Translate

Thursday, April 2, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በደህንነቶች የአሜሪካ ጉዟቸው ታገደ፣ ሻንጣቸው ግን ወደ አሜሪካ ተጉዟል

ይድነቃቸው ከበደ (አዲስ አበባ)
Eng. Yilkal Getnet, Chairman of the Blue Partyህጋዊ የጉዞ ሠንድ በአግብቡ እንደተሟላ አየር መንገዱ አረጋጧል፡፡ ይሁን እንጂ የወያኔ እንባ ጠበቃ ነጭ ለባሾች አማካኝነት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከአገር እንዳይወጣ ተከልክሏል፡፡ የሰጡትም ምንም ዓይነት ሕጋዊ ምክንያት የለም፤ ያሉት ነገር ቢኖር “እርሶዎ ከአገር እንዳይወጡ ትእዛዝ ተሰጥቶናል፣ ነገ ጠዋት 2፡30 ኢሚግሬሽን ይምጡ!” ከማለት በስተቀር፡፡ በኢ/ር ይልቃል ላይ እንዲህ አይነቱ የውንብድና ተግባር ሲፈፀምባቸው ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡
ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት
ኢ/ር ይልቃል ለጉዞ ያዘጋጁት ሻንጣ አስፈላጊው ፍተሻ ከተደረገ በኋላ አውሮፕላን ላይ የተጫነ ሲሆን፣ የሻንጣው ባለቤት የሆኑት ኢ/ር ይልቃል ወደ አሜሪካ መጓዝ ተከልክለው ሻንጣቸው ብቻ ከአገር እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

ገዥው መንግስት ከቦታ ወደ ቦታ የመዘዋወር አለም አቀፍ እንዲሁም ህገመንግስታዊ መብት ፣ ያለምንም ሕጋዊ መክንያት መገደቡ የወያኔ መንግሰትን አምባገነንነት ፍንትው አድርጎ የሚያሣይ ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ መንግስታዊ ውንብድና የያዝነውን ትግል የበለጠ አጠንክረን እንድንቀጥል ተጨማሪ ሃይል እንደመሆኑ መጠን በትግላችን የምናመጣውን ውጤት ያፋጥናል፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !

No comments:

Post a Comment