Translate

Wednesday, November 5, 2014

መጪው ምርጫ… (በአብዱራህማን አህመዲን – የቀድሞ ፓርላማ አባል)

በዓለም ላይ የዴሞክራሲ ስርዓት የመሰረቱ ሀገሮች ሕዝቦች የፖለቲካ መሪዎችንና የመንግሥት ባለስልጣናትን በኃላፊነት ቦታ ላይ ለማስቀመጥ (ለመሾም) ሙሉ በሙሉ የተቀበሉትና በተግባር የሚያውሉት አሰራር ቢኖር ምርጫ ነው፡፡ ይሁን እንጂ፤ በምርጫና በዴሞክራሲ መካከል ምንጊዜም የማይነጠል ግንኙነት አለ ብሎ ማሰብ ተገቢ አይሆንም፡፡
ምክንያቱም፤ ተዘውታሪ ምርጫ (Periodic Election) በሚካሄድባው ሀገሮች የምርጫ ስርዓት ስላለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን ሆኗል ለማለት አይቻልምና ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፤ በሚያስተዳድሩት ሀገርና ሕዝብ ላይ አምባገነን፣ ዘረኛና ጨካኝ የአገዛዝ ስርዓት እንዳሰፈኑ ዓለም የሚያውቃቸው የፖለቲካ መሪዎችና ፓርቲዎች ጭምር ፀረ-ዴሞክራሲ ተግባራቸውንና የጎደፈ ስማቸውን ለመደበቅ ይረዳናል በሚል መንፈስ ጊዜ ጠብቀው የተጭበረበሩ ምርጫዎችን ሲያካሂዱ የሚታዩ እድሜ ጠገብ አምባገነኖች በዓለም ላይ ለዘመናት ሲታዩ ኖረዋል::
የአንዳንድ ሀገር ንጉሶች የሕዝብ ድጋፍ እንዳላቸው ለማሳየት ምርጫ ያካሂዳሉ፡፡ በአንዳንድ ሀገሮች የአንድ ፓርቲ ስርዓት የመሰረቱ መንግሥታትም እንዲሁ ምርጫ ያካሂዳሉ፡፡ በእነዚህ ሀገራት መራጩ ሕዝብ አንድ ብቸኛ ንጉስ አሊያም አንድ ብቸኛ ፓርቲ እንዲመርጥ በሚገደድበት ሁኔታ የሚከናወን ምርጫ ዋነኛ ዓላማው  በነፃና ፍትሐዊ ምርጫ የተደገፈ የመንግሥት ስርዓት የተቋቋመ መሆኑን ከማመላከት ያለፈ አይሆንም፡፡
እዚህ ላይ ለመሆኑ ምርጫ ምንድነው? ምርጫና ዴሞክራሲ ግንኙነት አላቸው? የሚሉትን ጥያቄዎች ማንሳት ለጋራ ግንዛቤ ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ ምርጫን በሚመለከት የሚሰጠው ትርጉም (Definition) በቁጥር በርካታ በመሆኑ አንድ ወጥ ብያኔ ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው፡፡ እናም፣ ብዙዎች ይስማሙበታል ተብሎ የሚታሰበውን መውሰድ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት፤ ምርጫ ማለት “ለተወሰነ ሥራና ኃላፊነት ለውድድር ከቀረቡ ግለሰቦች ወይም ፓርቲዎች መካከል እንደ አስፈላጊነቱ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሚሆኑትን አስቀድሞ በተዘጋጀ የመምረጫ ሕግና ሥርዓት መሰረት በመምረጥ ውሳኔ ማሳለፍ ነው” በአጭሩ “ምርጫ ሕዝብ መሪዎቹን መርጦ የሚሾምበት ውሳኔ ነው” ብሎ ማስቀመጥም ይቻላል፡፡ ከዚህ ትርጓሜ አኳያ ምርጫ አንዱ የሕዝቦች ልዕልናና የዴሞክራሲ መገለጫ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል እንጂ፤ በአንድ ሀገር ምርጫ ስለተደረገ የዴሞክራሲ ስርዓት እውን ሆኗል ማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
EMF

No comments:

Post a Comment