Translate

Thursday, April 18, 2013

ተው ስማኝ


(የካናዳው ከበደ)

non-violence
ከቅኝ አገዛዝና ከሰብዓዊ መብት ረገጣ በሰላማዊ ትግል ‘ሰላም’ አግኝተዋል የሚባሉት አገሮች ሕንድ፤ አሜሪካና ደቡብ አፍሪካ ይመስሉኛል። የነዚሃን አገሮች ተመክሮ ወስደን፤ እነሱ በሄዱበት መንገድ ሄደን እንሱ ያገኙትን ሰላምና ነፃነት እናገኛለን ማለት ዘበት ይመስላል።
ከላይ በተጠቀሱት አገሮች የተደረገው ትግል ‘ከሰለጠነ’ ጠላት ጋር ነው። በጥቂቱም ቢሆን የሕግ የበላይነት ነበር። ለነፃነቱ የታገለው ሕዝብ በዘር፤ በቋንቋ፤ በቀለም፤ በሐይማኖት.. ወዘተ ቢለያይም አንድ-ወጥ የሆነ ራዕይ ነበረው። ያም ሆኖ የደቡብ አፍሪካው ANC አስፈላጊ የመሰለውን መንገድ ሁሉ የተጠቀመ ይመስለኛል። ሰላማዊ የሚባለው የትግል ዓይነት ሁልጊዜ ሰላማዊ መቋጫ ላይኖረውም ይችላል። ሕንድን ከእርስ በርስ ጦርነትና ከመገነጣጠል አላዳናትም።
ለነገሩ አገራችን የገጠማት ችግር ከማንም ጋር የሚመሳሰል አይደለም። መፍትሄውም እንደዚያው አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፤ ግን ከጥቃት ራስን መከላከል የተፈጥሮ ሕግ ነው።
ወያኔ ትናንት የሞተለት ዓላማ ነበረው፤ ዛሬ ደግሞ የሚሞትለት ሐብትና ንብረት አለው። በነ ስብሐት ነጋ ጭንቅላት ፈርሳ የተሠራች ኢትዮጵያን አያሳየን። አሜን!!

ተው ስማኝ አገሬ (ቁጥር አንድ)
ይሄ ‘ነፃ ትግል’ የምትሉት ነገር
ለማንም አልበጀ ከወያኔ በቀር
ሰው እየተገፋ
አገር እየጠፋ
አርባ ዓመት አምሣ ዓመት ‘በነፃ’ ታግላችሁ
ምንድን ለመሆን ነው አገር ከሌላችሁ?

No comments:

Post a Comment