Translate

Tuesday, April 9, 2013

“ህወሓት የአማራ ፖለቲከኞችን ከኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት ርዕዮተአለም እንዲወጡ ማድረግ ይፈልጋል”


ewew
ጃዋር መሀመድ የፖለቲካ ተንታኝ
ፍኖተ ነፃነት፡- ኢህአዴግ የብሔር ጥያቄ መልሻለሁ ይላል፤ ሆኖም ብሔርን መሰረት ያደረጉ በደሎች ሲፈፀሙ ይታያል፡፡ በርግጥ የብሔር ጥያቄ ተመልሷል ማለት ይቻላል?

ጃዋር፡- እንደምታውቀው የብሄር ጥያቄ ሁለት አይነት መልስ ነበር የሚያስፈልገው፡፡ አንደኛ እራስን በራስ የማስተዳደር፣ በራስ ባህል ላይ፣ በራስ አከባቢ ላይ ራስንችሎ ማስተዳደር ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የጋራ ሀገርን በጋራ ማስተዳደር፣ ማለትም እንደሀገር በጋራ ያፈሩትን በጋራ የመጠቀም፣ በጋራ ተካፍሎና ተቋድሶ መኖር ነው፡፡ ይህ ማለት የሀገሪቷን ኢኮኖሚ፣የሀገሪቷን ስልጣንና ባህላዊ እሴቶች በጋራ እያዋጡ በጋራ ተቋድሶ መኖር ማለት ነው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በርግጥ በተወሰነ ደረጃ ብሔሮች ክልላቸውን እንዲያስተዳድሩ ተደርጓል፤ ያም ቢሆን የተሟላ አይደለም፡፡
ምንም እንኳን የአካባቢው ሰው ሊቀመንበር፣ የወረዳ አስተዳዳሪ ይሁን እንጂ እውነተኛ ስልጣን የለውም፡፡ አንደኛ በህዝብ አይመረጥም፤ በእውነተኛ ምርጫ ስለማይመረጥ እውነተኛ የህዝብ ተወካይ አይደለም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ከተሾመም በኋላ ቢሆን ታአማኒነቱ ከላይ ስልጣን አፍነው ላሉት ለህወሐቶች ስለሆነ እውነተኛ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ለብሔሮች አልተሰጠም፡፡ ፈፅሞ ግን የሌለው በጋራ ተካፍሎና ተቋድሶ የመኖር (shared rule) የሚባለው ነው፡፡
እንደሚታወቀው ፌደራል መንግስቱ ሙሉ ለሙሉ በህወሐቶች ቁጥጥር ስር ነው፡፡ ወታደሩ ሙሉ ለሙሉ፣ ደህንነቱም እንደዛው፣ በኢኮኖሚውም፣ በውጪ ጉዳይ የአንድወገንና የአንድ ፓርቲ የበላይነት ያለስለሆነ የብሔር ጥያቄ ተደባብሶ፣ እንደውም ወደባሰ ሁኔታ እየገባ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
የፌደራል ስርአቱ ምንም እንኳን ለብሔሮች ባህላዊ አይነት መብቶችን ቢሰጥም እነዛን እሴቶች ራሳቸው በሚፈልጉበት መልኩ እንዳያሳድጉ የፖለቲካ ስልጣኑ ስላልተሰጣቸው፣ ማንነት እየከረረና እያደገ ሆኖም ግን እነዛ የማንነት መገለጫዎች በፖለቲካውና በኢኮኖሚው ውድድር ውስጥ ስለማይገቡ ለሀገራችን አደጋ እየጋረጠ ያለበት ሁኔታ ነው የሚታየኝ፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- በቅርቡ አማርኛ ተናጋሪዎችን የማፈናቀ ዘመቻ ተጀምሯል፤ ድርጊቱ ምን አይነት የፖለቲካ ቀውስ ሊያመጣ ይችላል?
ጃዋር፡- ወደ ትልቁ ሀገራዊ ጉዳይ ሳንገባ ግለሰቦቹ(ተፈናቃዮቹ) ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ማሰብ ያለብን ይመስለኛል፤ እንደምታውቀው በሀገራችን ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ውድነት አለ፣ እንኳን ያረሰውንና ቤቱ ያለውን እህል ጥሎ ወደ ሌላ ሀገር መሰደድ ይቅርና ሰዉ ልጆቹን መመገብ የተቸገረበት ሁኔታ እያለ፣ ሰውን ከቤቱ ማፈናቀል ዶፍ ዝናብ ባለበት ሁኔታ ሰውን ከቤቱ እንደማስወጣት ነው የሚታየኝ፡፡ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው መፈናቀል በጣም ያሳስበኛል፡፡
በጣም የሚያሳዝነውና አፅንኦት ሊሰጠው የሚገባው ይሄ ይመስለኛል፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- አማርኛ ተናጋሪዎችን የማፈናቀሉ አላማ ምን ሊሆን ይችላል?
ጃዋር፡-ይሄ ተግባር ለምን አላማ ተፈፀመ የሚለው፣ እንዳለመታደል ሆኖ ሀገራችን ላይ የሚመጡ መንግስታት ዜጎችን እንደሰዎች ሳይሆን ለፖለቲካ ስራ እንደተፈጠሩ ዕቃዎች ነው የሚያዩት፤ አሁን እያረጉ ያሉት ከደቡብና ከቤንሻንጉል ክልሎች ወደ ፊትም ከሌሎች ክልሎች በአማራ ተወላጆች ላይ የሚያደርጉት መፈናቀል የፖለቲካ አላማ እንዳለው ግልፅ ነው፡፡ አንደኛ በአማራውና በሌላው ብሔረሰብ መሀከል ተስማምቶና ተቻችሎ አብሮ ለዴሞክራሲና ለእኩልነት እንዳይሰራ በብሔሮች መሀከል ሁል ጊዜ መጠራጠር ግጭትና ቁጭት እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ ይሄ እንግዲህ ላለፉት 21 አመታት በደንብ ያየነው ጨዋታ ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ህወሐት የአማራውን ማህበረሰብ በመንካት የአማራ ፖለቲከኞችን ከኢትዮጵያዊ ብሔረተኝነት ርዕዮተአለም እንዲወጡ ማድረግ ይፈልጋል፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- ፌደራሊዝሙ ብሔር ላይ ያተኮረ መሆኑ ነው እንዲህ አይነቱ የዘር ማንነት ላይ ያተኮረ በደል እንዲፈፀም ያደረገው የሚሉ አስተያየቶች ይደመጣሉ
ጃዋር፡- ይሄ የኤትኒክ ፌደራሊዝም የፈጠረው ነገር አይመስለኝም፡፡ ኤትኒክ ፌደራሊዝሙ ችግር ፈጠረ ቢባል፣ የቤንሻንጉል ህዝብ ተነስቶአማራ ከክልላችን ይውጣ ብሎ ቢጠይቅ፣ በቤንሻንጉል ህዝብ ውስጥ ፀረ አማራ አመለካከት ቢድግ ኖሮና ህዝቡ አማራውን ከክልላችን ውጣ ቢለው የኤትኒክ ፌደራሊዝም ችግር ነው ትለዋለህ፤ ይሄ እኮ በፌደራል መንግስት ውሳኔ እተሰራ ያለ ስራ ነው፡፡
ቤንሻንጉል ሄደህ ተወላጆቹን ስለአማራ መፈናቀል ብት ጠይቃቸው አያውቁትም ልክ እንደኔና እንዳንተ ከሬዲዮ ነው የሚሰሙት፡፡ እኔ ወደ ስፍራው በመደወል ጉዳዩን ለማጣራት ሞክሬያለሁ፡፡ በርግጥ ፌደራሊዝሙ ሲቋቋም ምንም እንኳን የተወሰኑ ጥቅሞች ቢኖሩትም፣ ለህውሐት ህዝብን የመከፋፈል ሴራ እንዲያመች ተደርጎ መሆኑ ምንም ጥያቄ የለውም፡፡ ሆኖም ፌደራሊዝሙ ባይኖርም ይሄን ማድረግ ይችላል፡፡ በነገራችን ላይ ከህውሐት በፊት የነበሩትም መንግስታት ህዝብን እንደእቃ የመቁጠር ከሰሜን አንስቶ አማፂ ነው ወደ ሚሉት ወደ ደቡብ የማስፈር ነገር ነበራቸው፡፡
ለምሳሌ እንደቀድሞው እንደደርግ ቢሆን “ለምን ከጎንገር መጥተህ ጎጃም ገባህ” ብሎ መመለስ ማለትእኮ ነው፡፡ ፌደራሊዝሙን ባዋቀረው ህገመንግስት ውስጥ ማንኛውም ዜጋ በፈለገው ክልል ውስጥ እንደፈለገው መስራት እንደሚችል ይገልፃል፡፡ የእያንዳንዱ ክልል ህግም እንደዛ ነው የሚለው፡፡ አንድ ክልል ውስጥ ለመኖር የግድ የዛ ክልል ተወላጅ መሆን የለብህም፤ በየትኛውም ክልል ውስጥ መኖርና መስራት ትችላለህ፡፡
ስለዚህ ገዢዎቹ ሆነ ብለው ህዝብን ለማጋጨት ፣ህዝብን ለማሰቃየትና የፖለቲካ ባላንጣችን ናቸው የሚሏቸውን አካላት የሚያደርጉት ጨዋታ እንጂ ብዙም ከፌደራሊዝሙጋር የተያያዘ አይመስለኝም፡፡ ፌደራሊዝሙ ላይ ስናተኩር እርነተኛን የችግሩን ምንጭ እንዳናጣው እሰጋለሁ፤ እውነተኛው ምክንያት የገዢዎቹ ተንኮልና ደባ ነው፡፡
በታሪካዊ ሂደት አማራው በሁሉም ክልል አለ፤ ሆኖም እስከ አሁን የየክልሉ ህዝብ ተነስቶ አማራ ይውጣልኝ ሲል አላየሁም፡፡ ህወሐት የአማራን ህዝብ የሚነቅለውና የሚተነኩሰው ህዝቡ ጋር ለማጣላት ነው፡፡ ከዚህ በፊትም ሌላው ህዝብ ግጭት የነበረው በአማራው ህዝብ ስም ህዝብን ከሚጨቁኑ መንግስታት እንጂ ከአማራው ጋር አልነበረም፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- የማፈናቀል ዘመቻው በህዝቦች መካከል የሚፈጥረውን ችግር እንዴት ትገልፀዋለህ?
ጃዋር፡- እንግዲህ በአጭር ጊዜ ከመሀል ሀገር ርቀው በሚገኙ አካባቢዎች ባሉ ማህበረሰቦች መሀከል በፊት የነበሩትንና አዳዲስ ቁርሾዎችን ሊፈጥር እንደሚችል እሰጋለሁ፡፡ በከፍተኛ ደረጃ ግን እንደዛ ብሔሮችንና ማህበረሰቦችን በሃይማኖት ይሁን በብሔር እያጋጩ መሄድ ኢትዮጵያ ውስጥ እያለቀለት ያለ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ከዚህ በፊት ተደጋግሞ ያየነው ፊልም ነው፤ አንዱ ላይ ሲሰራ ቁጭብለን እናየው ነበር፤ እውነት ይመስለን ነበር፤ በኛም ላይ ሲደጋገምና ተደጋግሞ ስለቀረበ ሰዉ እንደዱሮው መታለል ያቆመበትና ለሚደርሰው የሰብአዊ መብት ጥሰትና ግፍ “የእከሌ ቡድን አደረሰው፣ የእከሌ ማህበረሰብ አደረሰው” ከማለት ባለፈ መንግስትን ተጠያቂ ወደ ማድረግ የገባበት ሂደት ያለ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ተመልከተው አሁን ቤንሻንጉል ውስጥ የክልሉ ሰው፣ የወረዳው ሰውና ገበሬው ነው ያፈናቀላቸው እንዳይባል፣ ፌደራል መንግስት ማስቆም ይችል ነበር፡፡ የማፈናቀል ተግባሩ ከተጀመረ አንስቶ ሁለት አመት የፈጀ ነው፤ ፌደራል መንግስት ስምምነት ባይኖር ኖሮ ይህን ማስቆም ይችል ነበር፡፡ አለማስቆሙም የሚያሳይህ ማፈናቀሉ የፌደራል መንግስቱ አላማ መሆኑን ነው፡፡ ህዝቡ የፌደራል መንግስት ድንቅ እጅና የህወሐት ሰዎች ሴራ እንደሆነ ገብቶታል፡፡ የቤንሻንጉል ሰዎችን ከመኮነን ይልቅ እውነተኛው ስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ተጠያቂ ወደ ማድረግ ገብቷል፡፡ በሙስሊሞቹም ደረጃ ብታየው በፊት በክርስቲያኑ ላይ እንዲያነጣጥሩ ስሞከር የነበረው፡፡ ሆኖም ጥፋተኛ የሆነው ማን እንደሆነ በግልፅ ታውቆ ሙሉ ለሙሉ በመንግስት ላይ ያነጣጠሩበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ይህ የሚያሳየን በሀገራችን የመብት ትግል ውስጥ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ነው፡፡ ከዚህ በፊት እርስ በርስ መፋጠጥ ነበር፤ አሁን ግን እውነተኛ ጨቋኝ በሆነው ስርአት ላይ ማፍጠጥ ተጀምሯል፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- መንግስት እየፈፀመ ያለውን የማፈናቀል ዘመቻ በተመለከተ ምን መደረግ አለበት?
ጃዋር፡- የአማራ ህብረተሰብ ሲነካ የአማራ ልሂቃን መናገራቸው ትክክል ነው፤ ግን ለእነሱ ብቻ መተው ያለበት ስራ አይደለም፤ አማራ ያልሆነ ዜጋም ሊቃወመው ይገባል፡፡ አንደኛ የማፈናቀሉ ተግባር የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው፤ ማንኛውም ሰው እንደዚህ አይነት ዘግናኝ ተግባር መቃወም አለበት፡፡ ሁለተኛ ደግሞ በሀገርና በህዝብ ላይ ሊያደርስ የሚችለውን አደጋ ሁሉንም ሊያዳርስ የሚችል ነው፡፡ ዛሬ አማራው ተጠቃ ነገ ሌላው ይጠቃል፡፡
ያም ብቻ ሳይሆን በአማራና በቤንሻንጉል ማህበረሰብ መሀከል ቁርሾ እየበዛ ከሄደ በእነሱ መሀከል የሚፈጠረው ግጭት በአካቢያቸው ያለው ሌላ ህብረተሰብ ላይም የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ ነው፡፡
እንደዚህ አይነት ተግባሮች መደገም የለባቸውም፡፡ ሶስተኛ ዛሬ አማራው ሲጎዳ ዝም ብለን የምናይ ከሆነ ሌላው ሲበደል ደግሞ አማራው ቁጭብሎ የሚያይበት ሁኔታ ስለሚኖር አደገኛ ሁኔታ ይኖራል፡፡
እንደውም አማራ ያልሆንን ልሂቃን ማፈናቀሉን በግንባር ቀደምትነት ወጥተን መቃወም ይገባናል፡፡ አማራው እኛ ከጎኑ እንዳለን ሲያውቅ እንደ ኢትዮጵያዊነትና እንደ ሰው ልጅነት በህዝቡ መካከል ያለው መተሳሰብና መፈቃቀር እየጨመረ ይሄዳል ብዬ ነው የማስበው፡፡ አማራ ያልሆነው ማህበረሰብ ለአማራው ድምፅ ሆኖ መውጣት አለበት፡፡ ኦሮሞው ሲጎዳ ኦሮሞው ብቻ የሚናገር ከሆነ፣ አማራው ሲጎሳ አማራው ብቻ የሚቃወም ከሆነ ሁላችንም በየፊናችን ተከፋፍለን የምንቀርበት ሁኔታ ነው የሚኖረው፡፡ ሀዲያ ሆንክ ከንባታ ሆንክ ሺናሻ ለዚህ ህዝብ መናገር አለብን፡፡ ይህ ሲባል ግን የአማራ ተወላጆችም በወገኖቻቸው ላይ በደረሰው ጥቃት መቆጣት መቃወም አለባቸው፤ ይሄ ተገቢ ነው ይህን በማድረጋቸው መኮነን የለባቸውም፡፡
ማህበራትም ሆኑ በጎፈቃደኛ ግለሰቦች እነዚህ የተፈናቀሉ ዜጎች መጉላላት እንዳይደርስባቸው የነብስ አድን ጥሪ በማድረግ ድጋፍ ሊያደርጉላቸው ይገባል፡፡
ወደ ቀድሞ ስፍራቸውም ሲመለሱ በተቻለ መጠን በፍጥነት እንዲቋቋሙ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ሌላው እንዲህ አይነት ወንጀል እንዳይደገም መንግስት ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ማድረግ አለብን፡፡
እንዲህ አይነቱ ወንጀል በሌላ ቦታም እንዳይደገም ለመፈናቀሉ እንዳይደገም ማድረግ የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡
በሌላ ደረጃ ግን በሰው ልጅ ላይ ያነጣጠረ ወንጀል እንዲቆም መንግስት ላይ ጫና ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- ከኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አንዱ የሆነውና አማራን እወክላለሁ የሚለው ብአዴን በአማርኛ ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን በደል በዝምታ መመልከቱ ምን ያሳያል?
ጃዋር፡- እውነቱን ለመናገር ብአዴንን ስታየው የአማራ ድርጅትም አይደለም፡፡
በተለይ የድርጅቱ ቱባ ባለስልጣናት የአማራ ተወላጆች አይደሉም፤ ከህወሐት ጋር በደምና በጥቅም የተሳሰሩ ናቸው፡፡
የአማራ ተወላጅ የሆኑትም እውነት የአማራን ህዝብ መብት ለማስከበር የሚችሉ፣ የህዝቡ ውክልና ያላቸው ሳይሆኑ ለእንጀራቸው እዛ ውስጥ ያሉ ናቸው፡፡ ብአዴን የአማራን ህዝብ ጥቅም ያስከብራል፣ የአማራ ህዝብ ይከላከላሉ ብሎ መጠበቅ ራስን ማታለል ይመስለኛል፡፡
የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ብሄር ድርጅት ይባሉ እንጂ እውነተኛ ስልጣን ላይ ላለው አካል አገልጋዮች ናቸው፡፡
ኢትዮጵያን እንደኩባንያ ከወሰድካት ህውሐት የኩባንያው ባለቤት ነው፡፡ እነብአዴንና ኦህዴድ የኩባንያው ሰራተኞች ናቸው፡፡ አይደለም እንወክለዋለን የሚሉትን ህዝብ መብት ሊያስከብሩ /እንደግለሰብ/የራሳቸውን መብትም ማስከበር የሚችሉ ድርጅቶች አይደሉም፡፡
በነገራችን ላይ ኦሮሚያ ውስጥ የሚፈፀም ብዙ ብዙ ግፍ አለ፤ በአሁኑ ወቅት ከ25 ሺህ በላይ የኦሮሞ ተወላጆች በየእስርቤቱ ይሰቃያሉ፡፡ ኦህዴድ አንድ ቀን፣አንድ ቀን ስለዚህ ተናግሮ አያውቅም፤ ታሳሪዎቹ በአካባቢያቸው የመዳኘት መብታቸው እንኳን አይከበርም፣ ፌደራል መንግስት ነው ጉዳያቸውን የሚያየው፤ ይህን አይነቱን ግልፅ ህገመንግስት ጥሰት ኦህዴድ እንቢ ማለት አይችልም ፤ ኦህዴድ ሳይችል አሁን ብአዴን ስለአማሮች መፈናቀል የሆነ ነገር ያደርጋል ብሎ መጠበቅ አይቻልም፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች እንወክለዋለን የሚሉትን ህዝብ አይወክሉትም፡፡ አንድ ድርጅት ህዝብን እወክላለሁ ሲል ከህዝቡ ውስጥ የወጣና የራሱ ኑሮ በህዝቡ ላይ የተንጠለጠለ ሲሆን ነው፡፡ እነዚህ ፓርቲዎችና በተለይ አመራሩ ከህዝቡ የወጡ አይደሉም፤ ህዝቡ አይደለም ስልጣን ላይ ያወጣቸው፣ ስልጣን ላይ ያወጣቸው ህወሐት ነው፡፡
ስለዚህ አገልግሎት የሚሰጡት፣ ተአማኒነታቸውም፣ የሚያስፈፅሙትም የህወሐትን ጥቅም ማስከበር ነው፡፡
ስለዚህ ብአዴኖች ከጉራፈርዳም ሆነ ዛሬ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ስለተፈናቀሉ የአማራ ተወላጆች አስመልክቶ በግል ሊቆጫቸው ይችላል፣ ግን አንድ እርምጃ እንወስዳለን ካሉ የህወሀትን ፖሊሲ መቃወም ነው የሚሆንባቸው፤ የህወሐትን ፖሊሲ መቃወም ደግሞ የራሳቸውን ማጋለጥ ስለሚሆን ሆዳቸውን እየቆጫቸውም ቢሆን ዝም የሚሉበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ አንዳንዶቹ ግን ቅድም እንዳልኩህ የአማራ ተወላጆችም ስላልሆኑ በደሉ ላይሰማቸውና ደንታም
እንደማይሰጣቸው ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከብአዴን መጠየቁ አግባብ ነው ሆኖም ከብአዴን መፍትሔ መጠበቅ አግባብ ያለው አይመስለኝም፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- መንግስት ዜጎችን እያፈናቀለ መሬታችንን ለባእዳን መሸጡ ምንአንድምታ አለው ?
ጃዋር፡- አሁን አማራ ላይ ያተኮሩበት የራሳቸው አላማ ስላላቸው ስለአማራው እናወራለን እንጂ ጋንቤላዎች፣ ቤንሻንጉሎች፣ ኦሮሞዎች ከመሬታቸው ላይ በሚሊዮኖች እየተፈናቀሉ መሬታቸው በርካሽ ለህንዶችና አረቦች እና ለተለያዩ ሀገርዜጎችና ኩባንያዎች እየተቸበቸበ ነው፡፡ ጋንቤላ ውስጥ የተሰራውን ዶክመንታሪ አይተኸዋል፤ ሌላው ሳጥቀር የኦሮሞ ባህላዊ ማዕከል የሆነውን ኦዳን ሳይቀር እየቀነቃቀሉት ነው፡፡ አንተካለህበት ወደ ቡራዩ ወደ ሰበታ ወጣ ስትል ህዝቡ የለም በሰላምጤፍ አምርቶ ይኖር የነበረው ማህበረሰብ ዛሬ የቀን ሰራተኛ ሆኖ ድንጋይ ይፈልጣል፡፡ ለምን ቢባል መሬቱን አፈናቅለው ሸጠው ብሩን ወደ ኪሳቸው ለመክተት፡፡ መንግስት በህገመንግስቱ መሬት የማስተዳደር እንጂ የመሸጥ መብት በህገመንግስቱ አልተሰጠውም፡፡ በጋንቤላና በተለያዩ ክልሎች የሚደረገው መሬት ጠመቸብቸብ ተግባር ህገወጥ ነው ፤ ለዛውም እጅግ በረከሰ ዋጋ ለነገሩ የኢትዮጵያ መንግስት ለዜጎች ደንታ የለውም ምክንያቱም በዜጎች የተመረጠ ስላልሆነ፡፡ በተለይ ይህን ስርአት ጠሚመሩት በግልፅ ሀብት ለማካበት ሌላውን ጠሚቦጠቡጡ ናቸው፡፡ በግልፅ ይሄን እያደረጉ ነው፡፡ አምና ለበአዶች መሬት የተቸረቸረውን ቁጭብለህ ብታሰላው ኢትዮጵያ በ50 አመት የምገኘውን የሀገራችን ገበሬዎች አስፈላጊው ግብአት ከቀረበላቸው በአንድ አመት ያስገቡታል፡፡ እነዚህ መሬት አጥተው የሚንከራተቱ ዜጎች በአግባቡ መሬት ቢሰጣቸውና በአመቺ ፖሊሲና ግብአት ቢደገፉ በአንድ አመት ሀገር የሚያሳድጉ ናቸው፡፡ ችግሩ ግን ስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ስለ ሀገር አይደለም የሚያስቡት፤ የኢኮኖሚ እድገት እያሉ ቁጥሩን ጨማምረው በዛው ኪሳቸውን የመሙላት ነው፡፡ ለነገሩ የሀገራችን ዜጎች ከአመት አመት ከድርቅ ካልተላቀቁና እርዳታ ከመንግስት እጅ የሚጠብቁ ከሆነ በህዝቡ ላይ አጠቃላይ ቁጥጥር ማድረግ ያስችላቸዋል፡፡ ስርአቱ ከአወቃቀሩም ዜጎችን የማስቸገር እንጂ ዜጎችን የመርዳት አላማ የለውም፡፡ መሬት ለበአዶች ከመቸብቸብ ዜጎች ከአንዱ ክልል ወደ ሌላ ክልል ሄደው የሚሰፍሩበትን መንገድ ተወያይቶ መቀየስ ይቻል ነበር፡፡
ሆኖም ዜጎችን ሳይዘጋጁበት ድንገት ማፈናቀሉ የራሱ የፖለቲካ አላማ አለው፡፡
ፍኖተ ነፃነት፡- ቀጣዩ ክፍል ሳምንት ይቀርባል

No comments:

Post a Comment