Translate

Sunday, November 30, 2014

በህዳር 27ቱ ሠላማዊ ሰልፍ እንሳተፋለን !!! ከኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሠማ ኮሚቴ የተላለፈ የአጋርነት መግለጫ

Image

ሠማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች የአንድነት መድረክ በመፍጠር ሰላማዊ ሰልፍ ከህዳር 27/2007 ዓ.ም እስከ ህዳር 28/2007 ዓ/ም ለማድረግ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልፀው የሐገሪቱ ህዝብ በቦታው በመገኘት ድምፁን እንዲያሠማ ባሳወቁት መሠረት የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሠማ ጊዜያዊ ኮሚቴ እና የማህበሩ አባላት በሠላማዊ ሠልፉ ላይ ከሌላው የሐገራችን ህዝብ ጋር በመሆን ድምፃችንን እንደምናሠማ እየገለፅን ለሠላማዊ ሠልፉ መሣካት የበኩላችንን ደርሻም ለመወጣት ዝግጁ መሆናችንን ስንገልጽ በዚህ በጨለማ ዘመን ኃላፊነት ወስደው ይህንን ታላቅ ሠለማዊ ሠልፍ ላዘጋጁት የሠለማዊ ሠልፉ አዘጋጆች ምስጋናችንን በማቅረብ ነው፡፡

ተማሪዎች፣ መምህራን እና የተቋማት ፕሬዚዳንቶች ለአመጽ ተነሱ!

ተማሪዎች፣ መምህራን እና የተቋማት ፕሬዚዳንቶች ለአመጽ ተነሱ!

ተማሪዎች፣ መምህራን እና የተቋማት ፕሬዚዳንቶች ለአመጽ ተነሱ!

Nov 29, 2014
ዘረኛውና አምባገነኑ የህወሓት አገዛዝ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ከካድሬ ማሰልጠኛ ማዕከላትነት ለይቶ የማያይ ስለመሆኑ በተቋማቱ ውስጥ የሚደረጉ ተግባራት ማረጋገጫዎች ናቸው። ለዚህ ተግባሩ በሰነድ ደረጃ መቅረብ ከሚችሉት የቅርብ ጊዜ ማስረጃዎች ዋነኛው በህዳር 2007 ዓ.ም. በሥራ ላይ የዋለው “የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኢህአዴግ የምርጫ ድል ልማት ሰራዊት ግንባታ አደረጃጀት ማንዋል” የተሰኘው በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላለፈው ሰነድ ነው።

Friday, November 28, 2014

የሕወሐት/ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ፒ.ኤች.ዲዎችን ከተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ተቋማት እየገዙ እንዳሉ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ።

 እየሩሳሌም አርአያ


የሕወሐት/ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ፒ.ኤች.ዲዎችን ከተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ተቋማት እየገዙ እንዳሉ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሐጐስ ጐደፋይና ምክትላቸው አቶ አታክልቲ እንደሚገኙበት የጠቀሱት ምንጮቹ ለሁለቱ ባለስልጣናት በመቀሌ ሆስፒታል የሚሰራ የባዮስታቲክስ ባለሙያ በኩል የጥናት ፕሮፖዛላቸውን አሰርተው ፕሮፖዛሉ ፀድቆ ዋናውን ጥናት ይህ ባለሙያ ግለሰብ እየሰራላቸው እንደሚገኝ አያይዘው ገልፀዋል። ባለስልጣናቱ ስለጥናቱ አንዳችም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ምንጮቹ አጋልጠዋል። ሌሎች ስድስት የህወሀት ባለስልጣናትም የማስተርስና ፒ.ኤች.ዲ ጥናት እየፃፈላቸው እንደሚገኝ ምንጮቹ አክለው ገልፀዋል። ሌሎች የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎችም የዚህ ህገወጥ ተግባር ተሳታፊዎች ናቸው ያሉት ምንጮቹ በተለይ ሪፍት ቫሊ የተባለውን የግል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሚስተካከል የለም ብለዋል። የኦህዴድ ባለስልጥናት ባለድርሻ የሆኑበት ይህ ዩኒቨርሲቲ ገንዘብ ለከፈለ ሁሉ ሰነድ አዘጋጅቶ ዲግሪና ማስተርስ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

Thursday, November 27, 2014

የህወሃቱን ፖለቲካ የአዋጁን በጀሮ!

የህወሃቱን ፖለቲካ የአዋጁን በጀሮ!

ህወሃት በተፈጥሮው የፖለቲካ ብዙህነት ወይም ብዝሃነትን ማቻቻል የሚባል ነገር አያውቅም። ሌላው ቀርቶ በራሱ በድርጅቱ ውስጥ የሚነሱ የተለዩ ሃሳቦችን ሁሉ እንደጠላት ሃሳብ ፈርጆ ሰዎችን ደብዛቸውን ማጥፋት የተለመደ የህወሃት አሰራር ነው። ይህን የህወሃት ባህርይ በቅጡ ለመረዳት በቅርቡ የቀድሞው የህወሃት አመራር አባል የነበረው አቶ ገብሩ አስራት የጻፈው መጽሃፍ ጥቂት ገጾች በማየት መረዳት ይቻላል። ተቃዋሚ ፓርቲ ሰላማዊም ሆነ አልሆነ በህወሃት እንደጠላት ነው የሚቆጠረው።
ሰሞኑን ከትግራይ የህዝብና የመንግስት ግንኙነት ቢሮ ከሚባለው መስሪያ ቤት በትግረኛ ተጽፎ ለአባለት በሚስጥር የተሰራጨ ደብዳቤ ማንኛውምንም ተቃዋሚና ከህወሃት ውጭ የሚያስብና ህወሃትን የማይከተል ሁሉ “ፀላኢቲ” ጠላቶች ሲል ይፈርጃል። በዚህ ባለ 5 ገጽ ደብዳቤ ውስጥ እነዚህን “ፀላኢቲ” እንዴት እንደሚያሳድዱ፣ እንዴት እንደሚያዋክቡና እንደሚያጠፉ የሚመክር መመሪያ የሚሰጡ ሃሳቦች ተቀምጠዋል። በደብዳቤው ላይ ከአናቱ ሆነው የሚያስተዳደሩትን ወገናቸውን እንኳን አይለይም። በአጭሩ እኛ እንዳንመርጥ የሚፈልግ፣ የሚቀናቀንና ሌሎች ሰላማዊ ፓርቲወችን የሚመራና የሚደግፍ ሁሉ ፀላኢቲ ነው።
ይህ ለ2007 ዓ.ም የክትትል ስራ የተመደበው የህወሃት ቡድን ስራውን የሚያከናውነው ከታክስ ከፋዩ በሚገኝ የመንግስት ገንዘብ መሆኑ ይታወቃል።
ዘንድሮ የምርጫ አመት መሆኑን ተከትሎ የፀላኢቲ ክትትልና አፈና ከአሁን ተጠናክሮ በመካሄድ ላይ መሆኑም እየታየ ነው። ጠንካራ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ በየክልሉ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን ሁሉ በመታፈንና ወህኒ በመውረድ ላይ ናቸው።
የህወሃት ኢህአዴግ መሪዎች በአለም ዙሪያ ነጻነቴን የሚል የህዝብ ድምጽ በሰሙ ቁጥር የሚሰማቸውን ድንጋጤ የሚቀንሱት ዜጎችን በማፈን፣ በመግደል፣ በማሰቃየትና በማሰር ብቻ ነው።

ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚደረግ ደባ፣ ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚደረግ ደባ፣ ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ለአራት አስርት ዓመታት እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው እና በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ከህዝብ ፍላጎት ውጭ በኃይል በስልጣን ወንበር ላይ ተፈናጥጦ የሚገኘው የወሮበላ የማፊያ ቡድን ኢትዮጵያን ለማጥፋት ቀጣይነት ያለው እና የማያቋርጥ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና የባህል ጦርነት በመክፈት ዕቅድ አውጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የህወሀት ኢትዮጵያን የማጥፋት ተልዕኮው እና ፍልስፍናው የተመሰረተው በተወሰኑ የአፈጻጸም ስልቶች፣ ፖሊሲዎች፣ የድርጊት መርሀ ግብሮች እና ተሞክሮዎች ላይ ሲሆን በዋናነት የሚከተሉትን የአፈጻጸም ስልቶች ያካትታል፣ 1ኛ) የኢትዮጵያውያንን/ትን ብሄራዊ ማንነት በጠባብ እና በጎሳዊ አመላካከት ተክቶ በመከፋፈል ኢትዮጵያውያን/ት ያሏቸውን የማህበራዊ የጋራ ልምዶች፣ የህዝቡን የተከበሩ እሴቶች፣ እምነቶች እና ልማዶች ፍጹም በሆነ መልኩ እንዲወገዱ አበርትቶ መስራት፣

Wednesday, November 26, 2014

ስለደፈራ፤ ደፈር ብለን ስናወራ (በእውቀቱ ስዩም)

Beweketu Seyoun joke about African leaders summit [Very Funny]
ኣስገደዶ መድፈር በእንስሳት በኣሶች እንዲሁም በነፍሳት ኣለም ውስጥም ይስተዋላል፡፡ይልቁንም ለሰው እሩብ ጉዳይ በሆኑ ዝንጀሮዎች ዘንድ የተለመደ ነው፡፡ተፈጥሮ በደፋሪነት ያጨቻቸው ባብዛኛው ወንዶችን ቢሆንም ሞገደኛ እንስቶችም ኣልጠፉም፡፡ለምሳሌ ወንዱ ንብ ከሴቷ ጋር ሲሳረር ሴቲቱ በዚያ ነገር ቆልፋ ትይዝበታለች፡፡በጦዘ ስሜት ውስጥ ሆና ኣልመዝምዛ ትቆርጥበታለች፡፡ወይም በጅንኖች ኣባቶቻችን ኣነጋገር ትሰልበዋለች፡፡ኮርማው ንብ በጀንደረባነት የመቀጠል እድል የለውም፡፡ በደረሰበት ጥቃት ያልጋ ቁራኛ ማለቴ የቀፎ ቁራኛ ሆኖ ይሞታል፡፡ሰራተኛ ንቦች ኣስከሬኑን ከቀፎው ጠርገው ወደ ውጭ ይጥሉታል፡፡
ኣብሬሽ ኣድሬ ሲነጋ ልሙት
ላፈር ኣይደለም ወይ የተፈጠርኩት
የሚለው የሙሉቀን መለሰ ዘፈን የኮርማ ንቦችን ህይወት በደንብ ይገልጣል፡፡

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር አመራሩ ድብደባ እንደተፈጸመበት ገለፁ።

አንድ ወር የትግል መርሃ ግብር ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎችና ህዝባዊ የለውጥ ንቅናቄዎችን በገዥው ፓርቲ አፈና እና ማስፈራሪያ እንደማይቆም ትብብሩ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡
ህዳር 7/2007 ዓ.ም የትብብሩ ህዝባዊ የአደባባይ ስብሰባ በኃይል መበተኑን፣ ይህንኑ አስመልክቶ ህዳር 7/2007 ዓ.ም ለሰማያዊ ፓርቲ ማስጠንቀቂያ መጻፉን እና ለህዳር 21 ለሚደረገው ስብሰባ የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ደብዳቤ በፖስታና በአካል ቢላክለትም ማሳወቂያ ክፍሉ አልቀበልም ማለቱን የገለጸው መግለጫው ስርዓቱ የትብብሩን የትግል መርሃ ግብር ለማስቆም እየጣረ መሆኑን ገልጾአል፡፡
በተጨማሪም የትብብሩ አንድ አባል እና ትብብሩ ህዳር 21/2007 ዓ.ም የሚያደርገውን የአደባባይ ስብሰባ የሚያስተባብረው መኢዴፓ ሊቀመንበርና የትብብሩ ገንዘብ ያዥ የሆኑትን አቶ ኑሪ ሙደሲር ላይ የድብደባ ወንጀል እንደተፈጸመባቸው አመራሩ ገልጸዋል፡፡

Tuesday, November 25, 2014

“የደም ከፈን!”

ኦባንግ ለስዊድኑ ባለሃብት ማስጠንቀቂያ ላኩ

redclothing

Monday, November 24, 2014

“ምስጢር ካወጣህ ቤተሰቦችህን እንፈጃቸዋለን” “ብዙ አይነት የድብደባና የስቃይ መአት ደርሶብኛል”




“የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል”
ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት

Sunday, November 23, 2014

ታሪክን ማደብዝዝም ማጥፋትም አይቻልም!

በአለማችን በተለይ አፍሪካ ዉስጥ የአገርን ብሄራዊ ኃብት የሚዘርፉ፤የህዝብን መብት የሚረግጡና አገርን እነሱ ባሰኛቸዉ አቅጣጫ ብቻ ይዘዉ የሚነጉዱ አያሌ ፈላጭ ቆራጭ መንግስታት አሉ። እነዚህ ህዝብን የሚበድሉ መንግስታት ሁሉም በጥቅሉ አምባገነን ይባሉ እንጂ በመካከላቸዉ ጎላ ብሎ የሚታይ ትልቅ ልዩነት አለ። ሀኖም የቱንም ያክል ልዩነት ቢኖርም እንደ ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች እንመራዋለን የሚሉትን ህዝብ የሚንቁና የኛ ነዉ የሚሉትን አገር የሚጠሉ አምባገነን መንግስታት የሉም፤ በታሪክም ኖረዉ አያዉቁም። አምባገነን መንግስታት የስልጣን ዘመናቸዉን ለማራዘምና ከስልጣን ጋር ተያይዞ የሚመጣዉን ክብር፤ ዝናና ጥቅማ ጥቅም እንዳይቋረጥ ሲሉ የሚቃወማቸዉንና ለስልጣን ዘመናቸዉ አደጋ ነዉ የሚሉትን ሁሉ ያስራሉ፤ ይደበድባሉ ወይም ይገድላሉ። እነዚህን ነገሮች የወያኔ መሪዎችም ያደርጋሉ፤ ነገር ግን በወያኔና በሌሎቹ አምባገነን አገዛዞች መካክል እጅግ በጣም ትልቅ ልዩነት አለ። ለምሳሌ ወያኔዎች ዘረኛ አምባገነኖች ናቸዉ፤ የወያኔ መሪዎች ኢትዮጵያን እንደ ጥገት ላም አንጂ እንደ አገራቸዉ አይመለከቱም። ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያን፤ ህዝቧንና ታሪኳን ይንቃሉ፤ ያንኳስሳሉ።
ባለፉት አምስትና ስድስት አመታት በግልጽ እንደተመለከትነዉ የወያኔ መሪዎች የኢትዮጵያን ገበሬ ከመሬቱ አፋናቅለዉ ለምለም መሬቱን ለባዕዳንና ለህወሓት የጦር መኮንኖች ሰጥተዋል። መሬቴንና ቤቴን አልለቅም ብሎ የተቀናቀናቸዉን ደግሞ በጅምላ ገድለዋል። በከተሞች ዉስጥም ከተሜዉን ምንም ካሳ ሳይከፍሉት ዕድሜ ልኩን ከኖረበት ቤቱ እያፈናቀሉ ከነቤተሰቡ ሜዳ ላይ ጥለዉት መሬቱን ባለኃብት ለሚሏቸዉ የወያኔ ባለሟሎች ሰጥተዋል። በአጠቃላይ የወያኔ መሪዎች በኢትዮጵያ አንድነት፤ በታሪኳና በህዝቧ ላይ እንዲህ ነዉ ተብሎ ለመናገር የሚዳግት ትልቅ በደል ፈጽመዋል። ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች በእናት አገራችን ላይ ያደረሱት በደል ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለምና ዛሬ ወደዚያ ዝርዝር ዉስጥ አንገባም፤ ዛሬ ትኩረት የምንሰጠዉ ወያኔ ደግሞ ደጋግሞ ከዘመተባቸዉና ሙሉ ኃይሉን ካሳረፈባቸዉ የአገራችን እሴቶች አንዱ ታሪካችን ነዉና የዛሬዉ ቆይታችን በዚሁ በታሪካችን አካባቢ ይሆናል።

ተቃዋሚዎች- ከመጠላለፍ ከወሬና ሃሜት ከሴራና ደባ ይልቅ እስትራቴጂ ያለው የፖለቲካ መስመር መከትል ወሳኝ ነው::

ተቃዋሚዎች - ግብታዊነት እና የሆያሆዬ ፖለቲካ መቆም ያለበት ጉዳይ ‪#‎Ethiopia‬

Imageከመጠላለፍ ከወሬና ሃሜት ከሴራና ደባ ይልቅ እስትራቴጂ ያለው የፖለቲካ መስመር መከትል ወሳኝ ነው::
‪#‎UDJ‬ ‪#‎Blueparty‬ ‪#‎AEUP‬ ‪#‎Medrek‬ ‪#‎Freedomforfairelection‬ 
‪#‎Election2007‬
ሃገሪቷ ህገ መንግስት አላት ቢደሰኮርም በስርኣት አልበኞች እየተጣሰ ህግ በህግ እየተሻረ እና ባለስልጣናት እየሸረሸሩት አማራጭ የፖለቲካ አመለካከቶች እና አስተሳሰቦች እንዳይንሸራሸሩ እና እንዳይወዳደሩ በማድረግ በህግ የተረጋገጠውን የብዙሃን የፓርቲ ስርኣት እንዳይሰፍን እንቅፋት ቢሆኑም ይህ ደሞ ከስርአቱ አምባገነንነት ጎን ለጎን የተቃዋሚዎች ድክመት ታይቶ የሚወሰድ እርምጃ ነው::

የአውሮፓ ህብረት ምርጫውን እንደማይታዘብ ታወቀ

ነገረ ኢትዮጵያ

የአውሮፓ ህብረት ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በምርጫው ጉዳይ አነጋገረ
• ጠቅላይ ሚኒስትሩንም ምሽቱን ያነጋግራል ተብሎ ይጠበቃል
• ህብረቱ ምርጫውን አይታዘብም ተብሏል
EU electionየአውሮፓ ህብረት ልዑክ ህዳር 11/2007 ዓ.ም ሶስት የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎችን ያነጋገረ ሲሆን፣ በኢህአዴግ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ለማነጋገር ምሽቱን ቀጠሮ መያዙን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በአውሮፓ ህብረት የልዑል መሪ ሻንታል ሔቤሬት የተመራው የልዑካን ቡድን የሰማያዊ ፓርቲና የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነትን፣ እንዲሁም የመኢአድና የመድረክን አመራሮች ማነጋገራቸው ታውቋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ሶስቱን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያነጋገረበት ዋነኛው አላማ ከምርጫ 2007 በፊት ያሉትን ችግሮች ለማወቅ የሚል ሲሆን በተቃዋሚዎቹ በኩል ያሉትን ችግሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚያቀርቡ ገልፀዋል፡፡

ኤሌክትሪክ በየሰዓቱ ይጠፋል “የእጃችንን አገኘን” -10 ቢ.ብር ሲባክን ዝም ብለናል


15 ቢ. ብር የፈጁትን የነፋስ ተርባይኖች፤ በ5 ቢ.ብር የውሃ ግድብ መተካት ይቻላል
ከ10 ቢ. ብር በላይ ሃብት በከንቱ ባከነ፤ እንደ ዘበት በነፋስ ተወሰደ ማለት ነው
በረሃብተኛ ድሃ አገር፣ ይሄ ሁሉ ብክነት እብደት ነው? ወንጀል ነው? ወይስ ምን?
ግን፤ ወይ ነገሬ አላልነውም፤ ወይ አብረን አጨብጭበናል፤ ወይ በዝምታ ፈቅደናል
የግድብ ግንባታን የሚቃወሙ የአካባቢ ጥበቃ ቡድኖች፣ መጫወቻቸው አድርገውናል
ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ፤ የአካባቢ ጥበቃ ቡድኖችን፤ “የድህነት ጠበቃ” ብለዋቸው ነበር

Saturday, November 22, 2014

የአንድነት ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት በማንኛውም አይነት ሁኔታ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ከሌላ አካል ጋር ሆነው ሲሰሩ የተገኙ በእስር ላይ ያሉት የአንድነት አመራር አካላት የኢትዮጵያ መንግስት ፍርድቤት የወሰነባቸውን የጥፋተኝነት ውሳኔ መጨረስ አለባቸው። እኛ የህሊና እስረኞች አንላቸውም ሲሉ ተናገሩ

የአንድነት ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት በማንኛውም አይነት ሁኔታ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ከሌላ አካል ጋር ሆነው ሲሰሩ የተገኙ በእስር ላይ ያሉት የአንድነት አመራር አካላት የኢትዮጵያ መንግስት ፍርድቤት የወሰነባቸውን የጥፋተኝነት ውሳኔ መጨረስ አለባቸው። እኛ የህሊና እስረኞች አንላቸውም ሲሉ ተናገሩየአንድነት ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት በማንኛውም አይነት ሁኔታ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ከሌላ አካል ጋር ሆነው ሲሰሩ የተገኙ በእስር ላይ ያሉት የአንድነት አመራር አካላት የኢትዮጵያ መንግስት ፍርድቤት የወሰነባቸውን የጥፋተኝነት ውሳኔ መጨረስ አለባቸው። እኛ የህሊና እስረኞች አንላቸውም ሲሉ ተናገሩ
ሰሞኑን የአንድነት ፓርቲ በመጪው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ መዘጋጀቱን በገለጹበት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የፓርቲው ም/ሊመንበር አቶ ግርማ ሰይፉ ድርጅታቸው የፍርድቤት ውሳኔን ማክበርን ከመንግስት በላይ እንዲከበር እንሰራለን። በኢትዮጵያ ሰላምና ፀጥታ የሚያደፈርስ ጉዳዮችን ከገዥው አካል በበለጠ እንቃወማለን። ስለዚህ የታሰሩት የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች አውቀውም ሆነ ሳያውቁት ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ሲሰሩ የተገኙ ፍርድቤት ጥፋተኛ ብሎ የወሰነባቸው የአንድነት የህሊና እስረኞች አይደሉም፤ የጥፋተኝነት ውሳኔውን በእስር ላይ ሆነው መጨረስ አለባቸው ሲሉ ለተሰብሳቢው አስታውቀዋል።

Friday, November 21, 2014

ሰበር ዜና – የአዲስ አበባ አስተዳደር ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል በሰማያዊ ፓርቲ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ

ነገረ ኢትዮጵያ
• ‹‹ማስጠንቀቂያውን እንደ ቁም ነገር አንቆጥረውም›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

• ‹‹ስርዓቱ ምን ያህል ዝቅጠት ውስጥ እንደገባ ያሳያል›› አቶ ግርማ በቀለ
blue_party_ethiopia101370869814-1የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህዳር 7/2007 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ ያስተባበረው የ9ኙ ፓርቲዎች የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ፀረ ህገ መንግስት በመሆኑና ነዋሪዎችን ሰላምና ፀጥታ በማወኩ በቀጣይ ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ካደረገ ለህዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠነቀቀ፡፡

አስተዳደሩ ትናንት ህዳር 11/2007 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ፤ ህዳር 6 ቀን ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል በሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ለህዝብ የተሰራጨው በራሪ ወረቀት ህገ ወጥ መሆኑን፣ ህዳር 7/2007 ዓ.ም በኢንጅነር ይልቃል ጌትነት መሪነት ሊደረግ የነበረው አደባባይ ስብሰባ ህገ ወጥ እንደነበርና በወቅቱ የስብሰባው ተሳታፊዎች ከፖሊስ ጋር ግብ ግብ ከመግጠማቸውም በተጨማሪ የአካባቢውን ህዝብ ሰላምና ፀጥታ አውከዋል ሲል ከሷል፡፡ አስተዳደሩ አክሎም ፓርቲው የአደባባይ ብጥብጥና ሁከት በመፍጠሩ እርምጃ እወስዳሉ ሲል ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ልኳል፡፡

በሃብታሙ አያሌው ላይ የቀረበው ክስ ዝርዝር (እንደወረደ

habtamu ayalew
(ዘ-ሐበሻ) በእስር ላይ የሚገኘው ታዋቂው ወጣት ፖለቲከኛ ሃብታሙ አያሌው በመንግስት አቃቤ ሕግ የቀረበበት የክስ ቻርጅ በፍርድ ቤት ተሰምቷል:: ሙሉው የክስ ቻርጅ ለዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ግንዛቤ ይረዳል በሚል እንደወረደ ቀርቧል::

Wednesday, November 19, 2014

የሚሊዮኖች ድምፅ ለህሊና እስረኞች!

የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት አንዱ አካል የሆነው የህሊና እስረኞችን የሶሻል ሚዲያ ንቅናቄ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ዘመቻ ሲሆን ከሚቀጥለው ከእሁድ ከህዳር 14 እስከ 20/2007 የሚቀጥል ፕሮግራም ነው። በዚህ ዘመቻ ሚሊዮኖች የፖለቲካ ይሳተፋሉ፤ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ ተገቢ የሆነ አያያዝ እንዲኖራቸው፤ በሰላማዊ መንገድ የሚታሉትን ማሰርና ማዋከብ እንዲቆም ድምፃቸውን ያሰማሉ፤
ዘመቻው ለመንግስት ባለስልጣናት፣ ለመንግስት መስሪያቤቶች፣ ኤምባሲዎች፣ ለታዋቂ ግለሰቦች፣ ለአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ተሟጓች ተቋማት፣ ለተለያዩ ሚዲያዎች፣ በE‐mail በsms፣ በinbox ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የህሊና እስረኞች አያያዝና የእስር ሁኔታ፣ የታሳሪዎች ማንነትና አሁን የሚገኙበት ሁኔታ ወዘተ በመግለፅ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ እንዲያሳድሩ ማድረግ ነው።

ለማላገጫ – የወያኔ ምርጫ። (ሥርጉተ ሥላሴ)

ሰሞኑን በተከታታይ የማነባቸው ሁሉ በምርጫ ላይ ያተኮሩ ናቸው። ቢሆን መልካም በነበረ። ህልሙ እሱ ስለሆን። ነገር ግን ምርጫ በዬትኛው ነፃነት ነው የሚከወነው?በዬጊዜው ጠንካሮችን እዬገበሩ አዲሶቹ እስኪለማመዱ ጊዜ እዬተገደለ፤ ለተመክሮና ለልምድ አዲስ – ገብ እስኪዋህድ ድረስ ወያኔ ያሻውን እንደ ልቡ እንዲከውን ነውን? ይህ አዟሪታማ ጉዞ የዛሬ አራት ዓመትም ይመጣል። ቀጣዩን አራት ዓመትም መሰሉን ለመከወን አቅዶ እንዳሻው ከባለ ጊዜ ጋር ደልቆ ይነጉዳል። ምርጫ ይመጣል – ይሄዳል። ተጠቃሚውና አትራፊው ግን በውጪ ድጋፍ ለጋሾች ሆነ በፈላጭ ቆራጭነት አገር ቤት – ወመኔው ወያኔ ነው።

Tuesday, November 18, 2014

ለነፃነታችን በጋራ ቆመን ታሪካዊ ግዴታችንን የምንወጣበት ጊዜው አሁንና አሁን ነው!

የኢትዮጵያ ህዝብ ፍትህና ነፃነት እንደናፈቀ፤ ሀገራችንም ቅን መሪ እንዳጣች ዘመናት ተቆጠሩ። በየጊዜው የመጡ ገዢዎቿ በህዝቧ መሥዕዋትነትና ታላቅ ተጋድሎ በተገኘ ድል ሥልጣን ላይ ከወጡ በሗላ፤ በህዝብ ፊት ቃል የገቡትን ወደ ገደል ሰደው፤ ዘግናኝ በሆነ ሥርዓታቸው በማፈን ህዝቧን ለከፋ ድህነትና ጉስቁልና ሲዳርጉት፤ አይናችን እያየ ጆሮአችንም እየሰማ፤ አመታት ተቆጥረዋል። የቅርብ ታሪካችን እንደሚመሰክረው፤ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፆታ፣ እድሜ፣ ሃይማኖት፣ ጎሳና፣ ዘር ሳይለይ ለአለፉት ዘመናት በተለይም በአምባገነኖቹና በጨካኞቹ የደርግና የህወሓት/ኢህአዴግ ስርአቶች እንደ ባእድ ወራሪ በገዛ ልጆቹና ሃገሩ የግፍ ግፍ ሲፈፀምበት፣ ምድሪቱም በደም ጎርፍ ስትታጠብና፣ ሁሉም በሚችለውና በአቅሙ እነዚህን የሰው አውሬዎች ከላዩላይ ለማስወገድ ሲኳትንና በመራራ ትግሉና በውድ ልጆቹ መስዋዕትነት የመጀመሪያውን ጭራቅ አስወግዶ ሁለተኛውን ሰይጣን ሲተካ ሃዘኑ ያልጠናበትና ፈጣሪውን ያላማረረ ኢትዮጵያዊ የለም።

አምባገነንነት ከምድረገፅ መጥፋት አለበት!

ባለፈው ሳምንት ቡርኪናፋሶን ለ27 ዓመታት እንደ ግል ንብረታቸው ሲያዙባት የከረሙት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ብሌስ ኮምፓዎሬ፤ የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ሲሉ ህገመንግስቱን ለማሻሻል ያደረጉት (ንቀትና ድፍረት የተቀላቀለበት ነው) ሙከራ ያስከተለው ውጤት ያልጠበቁት ነበር፡፡ (አመዳቸውን ቡን ሳይል አልቀረም!) ምንም ቢሆን የህዝብ አመፅ አይጠብቁማ፡፡ መቼም የሥልጣን እህል ውሃቸው ቢያልቅ ነው እንጂ አምባገነኖች እንዲህ በቀላሉ ከቤተመንግስት እኮ አይወጡም፡፡ (ያውም በአንዲት ቀን አብዮት?!) አመጽና ተቃውሞን በሃይል ለመመከትና ለማፈን ሁሌም ታማኝና አስተማማኝ ወታደራዊ ኃይል ከጎናቸው አይጠፋም፡፡ የስልጣን ገመዳቸው ተበጠስ ያለው ጊዜ ግን ወታደሩም ፊቱን ያዞርባቸዋል፡፡ በአምባገነኖቹ የአፍሪካ መሪዎች በእነ ጋዳፊ፣ ሁስኒ ሙባረክ…አይተነዋል፡፡
የአምባገነን መሪዎችን ባህሪና ነገረ ስራ እንደ አዲስ ለመፈተሽ ያነሳሱኝ (Inspiration ሆነውኛል!) ከስልጣን ከተወገዱ የሳምንት ዕድሜ ብቻ ያስቆጠሩት የቡርኪናፋሶው የቀድሞ መሪ ናቸውና ምስጋና ይገባቸዋል (አምባገነን ማመስገን ነውር ነው እንዳትሉኝ!) እናላችሁ ፍተሻዬን ውጤታማ ለማድረግ በአምባገነን መሪዎች ዙሪያ ያልበረበርኩት መረጃ የለም፡፡

Monday, November 17, 2014

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ በቢሮክራሲያዊ ሴራ የዜጎችን ህገመንግሥታዊ መብት ማፈን ሠላማዊ ትግሉን አያቆመውም!!



ዘጠኝ /9/ ህጋዊ ሰውነት ያለን ፓርቲዎች በትብብር ለመሥራት በተስማማነው መሠረት የአጭር ጊዜ የጋራ ዓላማችንን ማስፈጸሚያ ተግባራት የመጀመሪያ ዙር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የአንድ ወር ዕቅድ አውጥተን ወደ ሥራ መግባታችን ይታወሳል፡፡ የዚሁ የአንድ ወር ዕቅድ አካል ከሆኑት ተግባራት ቅዳሜ 6/03/07. ‹‹ዲሞክራሲያዊ ምርጫና የአፈጻጸም መርሆዎች›› በሚል ርዕስ የአዳራሽ ውይይት በተሳካ ሁኔታ አከናውነን በትናንትናው ዕለት 07/03/07. ደግሞ ከአዲስ አበባ ሰሜን ምስራቅ /ከአራት ኪሎና አካባቢው / ህዝብ ጋር በአደባባይ በቤልኤር ሜዳ ተገናኝተን በምርጫ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት የትብብራችን አባል የሆነው ሰማያዊ ፓርቲ ስብሰባውን እንዲያስተባብር በሰጠነው ኃላፊነት- የፖለቲካ ስብሰባ ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 3/1983 የምጠይቀውን ሁኔታ አሟልቶ ለከንቲባ /ቤቱ የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል 02/03/07 ደብዳቤ ማስገባቱ፣ የጽ/ቤቱ ክፍልም ለደብዳቤው 04/03/07 . መልስ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ከክፍሉ የተጻፈለት ደብዳቤ፡-

1.
የተሰጠው መልስ ዕውቅናውን በተመለከተ ግልጽ ያለመሆኑን፤

2.
ከላይ በተጠቀሰው አዋጅ መሰረት አንቀጽ 2 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ የተገለጸውን የሚጻረር መሆኑን፣

3.
በአዋጁ አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ ከተደነገገው ጋር የሚቃረን፤
በጥቅሉ በክፍሉ የተጻፈው ደብዳቤ በአዋጁ መሰረት 12 ሰዓት ውስጥ የተሰጠ ምላሽ ካለመሆኑም፣ ጊዜና ቦታውን ለመቀየር እንኳ አማራጭ ያልቀረበበት፣ ለስብሰባው ዕውቅና ለመንፈግ እንደ ምክንያት የቀረበውም ግልጽ ሆኖ ባለመቅረቡ ፓርቲው የተጻፈውን ደብዳቤ አሳማኝ ሆኖ እንዳላገኘውና እንዳልተቀበለው፣ በመሆኑም ስብሰባው አስቀድሞ በተገለጸው ቦታና ጊዜ እንደሚካሄድ 05/03/07 . በተጻፈ ደብዳቤ መልስ በመጻፍ ለክፍሉ ገቢ አድርጎ ዝግጅቱን ቀጥለናል፡፡ ከዚህ በኋላ ባለው ጊዜ ክፍሉ በደብዳቤም ሆነ በአካልና ስልክ ሳያገኘን ዝግጅታችንን አጠናቀን በዕለቱ በተገጸው ሰዓት ወደ ቦታው ስንሄድ ያጋጠመን ሁኔታ -