Translate

Wednesday, March 30, 2016

እነዚህን ከስር የምትመለከቷቸውን ፎቶዎች ወዳጆቼ ከባህር ዳር ዛሬ ሌሊት ላኩልኝ።

ኣማራ ሲሞት ሌላ ኣማራ ሲፈራ ( ሄኖክ የሺጥላ )
እነዚህን ከስር የምትመለከቷቸውን ፎቶዎች ወዳጆቼ ከባህር ዳር ዛሬ ሌሊት ላኩልኝ።



ስለ ፎቶዎቹ ምንነት ባጭሩ ላስቀምጥ
ተደብዳቢው -- አማራ!
ደብዳቢው--- ወያኔ ትግሬ!
የድብደባው ምክንያት--- አማራ መሆን!
ተጠያቂ ---የለም!!!
ይህንን ለማስቆም የሚቆም አማራ--- የለም!!!
ይህንን ኣይቶ ቁጭት ውስጥ ሊገባ የሚችል አማራ--- የለም!!!
ድብደባው ይቀጥላል ወይ?---- ኣዋ!
ይህንን ፎቶ ለብዙ ደቂቃ ተመለከትኩት ። ኣይኖቼ እንባ ተሞልተው ጥርሴን እያፋጨሁ ደግሜ ደጋግሜ ኣየሁት። ወዳጄ በውስጥ መስመር የፃፈልኝን ኣሳዛኝ ታሪክም ኣነበብኩ ። ማልቀስ ኣልችልም ፥ ኣሁንም ያለቀስኩ ኣይመስለኝም ፥ ግን ፊቴ ላይ እንባ የሚመስል ነገር እንደነበር ኣስታውሳለሁ ። መናደድም ኣልፈልግም ፥ ምክንያቱም ከመናደድ የሚመጣው ሽንፈት እንደሆነም ኣውቃለሁ ። ግን ማሰብ እፈልጋለሁ ፥ ድጋሚ ወደ ራሴ ተመልሼ እውነታውን በጥሞና ማየት እና መረዳት እፈልጋለሁ ። 

በቃላችን መሰረት የወዳጄን ምንነትም ሆነ ማንነት ለመናገር ኣሁን ጊዜው ኣይደለም ። ግን ይህ ድብደባ ምን ማለት እንደሆነ ላስረዳ።
ብዙ ለአማራ የሚጮህ ፥ እቆጫለሁ ባይ እኔ ባለሁበት ኣማሪካ ይኖራል ። እጅግ ብዙ ነገር ማድረግ የሚችል ኣቅም ያለው አማራ በየ ሃገሩ እንደሚኖር ኣውቃለሁ ። ትንታግ የሆኑ ፥ በሳል እና ብልህ አማሮች። ግን ደሞ ኣቅማቸውን የማያውቁ ፥ ከስብሰባ እና ጥናታዊ ፅሁፍ ከማቅረብ ውጪ እኔ እስከማውቀው ድረስ ኣንድ እርምጃ ወደፊት መራመድ ያልቻሉ መሆናቸውን ሳስብ ይገርመኛል። ነፃነት እና የኣማሪካ ህግ የተቀላቀለባቸው ተቆጪዎች በመሆናቸው ፥ ይቆጡና ግን መራመድ ይፈራሉ ፥ ይናደዱና ግን መተግበርን ይሰጋሉ ፥ ይበሳጩና ግን መሆንን ይሸሻሉ ። በመሆን እና ባለመሆን መሃከል የቆሙ ተቆርቋሪዎች ስለሆኑ ፥ ወገኖቻቸው ዛሬም ይደበደባሉ ፥ ይታሰራሉ ፥ ይታረዛሉ ፥ ይገደላሉ ። በመራመድ እና በመቆም መሃል ስላሉ ፥ ወገኖቻቸው እያለቁ ነው ። ይህም ፎቶ የነዚህ የኣማራ ልሂቃን ውሳኔ መዘግየት ውጤት ነው ። ሃያ ኣምስት ኣመት ለመራመድ የከበደን ፥ ሃያ ኣምስት ኣመት ቀና ለማለት የከበደን በውሳኔና በፈረንጅ ሃገር ህግ መሃል ስለቆምን ይመስለኛል ።
ኣማሪካንን ሳስብ የህግ ሃገር ነች ። የነፃነት ሃገር ነች ። የሰዎች መብት የሚከበርባት ሃገር ነች ። ይህ ሁሉ እውነት የሚሆነው ግን በመጀመሪያ ከማንም በላይ ለኣማሪካኖች እና ኣማሪካ ውስጥ ለሚኖሩ ህዝቦች ነው ። ኣማሪካ ከኣማሪካ ውጭ ሁል ጊዜ ልክ ነች ብዬ የማስብ እብድ ግን ኣይደለሁም ። ለምሳሌ ፕሬዝዳንት ኦባማ ኢትዮጵያ በሄደ ጊዜ የኢትዮጵያ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ነበር ሲል ተሰምቷል ። ምርጫው ፍትሃዊ ስለነበረ ነው ? ኣይደለም ! ኦባማ መረጃ ስለሌለው ነው ? ኣይደለም ! ዋነኛ ምክንያቱ ለኣማሪካ ልክ የሚሆነው ኣባባል ምርጫው ፍትሃዊ ነው የሚለው ኣባባል ብቻ ስለነበረ ነው ። ኣማሪካ ውስጥ ስኖር የኣማሪካን ህግ ኣክብሬ መኖር እሻለሁ ማለት የኣማሪካ መሪ የኢትዮጵያዊያኖች ስቃይ ቸል ብሎ ሲያልፈው እቀበላለሁ ማለት ኣይደለም ። ኣማሪካን ሃገር መስረቅ ያሳስራል ። ኦባማን መተቸት ግን ኣያሳስርም ። ለነፃነት መታገል ግን ኣያሳስርም ። ቢያሳስርም ታግዬ እታሰራለሁ እንጂ ፈርቼ ዝም ኣልልም ። ከዚ በባሰ እና በተወሳሰበ ደረጃ ባንድ ጎን ለኣማሪካ ህግ ተገዥ ለመሆን ኣስበን ፥ በልላ ጎን ደሞ የህዝባችን ስቃይ ኣስቆጭቶን ፥ ፍርሃት እና ውሳኔ ተጋጭቶብን ስለመቆማችን መካዳችን ይመስለኛል ለውጥ እንዳናመጣ ያደረገን ። የኣማሪካ ህግ ንፁሃን ዜጎች ይገደሉ የሚል ኣይመስለኝም ፥ የሚል ከሆነ ግን ኣላከብረውም ፥ የኣማሪካ ህግ የኣማሪካ መንግስት የተሳሳተ መረጃ እንዲናገር ፍቃድ ኣይሰጠውም፥ የሚሰጠው ከሆነ ግን በእንደዚህ ኣይነቱ ህግ ኣልገዛም ፥ የኣማሪካ ህግ ሰዎች በዘራቸው ተቆጥረው እና ተጠርተው ሲገደሉ በማየታችንን ይህንን ለማስቆም ማንኛውም ኣይነት ትግል ውስጥ ብንገባ እና ጉዳዩን እንደ ኣንድ መንግስት ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ ገዳዮቹን እያወደሰ « ምንም የተፈጠረ ነገር የለም !» ቢለኝ ፥ ኣሁንም እንዲህ ኣይነቱን ህግ ኣላከብርም ። እኔ በግሌ ህግ ከማይከበርበት ገነት ፥ በህግ የሚተዳደር ገሃነምን እመርጣለሁና።
ምን ለማለት ነው ፥ ኣማሮች የቱን ትመርጣላችሁ ? እንዲህ ብናደርግ ኣማሪካ እንዲህ ብታደርገንስ የሚለውን ፍርሃት ወይስ የማደርገው ነገር ህጋዊ ነው ፥ ለሰው ልጆች መብት የመቆም ትግል ነው ፥ የነፃነት ጥያቄ ነው በሚለው ላይ ኣምኖ ከፓናል ዲስኩር እና ከረባት ኣስተካክሎ ለማውራት ፥ ከመጨቃጨቅ እና ከመጠቋቆም ይልቅ ህዝባችሁን በቁርጠኝነት ከመከራ ለመታደግ ትግል መታገል ? ህዝቡ ትግል ይፈልጋል ፥ ህዝቡ እናንተን ያያል ፥ የህዝቡ በትረ ሙሴ ለመሆን ግን ፥ በማንነት እና በፍርሃት መሃል ከመቆም ነፃ መውጣት ያስፈልጋል ።
የኣማራ ደም በከንቱ ፈሶ ኣይቀርም !
ፎቶዎቹ ትናንት ሌሊት ከባህር ዳር ሆስፒታል የተገኙ ናቸው !
ሄኖክ የሺጥላ

No comments:

Post a Comment