Translate

Tuesday, April 21, 2015

“ሕገወጦቹ!”

“ሕገወጦቹ!”

balcha-and-eyasu


አይሲስ አሰቃቂ ግድያ የፈጸመባቸው ወገኖቻችን ቤተሰቦች መርዶ ሰምተው ሃዘን ተቀምጠው ባሉበት ወቅት ኢህአዴግና “የፌስቡክ የልማት አርበኛ ሚኒስትሮቹ” “ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እያጣራን፤ እስካሁን አላረጋገጥንም” እያሉ ያላግጡ ነበር፡፡

አዲስ አድማስ እንዲህ ይላል፡- “በአዲስ አበባ የኢያሱ ይኩኖአምላክ እና የባልቻ በለጠ ቤተሰቦች ድንገተኛ መርዶ የደረሳቸው እሁድ እለት ነው። በሰላሳዎቹ ዕድሜ ላይ የነበሩት ኢያሱና ባልቻ በአንድ ሰፈር ውስጥ ያደጉ ጎረቤታሞች ናቸው – በቀድሞው ወረዳ 21 ቀበሌ 25፤ በአሁኑ ወረዳ 10። የሟቾቹ ቤተሰቦች መኖሪያ ቤት አጠገብ ለአጠገብ ስለሆነ ለቅሶውም አንድ ላይነው፡፡
“ኢያሱና ባልቻ የዛሬ ሁለት ወር ገደማ ወደ ሊቢያ የሄዱት አንድ ላይ እንደሆነ የገለፀልን የኢያሱ ወንድም፤ የሊቢያውን የግድያ ወሬ የሰማው እሁድ ዕለት ነው – ስልክ ተደውሎ። የደወለለት ሰው፣ “የናንተ ሰፈር ልጆች ሊታረዱ ሲሉ የሚያሳይ ፎቶ በፌስቡክ ተለጥፏል” ብሎ ሲነግረው፤ በደንጋጤ “እነማን ናቸው?” ብሎ ጠየቀ። “የወንድሜን ስም ጨምሮ ነገረኝ፤ የወንድሜን ስም አያውቅም ነበር” ይላል የኢያሱ ወንድም።
“የኔ ፌስቡክ ስለማይሰራ ጓደኛዬ ጋር ሄጄ አየሁ። በደንብ ስላልታየኝ እንደገና ከምሽቱ አራት ሰዓት ስንከፍት ወንድሜን ተንበርክኮ አየሁት። ባልቻን ደግሞ ቀይ ቱታ ካደረጉት መሀል ለየሁት፡፡ ለእናቴ ከመንገሬ በፊት ለሩቅ ዘመዶች ለመናገር እያሰብኩ እያለ እነሱ ቀድመው ሰምተው ለቅሶ ላይ አገኘኋቸው” ብሏል የኢያሱ ወንድም።balcha-and-eyasu
“ኢያሱ ኳታር ሰርቶ የተወሰነ ገንዘብ ይዞ ስለመጣ የባልቻንም ወጪ ሸፍኖለት ነው አብረው የሄዱት። ከኢትዮጵያ ወጥተው በሱዳን ጉዞ የጀመሩት ከሁለት ወር በፊት ነው። “ሱዳን እያሉ በስልክ እንገናኝ ነበር። ገንዘብ ሲያስፈልጋቸው እልክላቸው ነበር” የሚለው የኢያሱ ወንድም፤ “ወደ ሊቢያ ከተሻገሩ በኋላ ግን ስልክ ቁጥር እሰጥሃለሁ ቢለኝም አንገናኝም ነበር” ብሏል።
ስም ለማውጣት፤ ቃላት ለመሰንጠቅና ለመቀመር አቻ የማይገኝለት ኢህአዴግ ለሙታንም ሃዘኔታ የለውም፡፡ “አደገኛ ቦዘኔ፣ አሸባሪ፣ ሕገመንግሥት የሚንዱ፣ የልማት ጸሮች፣ …” እያለ ስም የሚለጥፈው ሳያንሰው ሟቾችንም ህገወጥ እያለ ለመጥራት ምንም አይገደውም፡፡ ኢህአዴግ “እያለባማት” ያለችውን ኢትዮጵያ ጥለው ስለሄዱ “ህገወጥ” ናቸው፡፡ አውሮጳና አሜሪካ ደርሰው ግን “የውጭ ምንዛሪ” መላክ ሲጀምሩ “ዲያስፖራ”፣ “ባለሃብት”፣ “ኢንቨስተር”፣ “የልማት አጋር”፣ የሚለውን ስያሜ ይጎናጸፋሉ፡፡
the twoሰኞ ምሽት የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ላይ የቀረበው ኤርምያስ ዓለማየሁ አይሲስ ስለገደለው አጎቱ ባልቻ በለጠ ሲናገር እንዲህ ብሏል፡፡
“በአንድ አገር ስደት የሚመጣበትን መሠረታዊ ነገር መረዳት (ይገባል)፤ የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ነው እነዚህ ወገኖች የሄዱት፤ … መንግሥት ምንም ያመጣልናል ብለን አናስብም፤ … መንግሥት የመጀመሪያ ዜና ላይ አስተባብሏል፤ ኢትዮጵውያን መሆናቸውን አላረጋገጥንም ብሏል፤ መንግሥት ዕውቅና ሳይሰጥ የውጭ ጣቢያዎች ዕውቅና ሰጥተዋል፤ … ዛሬ በቪዲዮ ስለታየና ግልጽ የሆነ መረጃ ስለተገኘ እንጂ ብዙ ወንድሞቻችን ሄደው አልቀዋል፤ መንግሥት “ስደተኛ” አይላቸውም፤ “ተቸግረው” አይላቸውም “ህገወጥ” ነው የሚላቸው፤ ይህ ሊሰመርበት ይገባል፤ “ህገወጥ ስደተኞች ሞቱ” ብሎ ነው መንግሥት በተደጋጋሚ የሚዘግበው፤ “ሕገወጥ” የሚለው ቃል ለዚያ ነገር ያለውን አመለካከት በግልጽ የሚያሳይ ነው፤ ወንድሞቻችንን ከዚህ የሄዱት ደልቷቸው አይደለም። ተቸግረው ነው። መንግስት ወንድሞቻችንን ስደተኛ ለማለት እንኳን አይፈልግም። ከመንግሥት ምንም (የምንጠብቀውና) የምንፈልገው ነገር የለም”፡፡ (የኢያሱና ባልቻ ፎቶ ከአዲስ አድማስ የተወሰደ)

No comments:

Post a Comment