Translate

Friday, April 24, 2015

ብሄራዊ ሃዘንን ወደ ብሄራዊ እምቢተኝነት

በያዝነው ሰሞን የሚሰሙ ዜናዎች፣የሚታዩ ምስሎች፣የሚደመጡ የሲቃ ድምጾች አጥንት ድረስ የሚዘልቁ ብሄራዊ ቁስል ሆነውብናል። ፳፬ ዓመት በኢትዮጵያውያን ጀርባ የተሰበቀውን ፍላጻን በመሸሽ ስደትን እንደ አማራጭ የወሰዱ ወጣቶች የዓሳ ነባሪ የዕለት ከዕለት ቀለብ ሆነዋል፣ የደቡብ አፍሪካን ጫካዎች ሲያቋርጡ በአውሬ ተቆርጥመዋል፣ከሰባራ ጀልባና ከመንገድ ቀማኛ የተረፉት ባካባቢ አገራት ለመድረስ የቻሉትም በጎማና በቤንዚን ከነህይወታቸው ተቃጥለዋል በማጅራታቸውም ታርደዋል።addis ababa protest18
የዋሽንግተን እና አካባቢው የጋራ ግብረሃይል ባጠቃላይ ኢትዮጵያ ሆይ ፈጣሪ ያጽናሽ፤ ኢትዮጵያ ሆይ የልጆችሽ ደም ለአገር ተንሳዔ ያድርግልሽ ከማለት ሌላ ቋንቋ የለንም። ሐዘናችንን ስንገልጽ ግን ነገ የሚወጣውን የነጻነት ብርሀን ከቅርብ ርቀት በተስፋ እያየነው ነው። የኢትዮጵያ ወጣት ሆይ …
ዘረኝነትን ሸሽተህ ወደ ተሳለው ካራ ወደ እሚንቀለቀለው እሳት፣ እሚሰምጠው ጀልባ ላይ ከመሳፈር ነጻነት ያሳጣህን አረመኔ ዘረኛ ስርዓት እዛው በአገርህ ሜዳ ተናንቀህ ጥለህና ወድቀህ ነጻነትህን ብታውጅ የስደት እና የውርደት ምንጭ የሆነውን ከምንጩ ታደርቀዋለህ። መደራጀትም ምትሐት አይደለም ከየአካባቢህ የጎበዝ አለቃ መምረጥና መናበብ እንደሚቻል ጠንቅቀህ እወቅ። የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ …

ኢትዮጵያዊነት ፈተና ላይ ወድቋል ለበርካታ አመታት የዘለቀው መከራችን ዛሬ ላይ ደርሧል፤ ከሰሞኑ አይሲስ በተባለ ሰይጣናዊ ስራ የተቀሉ ወገኖቻችን አይሲስን እንጂ እስልምናን እንደማይወክል ተረድተህ ወያኔ ይህንን ሁናቴ ስልጣን ማራዘሚያ ለመጠቀም በኢትዮጵያ ሙስሊሞች እና ክርስቲያኖች መካከል ሊያጫጭሰው የሚፈልገውን ሴራ እንደጥንቱ ብልሃት አንድነትሕን አጥብቀህ በንቃት፣ በጋራ ትቋቋመዋለህ የሚል የጸና እምነት አለን።
የዋሽንግተን ዲሲ የጋራ ግብረ ሃይል!
dcjointtaskforce@gmail.com
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም በነጻነት ትኖራለች !!!

No comments:

Post a Comment