Translate

Wednesday, November 12, 2014

ሰለ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ፤ ለሰማዩ አምላኬ ጸሎት አደርሳለሁ…!

10484897_675825339202040_7611881303839978882_nሰለ ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ለሰማዩ አምላኬ ጸሎት አደርሳለሁ…!
ሰማያዊ ፓርቲ እና ሌሎች ዘጠኝ ፓርቲዎ በመተባበር ”ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ” በሚል ቀጣዩ ምርጫ ነጻ እንዲሆን ምርጫው ብቻም ሳይሆን በኢትዮጵያ ምድር የሰው ልጆች ነጻ እንዲሆኑ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ከህዝብ ጋር በመሆን ድምጻቸውን ሊያሰሙ የክንውን ቅደም ተከትሉን በቅርቡ ይፋ አድርገዋል። ይደረጋሉ ተብለው ከሚጠበቁት የሰላማዊ ተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ትልቁ መርሃ ግብር የሚሆነው ህዳር ሃያ ሰባት እና ሃያ ስምንት ሊደረግ የታሰበው የሃያ አራት ሰዓታት /የአዳር/ የአደባባይ ተቃውሞ ነው።
ከእርሱ በፊትም የፊታችን እሁድ በአዋሬ ቤልኤር ኳስ ሜዳ ላይ ከሚደረገው የአደባባይ ሰብሰባ በፊትም በጥቅሉ ከሁሉም መርሃ ግብሮች በፊት እነ ሰማያዊ ሁላችንም በየእምነታችን ለሰማዩ አምላክ ”አደራ ጎፍታ” ብለን እንድንጸልይ ጠይቀውናል… ታድያ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ለአደባባይ ተቃውሞውም ሆነ ለስብሰባው መድረስ ባልችል እንኳ እንደሚከተለው ለምን አልጸልይም… ብዬ አስብኩ…
አደራህን ጎፍታ
አደራህን ጌታ
ከባለ ሰይፎቹ ፊት

ሰልፍ ልንወጣ ነው ጥበቃህ ይበርታ
ብዙ ስንቅ ብዙ ትጥቅ እጅግ ያደራጁ
በስልጣን ወንበር ላይ ጎልምሰው ያረጁ
ስልጣን ብርጭቆ ውስጥ ስኳር በዝቶባቸው
እጅጉን ጣፍጧቸው
ስልጣን ብርጭቆ ውስጥ ብቅል በስቶባቸው
እጅግ አስክሯቸው
ቢጠጡት ቢጠጡት አልበቃም ያላቸው…
ምን ያደርጉን እንደሁ አናውቀውምና
ለኛም ብርታት ስጠን ለነርሱም ልቦና
አደራህን ጎፍታ
አደራህን ጌታ
ከባለ ሰይፎች ፊት
ሰልፍ ልንወጣ ነው ጥበቃህ ይበርታ….
(ይቺን ነገር፤ የግጥምን አድባር ተለማምነን ካረዘምናት እና ተስፋ ሰጪ ሆና ከተገኘች በሌላም መስኮት ይዘናት እንከሰት ይሆናል…!)

No comments:

Post a Comment