Translate

Sunday, August 24, 2014

አስራ አንድ ጋዜጠኞች ተሰደ


(ከላይ ከግራ ወደቀኝ) ቶማስ አያሌው፣ ዳንኤል ድርሻ እና ግዛው ታዬ፣ (ከታች) ሰናይ አባተ እና አስናቀ ልባዊ (Top, left to right) Thomas Ayalew, Daniel Dirsha and Gizawe Taye. (Bottom, left to right) Senay Abate and Asnake Lebawi
በአምስት ሣምንታዊ መጽሔቶችና አንድ ጋዜጣ ላይ የተመሰረተውን ክስ ተከትሎ አስራ አንድ ጋዜጠኞች ለስደት ተዳረጉ። አስራ አንዱ ጋዜጠኞች የተሰደዱት በፍትህ ሚኒስቴር ሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. “የዐመጸ ቅስቀሳና የሐሰት ወሬዎችን በመንዛት ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ ጥረት አድርገዋል” በሚል በተመሰረተባቸው ክስ መሆኑን ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ የደረሰን መረጃ ያስረዳል።
ፍትህ ሚኒስቴር ክስ የመሰረተባቸው ሎሚ፣ ዕንቁ፣ ፋክት፣ ጃኖ እና አዲስ ጉዳይ መጽሔቶች እና አፍሮ ታይምስ ጋዜጦች ሲሆኑ፤ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አስራ አንድ ጋዜጦች ለስደት መዳረጋቸውን ለማረጋገጥ ችለናል።
ተሰዳጆቹ ጋዜጠኞች 1፣ ቶማስ አያሌው (የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተር)፣

2፣ ግዛው ታዬ (የሎሚ መጽሔት አሳታሚ እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር)፣
3፣ ዳንኤል ድርሻ (የሎሚ መጽሔት ሚዲያ ዳይሬክተር)፣
4፣ ሰናይ አባተ ቸርነት (የሎሚ መጽሔት ዋና አዘጋጅ)፣
5፣ አቦነሽ አበራ (የሎሚ መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር)፣
6፣ ሰብለወንጌል መከተ (የሎሚ መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር)፣
7፣ እንዳልካቸው ተስፋዬ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት አሳታሚ)፣
8፣ ኢብራሂም ሻፊ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ምክትል ዋና አዘጋጅ)፣
9፣ እንዳለ ተሼ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ከፍተኛ አዘጋጅ)፣
10፣ ሃብታሙ ስዩም (የአዲስ ጉዳይ አዘጋጅና አምደኛ) እና
11፣ አስናቀ ልባዊ (የጃኖ መጽሔት አሳታሚ እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር) ናቸው።
ጋዜጠኞቹ የተሰደዱት በደረሰባቸው ወከባ፣ እንግልት፣ ማስፈራራት፣ የቢሮ መታሸግ እንዲሁም ፍትህ ሚኒስቴር በመሰረተባቸው ክስ እስከ አስራ ስድስት ዓመት በእስር ሊቆዩ እንደሚችሉ በመረዳታቸው መሆኑን ለመረዳት ችለናል።
ለነፃው ፕሬስ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ገዥው ፓርቲ በፃው ፕሬስ ላይ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚያካሂደውን ወከባ እያወገዙ ይገኛሉ። ላለፉት አራት ወራት በእስር ላይ የሚገኙትና በሽብርተኝነት የተከሰሱትን ሦስት ጋዜጠኞችና ስድስት ብሎገሮችን ተከትሎ በስድስት የሕትመት ውጤቶች ላይ የተመሰረተውን ክስ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ዛሬ ዜና አጠናካሪ ለነዚሁ ወገኖች ላቀረበላቸው ጥያቄ፤ “በሚቀጥለው ዓመት (2007 ዓ.ም.) ለሚካሄደው ምርጫ ገዥው ፓርቲ የያዘው የቅድመ ምርጫ የጽዳት ዘመቻ ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
በጋዜጠኞቹ እና በአሣታሚ ድርጅቶቹ ላይ ከተመሰረቱት ክሶች ውስጥ ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ከደረሱት ውስጥ ከዚህ በታች የቀረቡት ይገኙበታል።
በጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው ተካልኝ እና ለግዛውና ቶማስ ኢነተርቴይንመን የፕሬስ ሥራዎች ኃ/የተወ/የግል ማኅበር ላይ የተመሰረተባቸው ክስ
The charge on Thomas Ayalew, Afro Times managing director
The charge on Thomas Ayalew, Afro Times managing director

በጋዜጠኛ ግዛው ታዬ ሆረደፋ እና በዳዲሞስ ኢንተርቴይመንት እና የፕሬስ ሥራዎች ኃ/የተወ/የግል ማኅበር ላይ የተመሰረተባቸው ክስ
The charge on Gizaw Taye
The charge on Gizaw Taye
The charge on Gizaw Taye

በጋዜጠኛ አስናቀ ልባዊ መሸሻ እና በአስናቀ ኢንተርቴይንመንትና ፕሬስ ሥራዎች ኃ/የተወ/የግል ማኅበር ላይ የተመሰረተባቸው ክስ

No comments:

Post a Comment