Translate

Sunday, November 18, 2012

በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የአዲስ አበባና አጎራባች ከተሞች ሙስሊም ወደ ቃላቲ ጉዞውን ቀጥሏል


Seidhusen Hussen say’s
ክርስቲያን ወገኖቻችን ወደ ቃሊቲ ኮሚቲዮቻችንን ሊዘይር ለመጣው ህዝብ ከቤታቸው ውሀ በባልዲ እና በጄሪካን በማውጣት ሙስሊሙን እያጠጡ ይገኛሉ ምንም እንኳን ETV አሸባሪ ናቸው ቢልም ዉሸትነቱ የተረዱ ክርስቲያን ወገኖቻችን ሙስሊሙን በመርዳትና በማገዝ ላይ ናቸዉ አንዴ ተክቢር በሉላቸው!!
Ethiopian Christians serving water for Ethiopian Muslim protesters
***
(ዘግይቶ በደረሰን ዜና መሰረት፣ ወደ ቃሊቲ ውስጥ መገባት ተጀምሯል፡፡)

ወያኔዎች በሙስሊሙ የሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባታቸውን ተከትሎ የተቀሰቀሰው የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ አመጽ አንደቀጠለ ነው።
አመጹን ለማስቆም እንደተለመደው ወያኔዎች የመረጡት መንገድ መግደል፣ ማሰርና በድብደባ አካላዊ ጉዳት መፈጸም ቢሆንም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች “ወይ ፍንክች” ብለው ተቃውሟቸውን ዘዴ እየቀያየሩ ቀጥለዋል።
የመብት ተሟጋች ሙስሊሞች በሶሻል ሚድያ መረብ እየገለጹት እንዳለው ከሆነ በአሁኑ ሰዓት በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በቃሊቲው ማጎሪያ ፊት ለፊት እየተሰባሰቡ ነው። ረፋዱ ላይ የሙስሊሞቹ ቁጥር እጅግ ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል። ሙስሊሞቹ ወደ ቃሊት ማጎርያ እየተመሙ ያሉት የታሰሩ መሪዎቻቸውን ብርታት ለመስጠትና ለአሳሪዎቻቸው (ወያኔዎች) ደግሞ በትግላቸው እንደሚገፉበት ለማሳሰብ ነው።
አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ይህ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ጽናት ለሌሎችም አርአያ ሊሆን ይችላል እያሉ ነው።
ይህ በዚህ እንዳለ ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ጋዜጠኛ አበበ ገላው በድረ-ገጾች ባሰራጨው ጽሁፉ “ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያነሱት የመብት ጥያቄ በማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሊደገፍ ይገባል” ብሏል። አበበ ገላው በዚህ ጽሁፉ ካመላከታቸው እውነታዎች መካከል፣ አሁን በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ እየተደረገ ያለው ጣልቃ ገብነት እና አፈና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያንና ምዕመናን ላይ ባለፉት 20 አመታት ዉስጥ ሲደረግ የነበረና አሁንም በመደረግ ላይ ያለ ነው ብሏል። የአበበ ገላውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።
የሙስሊሞቹን የቃሊቲ ውሎ እየተከታተልን በዚህ ብሎግ ፖስት ላይ እንዘግባለን…

ድምፃችን ይሰማ፣

በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የአዲስ አበባና አጎራባች ከተሞች ሙስሊም ወደ ቃላቲ ጉዞውን ቀጥሏል፡፡ ማረሚያ ቤቱ አስከ አሁን አልተከፈተም፡፡ ሕዝቡ በተለመደው ታጋሽነት የማረሚያ ቤቱን መከፈት በጉጉት እየተጠባበቀ ነው፡፡
Ethiopian Muslims heading to the notorious Qality prison
Ethiopian Muslims heading to Qality prison

No comments:

Post a Comment