Translate

Thursday, September 29, 2016

የህወሃት መከላከያ ሰራዊት እጁን እየሰጠ ወደ ኤርትራ እየገባ ይገኛል

በልኡል አለም ሰበር መረጃ ! !
Ethiopian Soldiers ከምእራብ ትግራይ ወደ ኡምሃጅር የተወረወረ የህወሃት መከላከያ ሰራዊት የግንባር ጦር በገጠመዉ ድንገተኛ የተኩስ ልዉዉጥ ምክንያት እጁን እየሰጠ ወደ ኤርትራ እየገባ ይገኛል። ከሰሜኑ እዝ ከመከላከያ አባላቱ ዉስጥ ያፈተለከዉ መረጃ እንደሚጠቁመዉ ከሆነ የመዋጋት ፍላጎት የሌላቸዉ የህወሃት ወታደሮች በትናንትናዉ እለት ወደ አል-ፉሽቓ (Al fushqa) ሱዳን ድንበር በኩል አምርተዉ ለነጻነት ታጋዮች እጃቸዉን መስጠታቸዉ ታዉቋል። ብዛት ያላቸዉ ቀላልና ከባድ የጦር መሳሪያዎች በምርኮ መግባታቸዉንና የህወሃት መከላከያ ሰራዊት አባላትም መቀላቀላቸዉን የገለጸልን ምንጫችን በምርኮ የሚገቡትን ወገኖች የኤርትራ ወታደሮች ወደ መደበኛ ማረፊያ ማዘዋወራቸዉን ምንጮች አረጋግጥጠዋል፡፡ 
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !

Thursday, September 22, 2016

በአልሞ ተኳሽ እና በመሬት ስርቆት የታወቀው ህወሓት ለኢትዮጵያ አደጋ ተጠያቂ ነው – አክሎግ ቢራራ (ዶር)

አክሎግ ቢራራ (ዶር)
“እኛ ጠንካራ ለመሆን የምንችለው በመተባበር ብቻ ነው፤ በተጻራሪው፤ እኛ ደካማ የምንሆነው በመከፋፈል ነው።” ጀሪ ሮሊንግ፤ የቀድሞው የጋና ፕሬዝደንት
Ethiopia's killing squadዛሬ ግብጾች ስለ ኢትዮጵያ ያወጡትን ዘገባ ስሰማ ከዚህ በፊት ስለ ተሃድሶ ግድብ በተከታታይ ያቀረብኳቸውን ትንተናዎችና ማስጠንቀቂያዎች አስታወሰኝ። በአጭሩ ያሳሰብኩት ህወሓት/ኢህአዴግ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከፋፍሎና አፍኖ ይህን ለዚህ ግድብ ዋስትና ሊሰጥ አይችልም የሚል ነው። መጀመሪያ፤ ህወሓት ለራሱ የበላይነት በማሰብ ብቻ፤ ታላቋን ትግራይን ለመፍጠር ባለው ህልም ብቻ፤ ኢትዮጵያን በፈጠራ የሕዝብ ስርጭት ከፋፈላት፤ መተከልን ወደ ቤን ሻንጉል፤ ብዙ የጎንደርና የወሎ አማራ መሬቶችን ምንም ውይይት ሳይደረግ፤ ፓርላማው ሳያውቅ ወደ ታላቋ ትግራይ ቀላቀለ። የትግራይ ወሰን በአንድ ጊዜ ሱዳንን አካለለ፤ ወደ ደቡብ ሄዶ ቤን ሻንጉል ደረሰ። ታላቁን የተሃድሶ ግድብ ለአደጋ በሚያመች ሁኔታ ወደ ወዳጁ ሰሜን ሱዳን አስጠጋው። የግድቡ የውሃ ፈሰስ ለሱዳኖች እንዲጠቅም አደረገ፤ አደጋውን ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሸከም ወሰነ።

ብራቮ ሸገሮች፣ ብራቮ ጋዜጠኛ ሕይወት ፍሬ ስብሐት!!

በፍቅር ወርቁ
Addis Ababa University, Ethiopiaመንግሥት ከሰኞ ጀምሮ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ጋር የጀመረውን ውይይት በተመለከተ እየሰጣችሁን ያለው መረጃ እጅግ ሚዛናዊና የተብራራ ነው። የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን በሚያሳዝን ሁኔታ ስብሰባው በእጅጉ የተሳካና ያለ ምንም እንከን/ተቃውሞ እየተካሄደ እንዳለ ነው የዘገቡትና እየዘገቡት ያለው …።
ለአብነት ያህል ከሸገር ሬዲዮ ወጪ በመንግሥት ስር የሚገኙትም ሆነ የግሎቹ ኤፍ ኤም ሬዲዮኖች በስብሰባው የመጀመሪያ ቀን መንግሥት ለስብሰባው አጀንዳ ይሆን ዘንድ ባሰራጨው ሰነድ ላይ ፈጽሞ ለእኛ የማይመጥንና አገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ፖለቲካዊ ትኩሳትን ከግምት ውስጥ ያስገባ ባለመሆኑ በሚል- በተቃውሞ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የስብሰባው ተሳታፊ ምሁራን አዳራሹን ለቀው እንደወጡ የዘገበው የሸገር ሬዲዮ ብቻ ነው። በአጠቃላይ ከጅማሬው ቀን ጀምሮ የስብሰባውን ድባብ በሚዛናዊ መልኩ መረጃዎችን ለሕዝብ እያቀረባችሁ ነውና ሸገሮች ምስጋና እና አድናቆት ይገባችኋል። ለዚህ ለዛሬው የቁጭት ስሜት ለተቀላቀለበት አስተያየቴ ምክንያት የሆነኝ ግን፤

Thursday, September 1, 2016

የሕወሃት ብጥብጥ እና ሽሽት- ከውስጥ አዋቂ ምንጭ (ክንፉ አሰፋ)

ክንፉ አሰፋ
Ethiopia, TPLF officialsሕዝባዊ አመጹ ያመጣውን ቀውስ ተከትሎ በህወሃት ከፍተኛ አመራር ውስጥ ከፍተኛ መበጣበጥ እና የርስ-በርስ ፍጥጫ መከሰቱን ከታመነ የውስጥ አዋቂ ምንጭ መረጃ ደርሶናል። 
“Whoever sows injustice will reap calamity.”
“አመራሩ ክፉኛ ከመከፋፈሉ የተነሳም የርስበርሱ ችግራቸው ላይ ተወጥረዋል።” ይላል መረጃው። ቀንደኞቹ የህወሃት አባላት ስርዓቱ እንዳበቃለት ስለተገነዘቡ ንብረት እና ልጆቻቸውን በማሸሽ ላይ ናቸው።
ሕዝቡ ሁሉ እንደተፋቸው በግልጽ እየነገራቸው ስለተገነዘቡ፤ የህወሃት የደህንነት አባላት ሕዝቡን ተተው የራሳቸውን ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሰልሉ ተነግሯቸዋል። “ተጠርጣሪ” የኦህዴድ እና ብአዴን አባላት በነዚህ ሰላዮች ስለተከበቡ በፍርሃት መወጠራቸውን ከራሳቸው አንደበት እየተሰማ ነው።