Translate

Monday, March 14, 2016

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ግዛቸው ምትኩ ከስራ ተሰናበተ

ዳኛ ግዛቸው ምትኩ ይባላል። ተወልዶ ያደገው ጎንደር ውስጥ ነው። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆኖ ለአመታት ሲያገለግል ቆይቷል። የህግ ትምህርቱን የተከታተለው በአለማያ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን የአቶ መላኩ ፋንታን እና የወዲ ገብረዋህድን የሙስና ክስ በዋና ዳኝነት ይዞት የነበረው እሱ ነው። በተለይም አቶ መላኩ ፋንታ የታሰረው ያለምንም የሙስና ወንጀል በአማራነቱ ብቻ መሆኑን የሚያምነው ዳኛ ግዛቸው ከሌሎች ዳኞች ጋር መስማማት አልቻለም ነበር። በዚህም የተነሳ ለባለፉት 6 ወራት ከስራ ታግዶ ከቆየ በኋላ በዚህ ሳምንት ሊሰናበት ችሏል።
ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው ዳኛው ከስራው ለመባረሩ ከቀረቡበት ክሶች መካከል የሚከተለው ይገኝበታል
‹‹ተከሳሽ ዳኛ በቡድን ውይይት ወቅት በአንዳንድ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የአንድ ብሔር አባላት የበላይነት የሚታይ መሆኑን፣ እንዲሁም አማራ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል አላግባብ እየተፈናቀለ መሆኑን ሲገልጹ ነበር፡፡ በውይይት ጊዜም ከሌሎች የአማራ ብሔር ተወላጆች ጋር አላግባብ የመወገንና የመቧደን እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበርና በአጠቃላይ ተከሳሹ እንደ ድርጊታቸው ሕገ መንግሥቱን የመቀበልና የማመን ነገር እንደማይታይባቸውና አመለካከታቸውን ለማስተካከልም ዝግጁ አለመሆናቸውን፤›”
እንግዲህ አማራ መሆን እና ስለ አማራ ህዝብ መብት መቆርቆር አማራ በብዛት ባለባት ሃገር ውስጥ እንደማይቻል የ”ህግ ተቋማት” ይህን የህግ ሰው በማባረር አፅድቀውታል።
እንደ ዳኛ ግዛቸው ያሉ ለህዝባቸው የሚቆረቆሩ የአማራ ልጆችን በበዙ ቁጥር ድላችን ይፋጠናል።
ወንድማችን ስለ አማራነት በድፍረት ስለተናገርክ እንኮራብሃለን! እናከብርሃለን! እስከመጨረሻው ድረስ መላው የአማራ ልጅ ከጎንህ ነው።

No comments:

Post a Comment