Translate

Thursday, August 28, 2014

በድርጅቶች ውህደትና ቅንጅት አገርን ማዳን!!!

በድርጅቶች ውህደትና ቅንጅት አገርን ማዳን!!!

Untitled g7
ኢትዮጵያዊያንን በዘር እና በሀይማኖት ለያይቶን እርስ በርስ እያጋጨን በመግዛት ላይ ያለውን ወያኔን ለማሸነፍ እና ከምትኩም ከራሷ ጋር የታረቀች፤ ፍትህ የሰፈነባት፤ እኩልነት የተረጋገጠባት እና በኃያላን አገሮች እርጥባን ሳይሆን በራሷ አቅም የምትተማመን ጠንካራ ሀገር እንድትኖረን የነፃነትና የዲሞክራሲ ኃይሎት መተባበር እንዳለባቸው ሲነገርና ሲወተወት ቆይቷል። ይሁን እንጂ በህወሓት የከፋፍለህ ግዛው ፓሊሲ እና በፓለቲካ ባህላችን ኋላቀርነት ምክንያት እስካሁን የተደረጉ የትብብር ጥረቶች የተፈለገውን ውጤት ሳያስገኙ ቀርተዋል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ቀድሞ የተደረጉት ጥረቶች የተጠበቀውን ውጤት አለማስገኘት ተስፋ ሳያቆርጠን ከእያንዳንዱ ጥረት ልምድ እየወሰደን የኢትዮጵያዊያን አንድነት እስኪረጋገጥ ድረስ አዳዲስ የትብብር ጥረቶችን ማድረግ ያለብን መሆኑ ያምናል። በዚህም መሠረት የትብብር መርህ ነድፎ ትግል ውስጥ ካሉ ሁሉም የፓለቲካ ድርጅቶች ጋር ሲነጋገር እና ሲደራደር ቆይቷል። እንደሚታወቀው የንቅናቄዓችን አበይት የትብብር መርሆች ሁለት ናቸው። መርህ አንድ፣ ለውጥ እንዲመጣ የምንታገለው ኢትዮጵያ በምትባል አገር ውስጥ መሆኑ ማመን ነው። መርህ ሁለት ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም እርከኖች የመንግሥት ሥልጣን መያዝ የሚገባው በሕዝብ ነፃ ምርጫ ብቻ መሆኑን መቀበል ናቸው።

አነጋጋሪው የዪኒቨርስቲ ተማሪዎች የፖሊሲ ስልጠና

a a u
ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት የኢትዮጵያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሁለት ሳምንታት የፖሊሲ ስልጠና ላይ መሆናቸውን መንግስት አስታውቋል ።
Hauptcampus der Universität Addis Abeba AAU
ነሐሴ 20 የተጀመረው ይኽው ስልጠና ተማሪዎች በግዳጅ የሚሳተፉበት መሆኑን አንዳንድ ተማሪዎችና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይናገራሉ ።መንግሥት ግን ይህን ያስተባብላል ።

በድርጅቶች ውህደትና ቅንጅት አገርን ማዳን!!!


ኢትዮጵያዊያንን በዘር እና በሀይማኖት ለያይቶን እርስ በርስ እያጋጨን በመግዛት ላይ ያለውን ወያኔን ለማሸነፍ እና በምትኩም ከራሷ ጋር የታረቀች፤ ፍትህ የሰፈነባት፤ እኩልነት የተረጋገጠባት እና በኃያላን አገሮች እርጥባን ሳይሆን በራሷ አቅም የምትተማመን ጠንካራ ሀገር እንድትኖረን የነፃነትና የዲሞክራሲ ኃይሎት መተባበር እንዳለባቸው ሲነገርና ሲወተወት ቆይቷል። ይሁን እንጂ በህወሓት የከፋፍለህ ግዛው ፓሊሲ እና በፓለቲካ ባህላችን ኋላቀርነት ምክንያት እስካሁን የተደረጉ የትብብር ጥረቶች የተፈለገውን ውጤት ሳያስገኙ ቀርተዋል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ቀድሞ  የተደረጉት ጥረቶች የተጠበቀውን ውጤት አለማስገኘታቸዉ ተስፋ ሳያስቆርጠዉ ከእያንዳንዱ ጥረት ልምድ እየወሰደ የኢትዮጵያዊያን አንድነት እስኪረጋገጥ ድረስ አዳዲስ የትብብር ጥረቶች መደረግ አለባቸዉ ብሎ  ያምናል። በዚህም መሠረት የትብብር መርህ ነድፎ ትግል ውስጥ ካሉ ሁሉም የፓለቲካ ድርጅቶች ጋር ሲነጋገር እና ሲደራደር ቆይቷል። እንደሚታወቀው የንቅናቄዓችን አበይት የትብብር መርሆች ሁለት ናቸው።  መርህ አንድ፣ ለውጥ እንዲመጣ የምንታገለው ኢትዮጵያ በምትባል አገር ውስጥ መሆኑ ማመን ነው። መርህ ሁለት ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም እርከኖች የመንግሥት ሥልጣን መያዝ የሚገባው በሕዝብ ነፃ ምርጫ ብቻ መሆኑን መቀበል ናቸው።

Wednesday, August 27, 2014

የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን?

(ያልተገራው የማን ብዕር ነው?)

etv

“የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን” የኢዮጵያ ሬድዮና ቴሌቪዥን የሚለውን ቃል ለምን በትእምርተ ጥቅስ እንዳስቀመጥኩት የገባችሁ ይመስለኛል፡፡ ጣቢያው ስሙ እንደሚጠቁመው ለሀገር የብዙኃን መገናኛ ሳይሆን እራሳቸውን በመንግሥት ስም ያደራጁ በአብዛኛው ከሀገርና ከሕዝብ ጥቅም ተፃራሪ የሆነ ጥቅም ፍልጎትና አላማ ያለው ቡድን አላማ ማራመጃ ከሆነ ዐሥርት ዓመታት አልፏልና ነው በትእምርተ ጥቅስ ማስቀመጤ፡፡

፸ ደረጃ


(በውቀቱ ስዩም)
70  dereja


ሣልሳዊ ቴዎድሮስ ወይም “ቴዲ አፍሮ” በሰባ ደረጃ የተባለ(ች) ነጠላ ዘፈን ለቆልናል፡፡
“በሰባ ደረጃ”ን እኔ ስሰማው እልም ያለ የፍቅር ዘፈን ነው፡፡ ፍቅርን ልዩ በሆነ ቦታና ልዩ በሆነ ሥፍራ የሚያሳይ ዘፈን፡፡ በአማርኛ ዘፈን ባህል ውስጥ ቦታን ማስጎብኘት የተለመደ ነው፡፡ “የሐረር ልጅ ነች ወጣቷ/ጀጎል ነው ቤቷ” አይነት ዘፈን ሞልቶናል፡፡ አብዛኛው ያገራችን ዘፋኝ፣ ያስጎብኝነት ሚናም ደርቦ ሲጫወት ኖሯል፡፡ በዚህ ምክንያት ተፈቃሪዋ ሴት ሁሌም ከታሪካዊ ቦታ አጠገብ ለመወለድ ትገደዳለች፡፡

Tuesday, August 26, 2014

የተማሪዎች ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል


(ሥርዓቱን ለ 20ዓመት አይተነዋል መቀየር አለበት!)
Addis_Abeba_University


  • የኢትዮጵያ የባህር በር ለኤርትራ መሰጠቱ ስህተት ነው
  • የኢኮኖሚ እደገቱ እውነት አይደለም
  • የትምህርት ስርዓቱ ወድቋል
  • የተማረ ሰው ክብር አይሰጠውም
አዲስ አበባ ውስጥ ሳውዝ ካምፓስ (ልደታ)፣ አቃቂ (AASTU)፣ ፍቼ የግብርና ኮሌጅ፣ ስድስት ኪሎ፣ አምስት ኪሎ፣ አራት ኪሎ፣ የአዲስ አበባ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስት ትምህርት ክፍልና ሌሎችም አካባቢዎች ከነሃሴ 15 ጀምሮ ስልጠና ላይ የሚገኙ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን እንደቀጠሉ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ተማሪዎቹ ገዥው ፓርቲ አለ በሚለው እድገት፣ የባህር በር፣ የተማረው የማህበረሰብ በሚደርስበት በደል፣ የትምህርት ጥራት፣ የመምህራን የእውቀት ደረጃ ማነስ፣ ድህነትና አጠቃላይ ኢኮኖሚ ውድቀት ላይ ጠንከር ያለ አስተያየትና ተቃውሞ መሰንዘራቸውን ተገልጾአል፡፡

Monday, August 25, 2014

ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል

(ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

better

ጉልበት አራዊት የሚተዳደሩበት ሕግ ነው፤ ሕገ አራዊት የሚባለው አራዊት የሚተዳደሩበት ጉልበት ነው፤ በአራዊት ዓለም ማናቸውም ነገር በጉልበት ያልቃል፤ በሰዎችም መሀከል ጉልበት አድራጊ-ፈጣሪ ሆኖ ጎልቶ ሲወጣ የአእምሮንና የኅሊናን መዳከም ወይም ጭራሹኑ አለመኖር ያመለክታል፤ ጉልበት አለን በማለት፣ ወይም ተመችቶናል በማለት፣ ወይም ጠያቂ የለብንም በማለት የማንኛውንም ሰው ሰብአዊ መብቱንና ሰብአዊ ክብሩን መግፈፍ ሦስት ነገሮችን ያመለክታል፤ አንደኛ ጉልበት እንጂ አእምሮና ኅሊና እንደሌለ፣ ሁለተኛ ጉልበት እንጂ ሕግ እንደማይከበር፣ ሦስተኛ በአንተ ላይ እንዲያደርጉብህ የማትፈልገውን አንተም በሰዎች ላይ አታድርግ የሚለውን ሕግ መጣስን ያሳያል፤ በመጨረሻም፣ ዘግይቶም ቢሆን በራስ ላይ ቅሌትን መጋበዝን ያስከትላል፤ የሌላውን ሰውነት ስናረክስ ሰውነትን በጠቅላላው ማርከሳችን ነው፤ ሰውነትን በጠቅላላው ስናረክስ ራሳችንን ከነጉልበታችን ማርከሳችን ነው፤ ራሳችንን፣ ሰውነታችንን ካረከስን በኋላ ዋጋ የለንም፤ ለራሳችን ዋጋ ከሌለን ለሌለች ሰዎችም ዋጋ አንሰጥም፤ ያኔ ክፉ በሽታ ይይዘናል፤ እግራችን ስር በወደቀ ሰው ስቃይ የምንደሰትና የምንስቅ፣ የምንፈነድቅ  እንሆናለን፤ ያን ጊዜ የለየለት በሽተኛ ሆነናል።

Sunday, August 24, 2014

አስራ አንድ ጋዜጠኞች ተሰደ


(ከላይ ከግራ ወደቀኝ) ቶማስ አያሌው፣ ዳንኤል ድርሻ እና ግዛው ታዬ፣ (ከታች) ሰናይ አባተ እና አስናቀ ልባዊ (Top, left to right) Thomas Ayalew, Daniel Dirsha and Gizawe Taye. (Bottom, left to right) Senay Abate and Asnake Lebawi
በአምስት ሣምንታዊ መጽሔቶችና አንድ ጋዜጣ ላይ የተመሰረተውን ክስ ተከትሎ አስራ አንድ ጋዜጠኞች ለስደት ተዳረጉ። አስራ አንዱ ጋዜጠኞች የተሰደዱት በፍትህ ሚኒስቴር ሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. “የዐመጸ ቅስቀሳና የሐሰት ወሬዎችን በመንዛት ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ ጥረት አድርገዋል” በሚል በተመሰረተባቸው ክስ መሆኑን ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ የደረሰን መረጃ ያስረዳል።
ፍትህ ሚኒስቴር ክስ የመሰረተባቸው ሎሚ፣ ዕንቁ፣ ፋክት፣ ጃኖ እና አዲስ ጉዳይ መጽሔቶች እና አፍሮ ታይምስ ጋዜጦች ሲሆኑ፤ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አስራ አንድ ጋዜጦች ለስደት መዳረጋቸውን ለማረጋገጥ ችለናል።
ተሰዳጆቹ ጋዜጠኞች 1፣ ቶማስ አያሌው (የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተር)፣

Saturday, August 23, 2014

ከወያኔ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስልጠናዎች የተረዳነው:- ወጣቱ ለለውጥ ዝግጁ ነው፤ የቀረው ድርጅት ነው

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመሠረቱበት ዓላማ የእውቀትና ጥበብ መበልፀጊያና ማስፋፊያ እና የምርምር ማዕከላት እንዲሆኑ ነው። እውቀትና ጥበብ እንዲበለፅጉ እና የምርምር ሥራዎች እንዲዳብሩ የአካዳሚ ነፃነት መኖሩ ቁልፍ ጉዳይ ነው። የአካዳሚ ነፃነት ሳይኖር መምህራኑም ተማሪዎቹም በነፃነት ማሰብ፣ አስቸጋሪ ጥያቄዎችን ማንሳት እና ለጥያቄዎቻቸው መልስ ለመሻት መመራመር አይችሉም። የአካዳሚ ነፃነት ሳይኖር የተለያዩ እይታዎችንና ንድፈሀሳቦችን በገለልተኛነትና በሀቀኝነት መመርመር አይቻልም። በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የአካዳሚ ነፃነት እንዲኖር ተቋማቱ ከፓርቲ ፓለቲካ ገለልተኛ መሆን ይኖርባቸዋል። አንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የአንድ ፓርቲ ርዕዮተ ዓለም አራማጅ ከሆነ ተቋሙ የፓርቲው ካድሬዎች ማሰልጠኛ ሆነ ማለት ነው። ዛሬ በአገራችን የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙበት ሁኔታ ይህ ነው። የአገራችን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የወያኔ ካድሬዎች ማሰልጠኛ ሆነዋል። ይህ አጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ ህወሓት ካድሬ ማሰልጠኛነት መዝቀጥ አንድ ተጨባጭ ማስረጃ ሰሞኑን ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፕላዝማ ቴሌቪዥን አማካይነት በመሰጠት ላይ ያለው ፕሮፖጋንዳ ነው። በዚህ ፕሮፖጋንዳ ያልተጠመቀ ተማሪ የሚቀጥለው ዓመት መደበኛ ትምህርት አይቀጥልም በማለት ተቋማቱ ለካድሬ ማሰልጠኛነታቸው እውቅና ሰጥተዋል።
በዚህ ብዙ የአገር ሀብትና ጊዜ በፈሰሰበት ቅስቀሳ፣ የወያኔ ካድሬዎች ዘረኛና ከፋፋይ ፓሊሲዎቻቸውን ማር ቀብተው ወጣቱን ለመጋት እየጣሩ ነው። ለፓርቲ ቅስቀሳ የመንግሥትን መዋቅር መጠቀም በራሱ ወንጀል ቢሆንም ከዚህ በላይ ጉዳት ያለው ደግሞ የፕሮፖጋንዳው ይዘትና ዓላማ ነው። ወያኔ/ኢሕአዴግ ሁሉንም ነገር የሚያውቅ፤ ሁሉንም ነገር ማድረግ የሚችል ተደርጎ የተዘጋጀው ፕሮፖጋንዳ በትውልድ ላይ የሚያስከትለው የእውቀትና የሥነ ልቦና ኪሳራ ከፍተኛ ነው።

Thursday, August 21, 2014

የግንቦት 7 ሕዝባዊ ስብሰባዎች በዓለም ሃያ ስድስት ታላላቅ ከተሞች

የግንቦት 7 ሕዝባዊ ስብሰባዎች በዓለም ሃያ ስድስት ታላላቅ ከተሞች

ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በመላው ዓለም ላይ ከሚገኙ አባላት፣ ደጋፊዎቹና በአጠቃላይ ከኢትዮጵያውያን  ጋር በወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ለመመካከር ዝግጅቱን አጠናቋል።
በዚህም መሠረት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት 26 የዓለም ታላላቅ ከተሞች ሕዝባዊ ስብሰባዎችን ተጠርቷል።

መለስን ቅበሩት!(ተመስገን ደሳለኝ)

ከኢትዮጵያ ሀገሬ የደቀቀ ኢኮኖሚ ላይ በማን አህሎኝነት ወጪ ተደርጎ፣ ቅጥ ባጣ መልኩ በመላ አገሪቱ እየተከበረ ስላለው የቀድሞ አምባገነን /ሚኒስትር ሁለተኛ ሙት ዓመት ዝክርም ሆነ ሰውየውን ዛሬም በአፀደ-ህይወት ያለ ለማስመሰል እየሞከሩ ላሉት ጓዶቹ አንዲት ምክር ብጤ ጣል ማድረጉ ተገቢ ነው ብዬ ስለማስብ በአዲስ መስመር እንዲህ እላለሁ፡-

አብርሃ ደስታ ሃብታሙ አያሌዉና እና ኤርትራ ( ግርማ ካሳ)

ራሱን ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራ ድርጅት ጋር እና ከድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በመገናኘት ፤ እንዲሁም ከባንክ በትዕዛዝ ብር በመቀበል የግንቦት 7 ተልዕኮና አላማ ለመፈፀም፤ ቁጥራቸው ከ60 በላይ የሆኑ ግለሰቦችን ለዚህ ጥፋት እንዲሰማሩ በማድረግ» የሚል ክስ ነው በወዲ ሃዉዜን/ትግራይ በሆነው አንጋፋ ፖለቲከኛ እና ብሎገር ላይ ክስ የቀረበው። ሌላው አንጋፋና አንደበተ ርትኡ፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ፣ ሃብታሙ አያሌውም፣ «የግንቦት ሰባት ተባባሪ ነው» በሚል ነው ለመክሰስ ነው ዝግጅት እየተደረገ ያለው።

Wednesday, August 20, 2014

እውነት አብርሃ ደስታ አሸባሪ ወይስ ህወሓት እህአዴግ ነው ለሰላማዊ ትግል ፈሪ? [ክብሮም ብርሃነ-መቐለ]

ነሐሴ 1 ቀን 2006 ዓ.ም የአረና ትግራይ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚና የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር አብርሃ ደስታ በሽብር ተጠርጥሮ በተከሰሰበት ልክ በወሩ ፍ/ቤት እንደሚቀርብ በፌስ ቡክ አይቼ እኔም እንደ ዜጋና እንደ አድናቂው የሚቀርቡለትን የድራማ ክስ ለመስማት ጓጉቼ ፍ/ቤቱ ስደርስ እንደ እኔ አብርሃ ደስታን በአይናቸው ለማየትና የክሱን ድራማ ለማወቅ እንዲሁም ለቆራጡ ወጣት ፖለቲከኛ አብርሃ ደስታ የሞራል ድጋፍ ለመስጠት የተሰባሰቡ የተለያዩ የክልላዊና ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ አባላት፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች እንዲሁም የወጣቱ ፖለቲከኛ አድናቂዎች ሽማግሌዎችና ወጣቶች ተደማምረው ያልገመትኩት የሕዝብ ብዛት በቡድን 

ABRHA-DESTAበቡድን ሰብሰብ ብለው የአብርሃ ቆራጥነትና የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ሲወያዩ አገኘኋቸው፡፡
የክሱን ሁኔታ ለመመልከት የመጡ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች
1. የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ተክሌ በቀለ
2. የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ም/ፕሩዚዳንት አቶ በላይ ፍቃዱ
3. የሰማያዊ ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ስለሺ ፈይሳ
4. የመድረክ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጥላሁን እንደሻው
5. የጌድኦ ሕዝብ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኣቶ ኣለሳ መንገሻ እንዲሁም ጋዜጤኞች፣ ብዙ የታወቁ ሰዎችና ወጣት አድናቂዎቹ ተገኝተዋል፡፡

የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የአፍ ወለምታ (ኤፍሬም ማዴቦ)

ባለፈዉ ሰሞን ቻይና አፍሪካ ዉስጥ ሰላሳ አመት በማይሞላ ግዜ ዉስጥ ያደረገችዉ የኤኮኖሚና የፖለቲካ መስፋፋት ያሳሰባቸዉ የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ምነዉ ምን አድረግናችሁና ነዉ ፊታችሁን ያዞራችሁብን ብለዉ ለመጠየቅ በርከት ያሉ የአፍሪካ መሪዎችን ቤተ መንግስታቸዉ ድረስ ጋብዘዋቸዉ ነበር። በዚህ የሃሳብ ልዉዉጥ፤ ምክር፤ የእራት ግብዣና የዋሺንግተን ዲሲን ጉብኝት ባጠቃለለዉ የፕሬዚዳንት ኦባማ ድግስ ላይ በመልካም የዲሞክራሲ ጅምራቸዉ የሚወደሱት የጋናና የደቡብ አፍሪካን መሪዎች ጨምሮ እንመራሀለን የሚሉትን ህዝብ በየቀኑ የሚያስሩት፤ የሚደበድቡትና የሚገድሉት የወያኔ መሪዎችም ተገኝተዋል። በዚህ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ጠ/ሚ ደሳለኝ ኃ/ማሪያምን አጅበዉ ከመጡት የወያኔ ሹማምንት አንዱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ./ር ቴድሮስ አድሃኖም ነበሩ። ዶ/ር ቴድሮስ በዋሽንግተን ዲሲ ቆይታቸዉ ብዙዎቻችንን እየዋለ ሲያድር ደግሞ እራሳቸዉንም ግራ ያጋባ የሬድዮ ቃለ መጠይቅ ሰጥተዉ ነበር።

Tuesday, August 19, 2014

ጠብ-መንጃ አናነሳም! (ተመስገን ደሳለኝ)

ብሶት የወለደውኢህአዴግ ከሁለት አስርታት በፊት በሰሜን ተራሮች ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ጋር ያደረገውን የጎሬላ ውጊያአጃኢብበሚያሰኝ ቆራጥነት በድል መወጣቱ የማይታበል እውነትነው፤ ሥልጣን ከተቆናጠጠ በኋላም ለሚሰነዘርበት ማንኛውም አይነት የኃይል ጥቃት፣ ያውም ማቸነፍ አለማሸነፉን ሳያሰላ በፍጥነት ዘሎ ለመዘፈቅ ሲያንገራግር የተስተዋለበት ጊዜም አልነበረም፤ አሀዱ ብሎ የአመፅ ትግል ከጀመረበት ዕለት አንስቶ ላለፉት አርባ ዓመታት ከጀብሃ እስከ ኢህአፓ፤ ከኦነግ እስከ ኦብነግ፤ ከትህዴን እስከ አርበኞች ግንባር፤ ከሻዕቢያ እስከ አልሸባብበስም ተዘርዝረው ከማያልቁ ብረት-ነካሽ ድርጅቶች ጋር ወደ ፍልሚያ ለመግባት ከመወሰኑ በፊት ሰላማዊ መፍትሄዎችን ግራና ቀኝ የመፈተሽ ትዕግስትም ሆነ ልባዊ ፍላጎት እንዳልነበረው የራሱ የታሪክ ድርሳናት ሳይቀሩ በግላጭ ይናገራሉ፡፡

Monday, August 18, 2014

የኢትዮጵያችን ችግር ገዢዎች እና አደርባዮቻቸው የሚፈጥሩት የፖለቲካ ካንሰር ነው::…. .. እየተገፋን እስከመቼ?? ተነስ እንጂ ወገን !! (ምንሊክሳልሳዊ)


ሁኔታዎች ገዢው ፓርቲ ብቻ በሚፈልገው መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ደጋግሜ ለመናገር የምንፈልገው ለሃገርም ለህዝብም ከባድ እና አደገና አደጋ እንዳለው ነው:: በፖለቲካ ታማኝነት ያልተማሩ እና ከካድሬ ትምህርት ቤት ተመርቀው የወጡ በፖለቲካ ጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የአገርን አመራር እና የህዝብን አንድነት ሊጠብቁ ስለማይችሉ በሃገሪቱ የፖለቲካ መስክ ትልቅ በሽታ ሆነዋል::
በሃገሪቱ የተከሰተውን ደዌ ከማዳመጥ ይልቅ በሽሙጥ አንዱ አንዱን እየወገረው በመብረር ላይ እንገኛለን :; እርስ በእርስ ከመወጋገር ያድነን እንዳንል እየተወጋገርን ጸሎት ለቅጽበት ነው::ማን ከማን ይማር ሎሌ ከንጉሱ ሆኖብን ሆነና የራሳችንንም ሆነ የሃገራችንን ህመም ተጋግዘን እንዳናድን ራሳችን በሽታ ሆነናል::ምን እንደተባልን እንኳን ማዳመጥ አለመቻላችን አንዱ ደንቃራችን ሲሆን የምንናገረውንም ከማንነገርው መራርጠን መተንፈስ እስኪያቅተን ድረስ እያቃተትን በሽታችንን እያባስን ብዙሃዊ ተላላፊ ህመም አድርገነዋል ከዚህ ይሰውረን እንዳንል ራሳችን አሁንም ደንቃራ ሆነናል::
የኢትዮጵያችን ችግር ገዢዎች የሚፈጥሩት የፖለቲካ ካንሰር ነው::ልዩነት እንዳለ ሆኖ በጋራ ሃገራዊ መርህ ላይ ያልተመሰረተ ፖለቲካ እንዴት ህዝባዊ መተሳሰብ ሊፈጥር እንደሚችል በሃገራችን የሚገኙ ፖለቲከኛ ነን የሚሉ አልተረዱትም ወይንም አውቀው እየተባሉ እያባሉን እያነካከሱን ነው:: በጋራ መተሳሰብ ላይ ያልተመሰረተው ፖለቲካችን እና በመጭበርበር የሚያጭበረብሩን ገዢዎቻችን ለነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ አደገኛ የሆነ የፖለቲካ በሽታ እያወረሱ ይገኛሉ፤ የፖለቲካ በሽታ ብቻ ሳይሆን በአንድ ወጥ መርህ ላይ የተመሰረተ እና የደቀቀ ኢኮኖሚ ጭምር:: ይህ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የተገነባ ኢኮኖሚ የህዝቦችን የጋራ መደጋገፍ በማስመጥ ገዢው መደብ በፍጹም ከኔ ውጪ የሚነካ ካለ እሳት እንደነካ ነው በማለት በፍራቻ ላይ የተመሰረተ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ዜጎች በሃገራቸው ብሄራዊ አጀንዳ ጉዳይ እንዳይሳተፉ እንዳይተሳሰቡ እንዳይደጋገፉ እንቅፋት ሆኖ ይገኛል::ከማህበረሰቡ ተገልሎ እየተሰራ ያለውን ውጤት እያየነው ነው::

Sunday, August 17, 2014

እንደገና ይድረስ ለሠራቱ

“የትግሬ” ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ ራሱን የሠየመው የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን አገሪቷን እያጎሳቆለ ያለው ከሠራዊቱ ጀርባ ተንጠላጥሎ መሆኑ ይታወቃል። ይህ የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን የተሸከመውን ሠራዊት ሳይቀር በጉስቁልናና በድንቁርና እንዲኖር ፈርዶበታል። ህወሃት ሠራዊቱ እንዲማር፤ ዘመኑ ከሚፈቅደው የቴክኖሎጂ እውቀት ጋር ራሱን እንዲያዋህድ እና በራሱ የሚተማመን የዘመነ ሠራዊት እንዲሆን ፍላጎት የለውም።አሜሪካን በአገሯ በሚገኙ የጦር ትምህርት ተቋማት ውስጥ ወታዶሮችን ለማሰልጠን ፍላጎት ብታሳይም ሳሞራ የኑስና መለስ ዜናዊ እምቢ ማለታቸውን አብዛኛው የሠራዊቱ አባላት የሰሙት አይመስልም። አሜሪካን በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ 42 ወታደሮችን አገሯ ወስዳ ለማስለጠን በጠየቀች ግዜ ሳሞራ የፈቀደው 13 ወታደሮች ብቻ ሂደው እንዲማሩ ነው። እነዚህም ከህወሃቶች መካከል ፊደል የቆጠሩ ተፈልገው በመገኘታቸው መሆኑም ታውቋል። በሠራዊቱ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች የትምህርት ዝግጅት ቢኖራቸውም የትምህርት እድሉን ተከልክለዋል።
ህወሃት ከራሱ ውጪ ያሉት ሌሎች ላይ ምንም ዕምነት እንደሌለው በተለያየ አጋጣሚ ተናግሮታል። የትምህርት ዕድሉን ለምን መጠቀም እንዳልፈለጉ ሲጠየቅ ሳሞራ የኑስ “ሌሎችን አናምናቸውም አሜሪካን ሂደው ይቀራሉ” ብሎ መልስ መስጠቱም ተመዝግቦ ይገኛል። 11ኛ ክፍልን ያልዘለለው የህወሃቱ ኢታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስ ሠራዊቱን ታማኝና የማይታመኑ በሚል ይከፍላቸዋል። የህወሃት አባል የሆነ ወታደር ታማኝ ፤ ሌሎች የሠራዊቱ አባላት የማይታመኑ።
አሁንም የሠራዊቱ አባላት ስሙ !

Saturday, August 16, 2014

''አማራጭ የሌለው ምርጫ''

ሄለን ንጉሤ

ከኖርዌ

አንድ ሀገር እንደ ሀገር ለመቀጠል የሚያስችላትን ትልቁን ድርሻ የመወጣት ኃላፊነት ያለበት በስልጣን ላይ ያለው ስርአት ነው። ሥርዓቱ የሐገሪቱን ህገ መንግስት በመፈፀምና በማስፈፀም ህገ መንግስቱ ሳይሸራረፍና ሳይጣስ እንዲሁም ዜጎች ህገ መንግስታዊ መብቶቻቸውን ያለ አንዳች መድልኦ በመጠቀም በፍርድ ቤት የመከሰስና የመክሰስ፣ የመርታትና ያለመርታት መብታቸው ተከብሮ በሐገሪቱ የህግ የበላይነት ተረጋግጦ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ለማድረግ በስልጣን ላይ ያለው ስርአት ወሳኝነት አለው።  በአንፃሩ ደግሞ በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት ይህንን ማስፈፀም ካልቻለና ሆን ብሎ የሐገሪቱን ልዑአላዊነት ላለማስጠበቅ የሚሰራ ከሆነ ዜጎች እንደዜጋ የራሳቸውን መብት ማስጠበቅና በሐገራቸው መልካም አስተዳደር የማስፈን ግዴታ ያለባቸው ለመሆኑ ምንም አይነት ጥያቄ የማያስፈልገው የዜግነት ግዴታ መሆኑ በግልፅ ሊታወቅ ይገባል።

Thursday, August 14, 2014

“አሸባሪነት” በወያኔ አገዛዝ ሥር ባለችው ኢትዮጵያ

Weekly_Editorial_Tumbnail

በአገራችን፣ በወያኔ አገዛዝ መደበኛ ትርጉማቸውን ከሳቱ በርካታ ቃላት መካከል “የሽብር ድርጊት“ እና ”አሸባሪ“ የሚሉት ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። ሰፊ ተቀባይነት ያለው የአሸባሪ ትርጉም “የሽብር ድርጊቶችን የሚፈጽም ሰው ወይም ድርጅት” ማለት ነው። “የሽብር ድርጊቶች” የሚባሉት ደግሞ የተለመዱ ጥቃቶችን ሳይሆን የሀይማኖት፣ የፓለቲካ ወይም የርዕዮተዓለም ግብ ለማሳካት ሲባል በሰዎች ላይ ፍርሀትን ለማንገስ፤ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሱ አስከፊ ጥቃቶችን ነው። የሽብር ድርጊቶችን ሰላማዊውን ሕዝብ ጭዳ የሚያደርጉ በመሆኑ በጥብቅ ሊወገዙ ይገባል። ዓላማን በሽብር ድርጊቶች ማስፈፀም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።
በወያኔ መዝገበ ቃላት ግን “ሽብርተኛ” እና “የሽብር ድርጊቶች” በዘፈቀደ የሚነገሩ ተራ ቃላት ሆነዋል። ስለአገራቸው እና ስለትውልድ የሚጨነቁ፤ ሀሳባቸው በነፃነት የሚያራምዱ፤ የወያኔን ፕሮፖጋንዳ እንደ በቀቀን የማይደግሙ ዜጎች “አሸባሪዎች” እየተባሉ ወደ እስር ቤቶች እየተወረወሩ ነው። ጋዜጠኞች፣ ጦማርተኞች፣ ፍጹም ሰላምተኛ አማኞች እና ሰላማዊ ፓለቲከኞች በሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚውን ሥፍራ የያዙ ናቸው።

Wednesday, August 13, 2014

የስብሃት ነጋ ባለቤት ሻለቃ ፀአዱና ሟቹ ዶ/ር ልኡል

ሻለቃ ፀአዱ የህወሓት ታጋይ የነበረች ናት። ከኤርትራና ጣሊያን የዘር ግንድ ያላት ሻለቃ ፀአዱ የቀይ ቆንጆ ናት፤ ገፅታዋን በመመልከት ማንነትዋን በቀላሉ መገመት ይቻላል። የሽማግሌው ስብሃት ነጋ ባለቤት ነበረች። ሽማግሌው ስብሃት ከበረሃ ጀምሮ በአብዛኛው የድርጅቱ አባላት የሚታወቁበት ባህርይ ሴሰኝነታቸው ነው። ከፀአዱ ጋር ከበረሃ የጀመሩት ፆታዊ ግንኙነት እስከ 1990ዓ.ም ድረስ የዘለቀ ሲሆን በ <አብሮነት> ጊዜያቸው ልጆች አፍርተዋል።

የ”ብርቱው ሰው” መልዕክት – ከቃሊቲ እስር ቤት (በኤሊያስ ገብሩ)

1044303_169829796523576_1916727500_n
‹‹ለእውነት መቆም ካልተቻለ ስብዕና ይወርዳል፣ ሕሊናህም ይሞታል››
‹‹የክስ እና የእስር መብዛት … የድል ጊዜ እየቀረበ መሆኑን ያሳያል››
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ (ከቃሊቲ እስር ቤት)
‹‹እ… እስክንድር “The Iron man’’?››
የቃሊቲ ጠባቂ ፖሊስ

Tuesday, August 12, 2014

ኢንጅነር ይልቃል የአውሮፓ ህብረት እርምጃ እንዲወስድ አሳሰቡ



ዛሬ ነሃሴ 6/2006 ዓ.ም በኢትዮጵያ ተወካይ ያላቸው 20 የአውሮፓ አባል አገራት
ተወካዮች በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ቢሮ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እንዲያስረዱ የተጋበዙት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ ወደባሰ ችግር ሳትገባ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ አሳሰቡ፡፡

Monday, August 11, 2014

የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ባለቤትና አዘጋጆች ተሰደዱ

625580_262300080573506_2074737023_n
ነሃሴ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአንባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት የነበረው ሳምንታዊ መጽሔት ባለቤት እና የመጽሔቱ ሶስት አዘጋጆች ሀገር ለቀው ተሰደዋል። የመጽሔቱ ባለቤት አቶ እንዳልካቸው ተስፋዬ ለኢሳት እንደገለጸው፤ እርሱና ጋዜጠኞቹ በስርአቱ ሲደርስባቸው የነበረውን ወከባና አፈና ተቋቁመው የአዲስ ጉዳይ መጽሔትን ህልውና ለማስቀጠል ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት ፤ መጽሔቱዋ በህብረተሰቡ ዘንድ ከፍ ያለ ተቀባይነት ከማግኘቷም
ባሻገር በገንዘብ አቅምም ረገድ ጥሩ ደረጃ ላይ መድረስ ችላ ነበር። አዲስ ጉዳይ እንደ አንድ ጠንካራ የፕሬስ ተቁዋም በጥሩ የእድገት ደረጃ ላይ በደረሰችበት ወቅት በመንግስት በኩል ክሱ፣ወከባውና፣ ማስፈራሪያው እየጠነከረ መምጣቱን የገለጸው አቶ እንዳልካቸው፤ ይህም ሆኖ የህግን መስመር በጠበቀ መልኩ ሲያከናውኑ የነበረውን ስራቸውን ለመቀጠል እስከመጨረሻዋ ሰዓት ድረስ አስፈላጊውን ጥረት ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ሆኖም ከህግ አግባብ ውጪ እየደረሰባቸው ያለው ነገር እንዲቆምላቸው ለሚመለከታቸው አካላት አቤቱታ ከማቅረብ ጀምሮ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ጥረቶችን ቢያደርጉም ተገቢውን ምላሽ ከማጣታቸውም ባሻገር ይባስ ብሎ መንግስት በኢትዮጵያ ቴለቪዥን በይፋ በመጽሔቱ ላይ ክስ እስከመመስረት መድረሱን የአዲስ ጉዳይ መጽሄት ባለቤት ገልጿል።

የመለስ “ትሩፋቶች” ባለቤት አልባ ከተማ! የኢትዮጵያ ዊኪ ሊክስ ምን ይዟል ?

የመለስ “ትሩፋቶች” ባለቤት አልባ ከተማ!  የኢትዮጵያ ዊኪ ሊክስ ምን ይዟል ?

የመለስ “ትሩፋቶች” ባለቤት አልባ ከተማ

ደራሲ: ኤርምያስ ለገሰ

 ነጻነት አሳታሚ ድርጅት: ቨርጂኒያ:ዩ ኤስ ኤ 2014

408 ገጾች
ግምጋሚ: ቢላል አበጋዝ:: ዋሽግተን ዲሲ
ስለ “የመለስ “ትሩፋቶች” ከመጻፌ በፊት ስለ ነጻነት አሳታሚ ድርጅት በጥቂቱ:: እንደ ታዘብኩት ከሆነ ይህ ድርጅት መረጃ የሚያቀርቡ: የሚያስተምሩ ወደፊት ተኮር ስራዎችን እያቀረበልን የሚገኝ ነው:: ፍጹም አፈና ባለባት ኢትዮጵያ መንግስትና ባለስልጣናትን የሚያጣቅስ ጽሁፍ ይወጣል ማለት አይቻልም:: ነጻነት አሳታሚ ድርጅት ዓላማው ስለ ኢትዮጵያ ሀሳባቸውን: ቁጭታቸውን: ሊሰጡ የሚሹትን ትምህርት በግልጽ ለአገር ወዳዱ አንባቢ ማቅረቡን ላውቅለት እወዳለሁ:: ልንክባከበው ተገቢ የሚሆነው አገር መገንባት ካልን አፈናን መዋጊያ መሳሪያ ሳንይዝ አይሆንምና::

የአንዳርጋቸዉ ትዉስታዎች

የአንዳርጋቸዉ ትዉስታዎች

የአንዳርጋቸዉ ትዉስታዎች

ግንቦት 7
“በእኛ እምነት ታሪክ ከነባራዊ ሁኔታ ዉጭ በምኞትና በዘፈቀደ አይሰራም። የሚሰራ ቢሆን ኖሮ ነገስታቱና አምባገነኖቹ ዘሬም በዙፋናቸዉ ላይ በተገኙ ነበር። ባለንበት ወቅት የኢትዮጵያ ህዝቦች መስቀለኛ መንገድ ላይ ቆመዉ ከዚህ ወዴት እንደሚሄዱ ግልጽ ኢየባልሆነበት ሰዐት ሥልጣን ላይ ያለዉም ሆነ የሌለዉም የግሉን የተስፋ ጎዳናን እዉነተኛዉ የወደፊት ጎዳና አድርጎ የሚያይ ከሆነ ዛሬም እንደ ትናንቱ ከታሪክ መማር አልቻልንም ማለት ነዉ”።

Sunday, August 10, 2014

መኢአድና አንድነት ውህደታቸውን ለማራዘም መገደዳቸውን ገለፁ

ለውህደቱ መራዘም  ምርጫ ቦርድን ተጠያቂ አድርገዋል
መንግስት በግል ሚዲያዎች ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ አውግዘዋል
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ነገ ሊያካሂዱት የነበረውን ውህደት ለማራዘም መገደዳቸውን አስታወቁ፡፡ ለውህደቱ መራዘም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡
በሌላ በኩል  መንግስት በግል ሚዲያዎች ላይ እየወሰደ ያለው እርምጃ፣ የህዝብን መረጃ የማግኘት መብት የሚገድብና የመናገር ነፃነትን የሚያሳጣ በመሆኑ እንደሚያወግዙት ፓርቲዎቹ ገልፀዋል፡፡
“መኢአድና አንድነት ወደ ሰላማዊ የትግል ጦርነት ውስጥ መግባታቸውን ለህዝብ ማሳወቅ ይወዳሉ” በሚል ርዕስ ከትላንት በስቲያ ፓርቲዎቹ  በሰጡት መግለጫ፤ “መኢአድ በ2005 ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ምዕላተ ጉባኤ ያልተሟላ በመሆኑ መዋሀድ አትችሉም የሚል ተልካሻ ምክንያት በማቅረብ ምርጫ ቦርድ  ውህደቱን እንድናራዝም አስገድዶናል  ብለዋል፡፡
በ2005 በተካሄደው ጉባኤ ከ600 የጠቅላላ ጉባኤ አባላት 390 ያህሉ ተገኝተው ህጉ በሚፈቅደው መልኩ ጉባኤው መካሄዱን ራሱ ምርጫ ቦርድም ያውቃል ያሉት የመኢአድ ሃላፊዎች፤ጉባኤው ሲካሄድ የምርጫ ቦርድ ተወካዮች መጥተው ምዕላተ ጉባኤው መሙላቱን ቢያረጋግጡም ቦርዱ ግን ምዕላተ ጉባኤው አልተሟላም በሚል ለአንድ ዓመት ያህል አዎንታዊ ምላሽ ሳይሰጥ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

የግንቦት 7 ደጋፊዎችን የማሰባሰብ ጥረት!!!!

የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በህሊናና የፓለቲካ እስረኞች ሁሉ ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ መክበድ፤ በፀረ-ሽብርተኝነት ስም በሕዝብ ላይ የሚነዛው ወያኔያዊ ሽብር መብዛት፤ እስሩ፣ እንግልቱ፣ መሳደዱ፣ የሀብት ዘረፋው በየዕለቱ እየጨመረ መምጣት እና ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ኑሮ እየከበደ መምጣቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ ጋር ወሳኝ የሆነ ትግል መግጠሚያ ወቅት ላይ መደረሱ አመላካች ሆኗል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ የትግል መንፈስ መነሳሳት በተጨባጭ ከሚያረጋግጡ አመላካቾች አንዱ የግንቦት 7፡ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አባል ለመሆኑ የሚፈልጉ ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ መጠን መጨመር ነው። ይህንን ለውጥ ተከትሎም ግንቦት 7 የአባላት ቅበላን ሥራ ለማፋጠን የሚረዱ እርምጃዎች ወስዷል። ሆኖም ግን በአባላት ቅበላ ወቅት ሊታለፉ የማይችሉ ጥንቃቄዎች መኖር እንዳለባቸው ደጋፊዎችም እጩ አባላትም ይረዳሉ ተብሎ ይታመናል።
በዚህም ምክንያት አሁንም እየጨመረ የመጣን ንቅናቄውን የመቀላቀል ፍላጎትን ለማስተናገድ፤ ለተግባራዊ ሥራዎች የተነሳሱ፣ ዓላማችንና ንቅናቄዓችንን የሚደግፉ ሆኖም ግን በተለያዩ ምክንያቶች በድርጅት አባልነት መቀላቀል የማይችሉ ወይም የማይፈልጉ አባላትን ለማሳተፍ የሚረዳ መዋቅር ማዘጋጀት ተገቢ መሆኑ ታምኖበታል። ስለሆነም እነዚህን ወገኖቻችን የትግላችን አካል ብቻ ሳይሆን የንቅናቄዓችንም አካል ለማድረግ እንዲቻል በአባላት ጉዳይ ሥር የደጋፊዎች ማስተባበሪያ መዋቅር እንዲደራጅ ተደርጓል። ይህ አደራጀት ግንቦት 7ን ለማዘመን እና ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ የተመቸ ድርጅት ለማድረግ የሚደረገው ጥረት አካል ነው። ይህ አደረጃጀት በአንድ በኩል የድርጅቱን ምስጢራዊት ለመጠበቅ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ ባሉ ፍላጎቶች መካከል ያለውን ቅራኔ ለመቅረፍ የቀረበ መፍትሔ ነው።

Saturday, August 9, 2014

መነበብ ያለበት
እነ ማን ነበሩ? አሁንስ ማን ናቸው?
ገብረመድህን አርአያ , ፐርዝ፤ አውስትራሊያ
መነበብ ያለበት 
እነ ማን ነበሩ? አሁንስ ማን ናቸው?
ገብረመድህን አርአያ , ፐርዝ፤ አውስትራሊያ
ይህ ጽሑፍ ትኩረት የሚሰጠው በትግል በረሃ በነበርንበት ወቅት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህ.ወ.ሓ.ት.) በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖቶች ላይ ሲከተል የነበረውን አቋሙን ተቀብሮ ከነበረበት ጉድጓድ አውጥቼ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እነማን ናቸው የሚለውን ታሪካቸውን እና የተፈጸመውን ጸረ-እምነት ግፍ በአጭሩ ለማሳወቅ ነው። ህ.ወ.ሓ.ት. ገና ሲፈጠርና ተ.ሓ.ህ.ት. ተብሎ እንደተመሰረተ ሙልጭ ያለ ጸረ-ዲሞክራሲ ድርጅት ነው። በጸረ-ኢትዮጵያነትና በጸረ-ሕዝብነት የተሰማራ ቅጥረኛ ድርጅት መሆኑን ብዙ ጊዜ በጽሑፍና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለኢትዮጵያ ህዝብ ተናግሬአለሁ። የአሁኑ
ጽሑፌ ህ.ወ.ሓ.ት. በሃይማኖት ላይ ሲከተለው የነበረውን ፖሊሲ ገና ከመጀመሪያ ትግሉ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የነበረውን ጸረ- ሃይማኖት ተግባራቱን የኢትዮጵያ ሕዝብ በግልጽ አውቆታል። እኔ ደግሞ የራሴን ልበል።
በ1969 መጀመሪያ ጀምሮ “ወይን” በሚለው የድርጅቱ ልሳን መጽሔት ላይ በተደጋጋሚ “የክርስትና ሃይማኖትና አማራው” በሚል ርእስ ጽፎ የሚወጣው ጽሑፍ፣ “የክርስትና ሃይማኖት የአማራው ዋና መሳሪያና የግዛቱን ህልውና ማስጠበቂያ ነው፣ በመሆኑም የትግላችን ጠላት አማራውና መሳሪያው የተዋህዶ ክርስትና ስለሆኑ አብረው እንዲጠፉ ማድረግ አለብን” እያለ ያትት ነበር። ይህንን መጽሔት
በሰፊው ለታጋዩና ለአባላቱ በማሰራጨት ሰፊ ቅስቀሳ አካሂዶበታል። በነሐሴ 1969 “ወይን” መጽሔት አማርኛ ቋንቋም አብሮ መጥፋት እንዳለበት ሃተታ ይዞ ወጥቷል። “ወይን” የምትለውን መጽሔት የሚያዘጋጁት ከፍተኛ የአመራር አባላት በፕሮፓጋንዳ ቢሮ ሆነው ለዚሁ ተግባር የተዘጋጁ ጽሑፎችን
በስፋት የሚያሰራጩት፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየና መለስ ዜናዊ ነበሩ። እነዚህ ሶስቱ የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር አባላት እብዶችና በጸረ-ሃይማኖት፣ ጸረ-አማራ ባህሪያቸውና አቋማቸው በሰላማዊው ህብረተሰብና ታግዩም ጭምር በግልጽ የሚታወቁ ናቸው። የሕዝብ ግንኙነት ቢሮ የሚመራውም በነዚህ ሶስት እብድ አመራሮች ነበር። ከዚህ በመነሳት መስከረም 1970 በጸረ-ሃይማኖት፣ በተለይም
በተዋህዶ ኦርቶዶክስ ላይ ቅስቀሳውን በስፋት ለማካሄድ በማሰብ፣ ሕዝብ ያሳምናሉ ተብለውየ ሚታመንባቸውን ታጋዮች መርጠው እገላወረዳ መሬቶ ተብላ በምትጠራ ቁሽት ውስጥ ተሰብስበው ቦታ ተዘጋጅቶ ከላይ በተጠቀሱት ሶስቱ አመራር ሴሚናር ተዘጋጀ። በሴሚናሩ ላይ የሚከተሉት ታጋዮች ተካፍለው ነበር፤
1. መርሳ ረዳ
2. ሃለቃ ፀጋይ በርሄ
3. ቴዎድሮስ ሃጎስ
4. አባይ ወልዱ
5. ሃዳስ ዓለሙ
6. ኃ/ሥላሴ ገ/ኪዳን
7. ሃሪያ ሰባጋድስ
8. ቅዱሳን ነጋ
9. ጉእሽ ጓእዳን
10. ቢተው በላይ
11. ሃድሽ ገዛኸኝ
12. ሮማን ገ/ሥላሴ
13. አፈራ ተክለሃይማኖት
14. ወልደገብርኤል ሞደርን
15. አዲስዓለም ባሌማ
ከላይ የተጠቀሱት ታጋዮች በተካሄደው ሴሚናር በጸረ-ክርስትና እና በጸረ-እስልምና አስተሳሰብ በሶስት ቀን ውስጥ ተጠምቀው ጨረሱ። እንደጨርሱም በሶስት ሪጅን ተመደቡ፤ አመዳደባቸውም፤ ሪጅን 1 መርሳ ረዳ፤ ሪጅን 2 ሃለቃ ጸጋይ በርሄ፤ ሪጅን 3 አዲስዓለም ባሌማ በሃላፊነት እንዲመሩት ተመረጡ። ቀሪዎቹም በእነዚህ የበላይ ተጠሪዎች ስር ተደለደሉ።
ሪጅን 1 መርሳ ረዳ ተጠሪ
1-ጉእሽ ጓእዳድ
2-አባይ ወልዱ
3-ኃ/ሥላሴ ገ/ኪዳን
4-ሃርያ ሰባገድል
ሪጅን 2፡ ጸጋይ በርሄ ተጠሪ
1-ቅዱሳን ነጋ
2-ሃዳስ ዓለሙ
3-ቢተው በላይ
4-ሃድሽ ገዛኸኝ
5-ሮማን ገብረሥላሴ
ሪጅን 3፡ አዲስዓለም ባሌማ ተጠሪ
1-ቴዎድሮስ ሃጎስ
2-ወ/ገብርኤል ሞደርን
3-አፈራ ተ/ሃይማኖት
በዚህ መልክ ተደራጅተው በየሪጅኑ ተሰማሩ። ድጋፍ ሰጪ የሕዝብ ግንኙነት ካድሬዎችም በየድርጅቱ በስፋት ተሰማሩ። እነዚህም በተጠናከረ ሃይል ጸረ-ክርስትና፣ ጸረ-አማራ፣ ጸረ-እስልምና ቅስቀሳቸውን ቀጠሉበት። በተዋህዶ ክርስትና ላይ ሙሉ ሃይላቸውን በመጠቀም በስፋት ጸረ-ክርስትና ቅስቀሳውን በተከታታይ እሁድና ሌሎች በዓላት እንዳይከበሩና የሥራ ቀን መሆናቸውን በማወጅ በህብረተሰቡ ላይ ካባድ ተጽእኖ አሳደሩበት። ቀሳውስትና ዲያቆናት በማንኛውም በዓላት ቤተ ክርስቲያን ከፍተው ሲቀድሱ ቢገኙ ከባድ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠነቀቁ። አልፎ አልፎ ተቃውሞ ይገጥማቸው ስለነበር በበላይ አመራሩ ለእነ ስብሃት ነጋ ምን እናድርግ እያሉ ሪፖርት ያቀርቡ ነበር። ከአመራሩ የተሰጠው ምላሽ፣ ማንም ያንገራገረ ቄስ፣ ባህታዊ፣ ዲያቆን ወይም ሌላ እዛው ባለበት በሕዝቡ
ፊት ግደሉት የሚል መመሪያ ተሰጣቸው። በዚህ መሰረት አድዋ አውራጃ እንዳባጻህማ ወረዳ የሚገኘው እንዳሥላሴ ተብሎ የሚታወቀው ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን መሪ አባ ሃይለሥላሴ የሚባሉ ቄስ፣ “ሃይማኖታችንን አታርክሱት፣ የተቀደሰ ሃይማኖት ነው” ብለው ስላሉ በቦታው የነበረ ጸጋይ በርሄ የሚባል ታጋይ በያዘው አጭር ጓንዴ ተኩሶ ጭንቅላታቸው ላይ በመምታት በሕዝብ ፊት ገደላቸው። ቀሪው ምእመናን ተደናግጦና በርግጎ ተበታተነ። ሃለቃ ጸጋይ በርሄ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የነበረውን ንብረትና ሃብት ጠራርጎ ወሰደው። በተመሳሳይ፣ ዛና ወረዳ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን መሪ የነበሩት አባ ቄስ አርአያ ከአንድ የ90 ዓመት አዛውንት ባህታዊ ጋር ሆነው፣ “እባካችሁ ሃይማኖታችንን አታርክሱብን” በማለታቸው ከቢተው በላይ ጋር ተደራቢ ሆኖ የሄድው አርከበ እቁባይ ሁለቱን ንጹሃን ዜጎች
በሕዝቡ ፊት ገደላቸው። በስብሃት ነጋ፤ አባይ ፀሃየና መለስ ዜናዊ የሚመራው ጸረ-ክርስትና ሃይማኖት ከላይ የተጠቀሱትን 15 ታጋዮች የተግባሩ ፋጻሚዎች በማድረግ በርካታ ቤተ ክርስቲያናትን አቃጥለዋል። ከአድዋ፣ አክሱምና ተምቤን አውራጃዎች ብዙ ቀሳውስትና ባህታውያን እንዲሁም ዲያቆናት ሌሊትና ቀን እየታፈኑ ተውስደው የውሃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል።
የእስልምና ሃይማኖትን በተመለከተ፤ እስልምና ተከታይ ኢትዮጵያውያን ጸሎት ለመድረግ በሚሰበሰቡበት ጊዜ እየጠበቁ ጸረ-እስልምና ሰበካዎችን ለማራመድ በየመንገዱ ቅዱሱን ነብዩ መሃመድን እና ቅዱስ ቁርአንን ማብጠልጠልና ማራከስ በጀመሩበት ወቅት፤ ከሪጅን 1-3 በሚገኘው የእስልምና ተከታይ ሰፊ ተቃውሞ ገጠማቸው። በተለይ በሪጅን 3 አፋሮች የእስልምና ተከታዮች ስለሆኑ ጸረ-ወያኔ ተቃውሞ
በማሰማት ለእምነታችን እንሞታለን፤ እንዋደቃለን በማለት ከፍተኛ ተቃውሞ አሰሙ። በሪጅኑ የተመደቡትን የህ.ወ.ሓ.ት. አባላት ተከታትለው በማደን ገደሏቸው። ከተገደሉት መካከል፣ ትእግስት አሰፋ፣ የኋላሸት ገ/መድህን (አላሚን)፣ ፀሃየ አብርሃ ወዘተ ይገኙበታል። የዚህ አይነቱን ተመሳሳይ እጣ በታጋዮች ላይ በተደጋጋሚ አድርሰዋል። የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ስለሁኔታው ሲጠየቅ እስከ አሁን ድረስ
ድርጊቱን በመካድ በጦርነት ሞቱ እያለ ይዋሻል። በጦርነት ሳይሆን ነቢዩ መሃመድን በማንቋሸሻቸውና ቅዱስ ቁርአንን በማቃጠላቸው በአፋር ሕዝብ የተገደሉ ናቸው። ቀሪዎቹ ማለትም አዲስዓለም ባሌማ፣ ቴዎድሮስ ሃጎስና አፈራ ተክለሃይማኖት ጨለማን ተገን በማደግ ሸሽተው በዱር በገደል ሲያመልጡ ተሰባብረውና ገርጥተው ባንድ ወር ጊዜ አጋሜ አውራጃ ሶቦያ ደርሰው ሕይወታቸውን አዳኑ። በዚህ
ምክንያት ህ.ወ.ሓ.ት. እስከ 1976 ድረስ አፋር ውስጥ መግባት ስለፈራ እንቅስቃሴውን አቆመ።
በዚህ ወቅት በርካታ ቅዱስ ቁርአን እና መጽሐፍ ቅዱስ በህ.ወ.ሓ.ት. የተዘረፈ ንብረት ማጠራቀሚያ ውስጥ ታጉረው ለእሳት ማቀጣጠያ ይደረጉ እንደነበር በርካታ በጊዜው የነበሩ ታጋዮች የሚናገሩት የነበረ ሃቅ ነው። የእስልምና ታከታዩ ኢትዮጵያዊ በወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. የተጀመረውን ጸረ-እስልምና እንቅስቃሴ በሶስቱ ሪጅን የሚኖረው አማኝ ከፍተኛ ተቃውሞ በማስነሳት በአንድነት ቆመ። ወይ ወያኔ ይጨርሰን አለበለዚያ እኛ እንጨርሳችኋለን እንጂ በሃይማኖታችን አትገቡብንም በማለት የህ.ወ.ሓ.ትን አመራር ጉሮሮ ያዙት። የወያኔ አመራር በሁኔታው ተደናገጠ። በገጠርም ሆነ በከተማ የሚኖረው ሕዝብ ይህንን
ድርጊት የሚፈጽሙት የአመራር አባላት የሆኑት ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊና አባይ ፀሃየ መሆናቸውን በማወቁ እነዚህ ግለሰቦች በፍርሃቻ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አቆሙ፣ ከተንቀሳቀሱም በታጋይ እየታጀቡ ሆነ። በዚህ ጊዜ ወያኔ በኢ.ዲ.ዩና በኢ.ህ.አ.ፓ. የተወረረበት ወቅት ስለነበረ የአመራሩ የትግል ስሜት መሬት የወረደበት ጊዜ ነበር። ከዚህ በመነሳት ለጸረ-ሃይማኖት ተግባር ለተመደቡት ታጋዮች አስቸኳይ
ትእዛዝ በማስተላለፍ ጸረ-እስልምና እንቀቃሴአቸውን እንዲያቆሙ፣ ጸረ-ክርስትና ሃይማኖት ሥራቸውን ግን እንዲቀጥሉበት ታዘዙ። ጸረ-ክርስትናው ቀጠለ። በህ.ወ.ሓ.ት. ነፃ መሬት የሚኖሩት የእስልምና ሃይማኖት እህቶቻን እና ወንድሞቻችን ከዛች ቀን ጀምሮ ለወያኔ መታዘዛቸውን አቆሙ። ክርስቲያኑ ወገን የህ.ወ.ሓ.ት. ንብረት አመላላሽ እየሆነ ሲያገለግል የእስልምና ተከታዮች ኢትዮጵያውያን ግን
ሳይደፈሩ ተፈርተው ለዓመታት ቆዩ። የካቲት 1971 የህ.ወ.ሓ.ት. 1ኛው ጉባኤ በተካሄደበት ጊዜ የተመረጠው አመራር ማለትም፤ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ስብሃት ነጋ፣ የፕሮፓጋንዳው ሃላፊዎች መለስ ዜናዊን እና አባይ ፀሃየን መረጠ። እነዚህ ሶስቱ ጸረ-ሕዝብ አመራሮች ሃይላቸውን እና ጉልበታቸውን
በማጠናከር ድርጅቱ ያወጣውን በርካታ አዳዲስ ፖሊሲ ግንባር ቀደም በማድረግ በሥራ ላይ ማዋል ጀመሩ። እነሱም፣ የተዋቅህዶ ክርስትና ሃይማኖት የአማራው መሳሪያና መገልገያ ስለሆነ፣ እግዚአብሄር የሚባል ነገርም ስለሌለ፣ ከአሁን ጀምረን ከነፃ መሬታችን ጠራርገን ማጥፋት አለብን። ለወደፊትም የሃገራችን የትግራይ መንግሥት ሲቋቋም ሕዝባችን ከማንኛውም አጉል እምነቶች ነፃ የሆነ ሃገር እንመሰርታለን በማለት የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ወሰነ። ከላይ የተጠቀሰው እንዳለ ሆኖ፣ በአዲስ ጉልበትና አዲስ ጸረ-ተዋህዶ ክርስትናን ማዳከሚያ ፖሊሲ ተጠናክሮ ወጣ። በተግባር
ከተፈጸሙት መካከል፣
1. በህ.ወ.ሓ.ት. ነፃ መሬት የሚገኙት አብያተክርስትያናት ያላቸውን ሃብትና ንብረት በሙሉ ለህ.ወ.ሓ.ት. እንዲያስረክቡ ታዘዘ፣
2. ቄሶች ቆባቸውን እና ጥምጥማቸውን አውልቀው በመጣል የህ.ወ.ሓ.ት. “ወየንቲ” (ሚሊሻ ማለት ነው) እንዲሆኑ ተወሰነ፤ በተግባርም ታየ። ቄሶች የህ.ወ.ሓ.ት. ምንሽር፤ ጓንዴ፤ አልቤን እየተሸከሙ የህ.ወ.ሓ.ትን ነፃ መሬት ጠባቂ ሆኑ።
3. በህ.ወ.ሓ.ት. ነፃ መሬት የሚገኙ ዲያቆናት ትዳር የመሰረተ ትዳሩን አፍርሶ ከነሚስቱ ወደ ትግል ሜዳ እንዲቀላቀሉ፣ ትዳር የሌለው ደግሞ በቀጥታ ወደ ትግሉ እንዲገባ ተብሎ ተወሰነ። ብዙ ትዳር ፈርሶ በውዴታም በግዴታም የህ.ወ.ሓ.ት. ታጋይ ተደረጉ። ወላጆች ጧሪ አልባ ሆነው ቀሩ። አብያተ ክርስቲያናት ካለ ቀዳሽና አገልጋይ ክፍት ሆነው ቀሩ። አብያተ ክርስቲያናት በዘራፊው የህ.ወ.ሓ.ት. ማፊያ ቡድን ተዘረፉ። በወያኔ አመራር የተዘረፈው ጥንታዊና ታሪካዊ መጽሐፍት፤ ውድና ብርቅ ጥንታዊ ታሪካዊ ንብርቶች ሲዘረፉ፣ በርካታ የግእዝ የብራና መጽሐፍትና ቅዱሳን መጽሀፍት ተቃጠሉ። ይህንን ጸረ-ሃይማኖት ድርጊትና የማውደም ሥራ እንዲከናወን በተለያዩ ጊዜያት ትእዛዝና አመራር የሰጡት፤ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊና አባይ ፀሃየ ነበሩ። በተባባሪነት ተጨማሪ እርዳታ የሚያደርጉት ደግሞ፣ አርከበ እቁባይ፣ ኤርትራዊው ጻድቃን ገብረተንሳይ፣ አውአሎም ወልዱ፣ ዘርአይ አስገዶም፤ ስየ አብርሃ፣ ስዩም መስፍን ሳይጠቀሱ የማይታለፉ ናቸው። እነዚህ የአመራር አባላት የነመለስ፣ አባይና ስብሃት ታማኝና አገልጋይ አሽከሮች በመሆን ሕዝበ እስላሙን እና ክርስቲያኑን ሲያቃጥሉ የታዩ ናቸው። ብዙ አብያተ ክርስቲያናትንም በማቃጠል አውድመዋል፡ ይህ በዚህ አይነት እየቀጠለ ባለበት ጉዞ፣ ከየአብያተ ክርስቲያናቱ በውድም በግድም የለቀቁ ቄሶችና ዲያቆናት የካድሬ ሴሚናር ለሳምንታት ለመስጠት የሚከተሉት “መሪሕ ባእታ” ካድሬዎች ተመረጡ፤
1. ሙሉጌታ ጫልቱ
2. ዘርአይ አስገዶም
3. መርሳ ረዳ
4. አክሊሉ ደንበአርቃይ
5. ገብረኪዳን ደስታ
6. ጎበዛይ ወ/አረጋይ
7. አባይ ወልዱ
8. ቅዱሳን ነጋ
9. ግደይ በርሄ
10. ቢተው በላይ
እነዚህ ካድሬዎች በሪጅን 1 እና 2 በመመደብ በተለያዩ ቦታዎች በመሰማራት ቀሳውስትና ዲያቆናትን ከ1973 መጀመሪያ አንስቶ ለስድስት ወራት በመዘዋወር የማርክሲስም ሌኒኒዝም ትምህርት በማስተማር በክለው ጸረ-ክርስትና ሃይማኖት አደረጓቸው። በሚመረቁበት ጊዜ በእነ ኢያሱ በርሄ የሚመራው የባህል ቡድን በበዓሉ ላይ በመገኘት ቀሳውስቱ እስክስታውን (ስእሲኢት) አወረዱት፣ አምላክን አወገዙት፣ “ክርስትና ሃይማኖት ከአማራው ጋር አብረው ይደመሰሳሉ” እያሉ በየስብሰባው መክፈቻ መፈክራቸው አደረጉት።
4. በህ.ወ.ሓ.ት. ነፃ መሬት የሚከተሉት በአዋጅ ታግደው ነበር። በሕዝብ ግንኙነት በኩል ተፈጻሚ እንዲሆኑም ትእዛዝ ተሰጥቶባቸው ነበር፣ እነሱም
4.1 በህ.ወ.ሓ.ት. ነፃ መሬት ሠርግ ታገደ
4.2 ተስካር (ተዝካር) እና የሞት ፍትሃት ታገደ
4.3 አዲስ ለሚወለዱ ሕፃናት ክርስትና እና ጥምቀት ታገደ
4.4 በየወሩ በመሰባሰብ ጸበል ፀዲቅ ማድረግ ታገደ
4.5 በህ.ወ.ሓ.ት. ነፃ መሬት በየትኛውም ቦታ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በየዓመቱ የሚያካሂዱት በዓላት ታገዱ።
ከላይ የተጠቀሱትን የህ.ወ.ሓ.ት ትእዛዝ የጣሰ እንደ ጸረ-ህ.ወ.ሓ.ት ተቆጥሮ ሃለዋ ወያነ 06 ገብቶ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰድበታል። ሃብት ንበርቱ ለህ.ወ.ሓ.ት ገቢ ይደረጋል። የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ታጋዮችም ይህንን ተግባራዊ አደርገውታል። ስለሆነም ሕዝብ በሃሰት እየተከሰሰ ሃለዋ ወያነ በመግባት የስንቱ ሕይወት በከንቱ ጠፍቷል። ንብረታቸው ተወርሶ እናትና ልጆቿ ለክፉ መከራ ተጋልጠዋል። አብያተ ክርስቲያናት ገንዘባቸውና ሃብት ንብረታቸው ተዘርፏል። ይህ በ1969 የተጀመረው ድርጊት ህ.ወ.ሓ.ት እስከ መጨረሻው ቀጥሎበት ፖሊሲውን በተግባር አውሎታል።
ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ በ1969 መጀመሪያ ህ.ወ.ሓ.ት እንደ ግንባር ቀደም ፖሊሲው ያደረገው አማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው የሚለውን ነበር። ለዚህ ዓለማ ብለው የህ.ወ.ሓ.ት አመራር በፕሮግራሙ (ሕገ ደንቡ) የተጻፈውን ቀዳሚውን ፖሊሲውን በአጭሩ እንመልከት፤
አማራው በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ተጽእኖ በማጠናከር በትግራይ ሕዝብ ላይ በሚያካሂደው የኢኮኖሚ ብዝበዛ ሕዝባችንን ለድህነት፤ ለረሃብ፤ ለውርደትና መንከራተት ዳርጎታል።
ይህንን ግፍና በደል ጨቋኙ የአማራ ብሄር ሆን ብሎ ፈጽሞታል። በዚህም የተነሳ የትግራይ ሕዝብ በኑሮው እንዲጎሳቆል፤ ለሥራ አጥነት፤ ለሽርሙጥና፤ ለስደት፤ ለለማኝነትና መንከራተት ዳርጎታል። በተጨማሪም የትግራይን ሕዝብ ታሪኩን፣ ቋንቋውን እና ባህሉን እንዲጠፋ አድርጓል። የሶስት ሺህ ዓመታት ታሪካችንን ተነጥቀን የአማራው መመኪያና የግል ታሪኩ አድርጎታል። የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ያላት ታሪክ ከንጉሥ ምኒልክ የሚጀምርና እንደሃገር የኖረችውም ከ100 ዓመት አይዘልም። ኢትዮጵያ እንደ ሃገር የተፈጠረችው በአማራው ተስፋፊነት የተነሳ ስለሆነ ከምኒልክ ንግሥና በኋላ ነው። የአማራው ብሄር የትግራይን ሕዝብ ከአቅሙ በላይ ግብር እንዲከፍል በማድረግና በማስገደድና ጭቆናውን በማራዘም የትግራይን ሕዝብ ከሰብአዊ ፍጡር ውጭ አድርጎታል። የትግራይን ሕዝብ እንደ እንሰሳ በመቁጠር በሚደርስበት ጭካኔ የተሞላ አገዛዝ (ኢሰብአዊነት) ድህነት፣ ረሃብ፣ ውርደትና ስደት እንዲደርስበት አድርጓል። በተጨማሪም የትግራይ ሕዝብ ለረጅም ዘመን ሰብአዊና ፖለቲካዊ መብቱ
ተንፍጎ ሲጠላና ሲናቅ እንዲሁም አድልዎ ሲፈጸምበት ቆይቷል። ይህንን በደል ጨቋኟ የአማራ ብሄር ሆን ብላ እንደመንግሥት መመሪያዋ አድርጋ ስትሠራበት ነበር። ከላይ በጥቂቱ የዘረዘርኩት በህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራም ግጽ 8-14፣ 15-16፤ 18 ላይ ተመልክቷል። በአጠቃላይ ፕሮግራሙ ከመነሻው እስከ መጨረሻው አማራን ይወነጅላል። አሁን ደግሞ ደርግ ቀጥሎበታልም ይላል። የትግራይን ሕዝብ ቂሙን እና ጥላቻውን እያለ ይገልጻል። ጨቋኟ አማራም ሕብረተሰባዊ እርፍትና ስላም አታገኝም ብሎ ይደመድማል። ገጽ 16 ላይ ይመልከቱ።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው በኢትዮጵያ ውስጥ የአማራ መንግሥት የሚባል የለም፣ አልነበረምም። ኢትዮጵያ ብዙ ነገሥታትን አፍርታለች። ነገሥታቱም የሚነግሡት በዘር ሃረጋቸው ነበር። ይህም የቤተ መንግሥቱን መቀመጫ በሃይል ሳይሆን በቅብብሎሽ የሚደረግ ነበር። የአክሱም ቤተ መንግሥት ወደ ላስታ ተዘዋወረ፣ ከዚያም ወደ ሸዋና ጎንደር ሲዘዋወር በነገሥታቱም በሕዝቡም ተቀባይነት እያገኘ ነበር። በመጨረሻም ወንበሩ ሸዋ፣ አዲስ አበባ ላይ ሆነ። አፄ ኃ/ሥላሴም በዚሁ በዳግማዊ ምኒልክ ቤተ መንግሥት ውስጥ ነገሡ። የአፄ ኃ/ሥላሴ መንግሥትም ከኦሮሞ፣ ከትግራይ፣ ከኤርትራ፣ ከአማራ፣ አፋር፣ ጉራጌ ወዘተ ኢትዮጵያውያንን ማእከል ያደረገ ከፍተኛ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ነበራቸው። ከሚኒስቴር ዲኤታ እስከ መምሪያ ሃላፊዎች ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያቀፈ መንግሥት ነበር። እንዲያውም ቁልፍ የሆኑትን የሚንስቴር ቦታ ይዘው የነብሩት ትግሬዎች ነበሩ። በሥልጣን ክፍፍሉ አድልዎ አይታይም ነበር። በጤና እና በትምህርት ዋን ተጠቅሚ ትግራይ ነበረች። በዚህም አድልዎ አልታየም። አርመኔያዊ አገዛዝ፣ ኢሰብአዊነት (Dehumanisation) እያለ የህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራም የሚለፍፈው እንደዚህ አይነት ተግባር በትግራይ አልታየም። እውነቱን እንነጋገር ከተባለ የአፄ ኃ/ሥላሴ መንግሥት ምርጥ ምርጡን ለትግራይ ይሰጥ የሚል ስርዓት ነበረው። የትግራይ ሕዝብም ንጉሠ ነገሥቱን ከልብ ይወዳል፤ ንጉሡም የትግራይን ሕዝብ
ይወዱ ነበር። ደርግ አፄ ኃ/ሥላሴን እንደገደላቸው ባወቀ ጊዜ የትግራይ ሕዝብ ከትንሽ እስከ ትልቁ ደርግን ክፉኛ አውግዞት ነበር።
የትግራይ ሕዝብ ከአፄ ኃ/ሥላሴ ሞት በኋላ በኑሮው የተጎሳቆለና ለችግር የተጋለጠ ሕዝብ ሆነ። በደርግ ስርዓትም ቢሆን የትግራይ ሕዝብ ለችግርም ሆነ ለረሃብ ብዙ የተጋለጠ አልነበረም። ደርግ የመሬት አዋጁን በትግራይ ውስጥ ተግባራዊ አላደረገውም። ምክንያቱም የእርሻ መሬቱ አነስተኛ በመሆኑ ነበር። ደርግ በሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ በትግራይ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ወንጀል የለም። በኑሮም
አልተጎሳቆለም። በቀይ ሽብርም ቢሆን የተጠቃው አማራው ነበር። የትግራይን ሕዝብ ያጠቃ፣ ለድህነት የዳረገ፣ ለስደት፣ ለሸርሙጥና እና ለመንከራተት ያበቃውና ችግርና መከራ ይዞለት የመጣው ህ.ወ.ሓ.ት. ብቻ ነው። የህ.ወ.ሓ.ትን ፕሮግርራምና አፈጻፀሙን ካየን፣ ተግባራዊንቱን ደግሞ እንመልከት።
ወደዚህ ከመግባታችን በፊት ግን መመልከት ያለብን ነጥብ አለ። የአፄ ኃ/ሥለሴ መንግሥት ሃገር አቀፍ የሆነ ስርዓት እንጂ በአማሮች ብቻ የሚመራ መንግሥት አልነበረም። አማራው እንደቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ የተለየ ጥቅም ተቀባይ አልነበረም። እውነታው ይህ ሆኖ እያለ ህ.ወ.ሓ.ት. ለምን አማራውን ብቻ በጨቋኝነት፣ በዝባዥነትና በጸረ-ሰውነት ፈረጀው? ህ.ወ.ሓ.ት. በ48 ገጾች ሆን ብሎ አማራውን ለማጥቃት ያሰናዳው ፕሮግራም ወንጀል ነው። ከትግሉ መነሻ ጀምሮ አማራን ለማጥፋት 48 ገጽ ፕሮግራም ያወጣው ህ.ወ.ሓ.ት. ነው። አሁንም በሥልጣን ላይ ሆኖ በአማራው ላይ የዘር ማጥፋት ድርጊት የሚፈጽመው ህ.ወ.ሓ.ት. ነው። ፕሮግራሙን አርቅቀው እንዲተገበር ያደርጉት እነማን ናቸው? ዝርዝር ስማቸውን እንመልከት፤
1. አረጋዊ በርሄ
2. ስብሃት ነጋ
3. መለስ ዜናዊ
4. አባይ ፀሃየ
5. ሥዩም መስፍን
6. አውአሎም ወልዱ
8. ተወልደ ወ/ማርያም
7. ስየ አብርሃ
9. ገብሩ አስራት
10. አርከበ እቁባይ
11. ጻድቃን ገብረተንሳይ
12. ዘርአይ አስገዶም
13. ግደይ ዘርአጽዮን
ከነዚህ በተጨማሪ ከዚህ አለም በሞት የተለየው አታክለት ቀጸላ፣ በስብሃት ነጋ የተገደለ፤ አስፍሃ ሃገኦስ፣ ታሞ የሞተ፤ ግደይ ዘርአጽዮን ከ1969 ጀምሮ ህ.ወ.ሓ.ትን በጸረ- ዲሞክራሲነቱና በሽብርተኝነቱ ያወገዘ፤ ራሱን ከማንኛውም አስከፊ ተግባር ያገለለ፣ በታጋዩ ተከብሮና ታቅፎ የቆየና በ1977 ከህ.ወ.ሓ.ት. በመለስና በስብሃት ተባሮ የወጣው ኢትዮጵያዊ ይገኝበታል።
በህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራም በገጽ 16 ተጽፋ የምትገኘው ደርግንም የአማራ መንግሥት በማለት በመፈረጅ ታወግዛለች። ደርግ ግን የአማራ አልነበረም። ከዘረኝነት የጸዳ ነበር። የደርግ ስርዓት ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ያቀፈ ነበር። ህ.ወ.ሓ.ት. ይህን ሁሉ ውሸት የሚደረደረው ዋናው ምክንያት አማራውን ለማጥቃት የተቀነባበረ “ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” ነው። በገጽ 16 መጨረሻ ላይ ጽሑፉ እንዲህ በማለት ያጠቃልላል፣ “ጨቋኟ አማራም ህብረተሰብአዊ እረፍትና ሰላም አታገኝም” ይላል።
“ወይን” የሚባለው የህ.ወ.ሓ.ት. ልሳን መጽሔት ከ1969 መጀመሪያ በአማራው ላይ እንዲፈጸሙ በመሬት ላይ ተግባራዊ መሆን አለባቸው ተብለው በአጭርና በረጅም የትግል ጉዞ የተግባር ዝርዝር ሃታታ በስፋት በመዘርዘር አውጥተዋል። ከተዘረዘሩትም አንዱ የአማራው ሕዝብ እረፍትና ሰላም አያገኝም ለመኖርም አይችልም የምትለው የህ.ወ.ሓ.ት. አቋምና ፖሊሲ ይዛለች። ህ.ወ.ሓ.ት. በአማራው ላይ አጸፋዊ እርምጃ ይወስዳል። እርምጃውም አማራው ከመኖር ወደ አለመኖር ይለወጣል። በዚህ መሰረት በወይን መጽሔት የተዘረዘረው በጥር 1969 ወደ ተግባር ተለውጦ አማራው በተገኘበት መግደል ተጀምሮ ከዛም ወደ ወልቃይት ፀገዴ ተሸጋግሮ የዘር ማጥፋት ተካሂዷል።
1. ማንኛውም በህ.ወ.ሓ.ት. ነፃ መሬት የሚኖር አማራ ከትግራይ ለቆ በአስቸኳይ ይውጣ። በሕዝብ ግንኙነት ከያሉበት እየተለቀሙ በርካታ በጡረታ የተገለሉ ጦር ሰራዊት፣ ፖሊስ፣ ፊናንስ ፖሊስ፣ በሌላ የመንግሥት ሥራ ሲሰሩ የነበሩ በተለያዩ ቦታ ይኖሩ የነበሩ፤ ከትግራይ ሚስት አግብተው፤ ልጆች ወልደው ብዙዎቹም ልጆቻቸው ለትዳር የበቁ የልጅ ልጅ ያዩ ናቸው። ይህ ድንገተኛ ዘረኛ የህ.ወ.ሓ.ት. ፖሊሲ እንደተላለፈ አማራውም ከየቦታው እየተያዘ ሃለዋ ወያነ 06 ገብቶ ይጠፋል፣ ንብረቱም
ይወረሳል። የትግራይ መሬት ለትግራይ ሰዎች ብቻ በማለት ከሃገራችን ልቀቁልን ይላል። በትግራይ በ1969 የተጀመረው አሁን አማራው ከተለያየ ቦታ እየተጠረገ ተገፍቶ፣ ተፈናቅሎ በረሃ ላይ ወድቆ ይገኛል። ስለዚህ ከመሬታችን ውጡልን የተጀመረው በ1969 በህ.ወ.ሓ.ት. ሲሆን አሁንም ይህንን ክልል ተብለው የሚጠሩ የረጅም ጊዜ ውጥን ህ.ወ.ሓ.ት. በተግባር እፈጸመው ይገኛል። ከህ.ወ.ሓ.ት. ትግል መነሻ ጀምሮ እስከ ዛሬ አማራ ዘሩ እየጠፋ ነው።
2. ኢ.ህ.አ.ፓ. አባይ ኢትዮጵያ ከትግራይ ውጣ ሲባል፣ ትግራይ ኢትዮጵያ እኛም ኢትዮጵያውያን ነን ብለው አንወጣም በማለታቸው ለጥቃት ተዳረጉ። “ወይን” መጽሔት ከ1969 ጀምሮ በተከታታይ የሚያወጣው ጽሑፍ በህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራም ላይ የተቀመጡ የረጅም ጊዜ እቅድ በመተንተን እና በማብራራት ለታጋዩ ለውይይት በማቅራብ ሲያብራራ፣ ኢትዮጵያ ወይም ሞት ብሎ የሚናገረውን አማራ ማጥፋት ከሱም ጋር አብሮ የሚቀበረው አማርኛ ቋንቋ ይሆናል ይላል። በህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራምና በወይን መጽሔት እንደተዘገበው፣ አማራው የትግራይ ሕዝብ ጠላት እንደመሆኑ በግንባር ቀደምትነት ህ.ወ.ሓ.ት. አማራውን ማጥፋት ግዴታው ነው ይላል። ኢትዮጵያን ለማጥፋትና ከዓለም ካርታ ፍቆ ለማስወጣት አማራው ሲጠፋ ብቻ ነው በማለት ወይን መጽሔት ይዘረዝራል። ከጎንደር ጠ/ግዛት ከወሎ ለምና ሰፊ መሬት የነጠቀው ወያኔ በፕሮግርራሙ መቅድም V ላይ እንደዘረዘረው እውን ሆኖለታል። በሰፊና ለም መሬት የተከበበች ትግራይ “የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ” ነፃ ሃገር ማቋቋም ግብ አማራው ከጠፋ ተቀናቃኝ አይገጥመኝም በማለት የታቀደ የረጅም ጊዜ የስትራተጂ እቅድ ቀስ በቀስ ወደ ተግባር የሚለወጥ ነው። የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ኢትዮጵያን እገዛለሁ የሚል ተስፋም ህልምም አልነበረውም። ደርግ ተዳክሞ በራሱ ጉዞ እንደጠፋ ህ.ወ.ሓ.ት. በለስ ቀንቶት ግንቦት 1983 ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ እንደ ዋናው የፖሊሲ ፕሮጀክትና እቅድ በ1984 መጀመሪያ በተግባር ላይ ዋለ።
አማራውን ለብዙ ዓመታት ከኖረበት ቦታ ያፈራውን ሃብትና ንብረቱን፤ በትዳር ከኦሮሞው፣ ከሲዳማው፤ ከወላይታው ጋር ከተሳሰረበት ለአማራው “ነፍጠኛ፣ ተስፋፊ” የሚል ተለጣፊ ስም በመስጠት የአማራው ዘር እየተፈለገ በሁሉም እድሜ የሚገኙትን እየሰበሰበ በጥይት በመደብደብ፤ በገደል በመወርወር ፈጅቷል። ይህንን ተግባሩን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በመቀጠል በቤንች ማጂና ጉራ ፈርዳ ተመሳሳይ
ድርጊት ፈጽሟል። ሊገድላቸው ያልቻለውን ደግሞ የማንገላታት ተባሩን ቀጥሎ የአማራውን ብሄረሰብ እየነጠለ ከጉራ ፈርዳ፤ ከቤኒሻንጉል እንዲባረሩ በማድረግ ለክፉ ሰቆቃ ተዳርገዋል። ህ.ወ.ሓ.ት. ይህንን ሁሉ የሚያደርገው ከመመስረቱ ጀምሮ የወጠነውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ነው።
ይህንን ለመተግበር ወያኔ አስቀድሞ ያዘጋጀው እቅድ የአማራውን ቦታ ማጥበብ ነው። ትግራይ ከበጌምድርና ከወሎ ሰፊና ለም መሬት ወስዳለች። ከወሎ ሰፊ መረት ወደ አፋር ተከልሏል፤ የጎጃም መሬት ለአፋርና ለሌሎች ተሰጥቷል፤ ሸዋ እንዳለ የኦሮሞ ሆኗል። በዚህ
አይነት የአማራው መሬት ተከፋፍሎ የቀረችው መሬት የበሬ ግንባርም አታክልም። አንድ ነገር ካልተደረገ በስተቀር ነገ ደግሞ ከዚችው ከቀረችው መሬት ውጣ ሊባል ይችላል። ህ.ወ.ሓ.ት. ይህንን አማራውን የማጥፋት “Systematic elimination and genocide” ዋናው ፖሊሲ አድርጎ የተነሳው ገና ትግራይ በረሃ እዳለ ነው። አማራውን መግደል፤ ካልተቻለም በዘዴ ማጥፋት ብሎ ያቀደውን አሁን በግልጽ
እያስፈጸመው ነው። አማራው ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በመሆን እኩል መስዋእትነት ከፍሎ ሃገራችንን ዳር ድንበሯን በማስከበር ለብዙ ሺህ አመታት በነጻነት ያቆየን የሕዝብ አካል ነው።
ህ.ወ.ሓ.ት. አማራውን ለምን በጠላትነ ፈርጆ ያጠቃዋል? ለዚህ ብዙ ምክንያቶች መስጠት ቢቻልም ዋና ዋንዎቹን አንድ ሁለት ልበል፤
1. አማራውም ሆነ ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ነው። ኢትዮጵያዊነቱን አምርሮ የሚወድና የሚያፈቅር አማራ ነው ብሎ ስለሚያስብ አማራ ካልጠፋ ኢትዮጵያን ማጣፋትም ሆነ ማፍረስ ቀላ አይሆንም የሚል ግምት አለው። ስለዚህ አስቀድሞ የአማራውን አከርካሬ መስበር ከተቻለ ኢትዮጵያዊነትም አብሮ ይሰበራል የሚል ሕልም ስለአለው ነው።
2. ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. ሃገሪቱን በቋንቋና በሃይማኖት ከፋፍሎ እርስ በርሱ በማፋጨት ቂም በቀል እንዲይዝና አዳክሞ አገዛዙንማቅለል ከበረሃ ይዞት የመጣው ውስጣዊና ድብቅ ፖሊሲው ነው።
3. በዚች ዓለም ብዙ የተለያዩ ቋንቋዎች ይነገራሉ። ቢሆንም ብሄራዊ ቋንቋ የሌላቸው ሃገሮች የሉም ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያ ሃገራችንም ከ85 በላይ የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገርባት ሃገር ናት። ይሁን እና ለብዙ ዘመናት እንደብሄራዊ ቋንቋ ሲያገለግል የቆየው ግን በአማርኛ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የትኛውም ቦታ ቢኬድ አማርኛ ተናጋሪ አይጠፋም። የአማርኛ ቋንቋ መግባቢያ፣ መወያያና ሃሳብ ለሃሳብ መለዋወጫ ከሆነ በሺህ የሞቆጥር ዘመን አልፏል። ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. የአማርኛ ቋንቋ የጠላት ቋንቋ ስለሆነ መጥፋት አለበት ብሎ በፖሊሲ ደርጃ ይዞ የተነሳው ከ1967 ጀምሮ ነው። ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስርዓቱ ስር እንደወደቀች፤ ክልል ብሎ ከፋፍሎ እንዲያመቸው በከፋፈላቸው ግዛቶቹ በት/ቤቶች፤ በፍርድ ቤቶች፣
በመንግሥት መስሪያ ቤቶች አማርኛ ጥቅም ላይ እንዳይውል አገደ። ወያኔ ሥልጣኑን ከያዘ ወዲህ የተወለዱ ሕፃናት በትግራይ፣ ኦሮም፣ አፋር፣ ሲዳሞ፣ ጋምቤላ ወዘተ አማርኛ የማይናገረውና የማይሰማው በርክቷል። ይዞት በመጠው የጫካው ፖሊሲ አማካኝነት አማርኛን እያዳከመ በመቅበር ላይ ይገኛል። ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. የአማርኛ ቋንቋን በማዳከሙ ምን ትርፍ ያገኛል? የሚሉ አይጠፉም። በጥቂቱ ላስረዳ፤
1. የኢትዮጵያዊነት ብሄራዊ እምነትን ያዳክማል፤ ቀስ በቀስም ኢትዮጵያዊነትን ይደመሰስላል፤ ሃገር አልባና ባይተዋር ያደርጋል። የግል መገለጫና ማንነትን ያጠፋል።
2. ብሄራዊ ቋንቋ ስለማይኖር ከተወለድክበት ክልል መውጣት አትችልም። በማንኛውም የኢትዮጵያ ግዛት ተዘዋውሮ መሥራት አይቻልም። ይህ ሁሉንም የኢትዮጵያ ዜጋ የሚመለከት ነው። ይህ የወያኔ ፖሊሲ ወጣቱን ኢትዮጵያዊ አይኑን እና አእምሮውን ሸፍኖ ዜግነቱን እንዲረሳ የታቀደ ተንኮል ነው።
3. ብሄራዊ ቋንቋ እንዳይኖር እየተገበረ ስለሆነ፤ አመለካከትና አስተሳሰብ ከመንደር የዘለለ አይሆንም። ኢትዮጵያዊ ታሪክ፣ ባህልና
ማንነት አብሮ ይጠፋሉ።
4. ብሄራዊ ቋንቋ ካልኖረ እድገትና ልማት በምንም ተአምር በሃገሪቱ አይታይም። ይህም አንዱ የህ.ወ.ሓ.ት. ጸረ-ልማት ፖሊሲ ነው። ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. ክልል ብሎ ያስቀመጣቅቸው የኢትዮጵያ ሕዝብና ብሄራዊ የሆነውን የአማርኛ ቋንቋ በማዳከምና በማጥፋት ነው። አንዱን ክልል በሌላው ላይ መጠራጠርና ጥላቻ እንዲፈጥር ቢጥርም የፈለጉትን ያህል አልተሳካላቸውም። በሕዝቡ ብርታትና አልበገር ባይነት በተቻለው ሁሉ ኢትዮጵያዊነቱን ጠብቆ የሚኖር ኩሩ ሕዝብ እንደሆነ ይገኛል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የህ.ወ.ሓ.ትን ማንነት አውቆ ድርጊቱን በተለያየ መንገድ መግለጽ ከጀመረ ከራርሟል። ስለዚህ ህ.ወ.ሓ.ት. ይህንን የአማራውን የዘር ማጥፋት (Genocide)የረጅም ጊዜ እቅድና ፖሊሲ በማውጣትና በመተግበር በዋናነትየሚጠየቁት፤ ከነዘር ሃረጋቸው፤ እነማን ናቸው የሚለውን እንመልከት፤
1. መለስ ዜናዊ፣ በአባቱም በእናቱም ሕዝብና ሃገር ያጠፋ የባንዳ ዘር ኤርትራዊ
2. ስብሃት ነጋ፣ በእናቱ የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ (በናቱ በኩል)
3. አባይ ፀሃየ፣ የባንድ ልጅ አክሱም
4. ሥዩም መስፍን የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ
5. አርከበ እቁባይ፣ የባንዳ ልጅ አድዋ
6. ዶ/ር ሰሎሞን እንቋይ፣ የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ (በአባቱ በኩል)
7. ጸጋይ በርሄ፣ የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ
8. ጻድቃን ገብረተንሳይ፣ የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ
9. ቴዎድሮስ ሃጎስ፣ የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ
10. አባይ ወልዱ፣ የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ (በአባቱ በኩል)
11. ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ
12. ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ የባንዳ ልጅ (የሻእቢያ ፈዳያን የነበረ) ኤርትራዊ
13. አዜብ መስፍን፣ እድገቷ ኤርትራና ሱዳን ፀገዴ (ጸረ-አማራ)
ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉም ወላጆቻቸው የጣልያን ወራሪን በባንዳነት አሽከር ሆነው እያገለገሉ፣ ኢትዮጵያን የወጉና ሕዝቧን ያስፈጁ የጠላት ልጆች ናቸው። የወላጆቻቸውን ፈለግ በመከተል ወላጆቻቸው የሰጧቸውን አደራ በመከተል አሁንም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጥቃትና በደል እየፈጸሙ ነው። ኢትዮጵያን በማፍረስ፣ ሃብትና ንብረቷን በመመዝበርና በዘር ማጥፋት ወንጀል በመሰማራት በሕግ የሚያስጠይቃቸውን ድርጊት እየፈጸሙ ናቸው። ብ.አ.ዴ.ን. እና ኦ.ህ.ዴ.ድ. እንዲሁም የደቡብ ህዝቦች ንቅናቄም በዘር ማጥፋት አስፈጻሚነታቸው በወንጀል ተጠያዊ ናቸው። ይህንን የወያኔ ህ.ወ.ሓ.ትን እና የግብረአበሮቹን ሃገርና ሕዝብን የማጥፋት ተግባራቸው የመግቻው መፍትሄ ምንድን ነው? ለሚለው፤ እከሌ ከእከሌ፤ ፓርቲ ከፓርቲ፤ ግንባር ከግንባር፣ ወገን ከወገን ሳይለያይ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዞ አሻፋረኝ፣ አልገዛም፣ በቃኝ ብሎ በአጠቃላይ አንድ ሆኖ የሕዝብ አመጽ ማስነሳት ብቻ መፍትሄ ያመጣል እላለሁ።
ኢትዮጵያና ሕዝቧን እናድን
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር
ይህ ጽሑፍ ትኩረት የሚሰጠው በትግል በረሃ በነበርንበት ወቅት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህ.ወ.ሓ.ት.) በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖቶች ላይ ሲከተል የነበረውን አቋሙን ተቀብሮ ከነበረበት ጉድጓድ አውጥቼ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እነማን ናቸው የሚለውን ታሪካቸውን እና የተፈጸመውን ጸረ-እምነት ግፍ በአጭሩ ለማሳወቅ ነው። ህ.ወ.ሓ.ት. ገና ሲፈጠርና ተ.ሓ.ህ.ት. ተብሎ እንደተመሰረተ ሙልጭ ያለ ጸረ-ዲሞክራሲ ድርጅት ነው። በጸረ-ኢትዮጵያነትና በጸረ-ሕዝብነት የተሰማራ ቅጥረኛ ድርጅት መሆኑን ብዙ ጊዜ በጽሑፍና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለኢትዮጵያ ህዝብ ተናግሬአለሁ። የአሁኑ ጽሑፌ ህ.ወ.ሓ.ት. በሃይማኖት ላይ ሲከተለው የነበረውን ፖሊሲ ገና ከመጀመሪያ ትግሉ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የነበረውን ጸረ- ሃይማኖት ተግባራቱን የኢትዮጵያ ሕዝብ በግልጽ አውቆታል። እኔ ደግሞ የራሴን ልበል።

Friday, August 8, 2014

አቶ ሬድዋን ሁሴን በአሜሪካን የተዋረደበት ቪድዮ.


[Breaking News]
የኢትዩጵያ የመንግስት ጉዳዮች ኮምዪኒኬሽን ሚንስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን በአሜሪካ ተዋረዱ ከንግዲህ የወያኔ ባለስልጣናትምሆነ ተላላኪዎች ቦታም የላቸው

ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በጣምራ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ!

የሕውሓት/ ኢህአዴግ መንግሥት ምርጫውን ለማራዘም እንደሚፈልግ በካድሬዎቹ እና ለራሱ ቀረቤታ ባላቸው ግለሰቦች በኩል ሲያስወራ የቆየ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ይህን ተግባራዊ ለማድረግም የሰላማዊ ትግሉን ጨርሶ ለመዝጋት እያሳየ ባለው እኩይ እቅድ መሠረት ጠንካራ ፓርቲዎችን፣ የነፃ ጋዜጦችንና መጽሔቶችን ለመዝጋት ዳርዳር በማለት ላይ ይገኛል፡፡ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጠቅላላ ጉባዔውን ሐምሌ 13 እና 14 ቀን 2005 ዓ.ም ባደረገው የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ላይ ሁለት የምርጫ ቦርዱ አመራር ተወካዮች በተገኙበት ስብሰባውን አካሂዷል፡፡