Translate

Monday, March 14, 2016

ሶስት ሌ/ሎኔል ሁለት የ3ሻለቃ ማዕረግ ያላቸው መኮንኖች በወያኔ ወታደራዊ ደህንነት ተይዘው ከተወሰዱ በኋላ መድረሻቿው መጥፋቱ ታውቋል።


የወያኔ ቡድን መሪዎች ለስልጣናቸው ናቸው ብለው የሚጠረጥሯቸውን በሙሉ መግደል ማሰርና ማግለል የዘወትር ተግባራቸው ሲሆን በራሳቸው የጦር ኃይል ውስጥም ጦሩን ያሳምጻሉ ተብለው የጠረጠሩትን ሁሉ ከስብሰባና ከግምገማ አዳራሽ እየወሰዱ መዳረሻቸውን እየጠፉ መሆኑን ከወያኔ መከላከያ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለከታል። በዚህ መሠረት በወያኔ ሰሜን ዕዝ ውስጥ የከፍተኛ መኮንኖች ግምገማ ላይ ያነሱት ሃሳብ አመጽ ቀስቃሽ ነው፤ አፍራሽ ነው ብሄራቸው ተጠርጣሪ ነው በሚል ሶስት ሌ/ሎኔል ሁለት የ3ሻለቃ ማዕረግ ያላቸው መኮንኖች በወያኔ ወታደራዊ ደህንነት ተይዘው ከተወሰዱ በኋላ መድረሻቿው መጥፋቱ ታውቋል። ይህ በሰሜን ዕዝ የተፈጸመው ሁኔታ መረጃዎችና ወታደራዊ አዛዦችችን የበለጠ ስጋት ላይ ጥላችቸው። ተይዘው መዳረሻችው የጠፋ መኮንኖች ማንነትና ብሔራቸው ለጊዜው ያልታወቀ ሲሆን በርካታ የጦር አባላት ግን ሁኔታውን በቅርብ አየተከታተሉት መሆኑ ተገልጿል።

No comments:

Post a Comment