Translate

Saturday, April 27, 2013

ኢ-ፍትሃዊነትን አንዋጋለን የከፋፍለህ ግዛት አስተዳደርን አንቀይራለን በሩንም በሰላም አናንካካለን ካልከፈቱልን ገንጥለን አንገባለን

ተሜን ለቀቅ ፕሮፖጋንዳችሁን ጠበቅ
ጋዜጠኛም ሆነ የጥበብ ሰው
ንሴብህ እያለ ከደለቀ አታሞ
እውነት ስትጣራ ያልፋታል አርምሞ፡፡
ጋዜጠኛ ሲሆን የስርአቱ ቐሚ
እውነት ስትጣራ አታገኝም ሰሚ፡፡
ይህ ግጥም ታደለ ገድሌ ትንቅንቅ በሚለው የግጥም መድብሉ አውነት ስትጣራ በሚል ርዕስ የከተባት ነች፡፡ ግጥሙ የወቅቱን የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ቅልብጭ አድርጎ ይገልጸዋል ብየ ስላሰብኩ እንደ መግቢያ ለመጠቀም ወደድኩ፡፡ የጽሁፌ አላማ ወደ መቃብር እየተምዘገዘገ በመውረድ ላይ ስለሚገኘው የሀገራችን የጋዜጠኝነት ሙያ ሳይሆን ለሙያው ክብር ሲል ብቻ ከሰላሳ በላይ ክሶችን ተሸክሞ በመስራት ላይ ስላለው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የሚነሱ የስም ማጥፋት(ማጉደፍ)ዘመቻወችን መሞገት ነው፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪካ ካፈራቻቸው ድንቅ ድንቅ ወጣት ጸሀፍት መካከል የመጀመሪያውን ረድፍ ይይዛል(በኢህአዲግኛ አገላለጽ ግንባር ቀደም ነው እንደማለት)፡፡ተመስገን ፍትህ ብሎ በሰየማት ጋዜጣው ገጽ ሁለት ላይ አንድ በሉ ሲል በህወሀት መራሹ መንግስት እየተፈጸሙ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ሙስና ብልሹ አሰራርን ዘረኝነትን የወጣቶችን ስደት እና የሞራል ዝቅጠት የተቃዋሚ ፓረቲወችን የኤሊ ጉዞ ወዘተረፈ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት ባስኮመኮመን በሳል ብዕሩ የእድሜ አቻወቹን ብቻ ሳይሆን የያ ትውልድ አባላትን ጭምር እጅ ወደ ላይ ብሎ መማረክ የቻለ ተአምረኛ ነው፡፡በመደመም ስሜት እጃችን በአፋችን እንድንጭን ያደረገ ድንቅ የሀገር ባለውለታ ነው፡፡ተመስገን በተባ በዕሩ ፣በቃላት አጠቃቀሙና አሰዳደሩ፣በቐንቐ ችሎታው፣በታሪክ አዋቂነቱ፣ለሀገሩ ባለው ጥልቅ ፍቅር፣ለወገኑ ባለው ክብር አንቱታን ያተረፈ የብዕር ጀግና ነው፡፡ተሜ ምንም እንክዋን ፖለቲካና ኮረንቲ በሩቁ የሚለው ትውልድ አባል ቢሆንም ቅሉ ከድፍረቱ የተነሳ ኤይነኬ የተባሉትን ርዕሰ ጉዳዮች ሳይቀር በመረጃ በማስደገፍ በሚያቀርባቸው መጣጥፎቹ ተወዳጅነትን ብቻ ሳይሆን ለብዙ ወጣቶች አርአያ ለመሆን የበቃ ክስተት ነው፡፡
ተመስገን በቅርቡ እንዲህ ሲል ጻፈ፡፡እኔ ጋዜጠኛ ነኝ ለዲሞክራሲና ለመልካም አስተዳደር ጸልዩ ብየ ልመክር አልችልም፡፡ነገር ግን እልፍ ሆነን እንዘምር ዘንድ ድምጼን ከፍ አድርጌ አጠይቃለው፡፡
አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ
ይሄ ባንዲራ ያንተ አይደለም ወይ
ኢ-ፍትሃዊነትን አንዋጋለን የከፋፍለህ ግዛት አስተዳደርን አንቀይራለን በሩንም በሰላም አናንካካለን ካልከፈቱልን ገንጥለን አንገባለን የታሰሩትን አናስፈታለን…….እኔ ደግሞ እንዲህ አጨምራለው፡፡ሀገራችን ከነሙሉ ንብረትዋ እንረከባለን ወንጀለኞችን እናስራለን ያለ ጥፋታቸው የታሰሩትን እንፈታለን የተሰደዱትን ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ እናደርጋለን ለአርበኞቻችን ጣሊያን ድረስ የሚታይ መታሰቢያ እንገነባልን የ3000 ዘመን ታሪካችን ለአለም እናስተዋውቃለን ለአክሱም ሀውልት መገንባት የወላይታውን ድርሻ እንናገራለን ለጎንደር ስልጣኔ የኦረሞውን አስተዋጽኦ እንሰብካለን………..
ተመስገን ይሂን ስላለ ብቻ ነው እንግዲህ አንዴ በተላላኪነት ሌላ ጊዜ በተለጣፊነት የስም ማትፋት ዘመቻው የተከፈተበት፡፡የሚገርመው ደግሞ በነጻ ፕሬስ ስም የተደራጁትም ተባባሪ ብቻ ሳይሆን ፊት አውራሪ መሆናቸው ነው፡፡
ለማንኛውም የሰው ልጅ ሲፈጠር አላማ አለው፡፡ውድ ጊዜአችን ለተላላኪነት አጥፍተን መቸ የራሳችን ህይወት ልንኖር ነው፡፡ራስንም ብርሃኑ ደቦጭ እንዳው ወደ ቱቦነት ዝቅ ማድረግ ነው እላለው፡፡ ጀሮ ያለው መስማትን ይስማ!!!!!!!!!!!!!!
ማንም ይበለው ማን አላማችን መልክቱ ላይ በመሆኑ
ያለ ምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም!!!!!!!!!!
ሰላም Gashaw Mersha

No comments:

Post a Comment