Translate

Sunday, August 26, 2012

ወያኔዎች! አገር በውሸት ይፈርሳል እንጂ አይገነባም!


ዋለልኝ መኮንን
የያዝነው አመት የወያኔ በጣም አሳፋሪና ያገጠጠ ውሸትና ቅጥፈት ከመቼውም ጊዜ በላይ ገሃድ የወጣበት ወቅት ነበረ አሁንም እንደቀጠለ ነው:: በወያኔው የፕሮፓጋንዳ ተቁዋም በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቢጅን ድርጅትና በውጭ አገር በሚገኝው አገር ወዳድ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው ባደራጁት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቢጅን በመረጃ መረብ የሚጠቀሙ ድህረገፆች ብሎጎች ፓልቶኮች መካከል በመጀመሪያ በመለስ ዜናዊ ጤንነት ዙሪያ ቀጥሎም በህልፈተ ህይወታቸው ዙሪያ ግብ ግብ ተፈጠሮ ነበረ::

በመጀመሪያ የመለስ ዜናዊን መታመም ለህዝብ ይፋ ያደረጉት በስደት የሚኖሩት አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በግለሰብና በድርጅት ሆነው በፈጠሩዋቸው የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በተለይም ራዲዮና ቴሌቢጅንና በጣም በርካታ ድህረ ገፆች የመለስ ዜናዊን መታመም በዘገቡበት ወቅት በወያኔው የፕሮፓጋንዳ ተቁዋም በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቢጅን ድርጅትና በርካታ በወያኔ ደጋፊዎቻቸው የሚተዳደሩ ራዲዮኖች ቴሌቢጅኖችና ድህረ ገፆች ለማስተባበልና ነገሩን ለመደበቅ ሲዘባርቁ ታይተውና ተደምጠው ነበረ:: በተለይም ከፍተኛ የወያኔ ባለስልጣናት በመለስ ዜናዊ መታመም ዙሪያ እጅግ የተምታቱ መረጃዎችን አጎረፉ ለምሳሌ “ይህ የኢሳት የፈጠራ ወሬ ነው”, “ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አረብ አገሮችን አይነት አብዮት እንዲነሳ የሚፈልጉ አፍራሽ ሀይሎች የፈጠሩት ወሬ ነው”……………ብለው የተለመደ አይን ያወጣ ቅጥፈታቸውን ደረደሩ:: እናንተ በውጭ የምትገኙ የተለያዩ ራዲዮና ቴሌቢጅንና በጣም በርካታ ድህረ ገፆችን ውሸታሞች ናቹ ብለው ለማሳጣት መለስ ዜናዊን የሚመስል ክስት ግርጥት ያለ ግን እሱን የሚመስል ግለሰብ በወያኔ ቴሌቢጅን ቀርበው ለ 10 ደቂቃ እንዲያወሩ ተደረጉ::
በውጭ የሚትገኙ የተለያዩ ራዲዮና ቴሌቢጅንና በጣም በርካታ ድህረ ገፆች የመለስ ዜናዊን መታመም ባላቸው የመረጃ ምንጮች መሰረት እያጠናከሩ በተደጋጋሚ ለህዝብ ይፋ ማድረጋቸውን ቀጠሉ:: የወያኔ ባለስልጣናትም እየዘባረቁ ባሉበት ወቅት አንድ የአፍሪካ አገር መሪ መለስ ዜናዊ መታመማቸውን አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ከአፋቸው አመለጣቸው:: እኚህ የሴናጋል መሪን የወያኔ ባለስልጣኖች ለምን የኢሳት ወሬ ነው እንዳላሉዋቸው በጣም አስገርሞ ነበረ ነገር ግን ቀላል ህመም እንዳጋጠማቸው በቅርቡም ስራ ይጀምራሉ ብለው የተለመደ ውሸታቸውን ቀጠሉ::
የወያኔ ባለስልጣናትና የኢትዮጵያ ህዝብ ሆድና ጀርባ መሆናቸውን የሚያሳየው ድራማ በጣም ጎልቶ የወጣው የመለስ ዜናዊ ሞት በስደት የሚኖሩት አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በግለሰብና በድርጅት ሆነው በፈጠሩዋቸው የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ከተናገሩ በሁዋላ ነበረ:: የኢትዮጵያውያን ሳተላት ቴሌቢጅን ባገኝው ትክክለኛ መረጃ መሰረት የወያኔው ጠቅላይ ሚንስትር መሞታቸውን አረጋገጠ አሁንም ወያኔዎችና ደጋፊዎቻችው የውሸት መረጃ መሆኑን በግልም በቡድንም ለማስተባበል ተራራ ወጡ ወረዱ:: ሁሉም በመንግስት ባለስልጣናት የሚሰጡ መግለጫዎች እርስ በእርሳቸው የተጠላለፉ የውሸት ፈጠራዎች ነበሩ::ይባስ ብሎም መለስ ዜናዊን ለአዲሱ አመት ይዘው እንደሚቀርቡ ቃል እስከመግባ የደረሰ ነገር ግን ባናመጣውም ምንም አያገባችሁም የሚል መእዕክት ያዘሉ መግለጫዎችና ማስፈራሪያዎች የዝጎደጎዱ::
ከቀናት እሰጣ ገባ በሁዋላ የወያኔ ራዲዮና ቴሌቢጅን መለስ ዜናዊን በተገባልን ቃል መሰረት በአካል ማቅረብ ባይችልም የሞቱን ዜና ለማቅረብ ሞከረ:: ነገር ግን አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ቀድሞ በስደት የሚኖሩት አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በግለሰብና በድርጅት ሆነው በፈጠሩዋቸው የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች የመለስ ዜናዊን መሞት ስለሰማ የኢቲቢ የመርዶ ዜና በወያኔ አፍ ከመነገሩ ሌላ የጠቀመው ነገር የለም:: አንዳንድ ወገኖች ግን የ ኢቲቢ የመርዶ ዜና እጅግ የጠቀመን ነገር ቢኖር ስለ መለስ ዜናዊ መሞት ማውራት ትችላላቹ ተፈቅዶላችዋል ከሚል የዘለለ አይደለም ምክንያቱ ኢትዮጵያ ውስጥ በስደት የሚኖሩት አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በግለሰብና በድርጅት ሆነው በፈጠሩዋቸው የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ማድመጥና መመልከት ብሎም ከወያኔ ቀድሞ ማሰብና ማውራት በአሸባሪ ህግ ያስከስሳልና::
የወያኔዎችና የመረጃ ተቁዋሞቻቸው አሁንም አይናቸውን በጨው አጥበው የውሸት ድራማቸውን ቀጠሉ:: ያው የሞተ ሰው በባህላችን ክፉ አይባልም አይደል ግን ያልሆነውን ነው አይባልም:: በመለስ ዜናዊ ሞት ያየነው ግን በጣም የፈጠጠ በቅርብ ግዜ ውስጥ የሚያስተዛዝበን ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ የሆነ ነገር ነው:: አሁን አየተካሄደ ባለው የአምባገነኑን መለስ ዜናዊን የህይወት ታሪክ በተሳሳተ መልኩ እጅግ አጋኖ ማቅረብ በቀጠታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚጎዳው እርሳቸውን የወያኔ ባለስልጣናትንና እስከዛሬ በዘርና በጥቅም የተሳሰሪዋቸውን ግለሰቦችና ድርጅቶች መሆኑን ማሰብ ስላቃታቸው ይመስለኛል::
ሁሉም የመንግስት ባለስልጣናትና በወያኔ የውሸት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ የሆኑ ግለሰቦች በተደጋጋሚ እየተነገረች ያለች “መለስ ዜናዊ የጀመረውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ እናስፈፅማለን” እና ተመሳሳይ መልክት ያላቸው መፈክሮች ምን ያህል መንግስት በውሸት እንደተገነባ ያሳያል:: አንድም የመለስ ዜናዊን የግለሰብ አምባገነን አገዛዝ የሚያሳይ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት ሁሉም ግለሰቦች የጠቅላ ሚንስትሩ ተሳቢ ሆነው እንዳሳመሙዋቸውና ለመሞታቸው መንስኤ በሚሆን ደረጃ ብቻቸውን አገር ለማሳደግ ይደክሙ እንደነበረ ያሳያል በተጨማሪም ሁሉም የወያኔ ባለስልጣናት ምንም ችሎታና ስልጣን እንዳልነበራቸም ይገልፃል::
ሌላው የወያኔ ባለስልጣናትና የፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎቻቸው ሊዋሹን የሞከሩት ነገር ቢኖር መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ማዘኑን ነበረ በተለይም አዲስ አበባ የመለስ ዜናዊ አስክሬን የገባ ቀን (ከገባ ቆይታል አልቆየም ሌላ የወያኔ የውሸት ደራማ አለው) ቁጥራቸው በዛ ያሉ የወያኔ አባላት በጥቅምና በዘር የተሳሰሩዋቸው ግለሰቦች ድርጅቶች በወያኔ የውሸት ወሬ የተታለሉና እንደዜጋ ማግኝት ያለባቸውን ጥቅሞች በወያኔ ፍቃድ ብቻ እንደሚያገኙ ተደርገው እንዲያስቡ የተደራጁ ወጣቶች ተገኝተው ነበረ:: ነገር ግን መተኮር ያለበት እውን የአዲስ አበባ ህዝብ መለስ ዜናዊን ስለሚወዱት ነው ወይ አስክሬኑን ለመቀበል የወጡት?? እንደ ኢቲቢ ውሸታምነትና ማን አለብኝነት መለስን ስለሚወዱት ነው ሊሉ ይችላሉ:: ለመሆኑ የአዲስ አበባ ህዝብ መለስን ለተለያዩ ጉዳዮች ከአገር ሲወጣም ሆነ ወደአገር ሲገባ ሸኝቶት ተቀብሎት አይቶትስ ያውቅ ነበረ??
እንደውም በተቃራኒው መለስ ዜናዊ በገባና በወጣ ቁጥር በመንገድ የሚሄድ ፍጥረት ሁሉ (ሰውም እንስሳም) እየተገፈተረ በተገኝው ቀዳዳ እንዲገባ ሲደረግ ቀዳዳ ባልነበረበት ቦታዎች መለስ ዜናዊን እንዳያይ ፊት ወደ ግድግዳ እንዲያደርግ ወይንም ወደሰማይ እንዲያይ እንደጠፈርተኛ የታጠቁ አይናቸውን በሚያጉረጠርጡ ደም የጠማቸው በሚመስሉ ወታደሮች ይገደድ ነበረ:: አሁን የአዲስ አበባ ህዝብ ጭንቅላት የለውም? ነው ወይስ የማስታወስ ችሎታ የለውም? ነው እያላቹ ያላችሁት:: መልሱን ከወያኔዎችና ከፕሮፓጋንዳ መሳሪያቹ ከኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቭዝን ድርጅት አልጠይቅም በቅርቡ እራሱ የአዲስ አበባ ህዝብ ይነግራችዋል::
የኢትዮጵያ ህዝብ ማየት የፈልግ የነበረው መለስ ዜናዊ በስልጣን ዘመናቸው በነፃነት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ከሚስታቸውና ከልጆቻችው ጋር እንዲዘዋወሩ ነበር:: የወያኔ ባለስልጣናት በጥቅምና በዘር የተሳሰራቹ ግለሰቦችና ቡድኖች በወያኔ የተሳሳተ የፕሮፓጋንዳ ሰለባ የሆናቹ የህብረተሰብ ክፍሎች እያደረጋቹ ያላችሁት አስክሬን በመኪና ጭናቹ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች እያዞራቹ ህዝብ ይወደው ነበረ ለማለት ከሆነ ሞኞች ናችሁ::
የኢትዮጵያ ህዝብ መለስ ዜናዊን በህይወት እዳለ እንዴት ሊመለከተው ሊወደው ሊጠላው እንደሚችል ይህንን መቅረዐ ምስል ይመልከቱና ይረዱ ESAT The legacy of Meles Zenawi

No comments:

Post a Comment