Translate

Friday, November 30, 2012

የሁለቱ ም/ጠቅላይ ሚኒሰትሮች ሹመት ህገመንግስታዊ ድጋፍ የለውም ሲሉ አንድ ታዋቂ የህግ ባለሙያ ገለጹ


ኢሳት ዜና:-በሩዋንዳ ተቋቁሞ በነበረው የተበባሩት መንግስታት ድርጅት አለማቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ዋና አቃቢ ህግ በመሆን ያገለገሉት እና በህግ የማስተማር ሙያ ላይ ለረጅም ጊዜ አገልግሎት የሰጡት ዶ/ር ያቆብ ሀይለማርያም ለኢሳት እንደተናገሩት የሁለቱ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት ህገመንግስታዊ ድጋፍ የለውም። ዶ/ር ያቆብ ” የህገመንግስቱ አንቀጽ 75 ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማይኖሩበት ጊዜ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተክቶ እንደሚሰራ ይደነግጋል  እንጅ ከሁለት ወይም ሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች መካከል ተመርጦ አንዱ ይተካቸዋል አይልም” ብለዋልህዳር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ዶ/ር ያቆብ ሹመቱ ከመሰጠቱ በፊት የተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች በጋራ  ተስማምተው ህጉን ማሻሻል ይችሉ እንደነበር ገልጸዋል።
ምናልባት ሌሎች ያልታዩ የህግ ድንጋጌዎች በመኖራቸው በነዚያ ድንጋጌዎች መሰረት የተደረገ ሹመት ሊሆን አይችሉም ወይ ተብለው ለተጠየቁት ዶ/ር ያቆም ፣ ምንም የሚያሻማ ነገር ነገር የለም በማለት መልሰዋል
ኢህአዴግ ስለ ህገመንግስት  መታስ በተደጋጋሚ ይናገራል፣ በዚህ ድንጋጌ ላይ ህገመንግስቱ በግልጽ እንደተጣሰ ተናግረዋል፣ ኢህአዴግ እሞትለታለሁ የሚለውን ህገመንግስት ለምን በአደባባይ ለመጣስ የፈለገ የመስልዎታል በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ደግሞ፣ ዶ/ር ያቆም ኢህአዴግን በመሰረቱ 4 ድርጅቶች መካከል ያለውን የስልጣን ሽኩቻ ለማብረድ ታስቦ ሊሆን ይችላል ብለዋል
አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የህወሀቱን ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልንና የኦህዴዱን አቶ ሙክታር ከድርን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በማድረግ መሾማቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment