Translate

Tuesday, March 22, 2016

ሰሜን ጎንደር ውጥረቱ ከሯል:: ሕወሓት ራሱ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ ውጤት ዲቃላውን ብኣዴንን እየወነጀለ ነው::

ሕወሓት ራሱ በፈጠረው የጎሳ ፖለቲካ ውጤት ዲቃላውን ብኣዴንን እየወነጀለ ነው::
ሰሜን ጎንደር ውጥረቱ ከሯል::12243233_1699617866976076_4679020848657870642_n
12243233_1699617866976076_4679020848657870642_nሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ብሎ ራሱን የሚጠራው እና ታላቋን ትግራይ በመስፋፋት ካልመሰረትኩ ነጻ አውጪ የሚለውን ስሜን አልቀይርም በማለት በአማራ እና በአፋር ክልሎች የመስፋፋት እቅዱን ለመተግበር ሲሮጥ ከፍተኛ የሆነ እንቅፋት ከአማራው ሕዝብ ስለተጋረደበት ራሱ የፈጠረውን ዲቃላውን ኢሕዴን/ብኣዴንን መወንጀል መጀመሩ ከሕወሓት የገደል ማሚቱዎች የተገኙ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው::ሕወሓት ፊቱን ወደ ተላላኪዎቹ አዙሩ በምትካቸው ከሕወሓት ጉያ የተመለመሉ አማርኛ ተናጋሪ ሕወሓቶችን ለመተካት እየሮጠ ይገኛል::በሰሜን ጎንደር ተፈጥሮ የሚገኘው ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ አመጽ ወደ ግጭት የተቀየር ሲሆን ከጎንደር ከተማ ጀምሮ እስከ ዳንሻ ድረስ ሕዝቡ አስፈላጊውን የሕይወት መስዋትነት ለመክፈል ጥርሱን ነክሶ መሰሳቱ ታይቷል::

የሕወሓት የገደል ማሚቱዎች በጋራ እና በፍቅር የኖረን ሕዝብ በመለያየት ለማናከስ ያደረጉት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ መክሸፉን ካረጋገጡ በኋላ ብኣዴን የሚሉትን ድርጅት ማእከሉን አፍርሰው ዳግም ለመስራት ማቀዳቸው ታውቋል::ሕወሓቶች ብኣዴንን አፍርሰው ለመስራት ያቀዱት በአሁን ሰአት የያዙትን የግዛት ማስፋፋት እያደናቀፈብን ያለው ብኣዴን ነው ከሚል ድምዳሜ ላይ መድረሳቸው መሆኑ ታውቋል::ብኣዴን የቀድሞ አጼዎችን ስርኣት ዳግም ለመመለስ የሚለው የሕወሓት ኋላ ቀር እና ራስን ከሞቱ ስርኣቶች ጋር የማወዳደር ሱስ በያዝነው የሰለጠነ 21ኛው ክፍለዘመን ላይ አገርሽቶበታል::
ሕወሓት በዘር ጥላቻ የተሞሉ ካድሬዎቹን ቅርሻት ሲተፋ ያላወቀው ነገር ቢኖር የሕወሓትን የመስፋፋት ፖሊሲ ያማረረው የጠላው ሕዝቡ እንጂ ብኣዴን አለመሆኑን ነው::አሁን በስልጣን ላይ ያሉ የብኣዴን አመራሮችን ማርኛ ተናጋሪ በሆኑ የሕወሓት ካድሬዎች ለመተካት እና ካሰበው የመስፋፋት እቅድ ለመድረስ ብኣዴንን መወንጀሉ ሊያስደንቅ አይገባም ሲሉ የብኣዴን ሰዎች ይናገራሉ::የሕወሓት የግዛት የመስፋፋት እና ታላቋን ትግራይ የመፍጠር ሕልም እየተደናቀፈ ሲሆን የትግራይ ሕዝብ በራሱ የሕወሓትን አካሄድ እንደማይደግፈው ከአረና ፓርቲ አከባቢ የሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ::ሕወሓት በኢትዮጵያ ላይ የሚከተለው የጎሳ ፖለቲካ ከፍተኛ የሆነ አደጋ ጋርጦበታል::እንዲሁም በተጨማሪ የሕወሓትን አካሄድ ከከተማ እስከ ገጠር ያለው ሕዝብ ስለነቃበት ተቃውሞውን እያሰማበት ይገኛል::5901_980503108701290_7758757877225586348_n (1)
‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
5901_980503108701290_7758757877225586348_n (1)230369_981382735279994_9015726281602299769_n12119076_981382731946661_2790776424340746690_n

No comments:

Post a Comment