Translate

Sunday, November 18, 2012

አሸባሪው ማን እንደሆነ የአለም ህዝብ በተጨባጭ ያረጋገጠበት ታሪካዊ የዚያራ ቀን በሰላም ተጠናቀቀ !!


ሰላም ወዳዱ ሙስሊሙ ህዝባችን ለሰላም ያለውን ጥማት በተጨባጭ በማሳየት የዛሬው ቀን ዱብዳ የሆነባቸው የወያኔ ስረአት ጀሌዎች ለሁለት መከፈላቸው ከአዲስ አበባ የሚደርሱን ዜናዎች የገልጻሉ።
አሸባሪው እና ተሸባሪው ባለየበት ሃገራችን ኢትዮጵያ የሰላም ወዳዱን ህዝባችንን ተግስተኝነት እና አርቆ አስተዋይነት እንደ ፈረሃት እና አላዋቂ በመቁጠር ላለፉት 21 አመታት ሃገሪቷን እንዳሻው ሲመራ የኖሩት የወያኔ ስረአት መሪዎች ዛሬ በኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቻችን ተፈትነዋል።

እኚሁ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በትግ ዕስት እና
በሰለጠነ መንገድ የወያኔውን ስረአት ለማንበርከክ አሊያም ለህገመንግስቱ እና ለህግ የበላይነት እንዲገዛ ለማስቻል ላለፉት 11 ወራት እያደረጉ ያለው ህጋዊ እና ሰላማዊ ተቃውሞ በስረአቱ ሰላም ወዳድ ሃይሎች እና ጦረኛ አመለካከት ባላቸው ጥቂት የወያኔ ዝርያዎች መሃከል መከፋፈልን እንደፈጠረ ያገኘነው ምስጢራዊ መረጃ ያስረዳል።
ሙሉ ዝርዝር መረጃውን አጠናቅረን ሰሞኑንን ለንባብ የምናበቃ መሆኑንን እንገልጻለን ።


ዘግይቶ የደረስን ዜና ለዚያራ ወደ ቃሊቲ ሲያመራ ከነበረው ሰላማዊ ህዝብ ውስጥ ሁለት ፎቶ ሲያነሱ የነበሩ የህዝብ ወገኖች በታጣቂ መታፈናቸው ከስፍራው የሚደርሱ ዜናዎች ያመለክታሉ ።

No comments:

Post a Comment