Translate

Monday, August 27, 2012

የፖለቲካ እስረኞች፤ በመለስ ሞት የተነሳ ማስፈራሪያ እየተደረገባቸው ነው!


አቤ ቶኪቻው

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲነገር ሌላው ሲያለቅስ አንተ ስቀሃል ተብሎ አቶ ዘሪሁን ገብረእግዚአብሔር በእስር ቤት መደብደቡን ሰምተን ተደንቀናል። ተሳቀናልም።የፖለቲካ እስረኞች፤ በመለስ ሞት የተነሳ ማስፈራሪያ እየተደረገባቸው ነው!
አሁንም እስር ቤት ከሚገኙ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች አካባቢ እየተሰማ ያለው ነገር ይህንኑ የሚያጠናክር ነው። ስሙን ከምገልፅላችሁ ባልገልፅላችሁ የሚሻል አንድ የተፈረደበት ጋዜጠኛ በፊት ከታሰረበት ቦታ የተዛውረ ሲሆን “ጠቅላይ ሚኒስትሩን እኛ የገደልናቸው ይመስል ከባድ የሆነ ማስፈራሪያ እና ዛቻ እየደረሰብን ነው!” ሲል ሊጠይቁት ለሄዱ ቤተሰቦቹ ተናግሯል።
ባለፈው ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙ የዋልድባ መነኮሳት “መለስን እንዲታመም ያደረጋችሁት እናንተ ናችሁ መተተኞች” እየተባሉ በፖሊስ እንደተደበደቡ ሰምተን ተገርመናል። እንግዲህ አሁንም መገረማችንን እንቀጥላለን ማለት ነው!
እስቲ ቸር ያሰማን!
ይህ በእንዲህ እንዳለ አርብ ዕለት ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹን እንዳያገኝ ተከልክሎ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ቅዳሜ እና እሁድ ወዳጆቹ እና ቤተሰቦቹ ሊጠይቁት መቻላቸውን ሰምቻለሁ።

No comments:

Post a Comment