Translate

Tuesday, April 23, 2013

ከእሁድ እስከ እሁድ


(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)

sidama


በሲዳማ ህዝብ እያመጸ ነው
ሚያዚያ 6 ቀን 2005 ዓ ም ኢህአዴግ ብቻውን ሊያካሂደው የነበረውን ምርጫ አንቀበልም በማለት ከተለያዩ ወረዳ በትስስር የተቃወሙ የሲዳማ ብሔረሰብ አባላት መታሰራቸውን የጎልጉል ምንጮች አስታውቀዋል። ምንጮቹ እንዳሉት በአካባቢው ከፍተኛ ድጋፍ ያለው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ከምርጫው ራሱን ማግለሉ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንዳገኘም አመልክተዋል።

በቀበሌ የመሰብሰቢያ አዳራሾች የታጎሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው የብሔረሰቡ አባላት እንዲፈቱ በሚጠይቁና በታጣቂ ሃይሎች መላከል የተካረረ ግጭት ይነሳል የሚል ፍርሃቻ እንደነበር ያመለከቱት ምንጮች የሲዳማ ተወላጆች የታጠቁ ስለሆነ ኢህአዴግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ አንጋቾችን ማሰማራቱን አመልክተዋል።
ለምርጫው አንድ ቀን ሲቀረው እጩዎቼ፣ ታዛቢዎቼና አባላቶቼ በእስር፣ በድብደባና ከሥራ በመባረር እየተንገላቱ ነው በማለት ራሱን ከምርጫው ያገለለው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ፤ ከምርጫው በኋላም እስሩና እንግልቱ መቀጠሉን ማስታወቃቸውን፣ በአንድ ሳምንት 26 አባላቱ እስር እንደተፈረደባቸው፣ በሲዳማ ዞን በየወረዳው ጊዜያዊ ፍርድ ቤቶችና ሸንጎዎች እየተቋቋሙ የፓርቲው እጩዎች፣ ታዛቢዎችና አባላት ከ400 ብር በላይ የገንዘብ ቅጣትና ከ3ወር እስከ አንድ ዓመት ከስድስት ወር የሚደርስ እስራት እየተፈረደባቸውና ፍርደኞቹ ወህኒ መውረዳቸውን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ የደርጅቱ ጉዳይ ሃላፊ ዶ/ር አየለ አሊቶ በመጥቀስ ኢሳት ዘግቧል። የኢህአዴግ አመራሮች ከሳሽም ፈራጅም በሆኑበት ሁኔታ ዜጎቻችን እየተንገላቱ ነው፤ ከምርጫው ብንወጣም ትግላችን ይቀጥላል ማለታቸውን የኢሳት ዘገባ ያስረዳል። (ፎቶ: worancha blogpost)
የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ታስረው ተፈቱ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን መፈናቀል ለማጣራት ወደ መተከል ዞን አቅንተው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ semayawiሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ የፓርቲው ም/ል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳና የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ በቃሉ አዳነ በቡለን ወረዳ ታስረው ተፈቱ። ኢሳት ሚያዚያ 12 ቀን 2005 ዓም እንደዘገበው አመራሮቹ የታሰሩት ከፌደራል፣ ከክልል መንግስትና ከዞን ባለስልጣናት ወደ ወረዳው ገብተው ሰዎችን ለማነጋገር የሚያስችል የፈቃድ ወረቀት ይዛችሁ አልመጣችሁም በሚል ነው። “ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ያለፈቃድ ሄዶ ከአንዳንድ ሰዎች ጋር ለመነጋገር አይቻልም፣ በዚያ ላይ እናንተ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ናችሁ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ኢ/ር ይልቃል፣ እንዲህ አይነት ስራ ለመስራት በቅድሚያ ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ ፈቃድ እንደሚያስፈልግ፣ ይህን አለማድረግ ደግሞ የብሄረሰቦችን የራስን በራስ የማስተዳደር መብት መናቅ ተደርጎ እንደሚታይ እንደተነገራቸው ኢ/ር ይልቃል ከእስር ተለቀው እየተመለሱ እያሉ ለኢሳት መናገራቸውን ዘገባው ያስረዳል።
በስፍራው ተገኝተው አንዳንድ ሰዎችን በማናገር ያዘጋጁት ቪዲዮ በወረዳው ባለስልጣናት ትዕዛዝ እንዲደመሰስ መደረጉን ኢንጂነሩ ተናግረው፣ ይሁን እንጅ በአይናቸው ያዩት፣ በጆሮዋቸው የሰሙት በቂ መረጃ እንደሰጣቸው ኢሳት በዘገባው አመልክቷል።
ታሪካዊ የሪፖርተር አንደበት
“ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የመክፈቻ ንግግራቸውን አድርገው ሲያበቁ፣ በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የተዘጋጀ የሟቹ ጠቅላይ azebሚኒስትር መለስ ዜናዊ የሕይወት ዘመን ትውስታ ከሕፃንነት እስከ ግባተ መሬት ድረስ የነበረውን ዘጋቢ ፊልም ሲታይ በታዳሚዎች ላይ የተደበላለቀ ስሜት ሲፈጠር ተስተውሏል፡፡ በተለይ በዘጋቢ ፊልሙ የአቶ መለስ አስከሬን ከቤልጂየም ብራሰልስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስና ቤተሰቦቻቸው ከአውሮፕላኑ ሲወርዱ፣ አስከሬኑ ከቦሌ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ቤተ መንግሥት ሲጓዝ፣ የቀብራቸው ዕለት በመስቀል አደባባይ አስከሬናቸውን የያዘው ሳጥን ሲቀመጥና ከፍተኛ ዝናብ እየጣለ አስከሬኑ በሰረገላ ሆኖ ወደ ቅድሥት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሲያመራ የሚያሳየውን ፊልም የተመለከቱ በአፍሪካ ኅብረት የታደሙ ሰዎች፣ ከንፈራቸውን ከመምጠጥ እስከ እንባ ማፍሰስ ድረስ በሐዘን ስሜት ውስጥ ገብተው ተስተውሏል፡፡ ሌላው አዳራሹን ለተወሰኑ ደቂቃዎች የሐዘን ድባብ ውስጥ የከተተ ክስተትም ተፈጥሮ ነበር፡፡ ዘጋቢ ፊልሙን ከሚመለከቱ ታዳሚዎች መካከል የነበሩት የአቶ መለስ እህቶች ድምፅ አውጥተው ለቅሶ በመጀመራቸው፣ ከሰባት ወራት በፊት የነበረውን የሐዘን ሁኔታ ያስታወሰና የሁሉንም ታዳሚዎች ቀልብ የሳበ ሆኖ ነበር፡፡”
ምንጭ፤ የሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋቢ ታምሩ ጽጌ “ከለቅሶ ቤት” እንደዘገበው (10 April 2013)
አርበኞች ግንባር ማርኬ ገደልኩ አለ
የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ልዩ ስሙ ሰቋር እና አምቦ ጠበል በተባለ ስፍራ  በሁለት ተከታታይ ቀናት ከአገዛዙ  የፈጥኖ ደራሽ ሃይል ጋር ባካሄደው  የፊት ለፊት ውጊያ ወታደራዊ የበላይነትን ስለመቀዳጀቱ ለጎልጉል በላከው መግለጫ አስታወቀ።
eppfግንባሩ ሚያዚያ 8 ቀን 2005 ዓ ም በወሰደው የማጥቃት እርምጃ ሃያ አንድ የአገዛዙ ወታደሮችን ግዳይ ማድረጉን፣ ሃያ አምስት ማቁሰሉን፣ በቀጣይ ቀን በዋልድባ አምቦ ጠበል በተባለው ቦታ በተከፈተ ውጊያ  ሃያ አምስት የአገዛዙ ወታደሮችን መግደሉንና ሰላሳ ዘጠኝ በማቁሰል ከፍተኛ ድል እንዳገኘ በመግለጫው አመልክቷል።
ግንባሩ ካደረሰው ሰብአዊ ጥቃት በተጨማሪ  የተለያዩ የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎችንም ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መማረኩን አስታውቋል። የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር አገኘሁ ስላለው ድልና ተቀዳጀሁት በሚል በይፋ የገለጸውን ዜና አስመልክቶ ከመንግስት በኩል እስካሁን በይፋ የተሰጠ መልስ የለም። ግንባሩም ቢሆን ሪፖርቱን በምስል አላስደገፈም።
የአውሮፓ ህብረት አቋም አልጠራም
የሰብአዊ መብት ማስከበር የህልውናችን ጉዳይ ነው
ከሰብአዊ መብት፣ ከፕሬስ ነጻነት፣ ዜጎች አመለካከታቸውን በነጻ የማራመድና የተፈጥሮ መብታቸው መገፈፉንና አጠቃላይ በአገሪቱ ውስጥ የሰፈነው አምባገነንነት አስጊ ደረጃ መድረሱን አስመልክቶ የአውሮፓ ህብረት የጠራ አቋም አለመያዙ ታውቋል። አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ በአውሮፓ የቀድሞውን ወዳጅነት አጥብቀው እንደሚቀጥሉበት ለማረጋገጥ አውሮፓን  የዞሩትን  የጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ  ጉብኝትን አስመልክቶ የጀርመን ሬዲዮ እንደዘገበው የአውሮፓ ህብረት ኢህአዴግን ከማድነቅ አልፎ የ30 ሚሊዮን ዶላር ርዳታeu መስጠቱን አመልክቷል። በሶማሊያ ስለተፈጠረው መረጋጋት፣ በደቡብ ሱዳን ጉዳይና በምስራቅ አፍሪቃ አጠቃላይ ጉዳይ ላይ መምከራቸውን ያወሳው ሬዲዮው፣ የህብረቱ ሊቀመንበር ማሳሰቢያ ቢጤ ማስተላለፋቸውን አመልክቷል።
በኢትዮጵያ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ያደነቁት የህብረቱ ሊቀመንበር፣ “ይህ ዕድገት ቀጣይነቱ ሊረጋገጥ የሚችለው ፣ የአገሪቱ ሕዝብ መሠረታዊ መብቶች፣ የመናገርና ሐሳብን የመግለጽ ነፃነቶች ሲከበሩ ብቻ ነው” ብለዋል። በጋራ በተዘጋጀው መግለጫ አቶ ሃይለማርያም “የሰብአዊ መብቶች መከበር ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው”  አያይዘውም “የመሬት ወረራ ብሎ ነገር የለም፣ ሊኖርም አይችልም፤ አንድም ጋዜጠኛ ሃሳቡን በመግለጹ አልታሰረም “ሲሉ የተለመደውን የመለስን ዓይነት መልስ በመመለስ 

No comments:

Post a Comment