Translate

Tuesday, August 21, 2012

የመለስ ዜናዊ አስከሬን በቦሌ የሬሳ ማቀዝቀዣ ክፍል ውስጥ ተቀምጧል!!

 Reported: Ethiopian media forum.
(ኢ.ኤም.ኤፍ) የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም መለየታቸው ኦገስት 21፣ 2012 ዓ.ም. ታወጀ። ከአንድ ቀን በፊት የአቶ መለስ ዜናዊ የመለስ ዜናዊ አስከሬን በቦሌ የሬሳ ማቀዝቀዣ ክፍል ውስጥ ተቀምጧል!!አስከሬን፤ ከውጭ አገር እንዲገባ ተደርጎ በቦሌ ተርሚናል የሬሳ ማቀዝቀዣ ክፍል ውስጥ ተቀምጦ ነበር የቆየው። ሆኖም በኢቲቪ የዜና እወጃ ላይ፤ “በትላንቱ ምሽት በድንገት ህይወታቸው አልፏል።” የሚል ውሸት በድጋሚ ተሰምቷል።

በሌላ በኩል ለረዥም ጊዜያት እውነቱን ሲክድ የነበረው በረከት ስምኦን… “መለስ በቅርቡ ወደ ስራ ይመለሳሉ” በማለት፤ የሃሰት ቃል ሲያቀብል ከቆየ በኋላ ዛሬ ማለዳ ላይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን መሞት ለማርዳት በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ለማለት እንኳን ሳይደፍር ቀርቷል። የመለስ ዜናዊ ዜና እረፍት ከተሰማ በኋላ፤ ልጆቻቸውን በመለስ አስተዳደር
የመለስ ዜናዊ አስከሬን በቦሌ የሬሳ ማቀዝቀዣ ክፍል ውስጥ ተቀምጧል!!
የተነጠቁ ወላጆች፤ ፍትህ አጥተው በእስር እና በስደት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ደስታቸውን ሲገልጹ፤ ቀኑ የጨለመባቸው የኢህአዴግ ወገኖች ደግሞ ሆድ ብሷቸው ሲያለቅሱ ውለዋል።
በአሁኑ ወቅት. የመለስ ዜናዊን ቦታ ተክተው እንዲሰሩ የተደረጉት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሲሆኑ፤ የጠቅላይ ሚንስትርነቱ ቦታ ወደ ሌላ ብሄር መሄዱ በዘረኝነት አጥር ውስጥ የሚገኙትን በተለይም፤ የህወሃት ከፍተኛ አመራር እና የጦር አዛዦችን ያስኮረፈ ይመስላል። በአሁኑ ወቅት ጄነራል የሳሞራ የኑስን ህመም ተከትሎ የኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት በመንታ መንገድ ላይ ይገኛል። በአጠቃላይ የአየር ኃይል እና የምድር ጦር ሰራዊቱ ከአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መስመር ውጪ በህወሃት ከፍተኛ የጦር መኮንኖችም አመራር ስር መውደቁ ይታወቃል።
የአባ ጳውሎስ የቀብር ስነ ስር ዓት የፊታችን ሃሙስ በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የሚከናወን ሲሆን፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር የቀብር ስነ ስር ዓት የት እና መቼ እንደሚከናወን አልታወቀም። ሁለቱም ሰዎች በጥቂት ቀናት ልዩነት መሞታቸውን የታዘቡ ሰዎችም፤ ክስተቱን “ፍቅር እስከ መቃብር።” ብለውታል።
ዛሬ በታወጀው የኢቲቪ ዜና ላይ መለስ ዜናዊ ትላንትና በድንገት ሞቱ ይበል እንጂ፤ የት እንደሞቱ አልገለጸም። እውነቱ ግን አሁንም የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አስከሬን፤ ከውጭ አገር ከገባ በኋላ በቦሌ ተርሚናል የሬሳ ማስቀመጫ ክፍል ውስጥ ይገኛል። ይህ ድርጊት ለመለስ ዜናዊ ክብር ሳይሆን ውርደት ነው። በበረዶ ቤት ስለተቀመጠው አስከሬን… አቶ በረከት ስምኦን በቅርቡ ምን ይነግሩን ይሆን?

No comments:

Post a Comment