Translate

Wednesday, March 30, 2016

ህወሃት ራሱን በራሱ ሸንጎ አስገምግሞ የእጁን ደም ሊያጸዳ ነው

የኮሚሽኑ ሪፖርት በኢህአዴግ ጽ/ቤት መሰራቱ ተጠቆመ

ehrc
ህወሃት በኦሮሚያና በአማራ ክልል በንጹሃን ዜጎች ላይ የፈጸመውን ወንጀልና ርህራሄ አልባ ግፍ ራሱ አጣርቶ፣ ራሱ አጠናክሮ፣ ራሱ በፈጠረው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አማካይነት አቅርቦ፣ በራሱ ሸንጎ በማጸደቅ እጁን ከደም ሊያጸዳ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ለሪፖርቱ ማዳመቂያ የምስል ቪዲዮዎች መዘጋጀታቸው ታወቀ

እነዚህን ከስር የምትመለከቷቸውን ፎቶዎች ወዳጆቼ ከባህር ዳር ዛሬ ሌሊት ላኩልኝ።

ኣማራ ሲሞት ሌላ ኣማራ ሲፈራ ( ሄኖክ የሺጥላ )
እነዚህን ከስር የምትመለከቷቸውን ፎቶዎች ወዳጆቼ ከባህር ዳር ዛሬ ሌሊት ላኩልኝ።



ስለ ፎቶዎቹ ምንነት ባጭሩ ላስቀምጥ
ተደብዳቢው -- አማራ!
ደብዳቢው--- ወያኔ ትግሬ!
የድብደባው ምክንያት--- አማራ መሆን!
ተጠያቂ ---የለም!!!
ይህንን ለማስቆም የሚቆም አማራ--- የለም!!!
ይህንን ኣይቶ ቁጭት ውስጥ ሊገባ የሚችል አማራ--- የለም!!!
ድብደባው ይቀጥላል ወይ?---- ኣዋ!
ይህንን ፎቶ ለብዙ ደቂቃ ተመለከትኩት ። ኣይኖቼ እንባ ተሞልተው ጥርሴን እያፋጨሁ ደግሜ ደጋግሜ ኣየሁት። ወዳጄ በውስጥ መስመር የፃፈልኝን ኣሳዛኝ ታሪክም ኣነበብኩ ። ማልቀስ ኣልችልም ፥ ኣሁንም ያለቀስኩ ኣይመስለኝም ፥ ግን ፊቴ ላይ እንባ የሚመስል ነገር እንደነበር ኣስታውሳለሁ ። መናደድም ኣልፈልግም ፥ ምክንያቱም ከመናደድ የሚመጣው ሽንፈት እንደሆነም ኣውቃለሁ ። ግን ማሰብ እፈልጋለሁ ፥ ድጋሚ ወደ ራሴ ተመልሼ እውነታውን በጥሞና ማየት እና መረዳት እፈልጋለሁ ። 

ኢትዮጵያ ወዴት ነው የምትሄደው እና የማትሄደው? (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
(እ.ኤ.አ መጋቢት 27/2016 በማሪዮት ጆርጅታዎን  ከተማ  (ዋሺንንግቶን ድሲ ) ቪዥን ኢትዮጵያ በተባለው ድርጅት አስተባባሪነት “ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ፡ ሽግግር፣ ዴሞክራሲ እና ብሄራዊ አንድነት ጉባኤ” በሚል ርዕስ በእንግሊዝኛው ቅጅ ከቀረበው ንግግር የተወሰደ ነው፡፡)
Quo Vadis Ethiopia: Where Are You (not) Going?
“ስለወዲፊቷ ኢትዮጵያ፡ ሽግግር፣ ዴሞክራሲ እና ብሄራዊ አንድነት ጉባኤ” በሚል ርዕስ ስለተዘጋጀው ጉባኤ ቪዥን ኢትዮጵያን እና የጉባኤውን አስተባባሪዎች በሙሉ ለማመስገን እፈልጋለሁ፡፡
ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው ከወራት በፊት በዚህ ጉባኤ ላይ እንድገኝ እና እንድሳተፍ ጥሪ ባቀረበልኝ ጊዜ ኢትዮጵያን ገጥመዋት ባሉት መሰረተ ሰፊ የተሳትፎ መድረክ፣ ውይይት እና ክርክር ጉዳዮች ሀሳብ እጅግ በጣም ነበር የተደሰትኩት፡፡ የቪዥን ኢትዮጵያን አርዓያ በመከተል ሌሎችም እንደዘሁ በርካታ የውይይት መድረኮችን ያዘጋጃሉ የሚል ተስፋ አለኝ፡፡

አንድ ሰሞን ከሙኒኮች ጋር (በኤፍሬም ማዴቦ)

በኤፍሬም ማዴቦ
አባባ . . .  አባባ . . . . ስማ አባባ ረሳህ እንዴ አለኝ ያ ባለፈዉ ነኃሴ ወር ስንለያይ ያስለቀሰኝ ልጄ።  ምኑን አልኩት።  ቅድም ምሳ ላይ የነገርኩህን . . . እንዴ!  እሱንማ እንዴት እረሳለሁ። Please don’t አባባ! …… I will not! ሲረጋጋና ደስ ሲለዉ ታየኝና ልቤን ደስ አለው። ልጄ ኮሌጅ የሚገባበት ቀን እኔ ደግሞ ከትግል ጓደኞቼ ጋር የምንገናኝበት ቀን ናፍቆናል። አባባ Good luck አለኝ። እኔም ይቅናህ አልኩት። Good luck እና ይቅናህ የተባባልነው እኔ እሱ የሚመኘዉ ኮሌጅ እንዲገባ እሱ ደግሞ እኔ በድል ኢትዮጵያ እንድገባ ነበር። ሁለታችንም ይቅናን . . . አሜን!!!
አዉሮፕላን ዉስጥ ገብቼ ከተረጋጋሁ በኋላ ኢር ፎኑን ጆሮዬ ውስጥ ሰክቼ አይፎኔ ላይ “Play” የሚለዉን ስጫነዉ ጥላሁን ገሰሰ “አራዊቱ ሁሉ መጥቶ ቢከበኝ” እያለ ጀመረኝ። የምወደው ዘፈን ነበርና ደጋገምኩት። ጥላሁንኮ ድምጻዊ ብቻ አይደለም ነቢይም ነዉ፤ የዛሬ ስንትና ስንት አመት በአራዊቶች እንደምንከበብ ተንብዮ ነበር። የሚቀጥለው ዘፈን ገና ሲጀምር ምን መሆኑ ታወቀኝና. . . . . ኧረ በፍጹም. . . እንዴት ተደርጎ አልኩና አይፎኔን ዘግቼዉ ኪሴ ዉስጥ ከተትኩት። “መለያየት ሞት ነዉ” የሚለዉን የጥላሁን ገሰሰ ሙዚቃ ብወደዉም የጠነከረዉ ሆዴ እንዲባባ በፍጹም አልፈለኩም። አይፓዴን አወጣሁና የአስናቀች ወርቁን ሰዉነት እየሰረሰር ገብቶ አንጀት የሚያርስ ክራር መኮምኮም ጀመርኩ። አስናቀች ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ ቦታ ወሰደችኝ፤ ደግነቱ ዬትም ትዉሰደኝ ዬት መልሳ መላልሳ እዚያዉ አዉሮፕላኑ ውስጥ ታመጣኝ ነበር . . .  አለዚያማ!

ፈርዖናዊው የወያኔ አገዛዝ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ሲደገም ምን ይመስላል?

ከወልቃይት ጠገዴ ብጌምድር፤ ጎንደር  ኢትዮጵያ
በ24 አመታት ውስጥ በተለያዩ የኢትዮጵያ አከባቢ ጥቂት የሚባሉ መልካም ለውጦች ቢኖሩም እንኳ ጀግናው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ አይደለም የመልካሙን ለውጥ ሊያጣጥም እንዲያውም በተቀነባበረ ሁኔታ የዛሬ 24 አመት ከነበረበት የህልውናና  ኑሮ ብዙ እጥፍ አሽቆልቁሎ ተምዘግዝጎ ወርዶበታል፤ ወያኔ አሰቃይቶታል፤ ህይወቱና አኗኗሩ አመሰቃቅሎበታል፤ ለብዙ መከራና ስቃይ ሞትና እንግልት መታሰርና ደብዛ መጥፋት መሰደድና መሸማቀቅ ዳርጎታል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከ1972 ጀምሮ የወያኔ መርዝ የተርከፈከፈበት ህዝብ ነው። አሳዛኙ ነገር ወያኔ የፈጠረው ችግር በሁሉም የኢትዮጵያ መርዙን ከመትፋቱ ጋር ተያይዞ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወገኑ የየራሱን ህመም ሲያዳምጥ ስለኖረ ከህመም ሁሉ ህመም፣ ከእልቂት ሁሉ እልቂት ሲፈጸምበት፣ በእስራኤላውያን ላይ በኦሽዊትስ ካምፕ በናዚዎች የተቀነባበረው የዘር ማጥፋት በ21ኛው መ.ክ.ዘ በወያኔዎቹ በግልጽና በድብቅ ሲደገም የሚዲያ ሽፋን ስለማይደርሰው ኢትዮጵያዉያን ወገኖቹ ሊያውቁለትና ሃይ ሊሉት አልቻሉም መከራዉን ከ1972 አ/ም ጀምሮ ወገኖቹ ሳይደርሱለት ብቻውን ሲጎነጭ ኖሯል።
እዚህ ላይ ለማሳሰብ እምፈልገው ዋና ነጥብ  በአማራነታችን እየደረሰብን ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ህወሃት በመልካም አስተዳደር ስም ለማስተባበል መሞከር በፍጹም አይቻልም፤   የመልካም አስተዳደር ችግርማ አሜሪካም ውስጥ ቢሆን ይኖር ይሆናል። እኛ አንደላቃችሁ አኑሩን አይደለም እያልን ያለነው። ዋናው ጥያቄያችን የወልቃይት ጠገዴ ህዝብና መሬት አማራ ስለሆነ ወደ እናት አገራችን ወደ ጎንደር ወደ አማራነታችን መልሱን የሚል ነው። ሰላምን ፈልገው ከመለሱን እጅግ ደስ ይለናል ካልሆነ ደግሞ የእነርሱ ፈቃድና ምስክርነት ሳያስፈልገን በራሳችን ራሳችንን አማራነታችንን አስረግጠን እንመልሳለን።በቃ ይሔው ነው!!! ይህ በትግራይ ተስፋፊና ነጻ አውጭ ቡድን፣ በትግራይ ፖሊስ፣ በትግራይ ልዩ ሃይል፣ በአጋዚ ወታደር፣ በትግራይ አስተዳደር አመራሮችና ካድሬዎች ማዳፈን የማይቻል የሚፋጅ ረመጥ ጥያቄ ነው።

Tuesday, March 22, 2016

ኃይለማርያም ቋፍ ላይ የደረሱ ይመስላሉ!

“…እኔ ምን አባቴ ላድርግ…” አሉ

hailemariam


አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን የሚሰጡት አስተያየትና ንግግር ህወሃት/ኢህአዴግ ያፈጠጠበትን ችግር ብቻ ሳይሆን እርሳቸውም በቋፍ ላይ የደረሱ መሆናቸውን ያመላከተ እየሆነ ሄዷል፡፡ ወደ ሥልጣን ሲመጡ በሙስና ላይ ዘመቻ እንደሚያደርጉ በተደጋጋሚ ይናገሩ የነበሩት ኃይለማርያም እስካሁን የሚታይ ለውጥ ሳያመጡ ቀርተዋል፡፡ በቅርቡ ከምሁራን ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይም “የተለያየ አመለካከትን የማይቀበል ሥርዓት የጊዜ ጉዳይ እንጂ መውደቁ አይቀርም” ማለታቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ችግሩን በቀጥታ ከኢህአዴግ ጋር እያያዙ በግልጽ መናገራቸው በሕይወታቸው ላይ አደጋ እስከሚያመጣ የደረሰ መሆኑ ለጎልጉል የደረሱ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በመሆኑም የግል ጠባቂዎቻቸውና አጃቢዎቻቸው ላይ የተደረጉ ለውጦችን ከዚህም ጋር የሚያያይዙ ወገኖች ኃይለማርያም በእርግጥም በችግር ውስጥ እንዳሉ ጠቋሚ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ የዚያኑ ያህልም ኃይለማርያም የናሙና ወይም ተወካይ መሪ ስለሆኑና መዘውሩ በእጃቸው ስለሌለ በእርግጥም “እኔ ምናባቴ ላድርግ” ማለታቸው ይህንኑ የሚያሳይ ነው ይላሉ፡፡

ሰሜን ጎንደር ውጥረቱ ከሯል:: ሕወሓት ራሱ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ ውጤት ዲቃላውን ብኣዴንን እየወነጀለ ነው::

ሕወሓት ራሱ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ ውጤት ዲቃላውን ብኣዴንን እየወነጀለ ነው::
ሰሜን ጎንደር ውጥረቱ ከሯል::12243233_1699617866976076_4679020848657870642_n
12243233_1699617866976076_4679020848657870642_nሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ብሎ ራሱን የሚጠራው እና ታላቋን ትግራይ በመስፋፋት ካልመሰረትኩ ነጻ አውጪ የሚለውን ስሜን አልቀይርም በማለት በአማራ እና በአፋር ክልሎች የመስፋፋት እቅዱን ለመተግበር ሲሮጥ ከፍተኛ የሆነ እንቅፋት ከአማራው ሕዝብ ስለተጋረደበት ራሱ የፈጠረውን ዲቃላውን ኢሕዴን/ብኣዴንን መወንጀል መጀመሩ ከሕወሓት የገደል ማሚቱዎች የተገኙ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው::ሕወሓት ፊቱን ወደ ተላላኪዎቹ አዙሩ በምትካቸው ከሕወሓት ጉያ የተመለመሉ አማርኛ ተናጋሪ ሕወሓቶችን ለመተካት እየሮጠ ይገኛል::በሰሜን ጎንደር ተፈጥሮ የሚገኘው ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ አመጽ ወደ ግጭት የተቀየር ሲሆን ከጎንደር ከተማ ጀምሮ እስከ ዳንሻ ድረስ ሕዝቡ አስፈላጊውን የሕይወት መስዋትነት ለመክፈል ጥርሱን ነክሶ መሰሳቱ ታይቷል::

የማያልቀው ወያኔያዊ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ስቃይ

ይህ ጽሑፍ በመጀመሪያ በገጠሪቱ የጠገዴ ኣካባቢ ተወላጅ በሆኑ የስኳር በሽተኛ የነበረውን ልጃቸው በዳንሻ ኣካባቢ በሚገኘው በዲቪዥን ሆስፒታል በየሁለት ወሩ ክትትል እያስደረጉ ሲያሳክሙ የነበረውን፣ በመጨረሻም ከ3 አመት በፊት ሆስፒታሉ ውስጥ በሞተባቸውና እንዲሁም ባለቤታቸውን የዛሬ 5 ኣመት እዛው ሆስፒታል ውስጥ ባጡ ኣባት ለልጃቸው ናማ ጻፍልኝ ብለው በልጃቸው ጸሓፊነት በአባት ተራኪነት ለልጃቸው “በል እንግዲህ ይህ ለኣለም አሰማልኝ”  ብለው በነገሩት መሰረት በልጃቸው ዘመድ በኩል ደርሶን የተዘጋጀ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የሚደርሰውን ግፍ በጥቂቱም ቢሆን የሚያሳይ ነው። ለሁለቱም ልጃቸውና ሚስታቸው ወደ ጎንደር ሪፈር ጻፉልኝ ብለው ሃኪሞቹን እየለመኑዋቸው ሳለ ደህና ናቸው እየተባሉ እንደሞቱባቸው ይገልጻሉ።  እኝህ ኣባት ይህ “አልበቃ ብሏቸው ደግሞ…”

በደቡብ ኦሞ ዞን በኢንቨስትመንትና በስኳር ልማት ፕሮጄክት ስም የሚፈጸመው ሙስናና የሃብት ዘረፋ መረን የለቀቀ ነው

በልሁ ማንከልክሎት (ክፍል ሁለት)
  1. በኢንቨስትመንት ስም በሚደረገው የመሬት ቅርምት የወ/ሮ አዜብ መስፍን እጅ እንዳለበት ተገለጸ፤
  2. በመሬት ቅርምቱ አንድ መሬት/ቦታ ለተለያዩ ‹የሃሰት ኢንቨስተሮች › ተደጋግሞ እየተሰጠ ነው፤
  3. ህወኃቶች የዞኑን መሬት በመቀራመት ብቻ የሚዘርፉት የአገር ሃብት ከ930 ሚሊዮን ብር በላይ ይደርሳል፤
  4. በስኳር ልማቱ ፕሮጄክት በተለያዩ የሥልጣን ቦታዎች የህወኃት አባላት ተሰግስገዋል፤
  5. በስኳር ልማቱ ፕሮጄክት የሃሰት ሪፖርት እንዲያቀርቡ የተገደዱ ሠራተኞች እየለቀቁና እየተባረሩ ነው፤
  6. ደቡብ ኦሞ ዞን እኩይ ተልዕኮ ባለው ሰፈራ ስም የግጭት ቀጠና ሥጋት ተጋርጦባታል፡፡
This is 2016 Ethiopia where the government chains and forcefully removes indigenous peoplesባለፈው ሣምንት በደቡብ ኦሞ ዞን የህወኃት አባላትና ደጋፊዎች በኢንቨስትመንት ሥም የሚፈጸመውን የመሬት ቅርምት በሚመለከት በዞኑ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች  ባለሙያዎች በተደረገው ጥናት ላይ የተመለከተውን መረጃ ትክክለኛነት ያረጋገጡ ወገኖች ከ2006  በኋላ የተፈጸመውና የተገኘው መረጃ ደግሞ በእጅጉ የሚያስገርም ዓይን ያወጣ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህ ተጨማሪ መረጃ መሰረት 5 490 ሄክታር መሬት ‹ባለቤት› የኦሞ ሸለቆ አግሮ ኢንዱስትሪ የበላይ ጠባቂ ወ/ሮ አዜብ መሥፍን መሆናቸው፣ እንዲሁም ሳትኮን 16 500 ሄክታር መሬት ከተረከበና በመሬቱ ሥም ብድር ከወሰደ በኋላ መሬቱ ላይ አንዳችም ሥራ ሳይሰራ በመተው መሬቱ ለሌሎች ሰዎች መከፋፈሉን ፣…. የተገኙት ተጨማሪ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች የወ/ሮ አዜብ መስፍን እጅ እስከ ደቡብ ኦሞ መድረሱና የ፣ሳትኮን› ድርጊት በእጅጉ እንዳስገረማቸውና ህወኃት በአባላቱና ደጋፊዎቹ በአገሪቱ ሃብት ላይ የሚፈጽመውን ዘረፋ በግልጽ የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ  በመሆኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ትኩረት ሰጥተው እንዲከታተሉ ያስፈልጋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

Monday, March 21, 2016

ትግራይና ወልቃይትን የሚያገናኙ ጎዳናዎች መዘጋታቸው ተነገረ

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
Map of Dansheha, ethiopiaትግራይና ወልቃይትን የሚያገናኙ ጎዳናዎች መዘጋታቸው ተነገረ፤ ፌደራል ፖሊስና የትግራይ ልዩ ኃይል የወልቃይትን ምድር ወሮታል፡፡
የወልቃይት ህዝብ ያነሳውን የአማራ ማንነት ጥያቄ ለመቀልበስ ህወሓት አጠናክሮ የጀመረውን በህብረተሰቡ ዘንድ ተቅባይነት ያላቸውን ግለሰቦች አፍኖ ድብዛቸውን የማጥፋት ተግባር በመቃወም የወልቃይት ህዝብ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል፡፡ በመሆኑም ዋና፣ ዋና መንገዶችን በጠብመንጃ አጥሮ በመዝጋት ተከዜን ተሻግሮ ከትግራይ ወደ ወልቃይት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በመግታት ላይ ነው፡፡
የወልቃይት ታጣቂ ኃይሎች ከወለቃይትና ትግራይ ወሰን ላይ በመመሸግ በእግር ወደ ወልቃይት የሚጓዙ ሰዎችን መታወቂያ መጠየቅ ጀምረዋል፡፡

ሰበር ዜና — ወደ ኤርትራ ለመዝለቅ የሞከሩ የህወሃት ወታደራዊ ደህንነት ሰላዮች ተረሸኑ

በልኡል አለም
በኤርትራ እና በዙሪያዋ ለስለላ ስራ እንዲሁም ለቅኝት የዉጊያ ስምሪት እንዲጠቅሙ ተብለዉ የተሰማሩ የህወሃት ወታደራዊ መረጃ አባላቶች እየታደኑ መታፈናቸዉን የሚያረጋግጡ መረጃዎች አፈትልከዉ ወጥተዋል።Patriotic Ginbot7 Conference
በተልይም ሞላ አስገዶም ከኤርትራ ወደ ህዉሃት ከፈረጠጠ ወዲህ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ነጻነት ሐይሎች የደህንነት ክትትል ምክንያት በህወሃት መረጃ ሰንሰለት ስር የነበሩ ሰላዮች በሙሉ መረሸናቸዉን የወያኔ ወታደራዊ ደህንነት በማረጋገጥ ለመከላከያ ሚኒስቴሩ እና ለሚመለከታቸዉ የደህንነት ክንፎች አሳዉቋል።
ወታደራዊ ደህንነቱ ሌሎች በተለያየ ምክንያት ወደ ኤርትራ ሰርገዉ እንዲገቡ የተደረጉ የስለላ ሰዎች በተለይም የአርበኞች ግንቦት ሰባትን አጠቃላይ ፖለቲካዊና መሰረታዊ የአደረጃጀት እርከን፣ እንዲሁም ወታደራዊ ኮርሶችና ዲስፕሊኖችን፣ ስልታዊ መዋቅርንና አቀማመጥን ለመሰለል እንዲረዱ ከተሰማሩ ግለሰቦች ዉስጥ አንዳቸዉም የት እንደገቡ ለማወቅ ያለመቻሉን ምንጮቻችን ጠቅስዋል።

Saturday, March 19, 2016

ግልጽ ደብዳቤ ለጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም




ግልጽ ደብዳቤ ለጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም
Written by አስፋ ጫቦ
ግልጽ ደብዳቤ ለጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም
ይህን ደብዳቤ እንድጽፍልዎ ያስገደደኝ፣ ዛሬ አገራችን የገባችበት ማጥ ነዉ። ከፖለቲካነትን ይልቅ የ“ኧረ ምን ይሻላል! ኧረ ምን ይበጃል !” ደብዳቤ አድርገው ቢያዩልኝ ደስ ይለኛል። እንደ መፍትሔ አፈላላጊ የአገር ሽማግሌ ድምፅ ሆኖ እንዲታይልኝ/ቢታይልኝ እወዳለሁ። ነውም!! ”የጋራ ቤታችን” እንዲህ ማጥ ውስጥ ስትዘፈቅ የሚያይ አገር ወዳድ ሁሉ ድምጹን የመስማት ግዴታ ያለበት ወቅት ላይ ነን ብዬ አምናለሁ። ከፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ይልቅ የአገራችን የኢትዮጵያ መሰንበት፤ ከዚያም “በነጻነትዋ ለዘላለም ትኑር!” ማለት ይቅደም እንደማለት ነው። በደርግ ቋንቋ “ኢትዮጵያ ትቅደም!” እንደማለት!

Friday, March 18, 2016

የእንግሊዙ ጠ/ሚ/ር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባስቸኳይ እንዲፈቱ ለአቶ ሃለማሪያም ደሳለኝ በድጋሜ የተማጽኖ ጥሪ አቀረቡ

የእንግሊዙ ጠ/ሚ/ር አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ባስቸኳይ እንዲፈቱ ለአቶ ሃለማሪያም ደሳለኝ በድጋሜ የተማጽኖ ጥሪ አቀረቡ
ላለፉት ሁለት አመታት ያህል በእስር ላይ እየማቀቁ እንደሚገኙ የሚታመነው ከግንቦት 7 መሰራቾች አንዱ እና ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሁኔታ ያሰጋቸው የታላቋ ብሪታኒያ ጠ/ሚ/ር ዲቪድ ካሜሮን ለኢትዮጵያው አቻቸው ለአቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለሁለተኛ ጊዘ ደብዳቤ መጻፋቸውን ( ቡዝ ፌድ ነውስ) የተባለው ድህረገጽ ከእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ መ/ቤት ያገኘውን መረጃ ትነተርሰሶ በተላንተናው እለት( ሃሙስ መጋቤት 17 2016) እትሙ ዘግቧል።

ሾተላይ የሚጫወትባት ሀገር – ትንሽ ስለበውቀቱና ነቃፊዎቹ (ይሄይስ አእምሮ)

ይሄይስ አእምሮ
Bewketu Seyoum is a novelist and poet from Ethiopia.በዚያን ሰሞን በውቀቱ ሥዩም ከ“አሜን ባሻገር” የምትል አንዲት ግሩም መጽሐፍ ጽፎ ለንባብ አብቅቷል – ሳቢን መግረፍ የለመድነው ጥቂት እኛዎች እንደአህያዋ ማር አልጥመን ብሎ በስድብና በዘለፋ ተቀበልነው እንጂ፡፡ ይህችን መጽሐፍ ተከትሎ በውጪም በሀገር ውስጥም የሂስ መዓት ሲዥጎደጎድ ይስተዋላልኝ፡፡ እኔም ሲያቀብጠኝ ከመጽሐፊቱ በፊት ትችቶቹን እያነበብኩ ቅንጭላቴን ሳዞር ከረምኩኝ፡፡ እንዲያውም በሂሶቹ ሰበብ መጽሐፊቱን የማንበብ ፍላጎቴ ሣይቀር ደብዝዞብኝ ነበር፡፡ እርሷም በማከያው ከገበያ ጠፋች፡፡ ሁሉም ወደዳትና ልኩራ አለች፡፡ እናም ተሰወረች፡፡ በኋላ ግን ደግማ መጣችና ገዝቼ – ኧረ ንሺ እቴ የምን መዋሸት ነው – አንብቦ ካጨረሳት ጓደኛየ የቅሚያ ያህል ወስጄ ማንበብ ያዝኩ፡፡ በሣቅ እየነፈርኩ – ከንባብ ጋር የተጣላችውን ባለቤቴን ሌሊት ሌሊት እየረበሽኩ በሁለት ግማሽ ውድቅቶች ጨረስኳት፡፡ መጽሐፊት መጽሐፍ አይደለችም፤ ቅመም ናት፡፡ ሂሶችን ቀድሜ ማንበብ አልነበረብኝም፡፡ አጠፋሁ፡፡

የአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ስብሰባ (ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም)

መስፍን ወልደ ማርያም
(ይህ ጽሑፍ ሪፖርተር ጋዜጣ በጻፈው ግምገማ ላይ የተመሠረተ ነው፤ የምጠቅሰው ሁሉ ከዚያው ነው፤ ብዙ ቪድዮዎችን ለማየት ሞክሬ አፈናው ከባድ ስለሆነ አልቻልሁም፡፡)
Prof. Mesfin Woldemariam : is an Ethiopian Human Rights activist and philosopherአቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከሥልጣን ውጭ ያሉ ሰዎችን ሰብስቦ ለማነጋገር የመወሰኑን ሀሳብ መንፈስ ቅዱስ ሹክ ያለው ይመስላል፤ ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስና በኃይለ ማርያም ደሳለኝ መሀከል ጣልቃ የገባና መልእክቱን የለወጠው ኃይል አለ፤ ‹‹በብሔራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት — ስለኢትዮጵያ ሕዳሴ›› መነጋገር የሚለው ሀሳብ በመሠረቱ ጠቃሚና ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ፤ ሆኖም ይህ ጉዳይ የሚመለከታቸውና የሚያገባቸው ‹‹ምሁራን›› ብቻ ናቸው የሚል ቅዠት የለኝም፤ በተለይ ምሁራን ማለት ‹‹እኛው … ነን›› እንዳለው ከሆነ!
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ችግር ሁሉ እያለቀሱ የሚኖሩት ምሁራን አይደሉም፤ ችግሩን በትክክል ሳይረዱ ስለመፍትሔ ማሰብ የጉልበተኞች መንገድ መሆኑን ጠንቅቀን እናውቃለን፤ መፍትሔ የሚፈልግ ሰው ሰብስቦ ማነጋገር የሚያስፈልገው ችግሩ በየዕለቱ የሚገርፋቸውን የሚወክሉ ሰዎችን ነው፤ የተወሰኑ ምሁራን ለመፍትሔው ስለሚያስፈልጉ በታዛቢነት ቢኖሩ ጥሩ ነው፤ እንደዚያም ሆኖ ችግሩን የሚናገሩ ሰዎች ከፍርሃት ነጻ የሚሆኑበት መድረክ መኖሩን ማረጋገጥ ያሻል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ኮንሶ ልዩ ወረዳ ውጥረቱ እንደነገሠ ነው።

በህወሓት(ደኢህዴን) እና የእነሱ ቅጥረኛ በሆኑት የአካባቢው ሆድ አደር ተሿሚዎች ምክንያት የማንነት እና ዘር የማጥፋት አደጋዎች ከፊታችን ተደቅኖብናል፤ ከዚህ በፊትም በስውር ሲፈፀምብን ነበር ይላል አንድ የኮንሶ ወጣት በውስጥ መስመር በላከልኝ መልዕክት።
የኮንሶ ልዩ ወረዳ በደቡብ ኢትዩጵያ ውስጥ ከሚገኙት 8 ልዩ ወረዳዎች አንዷ ናት ። በማዕከላዊ እስታቲስቲክስ ዳታ መሰረት ወደ 305,000(ሶስት መቶ አምስት ሺ) የሚያክል ህዝብ ብዛት አላት። ይህንን የሚያክል ህዝብ ይዛ ቀድሞንም ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በወረዳ ደረጃ በመዋቀሯ ምክንያት የአካባቢው ህዝብ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በአቅራቢያው ባለማግኘት ምክንያት ምን ያክል በከፋ ስቃይ ውስጥ እንደነበር መገመት አያዳግትም። በነገራችን ላይ እንደ አጠቃላይ ከተመለከትን የደቡብ ኢትዩጵያ ህዝቦች በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ሁሉም ክልሎች ሲነጻጸር በመሰረተ ልማት ዝርጋታና በእድገት የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሆነ ወርልድ ባንክን ጨምሮ ሌሎች የአለም አቀፍ ድርጅቶች ከአንድ አመት በፊት ሪፖርት ማውጣታቸውን አስተውሳለሁ ። ከዚህ አንፃር ስንመለከት በኮንሶም ይሁን ሌሎች የደቡባዊ ኢትዩጵያ ወረዳዎች እና ዞኖች አንድ ገበሬ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለማግኘት በአማካይ የ5 ወይንም የ6 ሰዓት መንገድ በባዶ እግሩ መጓዝ ይጠበቅበታል። ደርሶ መልስ ባላጋንን የ11 ሰዓት መንገድ። ለዛውም በየአካባቢው በወያኔ መስፈርት የተሾሙት ትንንሽ መሳፍንቶችን ግልምጫ እና ስድብ ለማስተናገድ።

Thursday, March 17, 2016

እየሰመጠ ካለ መርከብ ራስን የማዳኛ ጊዜ አሁን ነው! (ከአርበኞች ግንቦት 7 ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ)

Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracyዛሬ መጋቢት 8 ቀን 2008 ዓ.ም የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ አድርጎ በምክር ቤቱ የመጀመሪያ ጉባኤ የተላለፉትን ውሳኔዎች አፈፃፀም ገምግሞ፤ በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ተግባራዊ ሊደረጉ የሚገባቸው ተግባራት ላይ ተነጋግሮ ውሳኔ አስተላልፏል።
በሥራ አስፈፃሚው ግምገማ መሠረት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የህወሓት አገዛዝ በሚያደርስበት በደል በቃኝ ካለ ቆይቷል፤ በዚህም ምክንያት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ በሥርዓቱ ላይ እያመፀ ነው። በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ፣ በአፋር፣ በጠቅላላው በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሕዝባዊ እምቢተኝነት እየተቀጣጠለ ነው። የአዲስ አበባ የታክሲ ሾፌሮችና ባለንብረቶች እንዲሁም የረዥም ርቀት አውቶቡሶች አሽከርካሪዎች ያደረጉት የሥራ ማቆም አድማ ትግሉ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያረጋግጡ ናቸው።
አርበኞች ግንቦት 7፣ የህወሓት አምባገናዊ አገዛዝ በትጥቅ ትግልና በሕዝባዊ እምቢተኝነት መወገድ እና በምትኩ የኢትዮጵያ ሕዝብ በነፃነት የመረጠው መንግሥት መተካት አለበት ብሎ ያምናል። በዚህም መሠረት በትጥቅ ትግሉ ዘርፍ የሚያደርገው ተጋድሎ ከዚህ በፊት ከነበረው በተሻለ አደረጃጀት ተጠናክሮ እንዲቀጥል፤ በየቦታው እየፈነዳዳ ያለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተቀናጅቶ አገራዊ እንቅስቃሴ ሆኖ እንዲወጣ የትግል አቅጣጫ ነድፎ ተግባራዊ እንዲሆን ወስኗል።

ሕወሓት እንደጥርስ መፋቂያ አንድ ጊዜ ተጠቅሞ የጣላቸውን የቀድሞ ወታደሮቹን እየሰበሰበ ነው


(አቶ አሰገደ ገብረሥላሴ እንደዘገቡት) የህወሓት ነበር ታጋዮች ለመጭው ቅዳሜ መጋቢት10/07/08 ዓ ም በህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ሥብሠባ ተጠርተዋል የዚህ ሥብሠባ ኣለማ ኣልታወቀም::
የታጋይ ነበር ሥብሠባ የሕወሓት መሪዎች በውሥጣቸው ቀውሥ ወይ መከፋፈል ሢፈጠር ሢጨንቃቸው የሚጠሩት ሥብሠባ ነው:: ያጋጠማቸው ችግር እሥከሚፈቱ ወይ እሥከሚረጋጉ ጡሮታ እንሠጣሃለን; መቋቋምያ እንሠጣሀለን; ሥራ እንፈጥርላሀለን በማለት እንደሚሠብኩትም ታውቀዋልLL በተጨማሪም ህወሓት የበላይነቱ እና ማንነቱ ተነጥቋል የሚል ሠበካ እንዳለም ከወዲሁ ይናፈሣሣል ::
ይህ ሥብሠባ በመላው ትግራይ ኣዲሥ ኣበባ ይደረጋል ተብሏል::

የኢትዮጵያ ህዝብ ማንንም ሳይጠብቅ ለነፃነቱ እንዲነሳ ጄኔራል ከማል ገልቹ ጥሪ አቀረቡ


ኢሳት ዜና:- ህብር ራዲዮ ከላስቬጋስ እንደዘገበው፤ የመገንጠል ሀሳቡን ከፕሮግራሙ ያወጣው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሊቀመንበር ጄኔራል ከማል ገልቹ፤ በአሁኑ ወቅት የግንባሩ ዋነኛ ዓላማ በተባበረ የኢትዮጵያ ህዝብ ክንድ ወያኔን በማንበርከክ ለህዝቡ ጥያቄ እንዲገዛ ማድረግ መሆኑን በድጋሚ በማረጋገጥ፤ ህዝቡ ሳይከፋፈልና ማንንም ሳይጠብቅ ለነፃነቱ እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃ……. ሐይለማያም ደሳለኝ በጥቂቱ አሻፈረኝ እያሉ ነዉ!!

Gudish Weyane's photo.
በትናንትናዉ እለት በቤተ መንግስት ዉስጥ በተጠራ ሚስጥራዊ ስብሰባ ላይ እጃቸዉን በመክተት የጸጥታ ሐላፊዎችን አስደንግጠዋል።
በቤተ መንግስቱ የጸጥታ ጉዳዬች ዙሪያ ለመነጋገር በሚል ሰበብ ተደጋጋሚ ሚስጥራዊ ስብሰባዎችን ታግሼያለዉ! አሁን ግን ከተለያዩ ክልሎች በተለይም አዲስ አበባ ላይ የሚገኙ ከፍተኛ የክቡር ዘበኛና የደህንነት የበላይ አካሎች ከመከላከያ የበላይ ሹማምንቶች ጋር የሚካሄደዉ ዉይይት በምን ጉዳይ ላይ እንደሆነ ማወቅ ያሻናል በማለት ስብሰባዉ በሓይለማርያም ደሳለኝ ትእዛዝ የተሰረዘ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ሪፖርት እንዲያደርጉ የተጠየቁ የክቡር ዘበኛ የበላይ ሐላፊዎች ግቢዉን ለቀዉ ወጥተዋል።
ጉድሽ ወያኔ

Monday, March 14, 2016

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ፈተናዎች

የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ፈተናዎች
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ (ኢሳት) ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት ሥድስት ዓመታት የመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ዐይን እና ጆሮ ሆኖ መሰንበቱ የመገናኛ ብዙኃኑ ተከታታይ እና ደጋፊዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ፤ ዕውነትን እንደ ሰደድ-ኢሳት የሚፈሩት ጠላቶቹም ጭምር እንቅልፍ አጥተው ሲከታተሉት እና ሲፈታተኑት በመቆየታቸው ሳይወዱት በግድ (በተግባራቸው) መስክረውለታል።

ሶስት ሌ/ሎኔል ሁለት የ3ሻለቃ ማዕረግ ያላቸው መኮንኖች በወያኔ ወታደራዊ ደህንነት ተይዘው ከተወሰዱ በኋላ መድረሻቿው መጥፋቱ ታውቋል።


የወያኔ ቡድን መሪዎች ለስልጣናቸው ናቸው ብለው የሚጠረጥሯቸውን በሙሉ መግደል ማሰርና ማግለል የዘወትር ተግባራቸው ሲሆን በራሳቸው የጦር ኃይል ውስጥም ጦሩን ያሳምጻሉ ተብለው የጠረጠሩትን ሁሉ ከስብሰባና ከግምገማ አዳራሽ እየወሰዱ መዳረሻቸውን እየጠፉ መሆኑን ከወያኔ መከላከያ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለከታል። በዚህ መሠረት በወያኔ ሰሜን ዕዝ ውስጥ የከፍተኛ መኮንኖች ግምገማ ላይ ያነሱት ሃሳብ አመጽ ቀስቃሽ ነው፤ አፍራሽ ነው ብሄራቸው ተጠርጣሪ ነው በሚል ሶስት ሌ/ሎኔል ሁለት የ3ሻለቃ ማዕረግ ያላቸው መኮንኖች በወያኔ ወታደራዊ ደህንነት ተይዘው ከተወሰዱ በኋላ መድረሻቿው መጥፋቱ ታውቋል። ይህ በሰሜን ዕዝ የተፈጸመው ሁኔታ መረጃዎችና ወታደራዊ አዛዦችችን የበለጠ ስጋት ላይ ጥላችቸው። ተይዘው መዳረሻችው የጠፋ መኮንኖች ማንነትና ብሔራቸው ለጊዜው ያልታወቀ ሲሆን በርካታ የጦር አባላት ግን ሁኔታውን በቅርብ አየተከታተሉት መሆኑ ተገልጿል።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ግዛቸው ምትኩ ከስራ ተሰናበተ

ዳኛ ግዛቸው ምትኩ ይባላል። ተወልዶ ያደገው ጎንደር ውስጥ ነው። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኖ ለአመታት ሲያገለግል ቆይቷል። የህግ ትምህርቱን የተከታተለው በአለማያ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን የአቶ መላኩ ፋንታን እና የወዲ ገብረዋህድን የሙስና ክስ በዋና ዳኝነት ይዞት የነበረው እሱ ነው። በተለይም አቶ መላኩ ፋንታ የታሰረው ያለምንም የሙስና ወንጀል በአማራነቱ ብቻ መሆኑን የሚያምነው ዳኛ ግዛቸው ከሌሎች ዳኞች ጋር መስማማት አልቻለም ነበር። በዚህም የተነሳ ለባለፉት 6 ወራት ከስራ ታግዶ ከቆየ በኋላ በዚህ ሳምንት ሊሰናበት ችሏል።
ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው ዳኛው ከስራው ለመባረሩ ከቀረቡበት ክሶች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል
‹‹ተከሳሽ ዳኛ በቡድን ውይይት ወቅት በአንዳንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የአንድ ብሔር አባላት የበላይነት የሚታይ መሆኑን፣ እንዲሁም አማራ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል አላግባብ እየተፈናቀለ መሆኑን ሲገልጹ ነበር፡፡ በውይይት ጊዜም ከሌሎች የአማራ ብሔር ተወላጆች ጋር አላግባብ የመወገንና የመቧደን እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበርና በአጠቃላይ ተከሳሹ እንደ ድርጊታቸው ሕገ መንግሥቱን የመቀበልና የማመን ነገር እንደማይታይባቸውና አመለካከታቸውን ለማስተካከልም ዝግጁ አለመሆናቸውን፤›”
እንግዲህ አማራ መሆን እና ስለ አማራ ህዝብ መብት መቆርቆር አማራ በብዛት ባለባት ሃገር ውስጥ እንደማይቻል የ”ህግ ተቋማት” ይህን የህግ ሰው በማባረር አፅድቀውታል።
እንደ ዳኛ ግዛቸው ያሉ ለህዝባቸው የሚቆረቆሩ የአማራ ልጆችን በበዙ ቁጥር ድላችን ይፋጠናል።
ወንድማችን ስለ አማራነት በድፍረት ስለተናገርክ እንኮራብሃለን! እናከብርሃለን! እስከመጨረሻው ድረስ መላው የአማራ ልጅ ከጎንህ ነው።

የአጋዚ ልዩ ሃይል በኮንሶ እስካሁን ሁለት ሰዎች ገሎ ሶስት ማቁሰሉ ታወቀ።

በኮንሶ ለወራት በዘለቀው የነዋሪዎቹና የልዩ ኃይል ፍጥጫ ምክንያት ትምህርት ቤቶች እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከየካቲት አጋማሽ ጀምሮ ዝግ ሆነዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኮንሶ ወረዳ እና የአካባቢው ባለስልጣናት ለግምገማ ተጠርተው ወደ ክልሉ መቀመጫ ሀዋሳ ቅዳሜ መጋቢት 3 ሄደዋል። የሰሞኑ የኮንሶ ውጥረት የተቀሰቀሰው የአካባቢው ባህላዊ መሪ የሆኑት ካላ ገዛኸኝ ወልደዳዊት መታሰርን ተከትሎ ነው። ካላ ገዛኸኝ በታሰሩበት አርባ ምንጭ በኮንሶ ሰዎች እና በወንድማቸው መጎብኘታቸውን ከአካባቢው የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ዜና መረጃ — ህወሃት አሉኝ የሚላቸዉ ጄኔራሎቹን አጣጣለ

በልኡል አለም
በ11/03/2016 በመከላከያ ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ ዉስጥ በተደረገ ድንገተኛ ስብሰባ ላይ የተገኙ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጄኔራሎች እራሳቸዉን ከኤርትራ ጄኔራሎች ብቃት ጋር በማወዳደር መናቆራቸዉን ምንጮች እየገለጹ ይገኛሉ።
general samora yenus
በሚኒስቴር ጀኔራል ሲራጅ ፈጀታ የዉስጥ ደንብና ምክክር የተጠራዉ ይህ ድንገተኛ ስብሰባ አሉ የሚባሉ የወያኔ ጄኔራሎችን ያካተተ ሲሆን የምክክር መድረኩ ባስገራሚ መልኩ ይዘቱን ቀይሯል። ይህዉም የኤርትራ ጄኔራሎችን ብቃት በተመለከተ ጠቅለል ያለ መረጃ ያቀረቡት ጠ/ሚኒስቴር ጄኔራል ሲራጅ ፈጀታ ለሻቢያ ስራዊት የመጀመሪያዉን ጥይት ከተኮሱ ከነ ሃሚድ ኢድሪስ አዉት ጀምሮ እስከ አሁኑ የጸጥታ ሐላፊ የበላይ ጠባቂ ከሜጄር ጄኔራል ፊሊፖስ ወልደዮሓንስ እንዲሁም እስከ እታች ለመዉረድ የሞከረ ሲሆን በንግግሩ መደምደሚያ ላይ ኤርትራን ለመዉጋት ብንነሳ እነዚህ የሻቢያ መኮንኖች ምን ያህል ይከላከላሉ የሚል እሳቤ ነበርዉ።

Saturday, March 12, 2016

ህወሃት – 9 ስደተኞችን ደብዳቤ ጽፎ ከአሜሪካ ወሰዳቸው

“ከህወሃት በላይ በራሳችን አዝኛለሁ” ኦባንግ ሜቶ

deportee letter
ከተለያዩ አገራት አሜሪካ ገብተው የስደት ማመልከቻ ያስገቡ 9 ኢትዮጵያውያንን ህወሃት ተረከቦ ወደ አገር ቤት እንደወሰዳቸው ታወቀ። አንዱ ራሱን ለማጥፋት ሞከሮ ነበር። ወደ ኢትዮጵያ ቢሄድም የጤናው ሁኔታ አልታወቀም። ድርጊቱን አስመልክቶ አቶ ኦባንግ ሜቶ “ከህወሃት ተግባር በላይ በራሳችን አዝኛለሁ” ሲሉ ወጣቶቹን ለማዳን ያደረጉት ጥረት መረጃው ዘግይቶ ስለደረሳቸው አለመሳካቱን አመለከቱ።

Wednesday, March 9, 2016

Ethiopia: Members of US Congress Urge Obama to Secure the release of Mr. Okello

President Barack Obama
The White House
1600 Pennsylvania Avenue NW
Washington, DC, 20500
Dear President Obama,
Okello Ochalla was seized in South Sudan by South Sudanese security forcesWe write to ask you to help secure the release of Mr. Okello Akway Ochalla from captivity in Ethiopia. Mr. Okello is an indigenous Anuak leader and the former Governor of the Gambella region in Ethiopia. His children and sister-in-law reside lawfully in the U.S. He has been a political prisoner in Ethiopia for nearly two years.
Okello Ochalla was seized in South Sudan by South Sudanese security forces
Mr. Okello Akway Ochalla
The United States is home to a large Ethiopian diaspora. Many Ethiopian Americans are alarmed by the ongoing human rights abuses in their country of origin. There is particular concern regarding the silencing of political opposition members. Mr. Okello is one of these political opponents who has been unjustly silenced and imprisoned.

የሕወሓት ካድሬዎች በኮንዶሚኒየም ቤቶች ላይ የሚያደርጉት ሕገወጥ ተግባር በቆጠራ ተደረሰበት::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለፉት አሥር ዓመታት የገነባቸውን የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ በጀመረው ቆጠራ፣ በሕወሓት ካድሬዎች  በርካታ ሕገወጥ ተግባራት የተፈጸሙባቸው ቤቶች መኖራቸው ታወቀ፡፡

የካቲት 21 ቀን 2008 ዓ.ም. የተጀመረው ቆጠራ ሳምንቱን የያዘ ሲሆን፣ ይቆጠራሉ ከተባሉት 104,258 ቤቶች ውስጥ 35 ሺሕ ያህሉ ተቆጥረዋል፡፡ በዚህ መሠረት በሕወሓት ካድሬዎች   ተሰብረው የተከራዩ፣ ፈርሰው ተቀላቅለው የተሠሩ፣ በግለሰቦች የተያዙ በርካታ ቤቶች መኖራቸው ተረጋግጧል፡፡ በተጨማሪም ትዳር እየፈረሰና ፍቺ እየተፈጸመ መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

Tuesday, March 8, 2016

የስድስት ሰዓት ሴት ተጠያቂዎች፣ ጥቂት ስለ ቃሊቲ የሴቶች መቆያ እና ማረሚያ ቤት (በማሕሌት ፋንታሁን)

Ethiopian Women political prisoners
በማሕሌት ፋንታሁን (ዞን9 ጦማሪ)
የማይቻል ነገር እንደሌለ በተግባር ለማየት ከሚያስችሉ ሁኔታዎች አንዱ የእስር ቤት ሕይወት ነው። እስር ቤት እንገባለን የሚል እሳቤ በአይምሯችን ውስጥ ስለማይኖር በአብዛኛው ከተለመደው የኑሮ ዑደት (መወለድ፣ ማደግ፣ መማር፣ መሥራት፣ ማግባት፣ መውለድ፣ ማደርጀት እና መሞት) እና ተያያዥ ጉዳዮች ተነስተን ነው የግል አቋማችንን የምንቀርፀው። “ከሰው ጋር መተኛት አልወድም/አልችልም፤ እንቅልፍ አይወስደኝም”፣ “ስፕሪስ ሳልጠጣ መዋል አልችልም”፣ “የቀዘቀዘ ምግብ አልወድም”፣ “ሲጃራ ሳላጨስ መኖር አልችልም”፣ “በቀን ቢያንስ ሁለት ፊልሞችን ካላየሁ አልደሰትም”፣ “እከሊትን/እከሌን ሳላይ መዋል አልችልም”፣ “ጨለምለም ካላለ ወደ ቤት መግባት አልወድም”፣ “መብራት ካልጠፋ እንቅልፍ አይወስደኝም” እና የመሳሰሉ የማይለወጡ የሚመስሉን አቋሞቻችን ፈተና ውስጥ የሚወድቁት የእስር ሕይወትን ‹ሀ› ብለን ስንጀምር ነው። ብዙ አልችልም ብዬ የማስባቸውን ነገሮችን ችዬ ስለወጣሁበት ስለ ቃሊቲ የሴት እስረኞች ግቢ ጥቂት ልበላችሁ።

ከጠመንጃ ‘ነፃነት’ ወደ ስኳር ባርነት! (ታሪኩ አባዳማ)

ታሪኩ አባዳማ – የካቲት 2008
INVESTORS, WELCOME TO ETHIOPIAለስኳር ማምረቻ ፋብሪካዎች ማስፋፊያ በሚል ሰበብ መጠነ ሰፊ መሬት ከዜጎች እየተዘረፈ መሆኑን ስንሰማ ቆይተናል። የታሪክ እና እምነት መናኸሪያ ዋልድባ ገዳም በይዞታው ስር የሚገኘውን ርስት በዚህ ምክንያት መቀማቱንም እንደ ዋዛ ሰምተን ነበር። ሰሞኑን በምናገኘው ወሬ ደግሞ የኦሞ ሸለቆ ልዩ ልዩ ብሔረሰብ ኢትዮጵያውያን ከክልላቸው ጭካኔ በተመላበት የወያኔ አስገድዶ ማፈናቀል ዘመቻ ከቄያቸው ሲጋዙ መክረማቸውን ተረድተናል። መሬታቸው ለሸንኮራ እርሻ ማምረቻ እና ስኳር ፋብሪካ ስለተመረጠ እነሱ ወዳልመረጡት አካባቢ በጠመንጃ አፈሙዝ ተገደው ተወስደዋል።
እንደ እንሰሳ በገመድ ተጠፍሮ ካሚዮን ላይ የተጫነውን ወገናችንን አተኩራችሁ ካስተዋላችሁ በስኳር ገበያ የጎመዘዘው የኦሞ ሸለቆ ክልል ህዝቦች ህይወት ስዕል ቁልጭ ብሎ ይታያችሁዋል። ስኳር የሚልሱ ጉልበተኛ ገዢዎች በዜጎች ጉሮሮ እንቆቆ እያንቆረቆሩ ስለመሆኑ በማያሻማ ሁኔታ ትገነዘበላችሁ። ለም የተባለ ያገሪቱ ምድር እንደ ጠላት ወረዳ ወረራ እየተፈፀመበት የይዞታው ባለቤት የሆኑ ነዋሪዎቹ ወደ ዘቀጠ ኑሮ እየተወረወሩ ይገኛሉ። በዚህም የወያኔ እውነተኛ ተፈጥሮ ይበልጥ ግጥጥ ብሎ ወጥቷል።

ዘ-ህወሀት በኢትየጵያ የታክሲ ሾፌሮች ላይ የከፈተው ጦርነት!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም  
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
Taxi drivers pix
Taxi drivers pixበአሜሪካ “ባለሶስት-ጥፋት ሕግ“ እያሉ ይጠሩታል፡፡ ወንጀለኞች ሶስት ከባድ ወይም ደግሞ አስከፊ ወንጀሎችን የሰሩ ከሆነ ከ25 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራት የሚያደርስ ቅጣት ይበየንባቸዋል፡፡
ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ የታክሲ አሽከርካሪ ሾፌሮች ላይ ጦርነት አውጇል!

ኦህዴድ ሳያገግም፤ ብአዴን ሊደገም? – “የአማራን ሕዝብ ትጥቅ አስፈቱ” አባይ ወልዱ


demeke-muktar-e1457323281819-620x310
ኦህዴድ ሳያገግም፤ ብአዴን ሊደገም (ፎቶ: addisfortune)

ኢትዮጵያን በተገንጣይ ስም የሚመራው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር – ህወሃት፣ የገጠመው ቀውስ እየተለጠጠበት ነው። ኦህዴድ አደረጃጀቱ ሊጠገን በማይችልበት …

Monday, March 7, 2016

ከድጡ ወደ ማጡ አሰብ በአረቦች እጅ ገባች‬

 ዶ‬/ርያዕቆብ ኃ/ማሪያም


የአገራችን አንድነትና ብሎም ሕልውና በቋፍ ባለበት በዚህ ቀውጢ ወቅት ውይይቱ ሁሉ ማተኮር ያለበት ለሥጋቶቹ ምንጭና ምክንያት ስለሆኑት ስለ ዴሞክራሲ ደብዛ መጥፋት፣ ስለፍትህ መቅጨጭ. በብሔረሰቦች መካከል ስለሚታዩት ጥላቻና ግጭቶች እነዚህን የወለደው ሥርዓት ስለመለወጥ ብቻ መሆን አለበት ሌላው ሁሉ ገብስ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ በአሁን ወቅት ከእነዚህ ውጭ በሆኑ ጉዳዮች ላይ መነጋገር ስርዓቱን ለውጦ ዴሞክራሲና ፍትሕ ለማስፈን የሚደረገው ትግል መዘናጋት ይሆናል የሚሉ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን የዚህ ጽሑፍ ዓላማ የአሰብ ወደብ ወደ ሳውዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ መተላለፍ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ለማሳወቅና በውጭ አገር በቪዥን ኢትዮጵያና በኢትዮ-ኤርትራ ሶሊዳሪቲ ኮሚቲ የሚደረጉ የኤርትራና የኢትዮጵያ ሕዝቦች የማግባባትና የማቀራረብ እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ ታስቦ የተጻፈ ነው፡፡ በተጨማሪም ዘላቂ የአገር ጥቅሞችን መዘንጋት የኋላ ኋላ ሕልውናን መፈታተን ደረጃ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ አገር ከሌለ ዴሞክራሲ ምን ሊፈይድ፣ ፍትሕስ ምን ሊረባ፡፡
ምናልባት የአገር ሕልውናን እስከመፈታተን ሊደርሱ ከሚችሉ ከዋነኛ የአገር እሴቶች አንዱ የባህር በር አለመኖር ነው፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ሁኔታ፡፡ በማይጨው ጦርነት ለሽንፈታችን ምክንያት ከሆኑ ከዋነኛ ምክንያቶች አንዱ ኢትዮጵያ የገዛችው የጦር መሳሪያ በጅቡቲ በኩል ወደ አገር እንዳይገባ ፈረንሳይ መከልከልዋ እንደነበር መዘንጋት የለብንም፡፡ 

ደቡብ ኢትዮጵያ አዲሷ ዳርፉር

የኢትዮጵያ የደቡብ ክልል አይን ያወጣ ግፍ የሚፈጸምበት አዲሱ ዳርፉር እየሆነ ነው፡፡በተለይ ከወላይታ ጀምሮ እስከ ሱዳን ክልል ያለው ቦታ በየዕለቱ ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እጅና እግር አውጥተው የሚታዩበት ቦታ ሆኗል፡፡
ይህ ምስልም ከክልሉ የተገኘ መሆኑን የክልሉን ፖሊሶችና ደቡብ ፖሊስ የሚል ጽሁፍ ያረፈባትን መኪና በማየት መረዳት ይቻላል፡፡
የሱርማ ተወላጆች መሬታችንን በኃይል አንለቅም በማለታቸው የፊጥኝ እየታሰሩ በደም እንደተለወሱ በገዛ ወገኖቻቸው ተወስደዋል፡፡
ምንም እንኳን የብሄራችን ተወላጆች ባይሆኑም ኢትዮጵያዊያን ከሁሉም በላይ ደግሞ ሰዎች በመሆናቸው ያሉበትን ስቃይ እንረዳላቸው፡፡
በደቡብ የቁጫ ተወላጆችም በደቡብ ህብረት ቀጭን ትዕዛዝ የማንነት ጥያቄ ባነሱ የአካባቢው ሽማግሌዎች፣ሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ላይ የግፍ መዓት ወርዷል፡፡የፌደራል መንግስቱም ዳንኤል ሺበሺን ያለ በደሉ ወህኒ በማውረድ የቁጫዎች ጩሕት በዳንኤል በኩል እንዳይሰማ አድርጓል፡፡
ኢትዮጵያዊ መሆን እልፍ ሲልም ሰው መሆን ወንጀልን ለመቃወም በቂ ነው፡፡ፈረንጆቹስ no one is free when others are oppressed ይሉ የለምን?
 

ምስራቅ ጎጃም ውጥረት ነግሷል!!

11041764_459898677512558_6207929217884897390_n
በኦሮሚያ የተነሳው ህዝባዊ ቁጣ ወልቃይት ጠገዴ ሀርማጮ ሁመራ በሰሜን ጎንደር የበረታው ትግል ጎጃም ደረሰ፡፡ በደብረ ማርቆስ ባህር ዳር አንዳች ነገር ሊፈዳ እያኮበኮበ መሆኑ እየተሰማ ነው፡፡ በርካታ ወጣቶች አፈሳና-ወከባ ቢደርስባቸውም እሱን ተቋቁመው ከነጻነት ትግል የትም አንርቅም እያሉ ይገኛል፡፡

የህወሃት መከላከያ ሠራዊት ወደ ኤርትራ መጠጋት እውን ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመግጠም ወይስ በኤርትራ የሚገኙ አማጽያን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ለማድረግ?

አንተነህ ገብርየ
አጭር መግቢያ፦ከ1998 እስክ 2000 የዘለቀው ጦርነት ከሁለቱም ወገን ከፍተኛ የሰው ሕይወትና የሀገር ሀብት ማውደሙ ይታወቃል።ያኔ ህወሃት ጨርቅ ነው ሲለው የነበረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጎ በማውለብለብ መላ ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንዲሰለፉ ጥሪ ማቅረቡ፤እንደ አሮጌ ቁና የጣለውንና የበተነውን የቀድሞ ሠራዊት መማጸኑም ይታወቃል ማንም አላቅማማም ሁሉም ጥሪውን ተቀብሎ ዘመተ ዘመቻው ቀጥሎ ወደ አሥመራ ብቅ ሲል የኢትዮጵያው ጦር እንዲያፈገፍግ ተደረገ የኢትዮጵያን መሬት ለኤርትራ በማስረከብ የተጠናቀቀው ጦርነት የኢትዮጵያ ድል ተብሎ በቅጥፈት ታወጀ።  ነገር አሁንም እልባት አላገኘም ገዥው የህወሃት ቡድን የንጹሐንን ደም በማጉረፍ ተኪ አይገኝለትምና ይህንም እንዲህ አድርጎት ፀጥ አለ።
ያኔ የቀድሞው ጦርም ሆነ ሕዝቡ ህወሃትን የተቀላቀለው የህወሃትን ውስጣዊ አጀንዳ ማንነትና ግብ ባለመረዳት ሲሆን ከዚያ ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ባለው ጊዜ ውስጥ ህወሃት ምን ያህል አረመኔያዊ ተቋም እንደ ሆነ በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ራሱን በተግባር አስተዋወቀ ይህ ጦሱም ብዙ የተቃዋሚ ኃይሎች እንዲያብቡ፤ በርከት ያሉ ጋዜጠኞች ጦማሪያን የሥርዓቱን ጭራቅነትና ዝርክርክነት በስፋት እንዲያጋልጡት አደረገ።

Friday, March 4, 2016

ህወሃት ራሱን “ሳያጸዳ” በሌላው ዘምቷል

የዳባ ደበሌና የሰለሞን ኩቹ መጨረሻ አልታወቀም!

daba
“የኢህአዴግን መርህ እስከተከተለ ድረስ መሃይምም ቢሆን ሚኒስትር እናደርጋለን” ያሉት መለስ ዙሪያቸውን “የበታች” በሆኑ ሹሞች አስከብበው የቆዩት ያለምክንያት አልነበረም፡፡ “አዋቂ፣ ጠቢብ፣ ባለራዕይ፣ ምንተስኖት፣ …” የሚሉ “ማዕረጎችን” አስገኝተውላቸዋል፡፡ ከዚህ አንጻር የፈለጉትን ሥልጣን ላይ ያስቀምጣሉ፤ ከዚያ በሙስና ያበሰብሳሉ፤ ከዚያም ወደ “ቆሻሻ ቅርጫት” ይጥላሉ፡፡ በሕይወት ለቆዩት “ቅርጫቱ” ትልቅ መድህን ሲሆን ለዚያ ያልታደሉት ግን ትርጉሙ ሌላ ነው፡፡ ይህ የመለስ አሠራር የህወሃት መመሪያ ሆኖ ቆይቷል፤ አሁንም እየተሰራበት ነው፡፡

“የመሬት ባላባቱን” አባይ ማን ይድፈራቸው?

“የመሬት ባላባቱን” አባይ ማን ይድፈራቸው?

tsehaye abay
ከተለያዩ አቅጣጫዎች በተቃውሞና ዓመጽ የተወጠረው ህወሃት/ኢህአዴግ በአስሩም ክፍለከተሞች የሚገኙ እስከ 600 የሚደርሱ የመሬት ባለሙያዎችን ካገደ በኋላ የአዲስ አበባ የመሬት አስተዳደር ሞሳኞች ያላቸውን 85 አመራሮችና ሠራተኞችን በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡ “የመሬት ከበርቴውን” አባይ ጸሃዬንስ ማን ይደፍራቸው ይሆን የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል፡፡

Thursday, March 3, 2016

ወግ ከርዕዮት አይበገሬዋ ጋር (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የጸሐፊው ማስታወሻ፡ በኢትየጵያ ውስጥ የፕሬስ ነጻነት እንዲከበር ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ላይ ካለችው ከአይበገሬዋ ርዕዮት ዓለሙ አስደናቂ ታሪክ ጋር በተያያዘ መልኩ ለማቀርበው ተከታታይ ውይይት ይህ የመጀመሪያው ክፍል ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዴሞክራሲ፣ በህግ የበላይነት፣ በሰብአዊ መብት ጥበቃ እና በተጠያቂነት ጠንካራ መሰረት ላይ ለምትገነባው በኢዲሲቷ ኢትዮጵያ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ልዩ የሆነ ጥረት በማድረግ ላይ ከሚገኙት በላስ ቬጋስ ከሚኖሩ ወጣት ኢትዮጵያውያን ጋር የሚደረግ ውይይት የሚቀርብበት ነው፡፡
ርዕዮትን እንዴት እንዳገኘኋት፣
Prof. Alemayehu G. Mariam with Reeyot Alemu
Prof. Alemayehu G. Mariam with Reeyot Alemu
ከግራ ወደ ቀኝ – እስከዳር አለሙ ፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም እና ጋዜጠኛ ርዮት አለሙ

Wednesday, March 2, 2016

ህወሓት “ከቡና ጠጡ” ወደ “መርዝ ጠጡ”

Dr.Tadesse Biru Kersmo
ህወሓት “ከቡና ጠጡ” ወደ “መርዝ ጠጡ”

የአዲስ አበባ ታክሲ ሾፌሮችና ባለንብረቶች ለሁለት ቀናት ያካሄዱት የሥራ ማቆም አድማ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ትምህርት ሊገኝበት የሚገባ ነው። ስታሊናዊ አፈና በሰፈነባት አዲስ አበባ ውስጥ እንዲህ ዓይነቱ አድማ መሞከሩ ብቻውን የሚያስደንቅ ሳለ ተግባራዊ ሆኖ ከተማዋን ለሁለት ቀናት ማስተኛቱ የታክሲዎችን ጉልበት፤ የሕዝባዊ እምቢተኝነት ውጤታማነት እና የተባበረ እርምጃ ስኬታማነት በተግባር አሳይቷል።

Tuesday, March 1, 2016

እጅ በደረት ኣድርገህ ንዳ ! የታክሲ ሹፌሮች እዳ ( ሄኖክ የሺጥላ )


የኣንደኛ ክፍል ተማሪ ሳለሁ ኣንድ ኣምባ ገነን መምህር ነበረኝ። ኣያሌው ይባላል ። ሰውየው በጎማ መጋረፍ ይወድ ነበር ። መፈራት ይወድ ነበር ። ከኣምባገነንነቱ ብዛት የክፍል ስራ ሰጥቶ እጅ በደረት ይለን ነበር ። ያ ኣልበቃ ብሎ በክፍል ውስጥ እየተዘዋወረ የክፍል ስራውን ያልሰራ ተማሪ ኣስወጥቶ በጎማ ይገርፍ ነበር ። በሱ ክፍለ ጊዜ በጎማ የማይገረፈው ትምህርት የቀረ ተማሪ ብቻ ነው ። ታዲያ ኣንድ ቀን እንደለመደው የክፍል ስራ ሰጥቶን ወዲያው « እጅ በደረት!» ብሎ ኣዘዘን ።

ብሶት የወለደው የኦሮሚያ አመጽ ተቆንጥሮ አስመራ ላይ ተላከከ!

“ለህወሃት ብቻ የትጥቅ ትግልን ህጋዊ ያደረገው ማን ነው?”

getachew -reda-ethiopia

በኦሮሚያ የተነሳውን ህዝባዊ እምቢተኛነትና ዓመጽ ተከትሎ ስለጠፋው የሰው ህይወት እርግጠኛ አሃዝ የሚጠቅስ አልተገኘም። ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና የአገር ውስጥ ቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደሚሉት የህወሃት አንጋቾች ከ200 በላይ ንጹሃንን ገድለዋል። በነጻ አውጪ ስም አገሪቱን እየመራ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር – ህወሃት፣ አመጹን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ ቆይቶ በስተመጨረሻ ችግሩን ቆንጥሮ አስመራ ልኮታል። ወታደርና ከባድ መሣሪያም ወደ ድንበር አስጠግቷል። መፍትሔው ጭፍን ብሔረተኝነት ሳይሆን ሁሉንም በሰብዓዊ ፍጡርነት ማየት ነው የሚሉ አካላት “ጆሮ ያለው ይስማ፣ ልቡና ያለው ያስተውል” እያሉ ነው፤ ርምጃቸውንም ከጊዜ ጋር አዋዝተዋል። ህወሃት የትጥቅ ትግልን የራሱ “ንግድ ምልክት” አድርጎ መውሰዱ የማይዋጥላቸው “ለህወሃት ብቻ የትጥቅ ትግልን ህጋዊ ያደረገው ማን ነው?” በማለት ይጠይቃሉ፡፡

በአዲስ አበባና አካባቢ የታክሲ ሥራ ማቆም ዓድማ እየተካሄደ ነው!

መመሪያው ለ3 ወራት ቢራዘምም ሰሚ አላገኘም

addis taxi

የካቲት 14 የጸደቀውን በተለይ ታክሲዎችን የሚመለከተው የአሽከርካሪዎች ሕግ በመቃወም ለሁለት ቀናት የተጠራው ዓድማ በአሁኑ ጊዜ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

“ሀገራችን ላይ እየኖርን አይመስለኝም” ታክሲ አሽከርካሪ

“አብዛኛው ታክሲ በአድማው ስላልተሳተፈ በማኅበራዊው እንቅስቃሴ ላይ የሚያመጣው ችግር የለም" ጌታቸው ረዳ

add taxi

“ሁላችንም የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ነን።ሕጉ ተግባራዊ የሚደረግ ከሆን በአጭር ጊዜ ውስጥ ክሥራ ውጪ እንሆናለን።’’ በዛሬው ዕለት የታክሲ ማቆም አድማ ካደረጉት የታክሲ አሽከርካሪዎች በከፊል፡፡