Translate

Monday, March 7, 2016

ምስራቅ ጎጃም ውጥረት ነግሷል!!

11041764_459898677512558_6207929217884897390_n
በኦሮሚያ የተነሳው ህዝባዊ ቁጣ ወልቃይት ጠገዴ ሀርማጮ ሁመራ በሰሜን ጎንደር የበረታው ትግል ጎጃም ደረሰ፡፡ በደብረ ማርቆስ ባህር ዳር አንዳች ነገር ሊፈዳ እያኮበኮበ መሆኑ እየተሰማ ነው፡፡ በርካታ ወጣቶች አፈሳና-ወከባ ቢደርስባቸውም እሱን ተቋቁመው ከነጻነት ትግል የትም አንርቅም እያሉ ይገኛል፡፡
የሸበል በረንታ አርሶ አደር ክፉኛ ተቆጥቶ ከስርዓቱ ቅልብ ወታደር ጋር ፍጥጫ ውስጥ ገብተዋል፡፡))) በጎጃም አሁን እንደከዚህ ቀደም አይደለም ሁኔታዎች ተቀይሯል ሲሉ ይናገራሉ፡፡ የጎጃም አርሶ አደር ጀግንነቱን በተግባር እያሳየ መሆኑ አገዛዙን አስጨንቆታል ህዝቡ በአንድ ድምጽ አሻፈረኝ በማለት ላይ ይገኛል፡፡ በሀገሪቱ የተቀጣጠለው ትግል ጎጃም ደረሶ በቃ,, እያለ ነው፡፡
 ብአዴን መድረሻ መውደቂያ ሲያሳጡት “ማንም ካድሬ እንደፈለገ ወደታች ወርዶ አርሶ አደሩን ሰብስቦ ማናገር አልቻለም፡፡ የብአዴን ሹማምንት በስድብ እየተዋረዱ ነው፡፡ በደብረ ማርቆስ ቀበሌ/03 የተደረገ የብአዴን ስብሰባ በውርደት እንደተጠናቀቀ ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡ በየወረዳው አሁን የካድሬ ትዛዝ ተቀበል ማለት ቀርቷል፡፡ በአርሶ አደሩና በካደሬው መካከል መተማመን ጠፍቷል፡፡ በምስራቅ ጎጃም ሁሉም ለማይቀው የነጻነት ትግል አምሮ ተነስቷል፡፡ የጎጃም ህዝብ መነሳሳት ስርዓቱ በመደናገጥ የሚይዘው ጠፍቶበታል፡፡ ስሞኑን ሸበል በረንታ የፈነዳው ቁጣ በሌሎችም አካባቢ እንደሚቀጣጠል ይጠበቃል፡፡ ሲሉ ነዋሪዎች ይናገራሉ በሌላ በኩል በባህር ዳር ዙሪያ የምትገኘው መራዊ ከተማ ትላንት የካቲት26/2008 ከምሽቱ 4:30 ጀምሮ በተኩስ ስትናጥ አምሽታለች መነሻቸው ከየት እንደሆነ ያልታወቀው መኪና መጡ በተባለ ታጣቂና ፖሊስ መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንዳለ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ አንዲት በአካባቢው ነዋሪ የሆነች ሴትን ጨምሮ 3 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ተሰምቷል፡፡

No comments:

Post a Comment