Translate

Saturday, November 24, 2012

የ አዲስ አበባ ባቡር ዝርጋታ ዲዛይኑ ካልተስተካከለ አደጋው ለቻይናም ይተርፋል(China Railway Eryuan Engineering Group Co. Ltd. (CREEC) from CSR point of view)

 አሁኑ አለም ቻይና የገባችበትን ፕሮጀክት ነቁጥየሚፈልጉ እና ሃያ አራት ሰዓት የሚሰሩ ሚድያዎች ምዕራቡ ዓለም መኖራቸውን  ኢትዮጵያ መንግስትመዘንጋት የለበትም። ቻይና  አፕል ኮምፑተር ምርት ጋርየገባችውን ውዝግብ መርሳት አይገባም
  • ባለንበት ዘመን ካምፓኒዎች  ህብረተሰባዊ ኃላፊነት(Corporate Social Responsibility-CSR) መላው አለም በሚለኩበት ዘመን ቻይናዎች የነገ  ሌላ አፍሪካ ሀገር ፕሮጀክት ዕድላቸውን የሚያበላሹላይሆኑ ይችላሉ
  • '' ሕብረተሰብ ጉዳቶች (ስለ መንገድ ፕሮጀክት ነው ከላይፅሁፉ የሚያብራራው ሁለት ደረጃዎች  ግንዛቤውስጥ ይገባሉ:- የመጀመርያው  ፕሮጀክቱ  ዲዛይንደረጃ ሲሆን ሁለተኛው  ልማት ዕቅዱ ትርጉም ላይ ነው።

 
ዛሬ  አዲስ አበባ የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት  ሰማአቱ  አቡነጴጥሮስን ሃውልት ይነሳል ቢባልም መንግስት  ቦታው እመልሳለሁ የሚል መልክት   መንግስታዊ የመገናኛ ብዙሃንም ጭምር እየተነገረ ነው። እስኪጉዳዩን  ፕሮጀክት አስራር በኩል ያለውን አንደምታ አንድ ሁለት ልበል።
አንድ ሃውልት ሲተከል እንዲነሳ ተደርጎ አይደለም  በጣም ጥብቅ ሆኖእንደሚሰራ የታወቀ ነው።ሃውልቱን ለማንሳት ብሎን እንደመፍታት ቀላልአለመሆኑን ነገር ግን  ስር መገዝገዝ እና መቁረጥ እንደሚያስፈልግለማወቅ መሃንዲስ መሆንን አይጠይቅም። 
ይህ ማለት ሃውልቱን ለመንቀል ወጪ ይፈልጋል ማለት ነው (በዶዘርእንደማይፈርስ ስለሚታሰብ )
እዚህ ላይ  ፕሮጀክቱን ወጪ ሂሳብ  ቀላል አስተሳሰብ (logic)እንመዝነው  እርግጥ ነው  ፕሮጀክትን ወጪ  ምሳሌ መገምገምአይቻልም።ዝርዝር መረጃን ስለሚፈልግ።  እዝያ በፊት ግን ማንኛውም ልማት ፕሮጀክት ማሟላት የሚገባው ቢያንስ ሶስት አይነት ግምገማዎችንእንደሚያደርግ ይታወቃል  ይህ ማለት  ባቡር ዝርጋታው ፕሮጀክት ሶስት ዋና የመለክያ ነጥቦች አንፃር ተገምግሞ እንደሚፀድቅ የታወቀነው።እነርሱም:-
 ወጪ-ገቢ ትንተና (cost-benefit Analysis):-  ባቡር ግንባታየሚወጣው ወጪ ከሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ጋር በማነፃፀር።
 አካባቢ ተፅኖ ዳሰሳ (Environmental Impact Assessment -EIA):-ፕሮጀክቱ  አካባቢያዊ ሁኔታዎች ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ተፅኖየሚለካበት እና
   /  ሕብረተሰብ ጥቅምና ጉዳት ትንተና (Social cost-benefit Analysis):-ፕሮጀክቱ  ማህበረሰቡ  ጤና፣የ ገቢ ፣ባህላዊ ፣ታሪካዊ እናሃይማኖታዊ እሴቱ ላይ የሚፈጥረው በጎ ያልሆነ ተፅኖ ሁሉ ያጠቃልላል።

ሐውልቱን መንቀል ዲዛይኑን ከማስተካከል የበለጠ ወጪአለው። 

የሃውልቱ መነቀል  ከላይ ከተጠቀሱት ወጪዎች አንፃር ሁሉም  እዚህፕሮጀክት ላይ የሚወድቁ ወጪዎች መሆናቸውን ለመረዳት በጣም ቀላልነው። ሃውልቱን ከመንቀል ይልቅ ዲዛይኑን ማስተካከል ( ትንሽ እርቀትባቡሩ እንዲያልፍ በማድረግ አዋጪ መሆኑን ለመረዳት ሃውልቱንመንቀል  ሁለት አይነት ወጪ እንደሚዳርግ መረዳት የግድይላል።እነርሱም:-
1/  ገንዘብ ወጪ(ቀጥተኛ ወጪ) ለዲዛይን ማስተካከያ ከመክፈል ሃውልት መንቀያ የሚያወጣው ገንዘብ ከፍተኛ እንደሚሆን ይገመታል።ለምን?።ሀውልቱ  እንዳይላላጥ እና እንዳይሰበር  አነቃቀል እስከማንቀሳቀስ ድረስ ኃላፊነት ሲወሰድ  መንቀል ፣የማንቀሳቀስ ሥራ እና  እዚህ ሁሉ  ዋስትና ክፍያውን ስናስበው ዲዛይኑን ከመቀየር ጋር ሊወዳደር አይችልም  በሐውልቱ መነሳት ላይ የሚከተለውን ሁለተኛወጪ ስንመለከት ደግሞ ዲዛይን መቀየር አዋጭ መሆኑን እንረዳለን 
2/  ሕብረተሰብ ጉዳት (Social-cost)-
ከላይ እንደጠቀሰው ''  ሕብረተሰብ ጥቅምና ጉዳት ትንተና'' (Social cost-benefit Analysis ) ቀጥተኛ ያልሆነ ወጪ ነገር ግን ጉዳቱ ብዙጊዜ ከፍተኛ ችግር የመፍጠር አቅም ያለው ነው። ይሄውም ፕሮጀክቱ ማህበረሰቡ  ጤና፣የ ገቢ ፣የ አካባቢ ብክለት ፣ባህላዊ ፣ታሪካዊ እናሃይማኖታዊ እሴቱ ላይ የሚፈጥረው በጎ ያልሆነ ተፅኖ ሁሉ መኖርአለመኖሩ የሚለካበት የልማት ፕሮጀክት መለክያ መንገድ ነው። ይህምበማንኛውም  ልማት ፕሮጀክቶች ላይ ፕሮጀክቱ ከመፅደቁ በፊት በሰፊውየሚተነተን መሆኑ ይታወቃል። አንድ የልማት ፕሮጀክት  ገንዘብወጪ-ገቢ (cost-benefit analysis) አንፃር ብቻ የሚለካበት ጊዜአልፏል። በተለይ በአሁኑ አለም ማንኛውም ፕሮጀክት ጤናማ የሚያሰኘውጥሩ የሆነ  አካባቢ ተፅኖ ዳሰሳ እና  ሕብረተሰብ ጥቅም-ጉዳት ትንተና(Social cost-benefit Analysis) ጥሩ የሆነ ሲሆን ብቻ ነው። 
እዚህ ላይ ልብ ማለት ያለብን ከላይ የተጠቀሱት ትንተናዎች የሚደረጉትበቅድምያ ፕሮጀክቱ ሥራ ላይ ከመዋሉ  ዲዛይን ደረጃ እና  ፕሮጀክቱስራም ላይ የመከለስ ዕድል መኖሩን ነው።

 አውሮፓ  ትራንስፖርት ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ  ትትራንስፖርትን ሕብረተሰብ ጉዳት ትንተና ፅሁፍ ላይ ማንጋውም የ ትራንስፖርት ግንባታ ፕሮጀክት  ሁለት ጊዜ የመከለስ ዕድል ስለመኖሩ   ኢኮኖሚ ልማት እናትብብር (OECD) እትም እንዲህ ይገልፀዋል :-

'' ሕብረተሰብ ጉዳቶች (ስለ መንገድ ፕሮጀክት ነው ከላይ ፅሁፉየሚያብራራው ሁለት ደረጃዎች  ግንዛቤ ውስጥ ይገባሉ:-የመጀመርያው  ፕሮጀክቱ  ዲዛይን ደረጃ ሲሆን ሁለተኛው  ልማትዕቅዱ ትርጉም ላይ ነው።''

''Social costs are taken into account at two different levels:first, in the design of projects, and then in the definition of development plans'' E Quinet - Internalisingthe social costs of transport, European Conference of Minister of Transport, OECD publication,1994,p.29
ዲዛይኑ ካልተስተካከለ አደጋው ለቻይናም ይተርፋል
 እዚህ በተረፈ ግን  አለም አቀፍ ሕብረተሰብ ከቅርስ ጋር በተያያዘየሚነሳ ጥያቄ  ኢትዮጵያ መንግስት ላይ መቅረቡ አይቀርም።ዩነስኮንጨምሮ አለም አቀፍ ድርጅቶች ጉዳዩን በጥብቅ እንዲያዩት መግፋትከማንኛውም ዜጋ የሚጠበቅ ግዴታ ነው። 
 አሁኑ አለም ቻይና የገባችበትን ፕሮጀክት ነቁጥ የሚፈልጉ እና ሃያ አራትሰዓት የሚሰሩ ሚድያዎች  ምዕራቡ ዓለም መኖራቸውን  ኢትዮጵያመንግስት መዘንጋት የለበትም። ቻይና  አፕል ኮምፑተር ምርት ጋርየገባችውን ውዝግብ መርሳትአይገባም።(http://www.nytimes.com/2011/02/23/technology/23apple.html?pagewanted=all&_r=0 ቻይና ፕሮጀክትሲወቀስ አብሮ  አፍሪካ መንግሥታት ጥሩ አርስት ተገኘላቸው ማለትነው። እናም ምርጫው  መንግስት ይመስለኛል። ዲዛይኑን አስተካክሎ ሰማአቱን ሃውልት አክብሮ ፕሮጀክቱን መጨረስ።
 እዚህ ባለፈ ግን ባለንበት ዘመን ካምፓኒዎች  ህብረተሰባዊ ኃላፊነት(Corporate Social Responsibility-CSR)  መላው አለምበሚለኩበት ዘመን ቻይናዎች የነገ  ሌላ  አፍሪካ ሀገር ፕሮጀክትዕድላቸውን የሚያበላሹ ላይሆኑ ይችላሉ። እና  CSR ሕግ መሰረትዲዛይኑ እንዲስተካከል እንደሚገፉ እገምታለሁ። በመሆኑም የ ግንባታውን ጨረታ ያሸነፈውና ስራውን  የሚያከናውነው  የ ቻይናው የ ባቡር እሯን ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ( China Railway Eryuan Engineering Group Co. Ltd. (CREEC)) (http://www.capitalethiopia.com/index.php?option=com_content&view=article&id=226:addis-ababa-light-railway-project-starts-&catid=35:capital&Itemid=27 ) ጉዳዩን እንዲረዳው ማለትም የሚደርስበትን ወቀሳ እንዲገነዘብ ማረግ ተገቢ ነው። የ ካምፓኒዎች ያለፈ የ ፕሮጀክት አፈፃፀም ወደፊት ከሚሰሩት ሥራ ጋር በ እጅጉ ስለምቆራኝ ቻይናዎች ዝም ብለው ያልፉታል ብሎ ማሰብ አይቻልም።

ለማጠቃለል
 ባቡር ዝርጋታው ፕሮጀክት አንዱ እና ዋናው  ትራንስፖርት ችግርመፍቻ መንገድ መሆኑ የታወቀ እና አስደሳች ሥራ ቢሆንም  ሀገሪቱአሻራዎች ላይ ያለው ጥቁር ነጥብ በደንብ ሊመዘን ይገባዋል። ነፃ ''ሚድያ''ለሌላት ሀገር እና ህዝቡ ስለ ጉዳዩ ለመወያየት ዕድል በሌለው ሁኔታ  ህዝቡ ዘንድ የሚፈጥረው ስነ-ልቦናዊ ጉዳት ለመለካት በጣም ከባድመሆኑን ለመረዳት አያዳግትም። 
አሁንም ያለው አማራጭ አንድ ይመስለኛል። ዲዛይኑን ማስተካከል እናስራውን  ሕዝብ ፕሮጀክት አርድርጎ መቀጠል። ይህ ሲደረግ ፕሮጀክቱቀረፃ፣ግምገማ እና የማረጋገጥ ደረጃ ሁሉ ሲያልፍ ገንዘብን እንጂ  ሀገሪቱንአሻራ ያልታያቸው ባለሙያዎችም ሆኑ ባለስልጣናት ሊወቀሱ ይችላሉ። ይህተፈርቶ ግን ፕሮጀክቱ ልክ ነው ብሎ መቀጠል  ወንጀሉ የሚጠየቁትንሰዎች  ማብዛት በቀር ትርፍ የለውም።ባቡሩም ይሰራልን ፕሮጀክቱምይስተካከልልን።
 
 
አበቃሁ።
 
ጌታቸው
 
ኦስሎ  

No comments:

Post a Comment