Translate

Monday, March 7, 2016

ደቡብ ኢትዮጵያ አዲሷ ዳርፉር

የኢትዮጵያ የደቡብ ክልል አይን ያወጣ ግፍ የሚፈጸምበት አዲሱ ዳርፉር እየሆነ ነው፡፡በተለይ ከወላይታ ጀምሮ እስከ ሱዳን ክልል ያለው ቦታ በየዕለቱ ለጆሮ የሚሰቀጥጡ ሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች እጅና እግር አውጥተው የሚታዩበት ቦታ ሆኗል፡፡
ይህ ምስልም ከክልሉ የተገኘ መሆኑን የክልሉን ፖሊሶችና ደቡብ ፖሊስ የሚል ጽሁፍ ያረፈባትን መኪና በማየት መረዳት ይቻላል፡፡
የሱርማ ተወላጆች መሬታችንን በኃይል አንለቅም በማለታቸው የፊጥኝ እየታሰሩ በደም እንደተለወሱ በገዛ ወገኖቻቸው ተወስደዋል፡፡
ምንም እንኳን የብሄራችን ተወላጆች ባይሆኑም ኢትዮጵያዊያን ከሁሉም በላይ ደግሞ ሰዎች በመሆናቸው ያሉበትን ስቃይ እንረዳላቸው፡፡
በደቡብ የቁጫ ተወላጆችም በደቡብ ህብረት ቀጭን ትዕዛዝ የማንነት ጥያቄ ባነሱ የአካባቢው ሽማግሌዎች፣ሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ላይ የግፍ መዓት ወርዷል፡፡የፌደራል መንግስቱም ዳንኤል ሺበሺን ያለ በደሉ ወህኒ በማውረድ የቁጫዎች ጩሕት በዳንኤል በኩል እንዳይሰማ አድርጓል፡፡
ኢትዮጵያዊ መሆን እልፍ ሲልም ሰው መሆን ወንጀልን ለመቃወም በቂ ነው፡፡ፈረንጆቹስ no one is free when others are oppressed ይሉ የለምን?
 

No comments:

Post a Comment