Translate

Sunday, November 18, 2012

ዜና ኮሚክ፤ ሰዎችን ያሰሩት፤ የሚኪና ታርጋዎችን ፈቱ!

Abe Tokchaw

ዜና ኮሚክ፤ ሰዎችን ያሰሩት፤ የሚኪና ታርጋዎችን ፈቱ!

ዛሬ ቃሊቲ ማሰሪያ ቤት አካባቢ በበርካታ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተሞልታ ነበር። ያው እንደሚታወቀው እስር ቤቷ ውስጥ ደግሞ ብዙ ፍትህ ናፋቂ ወዳጆቻችን ተቆልፎባቸው የለ…! እናም እነርሱን ለመጠየቅ ነበር እጅግ ብዙ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን ወደ እስር ቤቱ አጥር የሄዱት።
አካባቢውም በበርካታ መኪና እና ባለመኪና ተሞላ። ይሄንን የተመለከተ መንግስትም በብስጭት ተሞላ። ከዛም ትራፊክ ፖሊስ ላከ ትራፊኩም በአካባቢው የሚገኙ መኪኖችን ታርጋ ፈታ! ሰዉም አለ፤ “ታርጋ ከምትፈቱ የታሰሩትን ፍቱ!”
ዜና ኮሚክም ትመክራለች፤ አረ መንግስታችን እባክህን መቅሰፍት አትሁንብን!
ፎቶውን ከወዳጃችን አንዋር ጅላል ሙዞ ወሰድኩ፤ ደሞም አመሰገንኩ!

No comments:

Post a Comment