Translate

Thursday, August 30, 2012

“መለስ መጀመሪያ እናቴን አገባ፤ ቀጥሎ አባቴን አስገደለ” – የክንፈ ገ/መድህን ልጅ በረከት።…አዜብ መስፍንን ለማጽናናት በቤተመንግስት ይገኛል እውነት ለአባቱ ገዳይ ያለቅስ ይሆን ?


ወላጅ እናቱን ወ/ሮ አዜብ መስፍንን ለመጎብኘት ወደ ቤተ መንግስት እንዳይገባ በደህንነት ሚ/ሩ ጌታቸው አሰፋ የተከለከለው የሟቹ ክንፈ ገ/መድህን የጀመሪያ ልጅ “መለስ መጀመሪያ እናቴን አገባ ቀጥሎ አባቴን አስገደለ፤ መለስ ዜናዊን እፋረደዋለሁ”ብሎ በአደባባይ መናገሩ በርካታ ሲኒየር የሕወሓት አባላትን ማሳፈሩን ሆርን ታይምስ የተባለው መጽሄት ዘገበ።
አቶ መለስ ዜናዊ ከቀድሞው የደህንነት ሚ/ሩ ክንፈ ገ/መድህን የአሁኑ ባለቤቱን አዜብ መስፍንን በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ እንደወሰደ የዘገበው መጽሄቱ በረከት ክንፈ ያን ጊዜ የ2 ዓመት ሕጻን ልጅ ነበር ብሏል።   በረከት ክንፈ ወላጅ አባቱ አቶ ክንፈ ገ/መድህንን በ8 ጥይት መትተው የገዱሉት ሻለቃ ጸሐዬ የመለስ ቀኝ እጅ ናቸው በማለት ለ6 ዓመታት በ እስር ላይ በቆዩበት ጊዜ በተደጋጋሚ ሊጎበኛቸው ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ እንደሆነበርና የሻለቃ ጸሐዬ ባልታሰበ ለሊት ድንገት መገደል ምስጢሩን ለመደበቅ የተደረገ ሙከራ ነው በማለት ጥያቄ ማንሳቱን ሆርን ታይምስ መጽሄት አጋልጧል።

በተለይ ከአባቱ መገደል በኋላ የደባል ሱስ ባለቤት ሊሆን ችሏል የተባለው የአቶ ክንፈ ገ/መድህን ልጅ ወላጅ እናቱ አዜብ መስፍን ከቤተመንግስት ውጭ ሁልጊዜ እንደሚያገኙት መጽሔቱ ገልጾ በእንጀራ አባቱ አቶ መለስ ላይ አንድ ነገር ሊያደርግ ይችላል በሚል ፍራቻ ልጁ ወደ ቤተ መንግስት እንዳይገባ ተከልክሏል ብሏል።

በቅርቡ በኖርዌይ ኦስሎና በሲንጋፖር ለጭንቅላት ቲሞር ሕክምና ሄደ የነበሩት አቶ መለስ አሁን ባለው ሁኔታ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ/ር እርሳቸው ሳይሆኑ ባለቤታቸው አዜብ መስፍን ናቸው ማለት ይቻላል የሚለው መጽሔቱ ከርሱ በተጨማሪም የሕወሓት አንጋፋ ታጋይ አቶ ስብሃት ነጋም ወደ ቤተመንግስት እንዳይገቡ በወ/ሮ አዜብ ተከልክለዋል። የሟቹ የክንፈ ገ/መድህን ልጅ አንድ እርምጃ እንዳይወስድ በአዜብ የተመረጡት ባለስልጣናት ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ወርቅነህ ገበየሁ፣ጌታቸው አሰፋ፣ በረከት ስምዖንና አባ ዱላ ገመዳ መሆናቸውም ተዘግቧል።
የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሔኖክ ዓለማየሁ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚያሳትማት መዲና ጋዜጣ ላይ “ከክንፈ ገ/መድህን ግድያ በስተጀርባ የአቶ መለስ እጅ አለበት” በሚል ከአንድ የሕወሓት ሴት ታጋይ የተገኘ ምስጢራዊ ዜናን በማውጣቱ አቶ መለስ የሚያዙት ፍትህ ሚ/ር በአዘጋጁ ላይ ክስ በመመስረት ምንጭህን አምጣ በሚል ለእስር ተዳርጎ እንደነበርና፤“ምንጬን አልናገርም” ያለው ሔኖክ ለ24 ሰዓታት በማዕከላዊ እስር ቤት ጨለማ ክፍል ታስሮ በ10 ሺህ ብር ዋስትና መለቀቁ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነበር። በረከት ይህንን ቃል የተናገረው ባለፈው አመት ቢሆን በአሁን ሰአት ወላጅ እናቱ አዘብ መስፍን በሞት የተለያትን ባለቤቷን ለማጽናናት በረከት በቤተ መንግስት የሚገኝ ሲሆን ያለፈውን የአባቱን ግድያ ወደ ጎን በመተው ይቅር ለእግዚአብሄር በማለት ፍቅርን ለማስተማር እናቱን እያጽናናት እንደሆነ ምንጮቻችን ልከውልናል ።በተለይም ባባቱ ግድያ መቆጨቱን የሚናገረው በረከት ከወላጅ እናቱ አዜብ ጋር ምንም ግንኙነት ለማድረግ እንደማይፈልግ ወስኖ እንደነበር ቢታወስም አሁንግ ግን የጠቅላይ ሚንስትሩ ሞት የመቀራረቢያ መንገድ ብርሃን ሳይፈነጥቅለት እንዳላለፈ ይገልጻሉ ።ከተከለከለበት ቤተመንግስትም ለመግባት መቻሉን እና እናቱንም በጥልቅ ሃዘን ምሬት በመሆን እያጽናናት ነው ።…እውነት ለአባቱ ገዳይ ያለቅስ ይሆን >፧?

No comments:

Post a Comment