Translate

Sunday, January 28, 2018

ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ጆሮና አይኔ ወሎ ላይ ተተክሎ ሰንብቷል

መሳይ መኮንን
ከወልዲያው ጭፍጨፋ፡ ከቆቦዎች አይበገሬነት እስከመርሳዎች ጀግንነት፡ ክስተቶችን እዚያው አጠገባቸው እንዳለ ሆኜ ነበር ስከታተል የቆየሁት። ስሜቴ ከወዲህ ውዲያ ሲላጋ፡ ቅጭም ሲል፡ በሀዘን ሲመታ፡ ደግሞም በጀግንነታቸው ልቤ ሲሞቅ፡ ወዲያኑም በሚደርስባቸው የግፍ በትር ውስጤ ሲደማ፡ በሞታቸው ኩምትር ስልበወርቃማ መስዋዕትነታቸው ስጽናና፡ እንዲሁ ላይ ታች ስል ሰነበትኩ። አሁንም ከዚያው ነኝ። ከወልዲያ ምድር፡ ከቆቦዎች መንደር፡ ከሮቢት ሰፈር፡ ከሀራ ገበያ፡ ከጎቢዬዎች ሀገር፡ ከመርሳዎች መንደር፡፡ የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም የሚለው አባባል አይገባኝም። ወሎን ባላውቀውም ይናፍቀኛል።
Mesay Mekonnen, ESAT journalist
መሳይ መኮንን (የኢሳት ጋዜጠኛ)
ፖለቲካው ግሏል። ሙቀቱ ጨምሯል። ህወሀቶች መቀሌ ላይ የቀመሙትን መርዝ በእጅ አዙር ሊረጩት ተሰማርተዋል። የዘርዓይ አስገዶም ያልተጠና ዲስኩር የህወሀቶችን ቀጣይ አካሄድ እርቃኑን ያጋለጠው ሆኗል። አንጻራዊ የህዝብ ድምጽ በማሰማት ቀና ማለት የጀመሩትን የኦሮሞ ብሮድካስት ኔትወርክና የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅትን ወደ ቀድሞ አገልጋይነታቸውና በቀቀንነታቸው ለመመለስ በህወሀት አማካኝነት የተዘጋጀውና እነዘርዓይ የተላኩበት ዘመቻ ድባቅ ሲመታ ለመታዘብ ችለናል። አፋቸው ተሎጉሞ የከረሙት ወይም ከህወሀት አገልጋይነት መላቀቅ አቅቷቸው ህዝባቸውን ሲያሳዝኑ የምናውቃቸው እነንጉሱ ጥላሁን እንኳን አፍ አውጥተው፡ ወኔ አግኝተው፡ ድፍረት ተላብሰው ”በዘረኝነት ትዕቢት የተወጠረውን” ዘርዓይን እሳት እንዳየ ላስቲክ ኩምሽሽ ሲያደርጉት አይተናል።

Wednesday, January 24, 2018

አዲስ ድራኮኒያን ህግ! ( በቅርብ ቀን ይጠብቁ!)

በኤርሚያስ ለገሰ
Ermias Legesse, author and ESAT TV and Radio contributor
በቅርቡ የፀረ ሽብርተኝነት ህግ ተስተካካይ የሆነና ከሌሎች ጨቋኝ ህጐች (የፕሬስ ህግ፣ የፀረ ሽብርተኝነት ህግ) ጋር እርስ በራስ የሚመጋገብ አዋጅ ሊወጣ ያቆበቆበ ይመስላል። የአዋጁም ስያሜ ” የማህበራዊ ሚዲያ ህግ” ሊባል ይችላል። ይሄ ህግ ህውሓት የአርማጌዶ ፍልሚያ ጀምሬያለሁ በማለት በድርጅታዊ መግለጫው የገለፀውን ወደ ተግባር ለመቀየር የታሰበ ነው። እንደታዘብኩት ከሆነ ለዚህ አደገኛ ህግ ለመውጣት የሚያስችል ቅድመ ሁኔታዎች እየተሰሩ ነው። አንዳንድ ማሳያዎችን አንስተን ጉዳዩን እንመልከተው።

Tuesday, January 23, 2018

የእኛ ስሜት እና የቴዲ አፍሮ ቁስል

Image may contain: 1 person, standing
~አንድ እርምጃ ወደኋላ ሁለት እርምጃ ወደፊት!
(ጌታቸው ሺፈራው)
ቴዲ አፍሮ ባህርዳር ላይ "ጃ ያስተሰረያል!"ን ዝፈንልን ተብሎ ሳይዘፍን ከመድረክ ወረደ፣ ሕዝብም ቅር ተሰኘ አሉ። ይህን ስሰማ በሁለቱም ጫማ ውስጥ ገብቼ አየሁት። የኮንሰርት ተሳታፊ እና ዘፋኙን ሆኜ!
ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁስሉ እየጠዘጠዘው ነው። ቴዲ የብሶቱን እንዲዘፍንለት ይፈልጋል። ባህር ዳር ደም ያልደረቀባት ከተማ ነች፣ ቁስሉ ያልጠገገ፣ በየጊዜው እየደማ ያለ ሕዝብ ነው። ትናንት እንኳ ሕዝን የወልዲያን ሰቆቃ ሰምቶ ነው ወደ ኮንሰርቱ የገባው። ሕዝብ የፍቅር ሳይሆን የትግል ዜማ፣ የብሶት ዜማ ነበር መስማት የሚፈልገው።
በሌላ በኩል ደግሞ ቴዲ አፍሮ "ይህን ከዘፈንክ አይቻልም" እየተባለ ፍዳውን አይቷል። ገንዘብ ከስሯል። ዋናው ገንዘቡ አይደለም። አድናቂዎቹን ማግኘት አልቻለም። ሌላው ቀርቶ ስለ መተባበር፣ ስለ ሕዝብ ፍቅር በአካል ተገኝቶ መስበክ አልቻለም! ከ "ጃ" አንፃር ካላየነው በስተቀር አብዛኛው የቴዲ ዘፈን ፖለቲካ ነው። ሀገር የመሰረቱትን እንደሰይጣን የሚጠሉ ገዥዎች ባሉበት ሀገር "ጥቁር ሰው"ን ያህል ፖለቲካ ያለ አይመስለኝም። ቴዲ በቅርቡ ያወጣው አልበም የተወደደው "ጃ ያስተሰራልን"ስላካተተበት አይደለም። ዝም ብሎ ዘፈን ስለሆነም አይደለም። ፖለቲካም ስለሆነ ነው። ተወዳጁ ቴዎድሮስ ካሳሁን ስለዘፈነውም ጭምር ነው!
በመከራ ያለ ሕዝብ ስሜት ለማንም ሊያስቸግር ይችላል። የባሰው ሕዝብ በስልት፣ ቀስ እያልክ ከምትነግረው አፍርጠህለት ግንባርክን ብትባል "ወንድ" ይልሃል። እውነቱን ተናግሮ ከመሸበት ማደር የሚለውም ይህንኑ ነው። ይህ የሕዝብ ስሜት ከበደል ብዛት የመጣ ነው። የብሶት ነው!

Saturday, January 20, 2018

የህወሀት ጸሀይ እየጠለቀች ነው

Image may contain: 1 person
መሳይ መኮንን
ብዙ ምልክቶች በመታየት ላይ ናቸው። ተመልሶ የሚያንሰራራበት እድል ያለ አይመስልም። እየተንፏቀቀ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። እግሮቹ ተሰብሮ በደረቱ እየተሳበ ከቤተመንግስት የተወሰነ ጊዜ ሊቆይ ይችላል። ስጋው አልቆ በአጥንቱ ቆሞ ጥቂት ጊዜያት መቆየቱ የማይቀር ነው። በዘላቂነት ግን አልቆለታል ማለት ይቻላል። የህዝቡ ተቃውሞ ሳይቋረጥ ከቀጠለ፡ ከያቅጣጫው የበረታው ግፊት ጉልበቱን ጨምሮ ይበልጥ ከገፋ የሚንፏቀቀውን፡ እግሮቹ የተሰበረውን፡ በአጥንቱ የቀረውን ህወሀት ከታሰበው ጊዜ በጣም በቅርብ ዘላለማዊ ሞቱን የሚጨልጥ ስለመሆኑ አያጠራጥርም። እስቲ ምልክቶቹን አንድ በአንድ እንመልከታቸው፥-
የትግራይ ህዝብ
ህወሀት ከ2010 ዓም ዋዜማ ጀምሮ መቀሌ ከቷል። ላለፉት አምስት ወራት በስብሰባ፡ በኮንፈረንስ፡ በግምገማ፡ በህንፍሽፍሽ፡ በጉባዔ ተጠምዶ ከርሟል። አሁንም እንደሚኖር ይጠበቃል። ትግራይ የህወሀት የመጨረሻ ምሽግ ናት። ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ የኢትዮጵያ ልብ ማግኘት ያቃተው ህወሀት አክ እንትፍ፡ ተብሎ መተፋቱን አረጋግጧል። የኢትዮጵያን ህዝብ በፍቅርም፡ በጉልበትም መምራት እንደማይችል ተረድቶታል። ከእንግዲህ ወርቅ እንኳን ቢያነጥፍ የሚቀበለው እንደሌለ አውቆታል። ስለዚህ ወደ መጨረሻ ምሽጉ ፊቱን አዙሯል። ይህ ምሽግ የተወሰነ ዕድሜ እንደሚያዘልቀው ተማምኗል። በኋላ ኪሱ የሸጎጣትን ''የትግራይ ሪፑብሊክ'' ምስረታ ከተሳካለትም ይሞክራል። በኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት በበላይነት መቆየት ካልቻልኩ ያሉኝ አማራጮች ብሎ ከያዛቸው እርምጃዎቹ አንዱ ወደ ትግራይ ጠቅልሎ ገብቶ ምሽጉን ማጠናከር ነው።ለዚህም የትግራይን ህዝብ ልብ ሙሉ ለሙሉ ለማግኘት ቃል በመግባት ተግቶ እየሰራ ነው።

Friday, January 19, 2018

ልክ ያጣው የእነ ገብረ እግዚያብሔር እብሪት

ጌታቸው ሽፈራው
Ethiopian political prisoner Aschalew Desse.
አስቻለው ደሴ የፌደራል ፖሊስ አባል ነበር። አማራ በሰበብ በሚታሰርበትና በሚከሰስበት ግንቦት 7 አባል ነህ ተብሎ ታሰረ። የተለመደውና የሌለው የ”ሽብር” ክስ ተመስርቶበታል። የታሰረው ደግሞ የአማራ ወጣቶች ዘራቸውን እንዳይተኩ ከሚኮላሹበት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ነው። እንደሌሎቹ ወንድሞቹ አስቻለው ደሴንም ብልቱ ላይ ሁለት ሊትር ሀይላንድ ውሃ አንጠልጥለው ዘሩን እንዳይተካ አድርገውታል። ጆሮውንም ጎድተውታል። ለዚህ ሁሉ ቁስሉ ምንም አይነት የህክምና እርዳታ አላገኘም። በክሱና በማንነቱ ምክንያት ህክምና ተከልክሏል። ጥጋበኞች ላቆሰሉት፣ ለጎዱት አካልና መንፈሱ ምንም አይነት ህክምና አላገኘም።

የመንግስቱ ሃይለማርያም ልጅ ዶ/ር ትዕግስት መንግስቱ አወዛጋቢ ቪዲዮ ለቀቀች – “እንዴት ተደፈርን?”

(ዘ-ሐበሻ) የቀድሞው የኢትዮጵያ መሪ ኮ/ል መንግስቱ ሃይለማርያም ልጅ የሆነችው ዶ/ር ትዕግስት መንግስቱ በግብጽ እና በአባይ ፖለቲካ ዙሪያ አንድ ቪዲዮ ለቀቀች:: ቪዲዮውን የለቀቅችው በፌስቡክ ሲሆን የራሷን አስተያየት “እንዴት ተደፈርን?” ስትል ትጀምራለች:: ይመልከቱትና በአባይ ዙሪያ ያላትን አወዛጋቢ አቋም አስተያየት ይስጡበት::

Thursday, January 18, 2018

ከ23 በላይ ድርጅቶች የተሰባሰቡበት የኢትዮጵያ ማህበረሰባዊ ድርጅቶች ትብብር የውጭ ምንዛሬ “ሬሚታንስ” ተአቅቦ ጥሪን ደገፈ

ጉዳዩ፦ አለም አቀፍ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ግበረሀይል እያደረገ ያለውን የውጭ ምንዛሬ ተአቅቦ ዘመቻ ስለመደገፍ
A Call for Worldwide Remittance Embargo Against the Brutal TPLF Regime
የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን፣
ከዲሴምበር 29 ቀን 2017 ጀምሮ በአለም አቀፍ የኢትዮጵያዊያን የጋራ ግበረሀይል አስተባባሪነት የውጭ ምንዛሬ ተአቅቦ ዘመቻ እየተደረገ ይገኛል። የዘመቻው አላማ የገዳዩ እና ዘራፊው የህወሓት መንግስት በውጭ አገራት ከሚኖሩት ኢትዮጵያዊያን የሚያገኘው የውጭ ምንዛሬ እንዲቀንስ ማድረግ እና የአገዛዙን ኢኮኖሚያዊ አቅም ማዳከም መሆኑን ትብብራችን መረዳት ችሏል። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የወገናቸውን የነጻነት ትግል የማገዝ ሀላፊነት እና አቅም እንዳላቸውም ትብብራችን ያምናል። ግብረሀይሉ ያወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው እና ትብብራችንም እንደሚያምንበት፣ ኢትዮጵያዊያን ከታች የተዘረዘሩትን ጥሪዎች ተግባራዊ ለማድረግ ከተንቀሳቀሱ፣ በአገዛዙ ላይ ትርጉም ያለው ኢኮኖሚያዊ ጫና ማድረግ ይቻላል።

የበረከት ተመልሶ መምጣት ማረጋገጫ

በኤርሚያስ ለገሰ
Bereket-Simon
የዛሬው አዲስ ዘመን ርዕሰ አንቀፅ የበረከት ስምኦን ተመልሶ መምጣት የሚያረጋግጥ ነው። የአዲስ ዘመን ርዕሰ አንቀፅ የመንግስት አቋም የሚገለፅበት በመሆኑ የሚፃፈው በህውሃት/ኢህአዴግ የፓለቲካ መሪዎች ብቻ ነው። በተለይ በእንደዚህ አይነት የቀውጢ ወቅት አዲስ ዘመን ከስኳር መጠቅለያነት ወጥቶ የፓለቲካውን አቅጣጫ ማሳየት ስላለበት በፕሮፐጋንዳ ክፍሉ ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል። የሚፅፈው አሊያም በስልክ ዲክቴት የሚያደርገው ደግሞ በረከት ስምኦን ነው።

Wednesday, January 17, 2018

ከድንዛዜው መውጣት አለብን፣ የህወሀት አጀንዳ እንዲመራን አንፍቀድለት

መሳይ መኮንን
Merera Gudina is a professor and politician in Ethiopia.
Merera Gudina
ሰሞኑን የህወሀት አገዛዝ ከወዲህ ወዲያ እየዘለለ ነው። በፍትህ ስርዓቱ ላይ ጢባ ጢቤ እየተጫወተ ነው። ጠዋት የተናገረውን ከቀትር በኋላ ይሸረዋል። ምሽት ላይ የወሰነውን ንጋት ላይ ይሰርዘዋል። ይፈታሉ፡ አይፈቱም። ይቅርታ ነው። የለም ምህረት ነው። የፖለቲካ እስረኛ የሚባል የለም። ፖለቲከኞች ይፈታሉ። በሁለት ቀናት ውስጥ ይፈታሉ። በሁለት ወር ውስጥ ውሳኔ ያገኛል። ሪፖርተር ሌላ። ሬዲዮ ፋና ሌላ። ዋልታ ወዲህ- ኢቲቪ ወዲያ። ዥዋዥዌ።

Monday, January 15, 2018

የመቀሌው ስብሰባና የ’ፖለቲካ እስረኞች ፍቺ (መሳይ መኮንን)

Few of Ethiopian political prisoners in picture.
ይህን ጽሁፍ በማዘጋጅበት ሰዓት ጠቅላይ አቃቤ ህጉ መግለጫ እየሰጡ ነው። የእስረኞችን መፈታት በተመለከተ ትላንት መግለጫ እንደሚሰጡ ስንሰማ መቀሌ ወሰነች ብለን ነበር። ምክንያቱም የእስረኞች መፈታት ወሬ ከሃይለማርያም አፍ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በህወሀት መንደር የፈጠረው መንጫጫት የተባለው እንደማይሆን ከምልክትም በላይ ነበርና ነው። ከጠቅላይ አቃቤ ህጉ የዛሬ መግለጫ ለመረዳት እንደተቻለው ግን የሚፈታ የፖለቲካ እስረኛ የለም።

ታዳሚን እንባ ያራጨው የችሎት ውሎ

Image result for torture
(በጌታቸው ሺፈራው)
ዛሬ በጠዋት ሰብሰብ ብለን የገባነው ወደ 4ኛ ወንጀል ችሎት ነበር። ከ4ኛ ወንጀልችሎት ስወጣ 19ኛ ወንጀል ችሎት ታዳሚውን ያስለቀሰ፣ ዳኞቹን ሳይቀር ያሳዘነ ትዕይን እንደነበር ሰማሁ። 19ኛ ወንጀል ችሎት የነበረ አንድ ጓደኛዬን ማስታወሻውን እንዳየው ጠየኩት። የተጀመሩ ዐረፍተ ነገሮች፣ ያልተቋጩ ሀረጎችን አነበብኩ። በእርግጥ እንባ በሚያራጭ ትዕይንት ውስጥ መፃፍ ከባድ ነው። እኔንም ብዙ ቀን አጋጥሞኛል።የጓደኛዬ ማስታወሻ ላይ የሰፈሩ የተቆራረጡትን ዐረፍተ ነገሮች መዝግቤ፣ ጓደኛዬ በችሎት ያየውን እንዲያብራራልኝ ጠየኩት። በአማራ ክልል በነበረው ህዝባዊ ንቅናቄ ሰበብ የታሰሩትና በእነ ታደሰ መሸሻ አሰጌ ክስ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል 3ኛ ተከሳሽ የሆነው ዮናስ ጋሻው ደመቀ በሌሎች የአማራ ወጣቶች የሚፈፀመው ጭካኔ ተፈፅሞበታል። አስቻለው ደሴና ሌሎች አማራ ወጣቶች እንዳደረጉት ሱሪውን በችሎት አውልቆ "ህዝብ ይፍረደኝ" ብሏል። ሃይላንድ ያንጠለጠሉበትን ብልቱን አሳይቷል።በዚህ ወቅት ታዳሚው አልቅሷል። ጓደኛዬ ይህን ሰቆቃ እያየ በደንብ መፃፍ አልቻለም። ዳኞች እንኳ አንገት ደፍተዋል። በጠዋቱ ችሎት በተከሳሹ ሰቆቃ ያለቀሱትን ታዳሚዎችም አነጋግሬያቸው ነበር። ከሰዓትም ሀዘኑ ሳይለቃቸው ስለ ሰቆቃው ነግረውኛል።

Saturday, January 13, 2018

የተበላሸው ብድር 3.6 ቢሊየን ብር ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 4/2010)

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሰፋፊ እርሻዎች ካበደረው 5.6 ቢሊየን ብር ውስጥ 3.6 ቢሊየን ብር የተበላሸ ብድር ሆኗል ሲል አረጋገጠ።
ልማት ባንኩ ለሰፋፊ እርሻዎች መቀበል የጀመረውን የብድር ጥያቄም ማቆሙን አስታውቋል።
በአብዛኛው የትግራይ ተወላጆች ለተሰማሩበት የጋምቤላ የእርሻ ልማት የተሰጠው ብድር ከ63 በመቶ በላይ የተበላሸ ተብሎ የተሰረዘው ባለሀብቶቹ ተጠያቂ እንዳይሆኑ በሚል መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት ይገልጻሉ።
የኦክላንድ የምርምር ተቋም በጋምቤላ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከ70በመቶ በላይ የሚሆኑት የትግራይ ተወላጆች ናቸው ይላል።
ራሳቸው ባለሃብቶቹ በተወካያቸው አማካኝነት እንደተናገሩትም በአጋጣሚ የትግራይ ተወላጆች እንበዛለን ነው።

Monday, January 8, 2018

የኤርሚያስ ለገሠ ማስታወሻ ለዶ/ር አቢይ አህመድ

ሰላም ላንተ ይሁን።
ይህን ማስታወሻ የምፅፍልህ የምከትበው ነገር ላታስበው ትችላለህ ከሚል እምነት ተነስቼ አይደለም። በዙሪያህ ያሉ የድርጅቱ ሃላፊዎች እና አማካሪዎችም ያጡታል ከሚል ጥራዝ ነጠቅነት የመነጨ አይደለም። ነገር ግን በፓርቲው የፕሮፐጋንዳ እና ድርጅት እቅድ የማውጣት እና አፈፃፀሙን የመከታተል ስራዎች ላይ ቆይታ አድርጐ እንደነበረ ሰው ቀለል ያሉ ምክረ ሐሳቦችን ለመሰንዘር ነው። እነዚህ አስተያየቶች ቀላልና ህውሃት ቀርጾ ለሩብ ክፍለ ዘመን እየተገበረ ካለው ” ህጋዊ ማእቀፍ” ሳትወጡ ልትፈፅሙት የምትችሉት ናቸው።
ካልተቀየረ በስተቀር የድርጅትና ፕሮፐጋንዳ እቅድ ስታወጡ የሁኔታዎች ትንተና ( SWOT analysis) እንደምታደርጉ አውቃለሁ። ከእነዚህ የሁኔታዎች ትንተና ተነስታችሁ በአመቱ የምትፈፅሟቸው ቁልፍ እና አበይት ተግባራት እንደምትዘረዝሩም እገምታለው። በሌላ በኩል ይህ ከባድ ሃላፊነት በአንተ ጫንቃ ላይ እንደወደቀ ደግሞ ከያዝከው ስልጣን በመነሳት መገመት ይቻላል። መቼም እንደ ሰገሌው ዘመን ህውሓት በትግርኛ እቅድ አውጥቶ በአማርኛ እና ኦሮምኛ ተርጉማችሁ ወደ ስራ አውሉት የሚለው ዘመን ታሪክ የሆነ ይመስለኛል። እርግጥ እነ አባይ ፀሀዬና በረከት ስምኦን ይሄን ሊያደርጉት አይችሉም ብሎ መገመት ግን የዋህነት ነው። ይሁን እንጂ የበላይ አለቃህ የሆነው ለማ መገርሳ ” ቀዳድጄ ቅርጫት ውስጥ ከተትኩት!” እንዳለው አንተም የአለቃህን አርአያነት እንደምትከተል አልጠራጠርም። የፈጠነ አስተያየት ቢሆንም በአጭር ጊዜ ያሳየኸው የአመራር ጥበብ ለዚህ አገላለጤ መነሻ ነው።

Sunday, January 7, 2018

የረቡዕ ዕለት ቃል እስከአሁን አልተከበረም። የተፈታ እስረኛ አላየንም!!

Mesay Mekonnen
Image may contain: 1 person
የረቡዕ ዕለት ቃል እስከአሁን አልተከበረም። የተፈታ እስረኛ አላየንም። ብዙውዎች ገናን ለማድመቅ በዚያውም ፖለቲካዊ ነጥብ ለማስቆጠር በገና ዋዜማ የሚፈቷቸው ይኖራሉ ብለው ተስፋ አድርገው ነበር። በዚህም ወደቃሊቲና ቅሊንጦ የሄዱም እንደነበሩ ሰምተናል። ከሸዋሮቢት፡ ዝዋይና ሌሎች ቦታዎች እስረኞች በአውቶብሶች ተጭነው ወደአዲስ አበባ እየገሰገሱ ነው፡ በሚሌኒየም አዳራሽ ልዩ የአቀባበል ፕሮግራም ተዘጋጅቷል.....ብዙ ብዙ ተብሎም ነበር። ግን ወፍ የለም።
እንደሰማነው ህወሀቶች አልተስማሙም። የመቀሌውን የ35 ቀናት ዝግ ስብሰባ የስብሃት ቡድን አሽንፎ ወጥቷል የሚለው ድምዳሜ ወደ ኋላ የተቀለበሰ ይመስላል። አዜብ መስፍን በኢህአዴግ የ18ቀናቱ ጉባዔ መሀል ድንገት በር በርገዳ ገብታ ''መለስ ሞተ ብላችሁ ተጫወታችሁብኝ። የእጃችሁን ታገኛላችሁ'' ዓይነት ማስፈራሪያ አዥጎድጉዳ እንደወጣች ይወራል። ከሷ ጀርባ የተሰለፈውና መከላከያውን በበላይነት የያዘው ሳሞራ ድምጹ ጠፍቶ ቀና ማለት መጀመሩንም የሚያሳዩ ምልክቶች አሉ። እነሃይለማርያም ረቡዕ ዕለት ''የህወሀት/የትግራይ የበላይነት የለም'' የሚል መግለጫ ሲሰጡ አዜብ በዚያው ዕለት ለመሶበ ሲሚንቶ ፋብሪካ የጣሪያ ክዳን ፋብሪካ የ2ቢሊየን ብር ስምምነት ከውጭ ኩባንያ ጋር ተፈራርማለች። ''አለሁ። እጅ አልሰጠሁም'' መልዕክት ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል። የአዜብ ዳግም ብቅ ማለት የህወሀት ትርምስ አልበረደለትም- ገና ይናጣል- የሚል ግምትም እንዲሰጠው አድርጓል።

Friday, January 5, 2018

አገራችንን ከተደቀነባት አደጋ መታደግ የሚቻለው የሥርዓት ለውጥ በማምጣት ብቻ ነው። የአርበኞች ግንቦት 7 ርዕስ አንቀጽ !!



የአገራችንን ሉአላዊነት እና የህዝባችንን አንድነት ድርና ማግ ሆኖ አቆራኝቶ ለዘመናት ያቆዩትን እሴቶች ሙሉ በሙሉ በማጥፋት ህወሃት እንደ ድርጅት መሪዎቹም አንደ ቡድን ልዩ ጥቅም እናገኛለን በሚል የፖለቲካ ስሌት ላለፉት 27 አመታት ረጅም ርቀት ተጉዘዋል። በዚህም የተነሳ አብዛኞቹ አመራሮች እና ለአመራሩ ቀረቤታ ያላቸው ካድሬዎች እስከነ ዘመዶቻቸው የአገሪቱን ፖለቲካ ሥልጣን ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚውንም በበላይነት ለመቆጣጠር ዕድል አግኝተዋል። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያቤት ውስጥ የአፍሪካ ጉዳይ ረዳት ሚንስትር እና በተለያዩ አገሮች የአገራቸው አምባሳደር ሆኖ ለረጅም ጊዜ ሲያገለግሉ የኖሩት ሚስተር ሄርማን ኮሄን ሰሞኑን ለሚዲያ በሰጡት ምስክርነት ይህንን ሃቅ በይፋ በማጋለጥ የህወሃት የበላይነት የፈጠረው ችግር የበደሉ ገፈት ቀማሽ ከሆነው ህዝችባን አልፎ በምዕራባውያን ወዳጆቹ ዘንድም እንደሚታወቅ አረጋግጥዋል።

Tuesday, January 2, 2018

ኢህአዴግና እነለማ ከ“ምን ይዤ ልመለስ?” እስከ “መግለጫ” ማጽደቅ!


ህወሓት የሚዘውረው ኢህአዴግ ከሁለት ሳምንታት በላይ ስብሰባ አድርጎ “መግለጫ” ያለውን “ቀጭን ትዕዛዝ” በማውጣት ተጠናቋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በለውጥ አራማጅነት ሲጠቀሱ የነበሩት እነለማ መገርሳ “መግለጫውን” አብረው አጽድቀው ወጥተዋል። “የጨለንቆን ፍጅት የፈጸመው ማነው?” የሚለውም ደፋር አጀንዳ አብሮ የሞተ ጉዳይ ሆኗል። “ምን ይዤ (ወደ ሕዝቤ) ልመለስ?” በማለት ወደስብሰባው የገቡት ኦህዴድና ብአዴን “የተቀናጁ ተጨማሪ እርምጃዎች” እወስዳለሁ (መግደሌን እቀጥላለሁ) ለሚለው የህወሓት “መግለጫ” ይሁንታቸውን ሰጥተው ወጥተዋል።

ሀገርና ወገን ለማዳን አዉሬዉን ማስራብ

ሺፈራዉ አበበ
Remittance Embargo against the repressive Ethiopian government.
ላለፉት ሁለት አመታት የትዉልድ አገራችን በጣም አሳሳቢ በሆነ የፖለቲካና የሰላም ቀዉስ ዉስጥ ትገኛለች። በሺህዎች ሞተዉ፣ ባስር ሺህዎች ታስረዉ፣ በመቶ ሺህዎች ከቤት ከቀያቸዉ ተፈናቅለዉ ያሉበት ወቅት ላይ ነን። መንስኤዉ ግልጽና ቀጥተኛ ነዉ፤ ባንድ በኩል፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ስድስት ፐርሰንት ብቻ የሚወክሉ፣ ግን ያገሪቱን የመከላከያ፣ የደህንነት፣ የመንግስት ተቋማትና፣ ቁልፍ የኢኮኖሚ አዉታሮች ለ27 ዓመታት ተቆጣጥረዉ የዘለቁ፣ ለስልጣን ጥማቸዉና ለንዋይ ፍቅራቸዉ ዳርቻ የሌለዉ፣ እንደአገር መሪ ሳይሆን እንደመንደር ወሮበላ የሚያስቡና የሚሰሩ፣ ጸረ-ሀገር ህወሃት-ወያኔዎች አሉ።