Translate

Friday, April 26, 2013

ህዝቡ በወያኔ ላይ ያለውን ምሬትና ጥላቻ መግለጽ ጀምሯል!



የኢትዮጵያ ህዝብ እውነተኛ ምርጫና የቀልድ ምርጫ ምን ማለት እንደ ሆነ ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆኑን በ1997 አም ባደረገው አለምን ባስደመመ ሂደት አስመስክርዋል::
ወያኔና ጀሌዎቹ ግን ዛሬም ሊማሩ አይችሉምና ደግመው ደጋግመው ህዝባችን ሊያሞኙት ይሻሉ በ2002 አ.ም ምርጫ ቦርድ ከሚባለው ሎሊያችው ጋር ሆነው ድምጹን ሰርቀውና አሰርቀው አሽንፍዋል አሽነፍን ብለው አይናቸውን በጨው አጠበው ጨፍር ብለው አደባባይ አስወጡት፤ በጥቃቅን ስም ባደራጁቸው እበላ ባዮች ታጅበውም በአደባባይ አላገጡ በህዝብ ቁስልም ላይ ጨው ነሰነሱ ህዝብም ታዝቦ ዝም አለ ዘንድሮስ?
ዘንድሮ የተለየው ነገር ተቃዋሚዎች ተባብረው 33 የሚሆኑት በአንድ ላይ ቆሙ ከምርጫው በፊት ጥያቄዎችን አንስተው እንደራደርም ብለው ጠየቁ ትእቢተኛው ወያኔም እንደልማዱ አሻፈርኝ የት ልትደርሱ አላቸው ትኩረታቸውን በሙሉ በየቤቱ እየዞሩ ካርድ እንዲወስድ ያስፈራሩት ጀመር የፈራ ወሰደ ያልፈራም ሳይወስድ ቀረ ይህንንም ህዝብ በትዝብት ተመለከተ ፤ካድሬዎቹም ሆነ አለቆቻቸው ወያኔዎች እሁንም ህዝቡን ንቀውታል ምን ያመጣል በሚል ትእቢት ከ99.6 % ወደ 100፥ በመለወጥ ለማሸነፍና ለመጨፈርና ለማስጨፈር ዝግጅታቸውን ማጠናቅቅ ላይ ብቻ አደረጉ።
ተቃዋሚዎችም በአንድ ድምጽ በመሆን የወያኔ የምርጫ አሻንጉሊት ሆነን ለእሱ ፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያ አንሆንም ብለው በውሳኔያቸው በመጽናታቸው ወያኔን በእጅጉ አበሳጭቶታል፤ ይሁን እንጅ አጨብጫቢ የሆኑ ፓርቲዎችን መፈለጉ ግን አልቀረም ለምርጫ ጨዋታው አዳማቂነት። የምርጫ ዴሞክራሲያዊነት ከሚለካበት አንዱና ዋናው ፤ ህዝብ የሚፈልጋቸውን መሪዎቹ ያለማንም አስገዳጅነት መርጦ እንደሚሾሙና እንደሚሽር ማመን ሲጀምር መሆኑ ዛሬም ሊዋጥላቸው አልቻለም። ይሁን እንጅ ህዝብ ዛሬ ሳይሆን ከ97 ምርጫ ጀምሮ ወያኔን በህዝብ ድምጽ ተሸንፎ እንደማይወርድ የተገነዘበው አሁን ላይ ሆኖ ሳይሆን ትላንት መሆኑን ወያኔዎች አልተረዱትም ቢረዱትም ለህዝብ ድምጽ ደንታ አልሰጣቸውም።

ስለዚህም የህዝብ የበላይነት ማረጋገጫ የሆነውን ምርጫ ሂደት ወደ ልጆች መጫዎቻነትና ማላገጫ በመቀየር መሬት ላይ የሌለውን ምርጫ በቲቢ ምርጫ እንዳለ ለማስመሰል በኢቲቪ ተወዳድሮ የማሸነፍ ምኞታቸውን መራጭ በሌለበት ምርጫ ለማሳየት ሞክረዋል። ይህም የማስመሰል እና የማጭበርበር አመላቸው ሱስ ሆንባቸው የውድቀታቸውን፣ የሽንፈታቸውን ጽዋ እየተጋቱ እልል ሲሉ ያሳዩናል “በቀሎ እያረረ ይስቃል እንዲሉ”።
የሀገሪቱን ዜጎች በደልና ጥቃት የፍትህ ስርአት የነጻነት ጥያቄ በማፈን የአማራውን መፈናቀል ያልዘገበ ሚዲያና ጋዜጠኞቹ፤ እውን ምርጫ ስላልሆነ ተውኔት የአለቆቻቸውንና የስልጣን ጥመኞችን ውሸት እውነት አድርጎ በማቅረብ አለቆቻቸውን ሲደስቷቸው ሌሎችን ደግሞ አሳዝኗል።
ሚዲያ በታፈነባት ሀገረ-ኢትዮጵያ እንደ ኢቲቪ ያሉ ያዩትን ሳይሆን በወያኔ የተነገሩትን፣ የተዘጋጀላቸውን ሀተታዊ ድራማ በሚዘግቡ፤ እውነታን በማይናገሩ ቡችሎች ስለምርጫ ሲዘምሩ ይታያሉ። ካድሬዎቻቸው እንኳ ወጥተው ባልተሳተፉበት መራጭ የሌለውን፤ ውጤቱ የዜሮዎች ድምር ዜሮ የሆነውን የምርጫ ድራማ ተውኔትና ውርደታቸውን ሲያሳዩ በአንጻሩ ህዝብ እየተፈናቀለ እያዩ እንዳላዩ በመሆን ለማስመሰያ ጭዋታ የሀገሪቱን ንብረትና ሀብት ያባክናሉ።
ይህን ሁሉ ፈተና አልፎና ተገድዶ የሄደው ህዝብም ቢሆን ያገኘውን እድል በመጠቀም ወያኔዎችን ውረዱ፣ በቃችሁ፣ወንጀለኞች ናችሁ፣ የፖለቲካና የሃይማኖት እስረኞችን ፍቱ እና ሌሎችንም የወያኔ ባዶነትን ለመግለጽ ባዶ ወረቀቶችን በመስጠት ጥላቻቸውን በድጋሜ አረጋግጠውላቸዋል። ግንቦት 7 ህዝቡ ያሳየውን እምባይነት እያደነቀ ነገር ግን የወያኔዎችን ጭቆና ተቋቁሞ ትግሉን ከዚህም በላይ በመውሰድ በየአካባቢው በማፋፋም መቀጠልና ነጻ አውጪዎችን ሳይጠብቅ በራሱ ጎበዝ አለቃዎች በመደራጀት አልገዛም ባይነቱን እንዲቀጥል ጥሪውን በዚህ አጋጣሚ ማስተላለፍ ይወዳል።
ንቅናቂያችን ዛሬም ትክክለኛና ህዝብ በነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ተሳትፎ የሚመርጠው አካል፣ እንዲሁም ለህዝብ ተጠያቂ የሆነና ህዝብን የሚፈራ መንግስት፣ በህዝብ የሚሾም፣ የሚሻር አካል ለመፍጠር በቅድሚያ ወያኔን በማስወገድ ብቻ ነው ብሎ ያምናል።
ነጻነትን ለማግኘት ዝም ብለን ስለተመኘነው የሚመጣ አይደለም፣ ዝም ብሎም በራሱ ታምር ሆኖ አይከሰትም፤ ሁሉም ዜጎች ከወያኔ የምርጫ ማጭበርበሪያ ካርድ ወጥተው ተደራጅተውና አደራጅተው በተናጥልም ሆነ በቡድን ወያኔን አስወግዶ በሀገራችን ሁሉም ዜጎች በእኩልነት ተከብረው የሁሉም መሰረታዊ መብቶች ባለቤት ሲሆኑ ነው።
ይህ የሚሆነው ደግሞ ወያኔ እንደ ምጽዋት እስጣችኋለሁ በሚለው መንገድ ሳይሆን ፣ ብቸኛው ምርጫ በሆነው ነጻነታችንን ለማስከበርና የሀገራችንን ህልውና ለመታደግ ማናቸውንም አይነት የትግል ስልቶችን ተጠቅመን ደማችንን አፍሰን አጥንታችንንም ከስክሰን በሚከፈል ዋጋ መሆኑን አምነን ትግሉን በማፋፋም በመሆኑ በተለይም ወጣቶች ትግሉን እንድትቀላቀሉን ጥሪያችን ይድረሳቹሁ እንላለን።
በዚህም አጋጣሚ ግንቦት 7 ለወያኔ አባላት የሚያስተላልፈው መልእክት በፍላጎታችሁ እና በምርጫችሁ የመስራትና የመኖር ሰብአዊ ነጻነታችሁ በወያኔ የፖለቲካ ፓርቲ አሽከር አደግዳጊና ጉዳይ ፈጻሚ በመሆን ብቻ የምታገኙት እርጥባን ሳይሆን በዜግነታችሁና በሰውነታችሁ የተሰጣችሁ መብት በመሆኑ ከፍርሃት ወጥታችሁ ንጹህ ህሊናን ተጥቅማችሁ ወያኔን በማስወገድ በሚደረገው ህዝባዊ ትግል ውስጥ ጊዜው ሳይይረፍድ ከታጋይ ሀይሎች ጋር በመቀላቀል የበኩላችሁን አስተዋጽኦ በማድረግ ኢትዮጵያዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

No comments:

Post a Comment