Translate

Thursday, October 29, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ) በላንድ ክሩዘር መኪና ተሳፍረው ወደ አርባ ምንጭ ከተማ በፍጥነት ያመሩ የነበሩ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ፡፡


የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)
በላንድ ክሩዘር መኪና ተሳፍረው ወደ አርባ ምንጭ ከተማ በፍጥነት ያመሩ የነበሩ 10 የፌደራል ፖሊስ አባላት ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ከነመኪናቸው ሙሉ በሙሉ ተደመሰሱ፡፡
====================================================
በትናንትናው ዕለት አመሻሽ ላይ አስሩ የፌደራል ፖሊሶች መጀመሪያ አንድ አይሱዙ የጭነት መኪና በኃይል በማስገደድ አስቁመው የተሳፈሩ ሲሆን መኪናው መንቀሳቀስ ሲጀምር "የጫንካቸውን ፖሊሶች አራግፍ አለያ ከነንብረትህ አብረህ ትጋያለህ!" የሚል የስልክ ማስጠንቀቂያ መልዕክት ለአሽከርካሪው በመድረሱ አሽከርካሪው መኪናውን አቁሞ ፖሊሶቹን "አልሄድም" ይላቸዋል፡፡ ቀጥሎም ፌደራል ፖሊሶቹ ሾፌሩን ለማንገራገር ሞክረው ትዕዛዛቸውን በቀላሉ ሊቀበል ባለመቻሉ ስልክ ተደዋውለው ሌላ ላንድ ክሩዘር መኪና እንዲመጣላቸው በማድረግ ተሳፍረው ጉዟቸውን ቀጥለው ኮንሶ እና ቦረና መገንጠያ ድልድይ ላይ ሲደርሱ ቅፅበታዊ ጥቃት ተከፍቶባቸው ከነተሳፈሩበት መኪና ሙሉ በሙሉ ተደምስሰዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ሙሉጌታ አባ፣ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ እና በኃይሉ ሲሳይ የተባሉ የህወሓት ጆሮ ጠቢዎችና የአካባቢው ቆራጭ ፈላጮች ፎቶግራፋቸው በማህበራዊ ሚዲያው መሰራጨቱን ተከትሎ ከትናንት ምሽት ጀምሮ አርባ ምንጭ ከተማ ከከዚህ ቀደሙ በባሰ ሁኔታ በፌደራል ፖሊስ ተጥለቅልቃ እየታመሰች ትገኛለች፡፡ 


በእነ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ ትዕዛዝ በርካታ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች እየታፈኑ ወደ ልዩ እስር ቤት እየተወሰዱ ነው፡፡
አቶ አበበ አስፋው፣ ባለቤታቸው ወ/ሮ አልማዝ ካሳ እና ልጃቸው አየለች አበበ ዛሬ ጠዋት በደህንነቶች እና በፌደራል ፖሊሶች ታፍነው ወደ ወህኒ ተወስደዋል፡፡ በተጨማሪም ደረጀ የተባለ ወጣት ከሌሊቱ አስር ሰዓት በእንቅልፍ ላይ እንዳለ ታፍኖ ተወስዷል፡፡ ሉሉ የተባለው የሰማያዊ ፓርቲ አባልም በቁጥጥር ስር ውሎ በአሁኑ ሰዓት መኖሪያ ቤቱ በህወሓት ደህንነቶች እና ፌደራል ፖሊሶች በጥብቅ እየተፈተሸ ይገኛል፡፡
ባጠቃላይ በአሁኗ ሰዓት በአርባ ምንጭ ከተማ ከፍተኛ ውጥረት የሰፈነ መሆኑን ከቦታው እየደረሱን የሚገኙት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

No comments:

Post a Comment