Translate

Friday, November 23, 2012

አፋኝ ልዩ የኮማንዶ ሃይል በምስጢር ተመረቀ!!!

አፋን ልዩ የኮማንዶ ሃይል በምስጢር ተመረቀ!!!

 የወያኔ የመከላከያ ምንጮች እንደገለጡት ወያኔ ህዝብን ለማሳፈን ከየገጠሩ የሰበሰባቸዉን አዳዲስ ምልምል ልዩ የኮማንዶ ሃይሎችን በምስጢር አሰልጥኖ አስመረቀ::

በልዩ ሃይሎች ማሰልጠኛ ካምፕ ዉስጥ ላለፉት ስድስት ወራት ልዩ የኮማንዶ ሃይሎች የተመረቁት የህንን የአፈና ቡድን በበላይነት እና በተናጠል በሚመራው በሌ/ጄነራል ሳሞራ የኑስ ነው::
ይህንን የልዩ ሃይል የኮማንዶ ጦር በከፍተኛ ወጪ ከዉጪ አገራት በመጡ አሰልጣኞች በምስጢር አሰልጥኖ ያስመረቀው ወያኔ የሕወሓቱን የጦር ኣለቃ አብርሃ ተስፋይን የልዩ ሃይሉ አዛዥ አድርጎ የሾመ ሲሆን ጦሩ በአዲስ አበባ እና ለአዲስ አበባ ቅርብ በሆኖ የጦር ካምፖች ዉስጥ እንዲሰፍር ተደርጉዋል::

በኑሮ ዉድነት..በመልካም አስተዳደር እጦት..በግዴታ መዋጮ...እየተንገላታ ያለው ሰፊው ኢትዮጵያ ህዝብ በወያኘ አምባገነን ቡድን እና በሙስና በተጨማለቁ አመራሮቹ ላይ ተቃውሞ ቢያነሳ ምላሽ ሊሰጥ የሚችል ጦር የለም በሚል ጥርጣሬ ይህንን ልዩ ሃይል ያሰለጠኑ እና ለብቻው እየተቀለበ እንዲቀመጥ በምስጢር ትእዛዝ ተሰጥቱዋል::

ጦሩ ከተመረቀ  በሁዋላ የተወሰነው በቀድሞው አይሮፕላን ማረፍያ አቅራቢያ የሰፈረ ሲሆን ይህ ተወርዋሪ ጦር በዘመናዊ መሳርያ እና ትጥክ የተደራጀ መሆኑን የ አይን እማኞች ተናግረዋል ::
የምንሊክ ሳልሳዊ ምንጮች እንዳሉትበወሓቱ አብርሃ ተስፋይ የሚመራው ይህ ልዩ ሃይል ቀጥታ ከሳሞራ የኑስ የሚሰጠውን ትዛዝ ብቻ የሚተገብር ሲሆን በወያኔ ባለስልጣናት መካከል ለሚነሳው ይፋዊ የስልጣን ሽኩቻ ሕወሓትን ወግኖ እንዲሰለፍ የተዘጋጀ ጦር ነው::

No comments:

Post a Comment