግለጹ ይታወሳል። በቅርቡ አሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንትም ለኢትዮጵያ ህለውና አደገኛ የሆኑ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና እና የጎሳ ግጭቶችን በዝርዝር አቅርቧል።

No comments:

Post a Comment