Translate

Wednesday, April 3, 2013

ሰበር ዜና – በዋልድባ ገዳማችን አይታረስም ያሉ ወጣቶች በአሸባሪነት ተከሰሱ


Waldeba“ሴቭ ዋልድባ” በሚል በዓለም አቀፍ ደረጃ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ስብሰብ ያጠናከረው ዘገባ እንደሚከተለው ይቀርባል። የአዲርቃይ ፍርድ ቤት ገዳማችን አይታረስም በማለታቸው ወጣቶችን በአሸባሪነት ከሰሰ በዛሬማ የሚገኙ ነዋሪዎች በወጣቶቹ ላይ ምስክርነት አንሰጥም በማለታቸው እንግልት እየደረሰባቸው ነው
የሰሜን ጎንደር ጸጥታ ክፍል ክሱ በአሸባሪነት መሆን አለበት በማለት ትዕዛዝ አስተላልፏል  የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከገዳሙ በረከት ለመቀበል የመጡት ማስፈራሪያ እና ፍተሻ (strip search) ተደረገባቸው የጣሊያኑ ኮንስትራክሽን ሌላ አማራጮችን እንፈልግ ብሏል የወልቃይት ነዋሪም እርሻውን እንዲቀጥል እስከሚመጣው ዓመት ምንም ነገር እንደማይኖር እየተነገረው ነው

የዛሬ ዓመት አካባቢ ይሆናል የዛሬማ ወጣቶች ከመንግሥት ጋር ገዳማችን አይታረስም፣ የአባቶቻችንን ድንበር አናስነካም በማለት ከመንግሥት ታጣቂዎች ጋር ግብግብ የተፈጠረው፥ በወቅቱ የክልሉ ባለሥልጣናት በቦታው ተገኝተው ከዛሬማ ነዋሪዎች ጋር ስብሰባ አድርገው የዛሬማን ነዋሪ ውሳኔ እንዲሰጥ እያስፈራሩ ባሉበት ወቅት ነበር ጥቂት ወጣቶች የአባቶቻችንን ድንበር አናስነካም፣ ገዳማችንንም ፈቅደን አናሳርስም በማለታቸው ጥቂቶቹን በወቅቱ ወደ እስር ቤት ሲከቷቸው የተቀሩት አምልጠው ጫካ ገብተው ገዳማችንን ማንም ሊነካውም፣ ሊደፍረው፣ ሊረግጠውም አይገባም በማለት ጥሪያቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል የአካባቢውንም ገበሬ ማኅበራት፣ የሃገር ሽማግሌዎችን በማነጋገር እንዴት ዓይናችን እያየ ገዳማችንን የማንም አማቄላውያን (አረማውያን) መፈንጫ ይሆናል፣ ይሄ ቦታ እኮ የቅዱሳን ማረፊያ፣ የግዑሳን መጠጊያ ለእኛ ለተዳደፍነው እረፍት፣ በረከት፣ ቅድስና ለማግኘት የምንሄድበት እንጂ እንዴት እነዜህ አረማውያን ዛሬ እንደፈለጉት ያደርጉታል በማለት ተቃውሟቸውን በከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ከሃገረ ስብከቱ ሃላፊዎች ቢያቀርቡም የተወሰኑ የመንግሥት ሃላፊዎች በሃገር ሽማግሌዎች ምከሯቸው እና ወደ ቤታቸው እና ቤተሰባቸው ይመለሱ በማለት አግባብተው ወደ ሃገራቸው እና ቤተሰባቸው ከተቀላቀሉ የሦስት ወይም ሁለት ወር አይበልጣቸውም ነበር።
የዋልድባ ገዳም አባቶች የድረሱልኝ ጥሪያቸውን ያሰማሉ
ወጣቶቹም ወደ ሃገራቸው እና ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደተመለሱ ብዙም ሳይቆይ የአዲርቃይ ከተማ አቃቤ ሕግ ቢሮ ደብዳቤ ከሰሜን ጎንደር የጸጥታው ቢሮ ይደርሰዋል በደብዳቤውም ላይ “ከዚህ በፊት ታስረስው እና በምሕረት የተመለሱት ወጣቶች በሙሉ በአሸባሪነት፣ በመንግሥት ላይ በመነሳት፣ እና ከግንቦት 7 ታጣቂዎች ጋር በመተባበር” በአስቸኳይ እንዲከሰሱ እና የፍርዱንም ሄደት እንደሚከታተሉት ጠቅሰው ደብዳቤ ይጽፋሉ። ደብዳቤ የደረሳቸው የአቃቢ ሕጉ ቤሮ ሰራተኞች ወደ ዛሬማ በመሄደ ከከተማው የመንግሥት ተወካዮች እና የጸጥታው ሃላፊዎች ጋር መመካከር ይጀምራሉ፥ የዛሬማ ከተማ መስተዳደር እና የጸጥታው ሃላፊዎች እንዴት ብለን ነው በአሸባሪነት የምንከሳቸው? በምን መረጃ ነው ብለው ሲጠይቁ ሰዎችን አስመስክሩባቸው በማለት የአቃቢ ሕጉ ሰራተኞች ቢጠይቁም ጥቂት የአካባቢው ነዋሪዎች ተጠርተው የምስክርነት ቃላቸውን እነሱ በሚፈልጉት መልኩ ከመሰከቱ ወሮታውን መንግሥት እንደሚሰጣቸው ቢያብሏቸውም “እኛ በልጆቻችን ላይ የሃሰት ምስክር ልንሆን አንችልም፣ የምናውቀው ነገር ቢኖር ገዳማችንን አትንኩ ማለታቸውን ነው በማለት እንቢታቸውን ገልጸዋል” የአካባቢው ነዋሪዎችም እንሰዛሬ ድረስ ሰዎችን እንዲህ እየደረጉ ነው ለካ በሃሰት እየከሰሱ ያሉት እነኝህ ወጣቶች ያደረጉት ነገር ቢኖር ገዳማችን አትንኩ ከማለት በስተቀር እንኳን አሸባሪ ሊሆኑ ጭራሽ እንዴት እንዲህ ዓይነት ክስ ሊመሰርትባቸው ይችላል በማለት ቅሬታቸውን ደጋግመው በማሰማት የአካባቢው የጸጥታ ቢሮ እና የአዲርቃይ የአቃቢ ሕግ ሰራተኞች ተመካክረው ወጣቶቹን በአሸባሪነት ቀርቶ በሌላ ክስ ሊመሰርቱባቸው ተስማምተው ነበር ጉዳዩ
በዛሬ የተቋጨው በቀጣዩ ሁለት ሳምንም ማለት መጋቢት ፲፮ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. በአዲርቃይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የዛሬማ ወጣቶች ለቤተክርስቲያናቸው፣ ለገዳመ ዋልድባ፣ እንዲሁም ለቅርስ እና ለሃገራቸው ሃብት በመቆርቆራቸው የተነሳ እንደዋንጀለኛ ተከሰው በፍርድ ቤት ቀርበው የአዲርቃይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
፩ኛ/ ወጣት ደስታው በ $3000.00 ብር እንዲቀጣ
፪ኛ/ ወጣት ደፋሩ ታከለ በ $2000.00
፫ኛ/ ወጣት ማሙሽ አሰፋ በ $800.00
፬ኛ/ ወጣት ስሙን ያላገኘነው በ $1800.00 ብር እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል
የዛሬማ ነዋሪዎች በውሳኔው በጣም እንዳዘኑ እና ወጣቶቹ ያለ ጥፋታቸው መከሰሳቸውን እንዲሁም እነዚህ ወጣቶች ላይ የተወሰነባቸው ብይንም ህገወጥ ውሳኔ ነው ብለዋል። እስከዛሬ ድረስ መንግሥት እነእከሌን በሽብርተኝነት ተከሰዋል፣ እከሌ እምነት በማጉደል ታስሯል፣ እነ እንቶኔ ሃገር በመክዳት የሞት ፍርድ ተፍርዶባቸዋል እያሉን ግራ የሚያጋቡን ሁሉ ውሸት በጠቅላላ የሐሰት ዘገባ እንደሆነ ተረድተናል ሲሉም ተደምጠዋል። በወጣቶቹ ላይ የተወሰነውንም ውሳኔ በጥብቅ ተቃውመውታል።
በተያየዘ ዜና ከተለያየ የጎንደር ከተማ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ወደ 70 የሚጠጉ ተማሪዎች በየዓመቱ እንደሚያደርጉት ወደዋልድባ ገዳም በመሄድ ከገዳሙ በረከት ለመቀበል፣ በዮርዳኖስ ጸበል ለመጠመቅ፣ እንዲሁም ከመጋቢት መድኅኒዓለም ዋዜማ ጀምሮ በገዳሙ ትልቅ ክብር ስለሆነ የዚህ በረከት ተካፋይ ለመሆን ጉዞ እንደሚያደርጉ ይታወሳል፥ ዘንድሮም እንደአምናው እነዚህን ተማሪዎች ታጣቂዎች ከመንገድ አስወጥተው ምን ልታደርጉ መጣችሁ በማለት ብዙ ማንገላታታቸውንም የደረሰን መረጃ ያሳያል፣ ተማሪዎቹንም የተጠየቁት ጥያቄዎች
ከአካባቢው ሃገረ ስብከት ደብዳቤ ይዛችኃል ወይ?
እናንተ ባለፈው ጎንደር ላይ አመጽ ልታስነሱ ስትሞክሩ የነበራችሁ ናቸሁ፥
ዘራችሁ ምንድነው? አማሮች ከሆናችሁ ወደ ትግራይ ክልል መግባት አትችሉም፥
የግንቦት 7 ቡድን ናችሁ፣ ደፈጣ ለማድረግ ነው የመጣችሁት።
ጸረ ልማት እና ጸረ ሰላም ናችሁ
በሚል ክስ ወደ በረሃ ወስደው አንድ ቀን ሙሉ ልብሳቸውን ሲበረብሩ፣ ሻንጣቸውን ሲፈትሹ ውለው እጅግ ብዙ እንግልት እና ድብደባም ደርሶባቸው በመጨረሻ ከአንድ ቀን ሙሉ እንግልት በኃላ ወደሚፈልጉበት እንዲሄዱ ፈቅደውላቸዋል፤ ተማሪዎቹም እኛ ከገዳማችን በረከት ለመቀበል የማንንም ፈቃድ አንጠይቅም፣ የሃገረ ስብከት ተወካዮችም ሂዱ ወይም አትሂዱ ሊሉን የሚችሉበት ስልጣን የላቸውም እንደ ክርስቲያን ቤተክርስቲያንን ለመሳም እና በረከት ለመቀበል ፈቃድ ልንጠይቅ አይገባም በማለት ቁጣቸውን ቢገልጹም ታጣቂዎቹ ብዙ ማስፈራራት እና እንግልት አንዳደረሱባቸው ለመረዳት ግለናል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ እስከ ዛሬ ድረስ በገዳሙ ክልል ሊገነባ የታሰበውን ግድብ (እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ውዝግብ ያስነሳው ግድብ) የኮንስትራክሽኑ ሃላፊ የሆነው የጣሊያን ኩባንያ ለመጨው ሁለት ወራት ስራውን በደንብ ጥናት እንዲያደርግ እና መልሱን ለባለሥልጣናቱ እንደሚያሳውቅ አስታወቀ። ባለፉት 13 ወራት በ4 የተለያዩ ኩባንያዎች ግንባታውን ለመሥራት ጥረት ሲያደረጉ መቆየታቸው ይታወቃል። ነገር ግን የሰው ሕይወት ከመጥፋት በስተቀር፣ ምንም አይነት ስራ መስራት ባለመቻላቸው ተስፋ መቁረጥ የሚታይባቸው የጣሊያን ኩባንያ ባለሥልጣናት ተጨማሪ የሆኑ ቦታዎችን ተመልክተው የቦታ ለውጥ ለማድረግም ጥያቄ እንደሚያቀርቡ ይገመታል። የጣሊያኑ ኩባንያ ከሕንዱ ኪባንያ ተቀብሎ ስራዎችን ለመሥራት ያደረገው የ4 ወራት ጥረት ምንም መስራት ባለመቻላቸው ከመንግሥት ባለሥልጣናት ነቀፋ ቢደርስባቸውም ቀን ከሌሊት ቢሰሩም በመድኅኒዓለም ጥበቅ ግድቡ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ መስራት ባለመቻሉ ተስፋ መቁረጥ፣ እልህ፣ እና በቀል የሚታይባቸው የስኳር ፋብሪካ ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር አቶ አባይ ጸሐዬ ተጨማሪ ወይም ተለዋጭ ሃሳቦችን ከጣሊያኑ ኩባንያ እንደሚቀበሉ አስታውቀዋል።
የወልቃይት ገበሬ ማኅበራት እና በፕሮጀክቱ ምክንያት ከአካባቢው ትፈናቀላላችሁ ተብለው በስጋት ላይ ነበሩት አርሶ አደሮችም ለጊዜው ኑሮአቸውን መቀጠል እንደሚችሉ እና እርሻም ማረስ እንደሚችሉ የክልሉ ባለሥልጣናት ሲናገሩ ሰንብተዋል፥ የክልሉ ነዋሪም እምነቱን በእግዚአብሔር አድርጎ የእለት ተእለት ኑሮውን ቀጥሏል ነገ ምን ሊመጣ እንደሚችል ስለማይታወቅ ሁልጊዜም ባጣዳፊ ትነሳለህ ቢባል እንኳ ዝግጁ ሆኖ የነገን ስለማያውቅ በዝግጅት ላይ ይገኛል። እርሻውንም ለማረስ ምንም አማራጭ ያጡት የወልቃይት ገበሬዎች “ነገ ተነሱ ብንባል ደግሞ፥ ለከርሞ ቤተሰባችንን የምናበላው የለንም” እንዴት እንሁን በማለት ምሬታቸውን አሰምተዋል አንዳንዶችም እጃቸውን ወደ ሰማይ በመዘርጋት “አንተ ታውቃለሃ” በማለት አቤቱታቸውን ለአምላካቸው አቅርበዋል።
እኛም ለቤተክርስቲያናችን ፍጹም ሰላምን፣ በክፋት እና በድፍረት በአባቶቻችን ላይ ግፍ እና በደል ለሚያደርሱት ልቦን እንዲሰጥልን እንመኛልን።
የጻድቁ አባታችን አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ በረከት ይደርብን፥
እግዚአብሔር አምላካችን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን፣ ቅድስት ሃገራችንን፣ ሕዝባችንን በረደኤት ይጠብቅልን!
Let’s save waldba! together ዋልድባ እንታደግ!
ዘ-ሐበሻ

No comments:

Post a Comment